#FDREDefenseForce
በአሁኑ ሰዓት የ10ኛ ዙር ልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ዕጩ ተመራቂዎች የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን በሀዋሳ እያሳዩ ይገኛሉ።
የሠራዊቱ አባላት በልዩ ዘመቻዎች ኃይል የሰለጠኑ ሲሆኑ በነገው ዕለት የሚመረቁ ናቸው።
እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ትርዒት ፣ የሽብር ጥቃትን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም በከተሞች እና ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች ተልዕኮን እንዴት መወጣት እንደሚያስችል ያሳየ ነው።
ምንጭ፦ መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ሀዋሳ አዲስ ምክትል ከንቲባ ተሾመላት !
ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው በዛሬው ዕለት ተሹመዋል።
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤው እየተካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ በአቶ አብርሀም ማርሻሎ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቅራቢነት ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬን በም/ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሹመት ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
በም/ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የሆነበሩት አቶ ጥራቱ በየነ ከ2 ቀን በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው የሚታወቅ ነው።
Via Hawassa City Communication

#Hawassa
በም/ከንቲባ ማዕረግ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የከተማውን ቁልፍ ተረክበዋል።
PHOTO : SIDAMA MEDIA NETWORK

TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE የ6ኛው አገራዊ ምርጫ ኦፕሬሽን አስመልክቶ ፓለቲካ ፓርቲዎች ዛሬ ለምርጫው የተዘጋጁ ቁሳቁሶችን በኤግዚቢሽን ማዕከል እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡ በዛሬው ዕለት የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ርክክብ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ቀደም የሚዲያ አካላት ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ PHOTO : TIKVAH FAMILY (A.A) @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች ማዕከል ቢሮ ቁልፍ ርክክብ ዛሬ አካሂዷል፡፡
ማዕከሉ በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ ፓርቲዎች የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እንዲያከናውኑበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
ቢሮው የኮምፒውተር ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም መጠነኛ መሰብሰቢያ ቦታን ያካተተ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲሁም የኢትዮጵያ የሴት ፓለቲከኞች የጋራ ምክር ቤት በማዕከሉ ውስጥ ቢሮ ተሰጥቷቸው ከቦርዱ ቁልፍ ተረክበዋል፡፡
ማዕከሉ የራሱ ሰራተኞች ይኖሩታል፤ የሚተዳደረው በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይሆናል ተብሏል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች አገልግሎቱን ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር በመነጋገርና ቀጠሮ በማሲያዝ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
PHOTO : TIKVAH FAMILY

#UPDATE በ2 ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አልፏል ! በጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት…
#UPDATE
- የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ፣
- የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንዳሻው ጣሰው፣
- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣
- የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው፣
- የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬዓለም ሽባባው እና ሌሎችም የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ተገኝተው ከህብረተሰቡ ጋር እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችና ሌሎች የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል። (ENA)

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 510 ኩንታል ስኳር ለሸማቾች ሊከፋፈል ነው !
(የሸዋ ሮቢት ከተማ ኮሚኒኬሽን)
ከሰሞኑን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሲዘዋወር በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለ 510 ኩንታል ስኳር ከዛሬ ጀምሮ ለሸማች ማህበረሰቡ እንደሚከፋፈል የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳዳር ገልጿል።
እንደ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገለጻ ከሆነ ከቀናት በፊት 2 የጭነት ተሸከርካሪዎች ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ ሳይኖራቸው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በህገ ወጥ መንገድ 510 ኩንታል ስኳር ይዘው ሲንቀሳቀሱ በከተማው የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የከተማው የህገወጥ ተከላካይ ግብረ ኃይል ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው መረጃ መሰረት ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ግብር ኃይሉ ስኳሩ ለሸማች ማህበረሰብ ተሸጦ ገንዘቡ በአደራ መልክ እንዲቀመጥ ውሳኔ አሳልፏል።
ስኳሩ ለሸማችና ለቸርቻሪዎች የተሰራጨ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ማህበረሰቡ ኩፖኑን በመያዝ በተመደበት ሱቅ እና ሸማች ማህበር በመሄድ ስኳሩን መወሰድ የሚችል መሆኑን ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Nigeria
የናይጄሪያ ዜጎች የሀገሪቱ "ፖሊስ" የሚፈፅመውን የጭካኔ ድርጊት በመቃወም አደባባይ መውጣት ከጀመሩ 2 ሳምንት ሆኗቸዋል።
የሀገሪቱ መንግሥት በተቃዋሚ ሰልፈኞችና በፖሊስ መካከል ግጭቶች እየተባባሱ በመምጣታቸው ሊሰጥ የነበረውን የ2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እንዲቋረጥ ማድረጉን BBC ዘግቧል።
የሁለተኛ ደረጃ ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች የሚለዩበት ነበር።
ትላንት የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሃሪ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ተቃውሟቸውን በማቆም ከመንግሥት ጎን በመሆን "መፍትሄ በመፈለግ" እንዲተባበሩ መጠየቃቸውን BBC አስነብቧል።
* ይበልጥ ናይጄሪያ አሁን ስላለችበት ሁኔታ ለመረዳት ከላይ ያለውን አጭር የNow This ቪድዮን (5.1 MB) መመልከት ትችላላችሁ።

#ATTENTION📣
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከፍተኛ የሆነ የአፍላ ቶክሲን /Aflatoxine/ የተገኘባቸውን 14 የለውዝ ቅቤ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ብሏል።
ለውዞቹን የሚያመርቱ ተቋማት ላይ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ አምራቾቹን ለማግኘት አለመቻሉንም ተገልጿል።
የሚመለከተቻው የቁጥጥር አካላት ምርቶቹ ከገበያ ላይ በመሰብሰብ እንዲያስወግዱ ባለስልጣኑ ማሳስበቡን ኢዜአ ዘግቧል።
ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የታገዱት የለውዝ ቅቤዎች ፡-
- ምስራቅ የለውዝ ቅቤ
- ሳራ የለውዝ ቅቤ
- ዳና የለውዝ ቅቤ
- ሰገን የኦቾሎኒ ቅቤ
- አርሂቡ የለውዝ ቅቤ
- ረጃት የለውዝ ቅቤ
- ኢትዮ የለውዝ ቂቤ
- ጽዮን የለውዝ ቅቤ
- ማሀሩን የኦቾሎኒ ቅቤ
- ላቪሊ የሎዝ ቂቤ
- እናት የሎዝ ቅቤ
- ኤ.ኤፍ የሎዝ ቅቤ
- መና የኦቾሎኒ ቅቤ
- ሂር የለውዝ ቅቤ ናቸው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያቱ ምንድነው ?
ከጣና በለስ ወደ ባህርዳር በሚሄደው የ400 ኪሎ ቮልት የኃይል መስመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ዛሬ በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጣል፡፡
በመስመሩ ላይ የተከሰተው የቮልቴጅ መዋዠቅ በአጠቃላይ የአገሪቱ የኃይል አቅርቦት ላይ ችግር እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
በዚህም ምክንያት በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5 ሰአት ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ተከስቷል።
ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ በተሰሩ ስራዎች ከጊቤ 3 ኃይል ማመንጫ በስተቀር አብዛኛዎቹን የኃይል መመንጫዎች ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ማገናኘት ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ አብዛኛው አካባቢ እንዲሁም ባህር ዳር እና አካባቢዋ ኃይል ማግኘት የጀመሩ ሲሆን ሁሉንም የሀገሪቱን አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
ጥቅምት 13 ቀን 2013

የ2012 ትምህርት ዘመን "የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና" የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30/2013 ዓ/ም በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የፈተናውን የምዝገባ ሂደት ለማካሄድ በተዘጋጀው ሶፈትዌር 'Enrollment Kit' ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የአይሲቲ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በክልል ከተሞች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። (MoE)

#DrLiaTadesse
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,538
• በቫይረሱ የተያዙ - 536
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 858
በአጠቃላይ በሀገራችን 92,229 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,400 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 46,118 ከበሽታው አገግመዋል።
315 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

#PASSPORT
www.ethiopianpassportservices.gov.et
ኦንላይ (online) ላይ ፖስፖርት ለማደስና ለአዲስ ፖስፖርት አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ አገልግሎትን ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቁሙ👇
www.ethiopianpassportservices.gov.et
ደንበኞች በፕላትፎርሙ ላይ የሚገጥማቸው ጉዳይ ዘውትር በ [email protected] ላይ እና በስራ ሰዓት በ8133 ነጻ የስልክ መስማር ላይ INVEA ማሳወቅ ይችላሉ።
ተጨማሪ ፦
- ፓስፖርት ለማሳደስ ማሟላት ስላለባችሁ መስፈርት ይህ ተጭናችሁ ተመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/53852
- ፓስፖርት ለማግኘት ማሟላት ስላለባችሁ መስፈርት ይህን ተጭናችሁ ተመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/53851
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
www.ethiopianpassportservices.gov.et
ኦንላይ (online) ላይ ፖስፖርት ለማደስና ለአዲስ ፖስፖርት አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ አገልግሎትን ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቁሙ👇
www.ethiopianpassportservices.gov.et
ደንበኞች በፕላትፎርሙ ላይ የሚገጥማቸው ጉዳይ ዘውትር በ [email protected] ላይ እና በስራ ሰዓት በ8133 ነጻ የስልክ መስማር ላይ INVEA ማሳወቅ ይችላሉ።
ተጨማሪ ፦
- ፓስፖርት ለማሳደስ ማሟላት ስላለባችሁ መስፈርት ይህ ተጭናችሁ ተመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/53852
- ፓስፖርት ለማግኘት ማሟላት ስላለባችሁ መስፈርት ይህን ተጭናችሁ ተመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/53851
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Donald Trump ?
"...ግድቡን ያፈነዱታል" - ዶናልድ ትራምፕ
ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእስራኤል እና ሱዳን መሪዎች ጋር አዲስ በተደረሰው የሰላም ስምምነት ዙርያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የህዳሴ ግድብን ውሃ ሙሌት ተችተዋል።
ፕሬዜዳንት ትራምፕ ከተገሩት ፦
- ግድቡ ወደ ግብጽ የሚፈሰውን ውሃ ያቆማል።
- ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ያዘጋጀነውን ስምምነት ጥሳለች ፤ ይህ ጥሩ አይደለም ያንን ማድረግ አይችሉም ፤ ያንን ማድረግ ይችላሉ ብዬ አላስብም።
- በዚህ ምክንያት ብዙ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ቆርጠናል በውሉ ካልተስማሙ በስተቀር ያንን ገንዘብ ደግመው አያዩትም።
- ከሱዳን ጋርም በዚህ ጉዳይ ተነጋግሪያለው።
- ኢትዮጵያ ወደስምምነቱ መመለስ አለባት፤ ግብጽ ብስጭት ቢገባት ልትኮነን አይገባም፤ ያን ግድብ ልታፈነዳው ትችላለች።
- አሁን ያለው ሁኔታ አደገኛ ነው ፤ ግብፆች በዚህ ሁኔታ ሊኖሩ አይችሉም ፤ ግድቡን ያፈነዱታል።
(Tikvah Family, Elias Mesert, Alzool Media N.)

ዶናልድ ትራምፕ ?
ፕሬዜዳንት ትራምፕ: "ስምምነት እንዲደርሱ አድርጌ ነበር። ኢትዮጵያ ግን ስምምነቱን ጥላ ወጣች። ያን ግን ማድረግ አልነበረባቸውም። ትልቅ ስህተት ነው የሰሩት።
በዚህም ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል። ለስምምነቱ ተገዢ እስካልሆኑ ድረስ ያን ገንዘብ መቼም አያገኙትም።
ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም። እንዴት እየሆነ ነው? ምን ያውቃሉ?"
የሱዳን ጠ/ሚር አብዱል ሃምዶክ : "ሁሉንም ሊጠቅም የሚችል ሁሉን አካታች ስምምነት በቅርቡ እንደርሳለን ብለን እናስባለን"
ፕሬዜዳንት ትራምፕ: "እንደዛ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ስምምቱን አፍርሰዋል። ይህን ደግሞ ከፍተኛ አጣብቂኝ ፈጥሯል። ግብጽ በዚህ ሁኔታ መኖር አትችልም። ልታፈነዳው [ግብጽ] ትችላለች፤ ደግሜ እናገራለሁ ግብጽ ግድቡን ታፈነዳዋለች" (BBC)

ዶናልድ ትራምፕ ? ፕሬዜዳንት ትራምፕ: "ስምምነት እንዲደርሱ አድርጌ ነበር። ኢትዮጵያ ግን ስምምነቱን ጥላ ወጣች። ያን ግን ማድረግ አልነበረባቸውም። ትልቅ ስህተት ነው የሰሩት። በዚህም ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል። ለስምምነቱ ተገዢ እስካልሆኑ ድረስ ያን ገንዘብ መቼም አያገኙትም። ውሃ ወደ ናይል ወንዝ እንዳይፈስ የሚያቆም ግድብ ገነቡ፤ ግብጽ በዚህ ብትበሳጭ መኮነን የለባትም። እንዴት እየሆነ…
ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ !
ጥቅምት 14 2013
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ በፍጣሪዋ ታምና በሕዝቧ አንድነትና ጽናት የቆመች ሀገር ናት። ጥቂት ሰጥተው ብዙ ሊያዟት በሚሞክሩ ተማምና አታውቅም።
ሕይወታቸውን ሰጥተው ሊታዘዟት በተዘጋጁ ልጆቿ እንጂ። ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ነው። የገነቧት ደግሞ ልጆቿ ናቸው።
እነዚህ ልጆቿ በከፈሉት መሥዋዕትነት ዓለምን ጉድ ያሰኙ ታሪኮችን ሠርታለች። እነዚህ አስደናቂ ታሪኮችን ስትሠራ አብረዋት ታሪክ የሠሩ ወዳጆች ነበሯት። የከዷት ወዳጆችም ነበሩ። ይህ ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። ነገር ግን የዓለም ታሪክ ያረጋገጣቸው ሁለት ሐቆች አሉ።
ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም የሚለው ቀዳሚው ነው። ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለአንድ ዓላማ ከቆሙ ድል ማድረጋቸው አይቀርም የሚለው ደግሞ ሁለተኛው።
የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ግድብ ነው። ኢትዮጵያውያን፣ አሰቡት፤ ኢትዮጵያውያን ጀመሩት፤ ኢትዮጵያውያን ገነቡት፤ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ይጨርሱታል። አይቀሬ ነው።
ተጨማሪ ይህ ተጭነው ያንብቡ👇
https://telegra.ph/GERD-10-24