TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FDREDefenseForce

በአሁኑ ሰዓት ፤ የኮማንዶ ፣ የልዩ ሀይልና ፀረ ሽብር ሰልጣኞች ፣ የጠላትን ማዘዣ አጥቅቶ የመመለስ ትርዒት ፣ ለጦር ሀይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ለኦፕሬሽናል ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ እና ለሌሎች እንግዶች በማሳየት ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#300Lives3Months

ከትናንት በስቲያ ኢትዮጵያን የተመለከተ እና ለ24 ሰዓታት የዘለቀ የትዊተር ዘመቻ ተካሂዷል።

በዚህ ዘመቻ ጥቅም ላይ የዋሉት ሃሽታጎች (የዘመቻ ሐረጎች) ከ40 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ጋር መድረሳቸውን የትዊተር አናሊቲክስ ድረ-ገጾች አመልክተዋል።

ከቶክ ዎከር ድረ-ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጥቅምት 12 እና 13 ላይ #300Lives3Months የተሰኘው ሃሽታግ 44.5 ሚሊዮን ትዊተር ተጠቃሚ ሰዎች ጋር ደርሷል።

239 ሺህ ሰዎች ደግሞ #300Lives3Months የሚለውን ሃሽታግ የያዘን ትዊት ክሊክ አድርገዋል ፣ አጋርተዋል ፣ መውደዳቸውን አሳይተዋል (ላይክ አድርገዋል)፣ ተከትለዋል፤ አልያም አስተያየት ሰጥተውበታል።

ስለዚህ የትዊተር ዘመቻ ዓላማ/ግብ አስተባባሪዎቹ ወጣት እያስፔድ ተስፋዬ እና ሳሙኤል በቀለ ለBBC ተናግረዋል።

የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ዓለም አቀፍ እና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ከBBC ተጠይቀው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-10-24

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
''ፓርኩ ላይ የተደቀነ አደጋ አለ'' - አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ከሰሞኑ ምን አጋጥሞት ይሆን ? በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ 'አደጋ ላይ' መሆኑን እያነሱ መፍትሔ እየጠየቁ ይገኛሉ። ጉዳዩን በተመለከተ የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴን በስልክ አነጋግረናቸው ነበር። አተ ብርሃኑ በሰጡን ምላሽ ሰሞኑን የተከሰተ አዲስ ጉዳይ ባይኖርም በተደጋጋሚ…
የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ጉዳይ ፦

'ሠላምና ከተሞች' በሚል በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ፎረም የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የተደቀነበትን ሥጋት አስመልክቶ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በምላሹ መስሪያ ቤታቸው ከሚመለከታቸው ሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክን በሚመለከት ምላሹን ለማሳወቅ ቃል ገብተዋል፡፡

በፎረሙ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የተጋረጡበት ችግሮች ተፈተው ለቱሪስቶች ክፍት መሆን እንደሚገባው መግለጻቸውን ከጋሞ ዞን ኮሚውኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በ2 ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አልፏል ! በጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት…
የጉራፈርዳው ጥቃት ፦

በጉራፈርዳ በተፈፀመው ጥቃት የአካባቢው አርሶ አደሮች እጅግ በጣም እንደተጎዱ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

ከቀበሌያቸው ሸሽተው በሌላ ከተማ ከተጠለሉ ሰዎች መካከል አቶ ተዘራ ይማም ብዙ ቤተሰብ እንደተገደለባቸው ተናግረዋል።

አቶ ተዘራ ፥ እህት ፣ ወንድም ፣ ሰራተኛ ፣ የቅርብ ዘመድ እንደሞተባቸው ተናግረው፤ "እኛም እንዳለን አንቆጥረውም" ብለዋል።

አገዳደሉ የተደራጀ ነው በገጀራ ፣ በጦር ፣ በጥይት ነው የተፈፀመው ሲሉ ገልፀዋል።

ጥቃት ያደረሱ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው የማያዳግም እርምጃ ካልተወሰደ እንደማይዘልቁት ተናግረዋል።

ሌላው ቢፍቱ ከተማ የተጠለሉ ስማቸው ያልተገለፀ ተፈናቃይ ፤ ማንነታቸው እየተመረጠ ጥቃት እንደተፈፀመ ገልፀዋል።

ከወጣት እስከ አረጋውያን ፣ እናቶች ፣ ህፃናት ተገድለዋል ብለው ፤ አሁንም በቂ የፀጥታ ኃይል ካልገባ ጥቃቱ ሊብስ እንደሚችል ገልፀዋል።

የተገደሉት አብዛኞቹ ምንም የማያውቁ ገበሬዎች ናቸው ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጉራፈርዳ ወረዳ የተፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ መሆኑ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የመንግስትና የግል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የኮቪድ ፕሮቶኮል የሚጠይቀውን መስፈርት ሙሉ ለሙሉ አሟልተው መገኘታቸው እየተረጋገጠ ከጥቅምት 23 / 2013 ዓ/ም ጀምሮ የሰልጣኞች ቅበላ የሚያደርጉ ይሆናል ተብሏል፡፡

የቅበላ ጥሪ የሚደረግላቸው በ1ኛ ዙር የተለዩ የ2012 ዓ/ም ስልጠና አጠናቃቂዎች ብቻ ሲሆኑ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከላትም በዚሁ አግባብ በወጣው የአፈፃፀም መመሪያ መሰረት ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በነቀምቴ ቀበሌ 05 ቀሶ ምንድነው የሆነው ?

ትላንት በነቀምቴ ከተማ ቀበሌ 05 ቀሶ የሚባል ትምርትቤት አካባቢ የፀጥታ ኃይሎች አምስት (5) ወጣቶች መግደላቸው ተገልጿል።

ከአምስቱ አራቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሆኑና አንድ ላይ ተከራይተው ከሚኖሩበት ቤት ውስጥ አውጥተው መንገድ ላይ ነው የተገዱሉት ብለዋል የነቀምቴ መልዕክት አድራሾች።

በሰዓቱ የሰፈሩ ሰው ከቤቱ እንዳይወጣ አስክሬንም እንዳይነሳ ተከልክሎ ቆይቷል፤ በኃላ የፀጥታ ኃይሎቹ ከሄዱ በኃላ ነው አስክሬን የተነሳው። (ይህ መረጃ ከታቦር ድሪርሳ የተገኘ ነው)

በሌላ በኩል ፦

የነቀምቴ ከተማ ልዩ ፖሊስ "አራት የአባቶርቤ" አባላት ላይ እርምጀ ወስጃለሁ ማለቱን OBN ዘግቧል።

ግለሰቦቹ ሊገደሉ የቻሉት "አባቶርቤ" በሚል ስም በተለያዩ ጊዜያት የሰዎች ሕይወት በማጥፋት ተጠርጥረው ጥቅምት 13 /2013 ከቀኑ 5:30 ቀሶ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ላይ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው ጥረት ፖሊስ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው መሆኑን የነቀምቴ ከተማ የልዩ ኃይል ኃላፊ ኮማንደር ግርማ አብዲሳ ገልጸዋል፡፡

ከተወሰደው እርምጃ ጋር ተያይዞ 2 ቦምብ ፣ 3 ሽጉጦች ፣ ድምጽ አልባ የጦር መሳሪያዎች እንዲሁም የቀድሞ የአገር መከላከያ ሰራዊት አልባሳት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ግርማ ገልጸዋል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"በእርቅ ውስጥ ሁሉም አሸናፊ ነው" - ቀሲስ በላይ ለBBC

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅ/ቤት አደራጅ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እርቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅ/ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን ለመታረቅ መንገድ መጀመራቸውን ለBBC ገልፀዋል።

ይህንንም እየመሩ ያሉት የኦሮሚያ ቤተ ክርስቲያን እንዲደራጅ ሲኖዶሱን ሲጠይቁ የነበሩ የቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች እንዲሁም ለእምነቱ ቀናኢ የሆኑ በመንግሥትም ሆነ በግል ስራ የተሰማሩ ኃላፊዎች የተውጣጣ ኮሚቴ ፈቃደኝነታቸውን እንደጠየቁና መስማማታቸውንም ቀሲስ በላይ ተናግረዋል።

የሚስማሙባቸውን ዝርዝር ነጥቦች አስቀምጠው ለቋሚ ሲኖዶሱ ያስገቡ ሲሆን፤ ቋሚ ሲኖዶሱም ተቀብሎ ለምልዓተ ጉባኤው አቅርቦታል።

ምልዓተ ጉባኤው ይወስናል የሚል እምነት አላቸው። ዝርዝር ሁኔታውን ምልዓተ ጉባኤው ከወሰነ በኋላ እንደሚገልፁም አስረድተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-10-24-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የ33ኛ ዙር መሠረታዊ የኮማንዶ እንዲሁም የ10ኛ ዙር መሰረታዊ የልዩ ሀይልና ፀረ ሽብር ሰልጣኞችን እያስመረቀ ነው። በአሁን ሰዓት የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ለኦፕሬሽናል ጀነራል ብርሀኑ ጁላ እና ሌሎች እንግዶች የኮማንዶ ፣ የልዩ ሀይልና ፀረ ሽብር ሰልጣኞች የሚያሳዩትን ወታደራዊ ትርዒት በመከታተል…
#FDREDefenseForce

የጦር ሀይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ፣ ሠራዊቱ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶችን ለመመከት የሚያስችል የትጥቅ ፣ የብቃትና የሞራል አንድነት አለው ሲሉ በዛሬው የምርቃት ስነስርዓት ላይ ተናገሩ።

ጀነራል ብርሀኑ ፤ ፀረ ሰላም ሀይሎች የሚፈፅሙትን እኩይ ድርጊት በሠራዊቱ ፣ በፀጥታ ተቋሞች በህዝቡና በብሔራዊ አቅማችን እንመክታለን ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#አስቸኳይ

የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት በላከልን ደብዳቤ ከጥቅምት 13 እስከ ጥቅምት 20 ደረስ በወልቂጤ ከተማ ሁሉም ክ/ከተማዎች ፣ ቀበሌዎችና አጎራባች ቀበሌዎች የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባት /Yellow fever Vaccine/ እድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 60 ዓመት የሆናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጾልናል።

ስለሆነም ከላይ እድሜያቸው የተጠቀሰ የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ በአስቸኳይ ክትባቱን እንዲያገኙ መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBOT
ጉራፈርዳ ቲክቫህ አባላት ፦

በጉራፈርዳው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ህክምና የሰጡ ሃኪሞች ተጎጂዎችን አነጋግረው በላኩልን የቪድዮ መልዕክት ፥ አንዲት ታዳጊ በጥቃቱ እናቷ ፣ አያቷ ፣ የአክስቷ ባል እና አባት እንደተገደሉ ገልፃለች።

ከዚህ በተጨማሪም በቲክቫህ የመልዕክት መቀበያ ሳጥን መልዕክት ያስቀመጡ አባላት ፦

1ኛ. ጥቃቱ ማንነት መሰረት ያደረገ እንደሆነ፤

2ኛ. የመንግስት ኃለፊዎች በየሚዲያው እየወጡ ጥቃት አድራሾቹ ማንነታቸው ያልታወቀ በሚል የሚሰጡ መረጃ ፍፁም ተገቢ እንዳልሆነ፤

3ኛ. ጥቃት አድራሾቹ የተደራጁ እንደሆኑ ጥቃቱ በመሳሪያ፣ በገጀራ፣ በጦር መፈፀሙን ገልፀዋል።

መንግስት አሁንም የህዝብን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱ እንዲወጣ፣ የጥፋት ኃይሎች ላይም የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድና በመንግስት ኃላፊዎች በኩል በሚዲያዎቹ የሚሰጡ መረጃዎች ህዝቡን ያከበሩ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አማባሳደር ማይክ ሬይነርን በጽህፈት ቤታቸው አስጠርተው አነጋግረዋቸዋል፡፡

አቶ ገዱ አምባሳደሩን ያስጠሯቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የህዳሴ ግድብን አስመልክተው በሰጡት አወዛጋቢ አስተያየት ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ ነው፡፡

አቶ ገዱ ፥ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ በግድቡና በሶስትዮሽ ድርድሩ ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የተሳሳተ ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ግድቡ የናይል ወንዝን የውሃ ፍሰት ያቆመዋል ነው ያሉት፤ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም ሲሉ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ጦርነት ማወጅ በስልጣን ላይ ካለ አንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሚጠበቅ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል የቆየውን ወዳጅነት እና ስትራቴጂያዊ አጋርነትም አይመጥንም ብለዋል አቶ ገዱ ፤ የመንግስታት ግንኙነትን በሚገዛው ዓለም አቀፍ ሕግም ተቀባይነት የለውም ነው ያሉት። (EBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የሶማለኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ሊከፍት መሆኑን ገለፀ !

በዛሬው ዕለት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በህክምና ዶክትሬት እና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 347 ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።

በምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኝ፣ የጅግጅጋ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር በሽር አብዱላሒ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተው ነበር።

በዛሬው የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፊሬው ተገኝ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሶማለኛ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምር ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በበኩላቸው የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የጀመረው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመው ህዝቦችን ከማስተሳሰር አንፃር ሌሎችም ሊከተሉት ይገባል ብለዋል። (SRTV)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,454
• በበሽታው የተያዙ - 629
• ህይወታቸው ያለፈ - 19
• ከበሽታው ያገገሙ - 724

በአጠቃላይ በሀገራችን 92,858 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,419 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 46,842 ከበሽታው አገግመዋል።

306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

"...አሁን የመጣው የአንበጣ መንጋ ታይቶም አይታወቅም" - አቶ ክንደያ ግደይ (የትግራይ አርሶ አደር)

የበረሀ አንበጣ መንጋ በትግራይ ክልል ካሉት 7 ዞኖች 4ቱን ወሯል።

በ29ኝ ወረዳዎች 79ኝ ቀበሌዎች የሚገኝ ሰብልና የተፈጥሮ ሀብት በአንበጣው ጉዳት ደርሶበታል።

አስተያየታቸው ለDW ከሰጡ ገበሬዎች መካከል የ70 ዓመት እድሜ ያላቸው አቶ ክንደያ ግደይ ለDW ተከታዩን ብለዋል ፦

"ልጅ እያለሁ መኮኒ ፣ ማይጨው እና ወጅራት በአጠቃላይ የሸፈነ ትልቅ የአንበጣ መንጋ መጥቶ አስታውሳለሁ ፤ ይህ 60 ዓመታት ያለፈው ታሪክ ነው ፤ እንደኔ እንደኔ አሁን የመጣው ግን ታይቶም አይታወቅም።"

ከትግራይ ክልል ግብርና ቢሮ በተገኘው መረጃ በክልሉ ካለ አጠቃላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት 77,000 ሄክታር የሚሆነው በአንበጣ መንጋ ተወሯል።

በተለይም በዚህ ሁለት ሳምንት የአንበጣ መንጋው በስፋት እየተስፋፋ ይገኛል።

አምና በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ትግራይ የገባው የአንበጣ መንጋ ብዛት 18 ሲሆን ዘንድሮ ግን ከመስከረም ወዲህ ባሉ ቀናት ብቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አንበጦች የያዘ 21 መንጋ ወደ ክልሉ ገብቷል።

አንበጣው እስካሁን በትግራይ ውስጥ አጠቃላይ በቁጥር ተለይቶ ያልታወቀ ጉዳት በግብርና ምርት ላይ ማድረሱን ከ #DW ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካፍ በማረጋገጫው ኢትዮጵያን ክለቦችን አካቷል !

ካፍ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ቡድኖችን ይፋ አድርጓል ።

በዚህም መሰረት መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ እንዲሁም ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንደሚሳተፉ ካፍ ይፋ ባደረገው የማረጋገጫ መረጃ ላይ ታይቷል ።

Via @tikvahethsport
#AmboUniversity

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ ብሎ በሰየመውና በግቢው ዋና በር ፊት ለፊት የተሰራው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ዛሬ ተመርቋል፡፡ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ያሰራው ይህ ሀውልት ሲመረቅ ቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

(OBN)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ቅጥር ለመፈፀም 2 ቋንቋዎችን እንደግዴታ ያስቀመጠበት ህግ አልወጣም ሲል ገልጿል።

ቅጥርን በተመለከተ ሁለት ቋንቋዎችን መቻል እንደግዴታ ተቀምጧል እየተባለ የተናፈሱ መረጃዎች ከእውነት የራቁ ናቸው ተብሏል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ የተናገሩት ፦

"የአ/አ ከተማ አስተዳደር በቻርተር የሚተዳደር እና ቻርተሩ በ1995 በአዋጅ የቻርተር አዋጅ 361 ተብሎ በግልጽ እንደተቀመጠው "አማርኛ" የከተማ አስተዳደሩ የስራ ቋንቋ ሆኖ እንደሚያገለግል በግልጽ ተቀምጧል።

ይህ ቻርተር የወጣው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለሆነ አዋጁ ባልተሻሻለበት ሁኔታ ስራ ለመቀጠር ሁለት ቋንቋ እንደግዴታ ነው እየተባለ የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው።

ከተማ አስተዳደሩ ስራ ለመቀጠር እንደግዴታ ያወጣው ህግ ባለመኖሩ ምናልባት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ 2 ቋንቋ መቻልን እንደግዴታ የሚያስቀምጡ ማስታወቂያዎችን ካሉ ትክክል ባለመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ እርምጃ ይወስዳል።"

Via FBC
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ የሃይቅ - ቢስቲማ - ጭፍራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አስጀምረዋል።

በይፋ የግንባታ ስራው የጀመረው መንገድ 74 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል።

ግንባታውን የሚያከናውኑት ፓወርኮን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርና አሰር ኮንስትራክሽን በጋራ ናቸው።

የግንባታው ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት እንደሆነ ታውቋል።

የመንገድ ግንባታው በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia