TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FDREDefenseForce

ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተባለ።

ይህን የገለፁት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሜጄር ጄነራል መሀመድ ተሰማ ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

ሜ/ጄ መሀመድ ፥ "የህወሃት ቡድን በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ ወረረችን በማለት ህዝቡን እያደናገረ ነው" ብለዋል።

በተቀናበረ ድራማ ህዝቡ ሳይታለል ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን 'ድጋፍ አጠናክሮ' እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREAirForce

የአየር ኃይል ዋና አዛዥ የሆኑት ሜ/ጄ ይልማ መርዳሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የህወሓት ቡድን ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ኢላማዎች ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል ብለዋል።

አየር ኃይሉ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ኢላማዎችን ያለምንም ከልካይ አውድሟል ሲሉ ተናግረዋል።

ሜ/ጄ ይልማ ፥ "ፓይለቶቻችን የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው እየሄዱ ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ ይገኛሉ" ብለዋል።

አሁንም ይህ የጥፋት ኃይል ህግ ፊት እስኪቀርብ ድረስ ያለምንም ከልካይ ተፈላጊ ኢላማዎችን እናጠቃለን ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የጋዜጠኞች መታሰር'

የAddis Standard አዘጋጅ መድሃኔ እቁባሚካኤል እንደገና ለእስር መዳረግ፣ የአውሎ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው መታሰር እንዳሳሰባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገለፁ።

ኮሚሽነሩ ከሚዲያ ጋር የተገናኘ ጥፋት ጠፍቶም ከሆነ ፍትሃዊ በሆነ መንገድና ስርአትን በተከተለ ሁኔታም እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ የEPA ጋዜጠኞች ሃፍቱ ገ/እግዚአብሔር ፣ ፀጋዬ ሃዱሽ እና አብርሃ ሃጎስ እንዲሁም የOMN ጋዜጠኛ የሆነው ኡዲ ሙሳ ተጨማሪ 4 ጋዜጠኞች መታሰር ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

ቅዳሜ እለት ጥቅምት 28/2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው መድሃኔ ቢለቀቅም ሰኞ እለት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ/ም እንደገና እንደታሰረም ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ሲፒጄ የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው እንዲፈታ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጥሪ አቅርቧል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አርማው እንዲከበር ጠየቀ !

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በግጭቱ የተጎዱ የጦር ሰራዊት አካላትን የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ የሚሰጡ እና ጉዳተኞችን በአቅራቢያ ወደሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያደርሱ 3 አምፑላንሶቹ ላይ ጥቅምት 30 ቀን 2013 "በዳንሻ አከባቢ" የታጠቁ ሃይሎች ተኩስ በመክፈት ጉዳት እንዳደረሱበት አሳውቋል።

ከጥቅምት 24 ጀምሮ ከአስር በላይ አምፑላንሶችን በማሰማራት በሁለቱም ወገኖች በግጭቱ የተጎዱ ወገኖቹን እያገለገለ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ ድርጊቱ አለም አቀፍ መርህ እና የቀይ መስቀል አርማ አጠቃቀም ህግን የጣሰ ነውም ብሎታል።

ማኅበሩ በጎፈቃደኞች ፣ ሰራተኞች ሌሎች የህክምና አካላት በግጭት ወቅት የግጭት ተሳታፊ ያልሆኑትንና ተሳታፊ መሆናቸውን ለዘለቄታ ያቆሙ ሰዎችን ህይወት መታደግ እንዲችሉ ሰብዓዊ እንቅስቃሴያቸው እንዳይታወክ ጠይቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል!

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,183
• በበሽታው የተያዙ - 400
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 981

አጠቃላይ 100,727 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,545 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 62,497 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

292 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ፥ አሁን ችግሩ ያለው በ2ቱ መንግስት መካከል ሳይሆን በኢትዮጵያ አንድነት ፈላጊዎችና ኢትዮጵያን በሚበትኑ ሰዎች መካከል ነው ብለዋል።

የተፈጠረው ሁኔታ በኢትዮጵያ ህዝብ እና በጁንታው መካከል ነው ፤ ዝም ብሎ የፖለቲካ ጨዋታ አይደለም ሲሉ ገልፀዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ "ችግሩ በአብይ መንግስት እና በትግራይ መንግስት መካከል ነው የሚባል ነገር የለም ፣ እንደዚህ ወርዶ መቀመጥም የለበትም፣ እሱ ከሆነ ሁለቱን አስወግደህ ለምን ኢትዮጵያን አታስቀጥልም ? ችግሩ ግን ያ አይደለም" ሲሉ ለዶቼ ቨለ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'የሰላም ጥሪ በሚመለከት'

የሰላም ጥሪ ከኦፕሬሽን በፊት መጀመር ነበረበት አሁን ወደዛ መመለስ እንደማይቻል ተገልጿል።

ቀፎውን ተነክቶ ንቡ ከተነሳ በኃላ ንቡን ወደ ቀፎው መመለስ አይቻልም። ንቡ የሚፈልገውን ነገር ካደረገ በኃላ ነው ወደ ቀፎው የሚመለሰው ተብሏል።

አሁን ያለው ሁኔታ ወደኃላ የሚመለስ አይደለም።

የሚፍለጉት ሰዎች ስም ዝርዝራቸው ተቀምጦ እጅ ሲሰጡ ያን ጊዜ ሰላም ይፈጠራል ተብሏል።

መከላከያው በሀገር አንድነት ላይ የመጣን ነገር በድርድር መፍታት አይቻልም ብሏል።

* መከላከያ ሰራዊት
* ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
'የUNHCR ሪፖርት'

ባለፉት ሁለት ቀናት ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ለሸሹ 7,000 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የነብስ አድን እርዳታ ለማድረስ እየጣረ መሆኑን የተመድ የስደተኛ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ማሳወቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

UNHCR በፌዴራል መንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ሱዳን ከደረሱት አብዛኛውዎቹ ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን ገልጿል።

በገዳሪፍ ሉጅ እና በከሰላ ክፍለ ሀገር ሀም ዳየት በጊዜያዊ መጠለያዎች አርፈው ለጊዜው ምግብና ውሃ እየቀረበላቸው ነው።

በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ሁኔታ የሚፈናቀለው የሰላማዊ ሰው ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል በመገመትም በሌሎች የአካባቢው ሀገራት ተመሳሳይ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን UNHCR አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PMOEthiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እውቅና ያላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጨምሮ ሁሉም ግለሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያንፀባርቅ እና ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#BREAKING

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ 'በወንጀል የተጠረጠሩ' የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን አሳወቀ።

በዚህም መሰረት፦

- ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
- አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
- አቶ አባይ ፀሃዬ
- ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
- አቶ ጌታቸው ረዳ
- አቶ አፅበሃ አረጋዊ
- አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ ጨምሮ ሌሎችን ግለሰቦችን ያለመከሰስ መብታቸውን ምክር ቤቱ አንስቷል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች የጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋትና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው ተብሏል።

* በአጠቃላይ 38 ግለሰቦች ናቸው።

በሌላ በኩል፦

የህ/ተ/ም/ቤት አቶ ፍቅሩ ገ/ሕይወትን የምርጫ ቦርድ አባል አድርጎ ሾሟል። (HoPR)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት ! የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ ሰባት የጄኔራል መኮንኖች ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጿል። ጄኔራል መኮንኖቹ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በመናድ እና በሀገር ክህደት ወንጀል የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ፍርድ ቤት የቀረቡት በ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፍቃዱ መዝገብ የሚጠሩ 7 ተጠርጣሪዎች ናቸው።

የቀረቡት ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ነው።

የወንጀል ምርመራ ቢሮ ፦

ተጠርጣሪዎች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም መቐለ ከተማ ለሚገኘው 'የሕወሓት ቡድን አመራሮች' መረጃ በመስጠት እንዲሁም ተልዕኮ በመቀበል የሬዲዮ መገናኛውን በመጥለፍ ሠራዊቱ እርስ በእርሱ እንዳይገናኝ በማድረግ ሀገር የማፍረስ ወንጀል ሠርተዋል በሚል ጠርጥሯቸዋል።

ድርጊቱን በመፈፀማቸው በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለህልፈትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል ፤ ከባድ የሆነ የንብረት ውድመት ደርሷል ብሏል።

በእነዚህ እና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ፦

የተጠቀሰውን ወንጀል አልፈፀምንም ሲሉ ተከራክረዋል።

ፍርድ ቤት ፦

ግራ ቀኙን የመረመረው ፍርድ ቤት የወንጀሉን ውስብስብነት እና ክብደት በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ከግምት በማስገባት ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል።

የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅም ለህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

ዓለም የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ወደማግኘት እየተቃረበ ቢሆንም የኮቪድ-19 መከላከያዎችን ማላላት የለበትም ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰቡ።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ "የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) አሁንም የዛሬ 8 ወር እንደነበረው አስጊ ወረርሽኝ መሆኑን እንደቀጠለ ነው" ብለዋል።

በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኝ የሰላም ጉባዔ ላይ "በኮቪድ-19 ታክቶን ይሆናል ነገር ግን እርሱ ገና አልሰለቸንም" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም።

የአውሮፓ አገራት እየታገሉ ነው ነገር ግን ስርጭቱን ለማቆም የተወሰዱት እርምጃዎች እንዲሁም ቫይረሱ ምንም ለውጥ አላሳየም" ሲሉ ተናገረዋል።

ከሰሞኑን የተለያዩ ሀገራት ተመራማሪዎች "ውጤታማ" የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን እየገለፁ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ገና ደህንነቱ እና ውጤታማነቱ መፈተሽ ባለበት ክትባት ላይ መተማመን አደገኛ መሆኑን ገልፀዋል።

"ክትባት በፍጥነት ያስፈልጋል ፣ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን ቁጭ አንልም" ብለዋል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,478
• በበሽታው የተያዙ - 521
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 771

አጠቃላይ 101,248 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,554 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 63,268 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

313 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዶክተር ደብረፅዮን መገለጫ ፦

ዛሬ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ዶ/ር ደብረፅዮን እየተደረገ ባለው ጦርነት ኤርትራ ወታደሮች ከፌዴራል የፀጥታ ኃይል ጋር ግንባር ፈጥረው እየወጉን ነው ብለዋል።

ይህን በተጨባጭ ማሳየት እንችላለን ፣ የያዝናቸው የኢሳያስ (ኤርትራ) ወታደሮች አሉ ሲሉ ገልፀዋል።

እስካሁን ከ10 ሺ በላይ ወታደሮች ማርከናል ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የኢሳያስ ወታደሮች አሉበት ብለዋል።

ዶክተር ደብረፅዮን ፥ ለኢሳያስ ተሰጥቶ "በሻብያ ወታደሮች" ቁጥጥር ስር የነበሩ/የትግራይ ቦታዎችን ማስመለስ ችለናል ሲሉም ተደምጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም "የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፓዎር" የአየር ድብደባ ተፈፅሞበታል ፤ የትግራይ ከተሞችም ጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገዋል ሲሉ ከሰዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን፥ " አሁንም በተለያዩ አቅጣጫዎች የጦርነት ዝግጅቶች አሉ ። ውጊያው ገና ነው ፤ ገና ጅምር ነው " ሲሉ ተናገረዋል።

* ሙሉ መግለጫ (27 MB) ከላይ ተያይዟል (WiFi ተጠቀሙ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
* Federal Police Commission

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን "በሀገር መክዳት ወንጀል" ፈፅመዋል ያላቸውን የህወሓት አባላት ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ትዕዛዛ እንደወጣባቸው ባሰራጨው መግለጫ አሳውቋል።

* መላው ህዝቡ ፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ፣ ፖሊስ አባላት ፣ የደህንነት ተቋማት ተፈላጊዎቹን አድኖ ለህግ ለማቅረብ እያደረጉ ያለውን ጥረት ባለበት ሆኖ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ህዳር 3/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia