TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ካምፓኒ ከሁለት (2) ወር በኋሏ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ እንደሚጀምር ኢ/ር ታከለ ኡማ አሳውቀዋል።

ኢንጂነር ታከለ ዛሬ በሲዳማ ክልል ተገኝተው የሲዳማ ጎልድ ማይኒንግ ካምፓኒን ጎብኝተዋል።

ካምፓኒው በአካባቢው ተወላጆች እንዲሁም ነዋሪዎች ባለቤትነት የሚመራ እና የሚበረታታ መሆኑንም ኢ/ር ታከለ በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።

አካባቢው ከፍተኛ የመንገድና የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት በመሆኑ ችግሩን መፍታት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ጋር መነጋገራቸውንም አሳውቀዋል።

ችግሮችን ለመፍታት ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ለሚ ኩራ" ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል ፤ በጉባኤው "ለሚ ኩራ" ተብሎ የሚጠራ ተጨማሪ ክፍለ ከተማ በምክር ቤቱ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል። አዲሱ ክፍለ ከተማ 'ለሚ ኩራ' በምክር ቤቱ ከጸደቀ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ክፍለ ከተሞች ወደ 11 የሚያድጉ ይሆናል ፤ በከተማዋ አሁን ላይ 10 ክፍለ ከተሞች እና 116 ወረዳዎች…
"ለሚ ኩራ" የአዲስ አበባ 11ኛ ክፍለከተማ በመሆን በምክር ቤቱ ጸድቋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲሱ ክፍለ ከተማ ተጨማሪ ይዞታ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ከነበረው ከቦሌ እና ከየካ ክፍለ ከተሞች በመክፈል የተዋቀረ ነው ብለዋል፡፡

አዲሱ አደረጃጀት የነዋሪዎችን ብዛት በማመጣጠን ፣ አዳጊ የሆነውን የአገልግሎት ተደራሽነት እና የማስተዳደር አቅምን በማጎልበት ለከተማው ነዋሪዎች ሚዛናዊ በሆነ ርቀት እና ተደራሽ በሆነ መልኩ የአገልግሎት አቅርቦት በማመቻቸት ነዋሪው ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚረዳ ነው ተብሏል።

Via Addis Ababa Press Secretary
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሹመት !

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ በም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶችን አፅድቋል።

በዚህም መሠረት ፡-

1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ
2ኛ. ዶ/ር መስከረም ፈለቀ - ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
3ኛ. ኢ/ር አያልነሽ ሀ/ማርያም - ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
4ኛ. ዶ/ር መስከረም ምትኩ - የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
5ኛ. ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ - መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
6ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ - ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
7ኛ. አቶ ተፈራ ሞላ - ሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ
8ኛ. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል፡፡ (አዲስ ቴቪ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሰሜን ዕዝ የ20ኛ ቃሉ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን በአዲግራት ከተማ አካባቢ የአንበጣ መንጋ የመከላከል ዘመቻና የሰብል መሰብሰብ ስራ አከናውነዋል።

የክ/ጦሩ ዋና አዛዥ ብ/ጀ ኑሩ ሙዘይን እንደተናገሩት ፣ መንጋው የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የሁልጊዜ ርብርብ እንዲሚያደርጉና ለማንኛውም ችግር ከህዝብ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PASSPORT የኢሚግሬሽን ፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባጋጠመው የኔትወርክ ችግር ምክንያት የኦንላይን (online) አገልግሎቱን ዛሬ ጠዋት መጀመር እንዳልተቻለ ለ 'ኢትዮጵያ ቼክ' ገልጿል። አገልግሎቱ ከሰአት አካባቢ ይሰራል ተብሎ እንደሚጠበቅና ፣ ስራው ሲጠናቀቅ አገልግሎቱ ማግኘት የሚቻልበት ሊንክ ይፋ እንደሚደረግ ኤጀንሲው አሳውቋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተሬሳ ፥ ዛሬ ይጀምራል የተባለው ኦንላይን አገልግሎት ባጋጠመ የኔትወርክ ችግር ምክንያት ሳይጀምር መቅረቱን #ለetv ተናግረዋል።

ችግሩ ተቀርፎ በነገው ዕለት (ጥቅምት 11) አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል።

ከአየር መንገድ ፣ ከኢትዮ ቴሌኮምና ከንግድ ባንክ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ደሳለኝ ኦንላይን (online) ስርዓቱ ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ለቴሌቪዥን ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ባልደረባ የነበሩት ሲኒየር ፋርማሲስት አልማዝ ምትኩ ትላንት ለሊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የፋርማሲስት አልማዝ የአስክሬን ሽኝት በሆስፒታሉ ሰራተኞችና የስራ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

ፋርማሲስት አልማዝ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ነው በኮሮና ቫይረስ በሽታ ሳቢያ ታመው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት። (SPHMMC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ ከዶ/ር ሊያ ታደሰ ፦

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ባልደረባ ሲኒየር ፋርማሲስት አልማዝ ምትኩ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ዶርክተር ሊያ ለፋርማሲስት አልማዝ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናት ተመኝተዋል።

ፋርማሲስት አልማዝ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮቪድ-19 ተይዘው ትላንት ለሊት ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,602
• በቫይረሱ የተያዙ - 630
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 489

በአጠቃላይ በሀገራችን 90,490 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,371 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 43,638 ከበሽታው አገግመዋል።

301 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሹመት ! የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ በም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶችን አፅድቋል። በዚህም መሠረት ፡- 1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ 2ኛ. ዶ/ር መስከረም ፈለቀ - ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ 3ኛ. ኢ/ር አያልነሽ ሀ/ማርያም - ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ 4ኛ. ዶ/ር መስከረም…
ሹመት !

የአዲስ አበባ ከተማ 11ኛው ክፍለ ከተማ "ለሚ ኩራ" ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ መሀመድ ሆነው ተሹመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለሌሎች ክፍለ ከተሞች የዋና ስራ አስፈጻሚ አመራሮች ሹመት ተሰጥቷል።

በዚህም ፦

- ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ - ልደታ ክ/ከተማ
- ወ/ሮ ነጻነት ዳባ - ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ
- አቶ ሙቀት ታረቀኝ - ኮልፌ ክ/ከተማ
- አቶ አባዌ ዮሀንስ - ጉለሌ ክ/ከተማ
- ወ/ሮ ፈቲያ መሀመድ - አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
- ዶ/ር እመቤት ጌታነህ - አራዳ ክ/ከተማ
- አቶ አስፋው ተክሌ - የካ ክፍለ ከተማ ሆነው ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ባሉበት የቀጠሉ የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

- አቶ ጀማል ረዲ - ቂርቆስ ክ/ከተማ
- አቶ መኮንን አምባዬ - ቦሌ ክ/ከተማ
- አቶ ይታያል ደጀኔ - አዲስ ከተማ ክ/ከተማ

Via Addis Ababa Prosperity Party
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጉራ ፈርዳ ወረዳ 12 ሰዎች ተገደሉ !

ጥቅምት 8/2013 ምሽት 3:00 ገደማ ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ "ማንነታቸው ያልታወቀ" የተደራጁ ወንጀለኞች ባደረሱት ጉዳት የ12 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ እና በ5 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ አሳውቀዋል።

ኮሚሽነር ነብዩ፥ የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ተጨማሪ የፀጥታ አካላት ወደ አካባቢው መግባቱን ገልጸው ጉዳት የደረሰባቸው ወደ ህክምና መወሰዳቸውን ለደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ሀይሎች መረጃዎች በመስጠት ትብብር በማድረግ ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የሚሰረውን ስራ እንዲያግዝ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቲችንግ ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ አባል ሀኪም 12 ሰዎች መገደላቸው መረጃ እንዳለው በላከልን የፅሁፍ መልዕክት አረጋግጧል።

ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላቸው ከአንድ ቀን በኋላ የሄዱም እንዳሉ አሳውቋል ፤ ስለሁኔታው/ስለጥቃቱ መነሻ አለኝ ባለው መረጃ አንድ ሰው ተገድሎ መንገድ ላይ ተጥሎ መገኘቱ ነው ብሏል።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን 'ማንነታቸው ያልታወቁ የተደራጁ ወንጀለኞች ባደረሱት ጉዳት የ12 ሰዎች ህይወት ጠፋ" ብሎ ከመግለፅ በዘለለ መነሻው/ምክንያቱ ምን እንደሆነ የሚገልፅ መረጃ አልሰጠም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትጵያ አየር መንገድ ከቻይና ባለስልጣናት የአዲስ አበባ - ሻንጋይ በረራው ለጊዜው መታገዱን የሚገልፅ ማስታወቂያ እንደደረሰው ዛሬ ምሽት አስታውቋል፡፡

ይህ የሆነው በአየር መንገዱ ከአዲስ አበባ - ሻንጋይ ከተጓዙ መንገደኞች መካከል ጥቂቶቹ ኮሮና ቫየረስ ስለተገኘባቸው መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡

አየር መንገዱ ኮሮና እንደሌለባቸው የሚገልፅ ማስረጃ ያላቸውን መንገደኞች ብቻ አሳፍሮ የነበረ ቢሆንም በመዳረሻ አየር ማረፊያ በተረገ ምርመራ ከመንገደኞቹ መካከል ጥቂቶቹ ኮሮና ሊገኝባቸው ችሏል።

የተቋረጠውን በረራ ለማስቀጠል ከሚመለከታቸው የቻይና ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው መንገደኞች አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው ‘ሲልክ ሮድ ጄነራል ሆስፒታል’ ከተሰኘው የቻይናውያን የኮቪድ-19 ምርመራ ማዕከል ከቫይረሱ ነፃ ስለመሆናቸው ማስረጃ ካቀረቡት መካከል መሆናቸውን አየር መንገዱ ገልጿል፡፡

ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ ‘ሲልክሮድ ጄነራል ሆስፒታል’ የሚመጡ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማስረጃዎችን እንደማይቀበል ገልፆ ደንበኞቹም በተጠቀሰው ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንዳያደርጉ መክሯል፡፡ (ebc)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሹመት ! የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ በም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶችን አፅድቋል። በዚህም መሠረት ፡- 1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ 2ኛ. ዶ/ር መስከረም ፈለቀ - ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ 3ኛ. ኢ/ር አያልነሽ ሀ/ማርያም - ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ 4ኛ. ዶ/ር መስከረም…
#AtoTiratuBeyene

ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአ/አ ከተማ ስራ አስከያጅ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙትን አቶ ጥራቱ በየነን አመስግኗል።

አቶ ጥራቱ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ በታማኝነት ፣ በቅንነት እና በትጋት ሀዋሳ ከተማን ሲያስተዳድሩ መቆየታቸው ምንጊዜም የሚታወስ ነው ተብሏል።

በተጨማሪ በከተማዋ ሰላም እንዲሰፍን ፣ ልማት እንዲረጋገጥና መልካም አስተዳደር እውን እንዲሆን ሌት ተቀን በመስራት እውነተኛ የህዝብ ልጅ መሆናቸውን በቆይታቸው አስመስክረዋል ሲል ነው ከተማ አስተዳደሩ ያሳወቀው።

"በአሁን ሰዓት በተሰጣቸው የኃላፊነት ቦታ በታማኝነት እና በትጋት የማገልገልና አዳዲስ ሀሳብ የማፍለቅ እምቅ አቅማቸውን ተጠቅመው በተሻለ ተነሳሽነት እና በቁርጠኝነት ሀገራቸውን እንደሚያገለግሉ በሙሉ ልብ በማመን መልካም የስራ ጊዜ እንዲገጥማቸው ይመኛል" ብሏል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION📣

በአግባቡ የአውሮፕላን ጸረተባይ ኬሚካል ርጭት ባለመደረጉ የተነሳ የአምበጣ መንጋው ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አሳወቀ።

ከአምበጣ መንጋው በርካታ ከመሆን ጋር ተያይዞ የአውሮፕላን ርጭቱ በተደራጀ አግባብ ይሰራል ተብሎ ሲጠበቅ ነገር ግን አምበጣውን ለመቆጣጠር ሳይሆን ለመነካካት በሚመስል ርጭት በማድረግ ይባሱን አምበጣው ከከተማው ቁጥጥር ውጭ በመሆን በሰብሎች ላይ የከፋ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

ከተማው ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ምንም ማድረግ እየቻለ እንዳልሆነ አስታውቋል።

ቢያንስ እንኳን የተወሰነ ሰብል እንዲተርፍ የሚመለከተው የክልል እና የፌደራል አካል የአውሮፕላን ርጭት ስምሪት ስርአቱን በማስተካከል ርጭት ሊያደርግ እንደሚገባ የከተማ አስተዳደሩ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል የአንበጣ መንጋ ለመከላከል የሚውል ድጋፍ በሀገር ውስጥ እና ከውጭ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

የትግራይ ልማት ማህበር "gofundme" በመክፈት በኢንተርኔት እያደረገ በሚገኘው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እስካሁን 30,000,000 ብር የሚጠጋ ገንዘብ እገዛ አድርገዋል።

ይህ ለአንበጣ መከላከል የሚውለው የገንዘብ ድጋፍ በ13 ቀናት ውስጥ በ5,142 ሰዎች የተደረገ ነው።

በሌላ በኩል ፦

'ድጋፍ ለትግራይ ገበሬ' በሚል ውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኤርትራውያን በከፈቱት የእገዛ ማድረጊያ 'gofundme' በጥቂት ቀናት ውስጥ ከ1,800,000 ብር በላይ መሰብሰቸው ተሰምቷል።

የገንዘብ ድጋፉ የተደረገው ባለፉት 7 ቀናት በ579 ሰዎች ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia