TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የ2013 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።

PHOTO : TIKVAH, ENA, GONDAR COMMU. , AMMA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በሱዳን ደቡብ ዳርፉር አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ።

በሱዳን ደቡብ ዳርፉር ግዛት በሪዜይጋት እና ፈላታ ጎሳዎች መካከል ትናንት ሰኞ ግጭት መቀስቀሱን አል ዓይን የሱዳን ዜና ወኪልን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ (AlAIN) ዘግቧል፡፡

በአካባቢው አንድ እረኛ መገደሉን ተከትሎ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተገድለዋል፥ ቆስለዋል ሲሉ የደቡብ ዳርፉር አስተዳዳሪ ሙሳ ማህዲ ገልጸዋል፡፡

ከእረኛው ግድያ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ዳርፉር ዋና ከተማ ንያላ 85 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አል ጣዊል መንደር ፣ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ነው ሰዎች የተገደሉት እና የቆሰሉት፡፡

አሁን ከደረሰው ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ግጭቱ ወደተከሰተበት አካባቢ ተጨማሪ የጸጥታ ኃይሎች መላካቸውንም የግዛቱ አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡

ከ3 ቀናት በፊት ጥር 08 በሱዳን የምዕራብ ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ አል ጂኔይና በጎሳ ግጭት የሞቱ ሰዎች 129 መድረሳቸው መገለፁ ኣይዘነጋም። ~ አል ዓይን

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Sudan

እንደ AFP መረጃ በሱዳን በ "ደቡብ ዳርፉር" በኩል በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት እስካሁን 55 ሰዎች ሞተዋል ፥ 37 ሰዎች ቆስለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የጥምቀት በዓል በኤርትራ ተከበረ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመግታት በተቀመጠው ጥብቅ በሆነ ገደብ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል #በኤርትራ ተከብሯል።

በበዓሉ በኮቪድ-19 ምክንያት በርካቶች መገኘት አልቻሉም።

በኤርትራ መዲና "አስመራ ከተማ" (ከላይ ፎቶው ተያይዟል) በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች የጥምቀት በዓል በልዩ ሁኔታ ተከብሯል።

ኤርትራ ውስጥ እስካሁን በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 1,877 ሲሆን ከነዚህ መካከል 1,073 ሰዎች አገግመዋል ፤ 6 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሞተዋል።

ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ በሀገሪቱ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።

Photo : Yemane G. Meskel
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በጃንሜዳ ያደሩ ታቦታት ወደ መቅደሳቸው እየተሸኙ ነው።

አ/አ ጃንሜዳ ካደሩት የ15 ደብሮች ታቦታት መካከል የ12 ደብሮች ታቦታት ወደ መቅደሳቸው እየተሸኙ ነው።

ምዕመናኑ ታቦታቱን በእልልታና በሆታ፤ ካህናቱ በአኮቴት (ምስጋና) እና ሽብሸባ ታቦታቱን ወደ መቅደሳቸው እየሸኙ ይገኛሉ። ~ ENA

@tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ።

የጥምቀት በዓል በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች ተከብሯል።

PHOTO : ኢቲቪ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ጥምቀት በዮርዳኖስ ወንዝ ተከበረ።

በዛሬው ዕለት በእስራኤል (እየሩሳሌም) የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ገዳማት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንባቆም እንዲሁም የገዳሙ መነኮሳት እየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀበት ቦታ "ዮርዳኖስ ወንዝ" ወርደው በዓሉን አክብረዋል።

በዮርዳኖስ ወንዝ የሚከበረው በዓል ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ተራ የተሰጠ ሲሆን ፣ ዛሬ የግሪክ ኦርቶዶክስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ነገ የሶሪያና የግብጽ፣ በቀጣይ የአርመን፣ የሩሲያ እና ሌሎችም ያከብራሉ።

የዘንድሮው በዓል የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በወጣው መመሪያ መሠረት የእንቅስቃሴ ገደብ ስለተጣለ ለመግባት የተፈቀደው ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ በመሆኑ ብዙ ምዕመናን መሄድ አልቻሉም።

Via Ethiopian Embassy in Israel (AMMA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በከተራ በዓል ላይ በደረሱ የኤሌክሪክ አደጋዎች 2 ወጣቶች ሞቱ።

ትላንት በአማራ ክልል በሰቆጣ እና በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ሸረሮ ከተሞች የከተራ በዓል በሚከበርበት ወቅት በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ የ2 ወጣቶች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አሰታውቋል።

የሰቆጣ ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት በከተማው የከተራ በዓል በሚከበርበት ወቅት ታቦታቱን ከፀሃይ የሚከላከል ጥላ ከኤሌክትሪክ ጋር በመነካካቱ  በተከሰተ የኤሌክትሪክ አደጋ የአንድ ወጣት ህይወት ወድያው አልፏል።

በሌሎች ጥላውን በመግፈፍ ላይ በነበሩ ስምንት ወጣቶች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች በሰቆጣ ተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረሊባኖስ ወረዳ ሸረሮ ከተማ ለጥምቀት በዓል ማድመቂያ ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀል የሞከረ የ24 ዓመት ወጣት ህይወቱ ማለፉን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

ወጣቱ ፎቅ ላይ ሆኖ የወረወረው ገመድ 33 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ ገመድ ላይ በማረፉ በእርጥብ እንጨት ለማንሳት ሲሞክር በኤሌክትሪክ ሀይል ተገፍተሮ ሊወድቅ ችሏል።

ወጣቱ ወደ ሽረሮ ጤና ጣቢያ ቢወሰድም ከ30 ደቂቃ በኃላ ህይወቱ አልፏል። ~ ENA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT