TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbabaPoliceCommission

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሠላም መጠናቀቁን አስታውቋል፤ ህብረተሰቡ ለበዓሉ በሠላም መጠናቀቅ ላበረከተው አስተዋፅኦ ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ጃንሜዳ በከተራ እና በጥምቀት በዓላት ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በከተራና በበዓሉ ዕለት በነበረው የፀበል መርጨት ስነ ስርዓት ወቅት የነበረውን ግፊያ እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም 5 የስርቆት እና 1 የቅሚያ ወንጀል ተፈፅሟል፡፡

እንዲሁም አንድ ግለሰብ አደንዛዥ ዕፅ ይዞ ሲንቀሳቀስ በፍተሻ ተገኝቶበታል፡፡

በአጠቃላይ ወንጀሎቹን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 7 ግለሰቦች ተይዘው ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን 5 የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችም በተጠርጣሪዎቹ እጅ መገኘታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በበዓላቱ ወቅት ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎችን አስቀድሞ ከመከላከል ባሻገር ተፈፅመው ሲገኙ ምርመራ በማጣራት አገልግሎት ለመስጠት በጃን ሜዳ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ በመክፈት እና የምርመራ ቡድን ተደራጅቶ ከዐቃቤ ህግ ጋር መሰራቱን ኮሚሽኑ ገልጿል።

Via Addis Ababa Police Commission
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በሁመራ፣_በዳንሻ_እና_በቢሶበር_ሲቪል_ሰዎች_ስለሚገኙበት_ሁኔታ_የተደረገ_አጭር_የክትትል_ሪፖርት_2.pdf
199 KB
ትግራይ እና አማራ ክልል ፡ የሲቪል ሰዎች ደኅንነትና ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ ወደ ሰብአዊ ቀውስ ሊያመራ ይችላል።

አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እና ድጋፍ ሊቀርብ ይገባል። - ኢሰመኮ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"..ያለው ችግር ከሚነገረው በላይ ነው" - የትግራይ ቲክቫህ አባላት

በትግራይ ክልል ባለው የኔትዎርክ መቋረጥ አሁንም ድረስ በርካታ የትግራይ የቲክቫህ አባላትን ማግኘት አልተቻለም።

ነገር ግን የተለያዩ የትራንስፖርት አመራጮችን ተጠቅመው ወደ መቐለ የገቡ አባላት በርካታ ጉዳዮችን በስልክ እያሳወቁ ይገኛሉ።

በጦርነቱ ወቅት ያለፉትን ግዚያት በሚመለከት ወደፊት ለቲክቫህ አባላት በይፋ እንደሚያሳውቁ ገልፀው አሁን ላይ በትግራይ ስላለው መጠነ ሰፊ ችግር ማሳወቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በተለይ ደግሞ ከከተሞች ወጣ ባሉና ጦርነቱ ከፍተኛ በነበረባቸው ቦታዎች ያሉ ሰዎች ዛሬም ድረስ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሆኑ አሳውቀዋል።

ያለው ችግር ከሚነገረው በላይ ነው የሚሉት የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ችግሩ በመንግስት ብቻ ይፈታል ብለው እንደማያስቡ አስገንዝበዋል።

ከዚህ ቀደም ሰርተው ግቢ የሚያገኙ፣ የሚበሉ በጦርነቱ ምክንያት የከፋ ችግር ውስጥ ወድቀዋል።

አሁንም የደህንነት ችግር ያለባቸው ቦታዎች እንዳሉ ጠቁመው ፣ ባለፉት ወራት ኤሌክትሪክ ኃይል ባለመኖሩ ፣ ምግብ ማግኘትም አስቸጋሪ በመሆኑ፣ ባንክ ባለመኖሪ፣ ስራ ለመስራት ባለመቻሉ በርካቶችም ለረሃብ አጋልጧቸዋል ብለዋል።

"ጦርነት እጅግ አስከፊ ነገር ነው ፤ በጦርነት ወቅት ስለምን ማሰብ እንዳለብህ እንኳን አታውቀም ሁሉም ነገር ቀጥ ብሎ ይቆማል ፤ በዚህ መሀል በተለይ ህፃናት፣ ተማሪዎች፣ ሴቶች ፣ እናቶች፣ እጅጉን ይጎሳቆላሉ ከነዚህ አካላት ጋር አብሮ መቆም ያስፈልጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ :https://telegra.ph/TikvahEthiopia-01-19

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...ለሶስት ወራት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ነን" - በትግራይ ክልል መንግስት ሰራተኞች

(በጀርመን ሬድዮ)

በትግራይ ክልል ማይጨውና አካባቢው የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ደምወዛቸው ለ3 ወራትያ ህል ባለመከፈሉ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጋቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

አንድ የማይጨው ከተማ ነዋሪ፥ "ምንም እንኳ ባንኮች ለአገልግሎት ክፍት ቢሆኑም ፣ ትራንስፖርት አገልግሎት ቢቀጥልም ሆነ ኤሌክትሪክ ሥራ ቢጀምሩም ደመወዝ ከኅዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ አልወሰድም፤ በከፍተኛ ችግር ላይ ነን" ሲሉ ተናግረዋል።

መንግሥት ደመወዝ ባለመክፈሉ ምክንያት የእለት እርዳታም ለማግኘት የመንግሥት ሠራተኛ ናችሁ በመባላቸው ብዙዎቹ ለችግር ተጋልጠዋል።

አንድ መምህር ዳግሞ እስካሁን ኑሯቸውን የሚገፉት ከእነርሱ የተሸለ ገቢ ካላቸው ወገኖች በሚያገኙት ድጋፍ መሆኑን ገልፀው መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ፥ በነበረው ችግር ምክንያት ባንኮች አገልግሎት ሳይሰጡ መቆየታቸውን አስታውሰው አሁን ላይ የተሸለ ነገር ስለተፈጠረ ለሠራተኞቹ በቅርቡ ደመወዛቸው ይከፈላል ብለዋል፡፡ 

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...ወታደሮቼ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት አልተሳተፉም" - ሶማሊያ

የሶማሊያ መንግሥት ወታደሮቹ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ተሳትፈዋል ሲሉ የወጡ ዘገባዎች ትክክል አይደሉም አለ።

ይህን ያለው የቀድሞ የሶማሊያ ከፍተኛ የደኅንነት ባለስልጣን ከጥቂት ወራት በፊት ኤርትራ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ወታደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ተገድለዋል ካሉ በኋላ ነው።

አብዲሰላም ጉሌድ የተባሉት የሶማሊያ ብሔራዊ የደኅንነትና መረጃ ተቋም የቀድሞ ምክትል ኃላፊ ተጨባጭ #ማስረጃ ሳያቀርቡ ለአንድ የግል ሬዲዮ "400 የሚደርሱ የሶማሊያ ወታደሮች" በትግራይ ክልል በተካሄደው ውጊያ ተገድለዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የቀድሞው ባለስልጣን ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ጋር ተሰልፈው ሲዋጉ ተገድለዋል ያሏቸው የሶማሊያ ወታደሮች በ20 እና በ30 ዓመት ዕድሜ ውስጥ የነበሩ ናቸው።

ይህ የግለሰቡ ንግግር በተለያዩ የሶማሊያ ክፍሎች ውስጥ ቁጣን ቀስቅሷል።

ልጆቻቸው ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ውጪ አገራት የሄዱ ቤተሰቦች ጉዳዩ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ መንግሥት ልጆቻቸው የት እንዳሉ እና በሕይወት ይኑሩ ወይም ይሙቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

የሶማሊያው የማስታወቂያ ሚኒስትር ኦስማን አቡከር ዱቤ ፥ "የሶማሊያ ኃይሎች በቅርቡ በኢትዮጵያ በተካሄደው ውጊያ ላይ አልተሳተፉም" ብለዋል።

ሚኒስትሩ ከቢቢሲ የሶማሊኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልልስ "ከዚህ ቀደም የሶማሊያ ወታደሮች በሊቢያና በአዘርባጃን ውስጥ በተካሄዱ ውጊያዎች ውስጥ ተሳትፈዋል ተብሎ ቢወራም ኋላ ወሬው ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል" ብለዋል።

ጨምረው የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያው ግጭት ውስጥ ተሳትፈዋል የተባለው ወሬ ሐሰተኛ ነው ብለዋል። ~ ቢቢሲ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KonsoZone

ኮንሶ ዞን ካራት ከተማ በዛሬው ዕለት የተከበረው የጥምቀት በዓል እንዲሁም ትላንት የተከበረው የከተራ በዓል ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁ ተገልጾልናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tigray

"...የዕለት ደራሽ እርዳታው በተገቢው መንገድ እየደረሰን አይደለም" - በመቐለ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች

ባለፉት 2 ወራት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች ከሌላው አካባቢ በተለየ ሁኔታ ወደሌላው የትግራይ አካባቢ እና ወደ ሱዳን ተፈናቅለዋል።

ተፈናቃይ ወገኖች በጦርነቱ ምክንያት ለከባድ ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተዳርገዋል።

የተለያዩ ቤተሰቦቻቸው ወደ ተለያየ ቦታ በመበታተናቸው ህልውናቸውን ለማረጋገጥ እና ወደ ቤታቸው ለመመለስ የተመቻቸ ነገር እንደሌለ በመቐለ የተጠሉሉ ዜጎች ለትግራይ ቲቪ ተናግረዋል።

ከተፈናቃዮች መካከል አንደኛው ከወላጅ እናቱ እና ከእህቱ ጋር ይኖር እንደነበር እና ሁሉም ህይወቱን ለማትረፍ ወደ ተለያየ ቦታ እንደሸሸ ገልፆ በዚህም ምክንያት እናትና እህቱ የት እንደገቡ ፤ ይኑሩ ይሙቱ እንደማያውቅ እነሱም ስለሱ የሚያወቁት ነገር እንደሌለ ተናግሯል።

ሌላኛው ከሁመራ የተፈናቀለ ግለሰብ፥ ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይሁን ሌላ አካል ያደረገው ነገርና ስለመመለሳቸውም የተሰጣቸው መረጃ እንደሌለ ገልጿል።

ተፈናቃዩ ፥ ቤቶቻቸውን ሌሎች ሰዎች እንደገቡባቸውና ብዙ ንብረት ትተው በመፈናቀላቸው ከባድ ችግር ውስጥ እንዳሉ ገልጿል።

አንድ እድሜያቸው ገፋ ያለ እናት ደግሞ : "የራሴ ቤት እና እርሻ ነበረኝ፥ ልጄ እዛው ነው በስልክ እንደነገረኝ ከሆነ ንብረታችን በሙሉ እየተወሰደ ነው። ለኔ ግን እንኳን ልጄ አልሞተ እንጂ ንብረት ቀረብኝ አልልም ሰርቼ መልሰዋለሁ።" ብለዋል።

የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የዕለት ደራሽ እርዳታ እየሰጠ ቢሆንም ተፈናቃዮች ተገቢውን እና በቂ ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tigray

ዛሬ ጥር 11/2013 ዓ.ም የሰላም ሚኒስቴር ለሚዲያዎች ባሰራጨው መግለጫ : በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እየቀረበ ነው ብሏል።

ሚኒስቴሩ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እና የሕክም አቅርቦቶችን የያዘ የሰብዓዊ ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 1.8 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ደርሷል ብሏል።

አክሎም በክልሉ 2.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ገልጿል።

* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...ከተራ እና ጥምቀት በሰላም ተከብሯል" - አማራ ክልል ፖሊስ

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች የከተራ እና የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም መከበሩን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ2013 ዓ.ም ጥምቀት በዓል በትግራይ ማይጨው ከተማ ተከብሯል።

በዓሉ የእምነት አባቶች ፣ በርካታ ምእመናን በተገኙበት ነው የተከበረው።

በሌላ በኩል በትግራይ መዲና በመቐለ ቅድስት ማርያም (ማርያም ጉግሳ)፣ በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የ2013 ጥምቀት በዓል ተከብሯል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT