TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
4 መኮንኖች በዋስትና እንዲለቀቁ ተፈቀደ።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን በመመልመል ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ 4 መኮንኖች በ100 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወሰነ።

ተጠርጣሪዎቹ ሌ/ኮሎኔል ምሩፅ በርሔ ፣ ኮሎኔል ገብረመድሕን ገብረመስቀል ፣ ኮሎኔል ተስፋይ ሃጎስ እና ኮሎኔል መብራቱ ተድላ ናቸው።

4ቱ መኮንኖች ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በርካታ ቀናት መቆጠሩን እንዲሁም መርማሪ ፖሊስ በተደጋጋሚ ሚሰጠውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መረጃዎችን በአግባቡ እየሰበሰበ ባለመሆኑ እያንዳንዳቸው የ100 ሺ ብር ዋስትና አስይዘው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ~ ENA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#AyatollahAliKhamenei የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ በአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም የተመረቱ ክትባቶች ኢራን ውስጥ እንደታገዱ በይፋ ተናገሩ። አል ካሚኒ በክትባቶቹ ውጤታማነት ላይ እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል። በUK እና US ክትባት ላይ ያላቸውን ስጋት ለኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ካሳወቁ በኃላ በይፋ እንደተናገሩ ገልፀዋል። አሊ ሃሚኒ "የነዚህ ሀገራት (US እና UK…
#Iran

የኢራን ፕሬዝዳንት ሐሰን ሩሀኒ ኢራን ውስጥ የምዕራባዊያን አገሮች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ሙከራ እንዳይደረግ ከለከሉ፡፡

ሃሰን ሩሀኒ ኩባንያዎቹ ለክትባት ሙከራው ወደ ኢራን እንዳይመጡ ከልክለዋል።

ፕሬዝዳንት ሩሃኒ ህዝባችን የምዕራባዊያን የክትባት መሞከሪያ አይሆንም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ከቀናት በፊት የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ በአሜሪካ እና በብሪታንያ የተሰሩ ክትባቶች ኢራን ውስጥ ስለመታገዳቸውን በይፋ መናገራቸው ይታወሳል።

መረጃው የሚድል ኢስት ሞኒትር / ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው።

@tikvahethiopia
#FDREDefensForce

የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የህወሓት አመራሮች ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ማስረከቡን አሳውቋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ያስረከባቸው የትግራይ ክልል የቀድሞ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ ፣ የቀድሞ ምክትል ር/መስተዳደር ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የህወሓት አመራሮችን ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ አለፈ።

በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 128,616 ደርሷል ፤ ከነዚህ መካከል 113 ሺህ 563 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 201 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና እየተከታተሉ ነው።

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElectricPower

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በትግራይ ክልል የ'ህግ ማስከበር ዘመቻ' ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ከተሞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አዳጋች እንደሆነበት ለአሃዱ ሬድዮ ገለፀ።

መንግሥት በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረውን የ "ህግ ማስከበር ዘመቻ" አጠናቅቅያለሁ ባለ ሰሞን በትግራይ ክልል ከተሞች የተቋረጠውን የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በአጭር ጊዜ እንደሚመልስ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁንም ድረስ በአክሱም ፣ በአድዋ፣ በሽረ እና በሌሎች ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አዳጋች እንደሆነበት አስታውቋል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለመመለስ በኤሌክትሪክ መስመሮቹ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ መሳሪያዎች ላይ ከፍተኛ ጥገና ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በመሆኑም ጥገናውን ለማድረግ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል እና ወጪ ከፍተኛ መሆኑ አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግሯል፡፡ ~ አሃዱ ሬድዮ ጣቢያ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
👆ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የሶስትዮሽ ስብሰባ የፕሬስ መግለጫ። የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂደዋል። ሱዳን የባለሙያዎቹ የተጨማሪ ሃላፊነት ቢጋር ካልተዘጋጀ በቀር ውይይት መካሄድ አይችልም የሚል አቋም መያዟ ተገልጿል። ኢትዮጵያ የሱዳንን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል በግድብ ደህንነት ፣ በመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በሌሎች…
ሱዳን ወደ ግድቡ ድርድር ተመለሰች።

ሱዳን ትናንት ውድቅ ያደረገችውን ፣ ከባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ የማድረግ ሀሳብ መቀበሏን ገልጻለች።

የአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ከፍተኛ ሚና ካልኖራቸው በድርድሩ አልሳተፍም በሚል ሱዳን ራሷን ከድርድሩ ማግለሏን ገልጻ ነበር፡፡

ምንጭ ፦ አል ዓይን ኒውስ (telegra.ph/AlAIN-01-11)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የታህሳስ ወር ደመወዝ መዘግየት ...

በ2013 በጀት ዓመት በወላይታ ዞን ከተበጀተው ጠቅላላ በጀት ወደ 8 መቶ ሚሊዬን የሚጠጋ የድጎማ ቅነሳ በተለያየ ምክንያት በመደረጉ (በመቀነሱ) በወላይታ ዞኑ የጥሬ ገንዘብ እና የበጀት እጥረት መከሰቱን የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ገለፀ።

መምሪያው ከታህሳስ ወር ደመወዝ መዘግየት ጋር በተያያዘ እየተነሳ ለነበረው ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል።

መምሪያው የየሴክተር መሥሪያ ቤቶች የደመወዝ ክፊያ ጥያቄ ባቀረቡት መሠረት ፔሮል ተሠርቶ ደመወዝ የሚከፈልበት ሥርዓት በባንክ በመሆኑ በጊዜ የደመወዝ ክፊያ ትዕዛዝ ወደ ባንክ ተልዕኮ ከኔትወርክ ችግር የተነሳ ወደ ሠራተኛው አካውንት ደመወዝ በጊዜ ሳይገባ ቀርቷል ብሏል።

ይህ የኔትወርክ ችግር የተፈጠረው በገና በዓል ዋዜማ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በመሆኑ ለሠራተኛው ለበዓል ደመወዝ እንዳይደርስ እንዳደርግ አስረድቷል።

የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደስታ ዳና ችግሩ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ቁጥጥር ውጪ መሆኑን በመግለፅ ተመሣሣይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት ከባንኩ ጋር በመናበብ ይሠራል ማለታቸውን ከዞኑ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#SolomonMuchie

ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሙጬ ለፋሲል ከነማ የስፖርት ክለብ ገቢ ማስገኛ ባለፈው ክረምት ካሳተመው "ዳሳሽ መዳፎች" ከተባለው ድርሰቱ የ40 ሺህ ብር ወይም 200 መጽሐፍቶችን በነፃ አበረከተ።

ጋዜጠኛው ፋሲል ከነማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ሲቀላቀል በሬዲዮ ፋና ዘገባውን የሰራ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል ፋሲል ከነማ በሜዳው ያደርጋቸው የነበሩ ጨዋታዎችን በጎንደር ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ሬድዮ ጣቢያ በቀጥታ በማስተላለፍም ይታወቅ ነበር።

"ለምወደው እና ታሪኩንም በድርሰቱ ውስጥ ላካተትኩበት ፋሲል ከነማ መጽሐፍቶችን ሳበረክትለት እጅግ ከከፍተኛ የደስታ ስሜት ጋር ነው።" ብሏል ጋዜጠኛ ሰለሞን በላከልን መልዕክት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia