#ችሎት
የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩ እና ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን "በሽብርተኝነት" ሊከሳቸው መሆኑን ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ የፌደራል መንግስት "ከስልጣን ስለገፋን" በማንኛውም መንገድ እንዲወገድ መደረግ አለበት በማለት ሚስጥራዊ ወታደራዊ ዕዝ ማቋቋማቸውን ዐቃቤ ሕግ የፖሊስ የምርመራ መዝገብን ጠቅሶ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ገልጿል፡፡
በቀዳሚ ምርመራ የምስክርነት ቃላቸውን የሚሰጡ 83 ሰዎች መዘጋጀታቸውንም ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤት አብራርቷል፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የነበሩት ወ/ሮ ሕርቲ ምህረተአብ እና የክልሉ መንግስት አማካሪ የነበሩት ወልደጊዮርጊስ ደስታ ፣ በቂ ዋስ ጠርተው ቢለቀቁ ዐቃቤ ሕግ እንደማይቃወም አስታውቋል፡፡
ሌሎች ተጠርጣሪዎች ግን ሕገመንግስታዊ ስርዓትን በኃይል መናድ ፣ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ናቸው በሚሉ እና በሌሎች ወንጀሎች ጠርጥሮ እንደሚካሳቸው ለፍርድ ቤት ገልጿል፡፡
በዚሁ መሰረት የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ እንዲዘጋለት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡
የተጠርጣሪ ጠበቆች ሂደቱን በመቃወም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማቅረባቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ።
በ2012 ዓ/ም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ሳይሰጥ የቀረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከየካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለ4 ቀናት ሲሰጥ ነበር።
ፈተናው በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
@tikvahethiopia

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የአ/አ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2/2013 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ በሰላም መጠናቀቁ የከተማው ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ ፈተናውን 23,986 ተማሪዎች ለመፈተን ተመዝግበው 23,569 የሚሆኑ ተማሪዎች በ41 የፈተና ጣቢያዎች ወስደዋል።
አቶ ዲናኦል ፥ ፈተናው በ7 ሴሽን ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ በስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት መጠናቀቁን ገልፀዋል። ፈታናው ያለ ምንም እንከን መጠናቀቁን አሳውቀዋል።
በአዲስ አበባ ደረጃ ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በተለይም የጸጥታ አካላት እና የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ተሳትፎ የጎላ በመሆኑ ለእነዚህ አካላት ላበረከቱት አስተዋፆ ምስጋና ቀርቧል።
Via Addis Ababa Education Bureau
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

"የዘንድሮው ፈተና ሳይሰረቅ ነው የተሰጠው" - ትምህርት ሚኒስቴር
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ የዘንድሮው ፈተና ሳይሰረቅ እንደተሰጠ ነው የገለፀው።
የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት 8 ፈተናዎችን በ32 ስብጥር በማድረግ ኩረጃ እንዳይኖር መደረጉንም አንስቷል።
ሚኒስቴሩ በመግለጫው ከ358 ሺህ በላይ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መውሰዳቸውን አመልክቷል።
ፈተናው የጸጥታ ችግር በነበረባቸው የትግራይና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞንን ጨምሮ በመላ ሃገሪቱ ተሰጥቷል ብሏል።

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ።
የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል።
እንዲሁም ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የትግራይ ክልል የቀድሞው ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወስኖላቸዋል።
በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የክስ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን በፍ/ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የክልሉ የቀድሞው ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና በመዝገቡ 8ኛ ተጠርጣሪ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ዐቃቤ ህግ ለከፈትኩት የምርመራ መዝገብ የሚያስጠረጥር በቂ ማስረጃ ባለማግኘቴ በዋስ ይለቀቁ ሲል ለፍ/ቤት አመልክቷል።
በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩት አቶ ስብሀት ነጋን ጨምሮ አቶ ሰሎሞን ኪዳኔ ቅዱሳን ነጋና ሌሎች የመዝገቡ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በቀዳሚ ምርመራ እንዲታይ ዐቃቤ ህግ ለፍ/ቤቱ አመልክቷል።
ጉዳዪን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው መሠረት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ እያንዳንዳቸው በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ አዟል።
አቶ ስብአት ነጋን ጨምሮ የመዝገቡ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ እንዲታይና እስከዛው በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

"የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላይ ለትግራይ ክልል እና መተከል ዞን አካባቢ ተፈታኞች አስተያየት ይደረጋል" - ትምህርት ሚኒስቴር
በትግራይ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አካባቢ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ወደ ከፍተኛ ትምርት ተቋማት በሚያስገባው የማለፊያ ነጥብ ላይ አስተያየት እንደሚደረግ ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ በሰጡት መግለጫ፤ የ12ኛ ክፍል ፈተና በትግራይ ክልል እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
ተማሪዎቹ በአካባቢያቸው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ስነበሩ በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ላይ አስተያየት እንደሚደረግላቸው ጠቅሰዋል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን እና በአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች ፈተናው በሰላም መከናወኑን አመልክተዋል።
ለዚህም የመከላከያ ሰራዊት ላደረገው ትብብር ምስጋና ማቅረባቸውን ኢፕድ አስነብቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
የ2ተኛው ቀን የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ተሰጥቷል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ትላንት የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ/ም መጀመሩ ይታወቃል። በዛሬው ዕለት የ2ኛው ቀን ፈተና በመላ ሀገሪቱ ሲሰጥ ውሏል። ከፈተናው ሂደት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች ከተማሪዎች እና ከተማሪ ወላጆች እያደረሱን ይገኛሉ። አንዳንድ ተማሪዎች ስልክ ይዞ የመገኘትም ነገር እንደነበረ ተፈታኞች ለቲክቫህ እያሳወቁ ነው።…
#Telegram
ቴሌግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰዓታት ተቋርጦ ነበር።
ዛሬ ጥዋት #ቴሌግራም ተቋርጦ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አገልግሎቱ የ12ኛ ክፍል ፈተና ማብቃት ከታወቀ በኃላ ተመልሷል።
ምንም እንኳን ዛሬ ሙሉ በሙሉ ቢቋረጥም ከትላንት ጀምሮ ፍጥነቱ ቀንሶ ፣ ፎቶዎች እና ቪድዮችን ለመለዋወጥ አስቸጋሪ ሆኖ ነበር።
ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት የተማሪ ወላጆች እና ተፈታኝ ተማሪዎች ያነሷቸውን ቅሬታ አጋርተን ነበር።
በአንዳንድ ቦታዎች የሞባይል ስልክ ይዘው ወደ መፈተኛ ክፍሎች የሚገቡ ተማሪዎች ፈተናውን ፎቶ በማንሳት በቴሌግራም የመስራት ሁኔታ እንደነበረ በቂ ማስረጃ እንዳላቸው የቲክቫህ አባላት የሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች መግለፃቸው አይዘነጋም።
ምንም እንኳን ቴሌግራም ከትላንት ጀምሮ ፍጥነቱ ቢቀንስም ፥ ዛሬ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ቢዘጋም VPN በመጠቀም የዛሬውን ፈተና ከመፈተኛ ክፍል ውስጥ ፎቶ በማንሳት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት ባላቸው የቴሌግራም ግሩፖች ላይ የማሰራጨት ነገር እንደነበር ተስተውሏል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ዘንድሮ የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት 8 ፈተናዎች በ32 ስብጥር በማድረግ ኩረጃ እንዳይኖር ለመከላከል መሰራቱን አሳውቃል።
በተጨማሪ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በፍፁም እንዳልተሰረቀ አረጋግጣለሁ ብሏል ፤ በአንዳንድ የፈተና ጣቢያዎች ስልክ ይዘው የገቡ በጣም ጥቂት ተማሪዎች መኖራቸውን ግን ገልጿል ፤ ይህ ሁኔታ ከፈተና ኩረጃ ጋር የሚያያዝ እንጂ የፈተና ስርቆት ነው ማለት አያስችልም ብሏል የትህምርት ሚኒስቴር።

የግብፁ ፕሬዜዳንት ሱዳን ገቡ። የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብተዋል። ፕሬዜዳንቱ ሱዳን የገቡት ከከፍተኛ የሀገሪቱ ልዑክ ጋር ነው። አልሲሲ ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ተቀብለዋቸዋል። የአንድ ቀን ቆይታ በሱዳን ይኖራቸዋል የተባለው ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ምክክር…
የሱዳኑ ጠ/ሚ ግብፅ ገቡ።
የሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ ከከፍተኛ ልዑካን ጋር በመሆን ዛሬ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።
ሃምዶክ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ የግብፅ ጠ/ሚ ሙስጠፋ ማድቡሊና ሌሎች ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል።
ከሃምዶክ ጋር ወደ ግብፅ ካቀኑት የልዑካን ቡድን መካከል የውጭ ጉዳይ ፣ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ፣ የግብርና ደን፣ የንግድ፣ የውሃና መስኖ፣ የትራንስፖርት ፣ የኢንቨስትመንት ልዑካን እንደሚገኙበት ታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግብፅ ከመሄዳቸው በፊት ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የነበሩ ሲሆን በቆይታቸው ከልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ጋር ውይይት አድረግዋል።
ከቀናት በፊት የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ሱዳን ካርቱም ተገኝተው እንደነበር አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ፦
የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ በዛሬው እለት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መገለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው ፦
- ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች 49 ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ውስደዋል።
- ምርጫ ምልከት ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች ውስጥ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል።
- 47ቱ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 8209 እጩዎች አስመዝግበዋል።
- ከፍተኛ እጩ ካስመዘገቡ ፓርቲዎች መካከል የመጀመሪያው ብልፅግና ፓርቲ ሲሆን 2,432 እጩዎች አስመዝግቧል ፣ 2ተኛ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1,385 እጩዎች አስመዝግቧል ፣ 3ተኛ ደግሞ እናት ፓርቲ ሲሆን 573 እጩዎች አስመዝግቧል።
- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እጩዎቻቸውን ያላስመዘገቡ ፓርቲዎች ናቸው።
- በአጠቃላይ እጩ ካስመዘገቡት 47 ፓርቲዎች ውስጥ 4 ለክልል 2 ደግሞ ለፓርላማ የሚወዳደሩ ናቸው።
- 125 እጩ ተወዳዳሪዎች በግል ተመዝግበዋል።
- በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ችግሮች አጋጥመው ነበር ፤ ከ16 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታዎችን አቅርበው መፍትሄ ተሰጥቷቸዋል።
(Al AIN፣ Ethiopia Insider)

እነአቶ ስብርሃት ነጋ ወደማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ።
አቶ ስብሃት ነጋ ፣ ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ፣ አምባሳደር አባይ እና ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ።
ተጠርጣሪዎቹ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ የታዘዘው ዐቃቤ ህግ በመዝገብ ቁጥር 220866 የቅድመ ምርመራ መዝገብ በመክፈቱ ተከትሎ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ነው።
ጠበቆቻቸው በበኩላቸው ደንበኞቻቸው ቂሊንጦ ማረሚያቤት ለደህንነታቸው ያሰጋቸዋል ሲሉ አቤቱታ ያሰሙ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ማመልከቻ አቅርቡ ብሏል።
ፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አባባ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ አዟል።
More : https://telegra.ph/FBC-03-11
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የሱዳኑ ጠ/ሚ ግብፅ ገቡ። የሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ ከከፍተኛ ልዑካን ጋር በመሆን ዛሬ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል። ሃምዶክ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ የግብፅ ጠ/ሚ ሙስጠፋ ማድቡሊና ሌሎች ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል። ከሃምዶክ ጋር ወደ ግብፅ ካቀኑት የልዑካን ቡድን መካከል የውጭ ጉዳይ ፣ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ፣ የግብርና ደን፣ የንግድ፣ የውሃና መስኖ፣ የትራንስፖርት ፣ የኢንቨስትመንት ልዑካን…
#Update
የግብፁ ጠ/ሚር ሙስጠፋ ማዱቡሊ ሀገራቸው ፥ የኢትዮጵያን እድገት እንደማትቃወም ገልፀዋል ፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ እድገቷ ሱዳንና ግብፅን በሚጎዳ መልኩ መሆን የለበትም ነው ያሉት።
ጠቅይላይ ሚኒስትሩ ይህ የተናገሩት ከሱዳን ጠ/ሚር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
በሌላ በኩል ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክን በቤተ መንግስታቸው ተቀብለው ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው ከነበሩ አጀንዳዎች መካከል የህዳሴው ግድብ ጉዳይ እና የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውጥረት እንደነበረ ተሰምቷል።

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ መግለጫ ፦
[By : Deutsche Welle-Seyume Getu]
የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ፦
- 14 ሴት ተማሪዎች ፈተና በመውሰድ ላይ ሳሉ ወልደዋል፤14ቱ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ወዳለው የጤና ተቋም ተወስደው ከወለዱ በኋላ እንዲያርፉ ተደርገው ፈተናውን ወስደዋል፡፡
- ፈተናው ያለ ፀጥታ ችግር «በተሳካ» ሁኔታ በመላው ክልል 336 የፈተና ጣቢያዎች ተሰጥቷል።
- 150,651 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደሚወስዱ ቢጠበቅም 148 ሺ 149 ተማሪዎች ማለትም 98.43 በመቶው ፈተናውን ወስደዋል።
- የኦሮሚያ ክልል ተፈታኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 36 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ።
- በፈተናው ያልተገኙ የ2,362 ተማሪዎች እጣ ፈንታ በትምህርት ሚኒስቴር ይወሰናል።

ጥናት ፦
በብሪታንያ የተከሰተው ልውጡ ኮሮና ቫይረስ ዓይነት የያዘውን ሰው ከቀደሙት ዝርያዎች ይበልጥ ሊገድል የሚችል መሆኑን ጥናት አመልክቷል።
ጥናቱ በብሪታንያ የህክምና ጆርናል ላይ ታትሟል።
ይህ ጥናት እንደሚያሳየው /B.1.1.7/ የሚባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የያዛቸው ሰዎች፣ ከሌሎቹ ዓይነቶች በንጽጽር ከ30% እስከ 100% በሚደርስ መጠን የህልፈት የሚያደርስ አቅም አለው።
የብሪታንያ ልውጥ ኮሮና ቫይረስ መጀመሪያ በሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል የተገኘው በመከረም ወር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከመቶ ወደሚበልጡ ሃገሮች ተዛምቷል።
በሌላ በኩል ፦
የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19ን ዓለማቀፍ ወረርሺኝ ብሎ ካወጀ ዛሬ አንድ ዓመት ሞልቶታል።
Via ቪኦኤ

#Attention😷
በሀገራችን ኮቪድ-19 በእጅጉ እያሻቀበ ነው።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,065 የላብራቶሪ ምርመራ 1,332 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 17 ሰዎች ሞተዋል።
ትላንት 805 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 171,210 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,483 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 140,840 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 428 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose #Tikvah

የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦
- የትግራይና አማራ ክልል አስተዳደር እና ወሰን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ የትግራይ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን መግለፁ።
- በ3 ቀናት ብቻ ከ70 ሺ በላይ ሰዎች ከምዕራብ ትግራይ መፈናቀላቸውን የትግራይ አስተዳደር ማሳወቁ።
- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሕወሓት የሚያሰራጫቸው የውሸት መረጃዎች ለአስተዳደሩ ፈተና እንደሆኑበት ማሳወቁ።
- አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ "የዘር ማጥፋት/ማፅዳት" ፤ የአማራ ክልል እና የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ይውጡ ለታቸው።
- የአማራ ኃይል ትግራይ ውስጥ እንደሌለ አሁን የተያዙት ቦታዎች በታሪክ የትግራይ አለመሆናቸውን መግለፁና ሰፊ የሰው ቁጥር ተፈናቅሏል ስለሚባለው ጉዳይ "ፕሮፖጋንዳ" ነው ማለቱ።
- የአቶ ደመቀ መኮንን እና የሙሳ ፋኪ ውይይት።
- የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ።
- የዓለም ባንክ ለትግራይ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፁ።
[ለቲክቫህ አባላት የቀረበ]
መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ/ም
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
https://telegra.ph/Tigray-Report-Tikvah-03-11

Telegraph
Tigray Report [Tikvah]
የትግራይ እና አማራ ወሰን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ የትግራይ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን መግለፁ ፦ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ያለው የአስተዳደር እና ወሰን ችግር ከአማራ ክልል ጋር በመነጋገር ለመፍታት አስተዳደራቸው ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር ሙሉ ፥ “በዚህ ወቅት ከትግራይ ህዝብ ጎን ሆኖ ከማረጋጋት ይልቅ በችግር ላይ ችግር…
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention😷 በሀገራችን ኮቪድ-19 በእጅጉ እያሻቀበ ነው። በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,065 የላብራቶሪ ምርመራ 1,332 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 17 ሰዎች ሞተዋል። ትላንት 805 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 171,210 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,483 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤…
የዛሬ እውነታዎች (መጋቢት 2/March 11) ፦
የኮቪድ ነገር እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው። ዛሬ በተደረገው ምርመራ እንደ ሀገር በሽታው የመገኘት ምጣኔ 19 በመቶ ሲሆን በሽታው የመግኘት ዕድል በጣም ከፍተኛ የሆነበቸው አራት ከተሞች ፦
1. ሐዋሳ - 42%
2. ድሬዳዋ - 27%
3. አሶሳ - 23.5%
4. አዲስ አበባ - 20%
ሁሉም (17) ሞቶች ከአዲስ አበባ ናቸው።
እነዚህ ቁጥሮች በዓለም ጤና ድርጅት መመዘኛ ወደ complete shutdown የሚወስዱ እና እጅግ ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃ የሚያስፈልጋቸው ናቸው::
አሁንም ፦
1. የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም
2. የእጅ ንፅህና መጠበቅ
3. አላስፈላጊ መሰባሰብ መተው
4. ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል።
ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር
#SPHMMC

ሰሞኑ በሀገራችን በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል ፦ "...ልክ ፀሎት ይደረግ ተብሎ ፤ በፀሎት ሲጀመር የታጠቁ ኃይሎች መጥተው ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ አደረጉ" - በአማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበለ የተፈፀመው ጥቃት ዓይን እማኝ ከሰሞኑ ጥቃት ካስተናገዱ አካባቢዎች አንዱ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ ዳኖ ቀበሌ በእርቅ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ተፈፀመው ነው። በጥቃቱ በርከቶች ሞተዋል፤ ብዙዎችም ቁስለኛ ሆነዋል። …
እንደ ኦሮሚያ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ፦
- በ27/06/2013 ዓ/ም በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ዳቢስ ቀበሌ 22 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
- በ30/06/2013 ዓ/ም በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርቴ ጃርዴጋ ወረዳ በሀሩዳኢ ቀበሌ 20 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
በአጠቃላይ በሁለቱ የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ወረዳዎች 42 ንፁሃን ዜጎች በታጣቂዎች ተገድለዋል። በርካቶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል ገብተዋል።
ከቅዳሜ የካቲት 27/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ቀናት የተፈፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ ሲሆን ሕፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት ነው።

"...ክትባቱ የደም መርጋት አያመጣም" - የአውሮፓ ህብረት
ኮቪድ-19 እንዲከላከል ተብሎ የተሠራው የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል የተባለው ሃሰት ነው ሲል የአውሮፓ ሕብረት የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
የአውሮፓ ሕብረት ይህን ያለው ዴንማርክና ኖርዌይን ጨምሮ አንዳንድ ሃገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው መስጠት ማቆማቸውን ተከትሎ ነው።
ሃገራቱ ክትባቱን መስጠት ያቆሙት ጥቂት ሰዎች ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ምልክት አሳይተዋል ተብሎ ነው።
የEU የመድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን እንደሚለው የደም መርጋት የታየባቸው የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ካልተከተቡ ሰዎች ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው።
ባለስልጣኑ ክትባዩ የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል የተባለው ሃሰት ነው ሲልም አሳውቋል።
አስትራዜኔካ በቃል አቀባዩ አማካይነት የክትባቱ ደህንነት በብዙ ምርምርና ፈተና የተረጋገጠ ነው ብሏል።
በዩናይትድ ኪንግደም የመድኃኒት ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ክትባቱን ከደም መርጋት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም ብሏል።
ስለዚህ ሰዎች በተጠየቁ ጊዜ ሄደው ክትባቱን እንዲወስዱ እንመክራለን ነው ያለው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ