TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ ከትናንት ማታ አራት ሰዓት ተኩል ጀምሮ በሰባት (7) ቀበሌዎች ውስጥ ጎርፍ ተከስቷል።

ጎርፉ ከባድ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በውሃ የተከበቡ ነዋሪዎችን በማውጣት በሌላ አካባቢ ለማስፈር  በሄሊኮፕተር የታገዘ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአሚበራ ወረዳ የአርብቶ አደርና ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በአሚባራ ወረዳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሁንም ጎርፉ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም አካል እንዲረባረብ / አቅም ተጠናክሮ ነዋሪዎችን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ገንዘቡ የታገደው በፕሬዘዳንት ትራምፕ ትዕዛዝና አመራር ነው" - Associated Press

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልትሰጥ የነበረውን 130 ሚልዮን ዶላር ገደማ በቅርቡ ያገደችው በፕሬዝደንት ትራምፕ ትእዛዝ እና አመራር መሆኑን ስቴት ዲፓርትመንት ያሉ ምንጮቼ ነግረውኛል ሲል AP ዘግቧል።

ይህም ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ስታደርግ የነበረው ውይይት ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ ኢትዮጵያን ተጠያቂ በማድረግ እንደሆነ ተጠቅሷል። በተጨማሪም "ስምምነት ላይ ሳይደረስ የግድቡን ሙሌት በቅርቡ በማከናወኗ" ነው ተብሏል።

ሙሉ የAP ዘገባ : https://apnews.com/7ce2f23741eed4886a09e39c0064b894

Via Elias Meseret (Associated Press)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሺህ አለፈ!

ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የነሃሴ 27/2012 ሪፖርት እንዳገኘነው መረጃ ከ800 የላብራቶሪ ምርመራ 134 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 25 ሰዎች አገግመዋል።

በቫይረሱ ከተያዙት 134 ሰዎች መካከል 44 ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበሩ ፣ 2 በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ፣ 88 ደግሞ ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።

እስከሁን ድረስ በትግራይ ክልል 48,446 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 4,112 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ ከነዚህ መካከል የ21 ሰዎች ህይወት አልፏል ፣ 2,537 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኬንያው አየር መንገድ ለጤና ባለሙያዎች የአውሮፕላን ቲኬት ቅናሽ ሊያደርግ ነው!

በአለም ዙሪያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ወደ የትኛውም አቅጣጫ በኬንያ አየር መንገድ ሲጓዙ ግማሽ ክፍያውን አየር መንገዱ እንደሚሸፍን አስታወቀ፡፡

በመጪው መስከረም ወር የሚጀምረው ቅናሹ ቢዝነስ ክላስና ኢኮኖሚ ከላሰን እንደሚጨመርም ተጠቅሷል፡፡

እንደ አየር መንገዱ ገለፃ በአውሮፕላን ቲኬት 50 በመቶ ቅናሽ ለማድረግ የወሰነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ፊትለፊት በመጋፈጥ ህዝቦቻቸው ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ነው ብሏል፡፡

ወረርሽኝን ተከትሎ መንግስታት አየር መንገዶችን በረራ እንዲያቆሙ ከማስገደዳቸው አስቀድሞ፤ ብሔራዊው አየር መንገዱ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ለመቋቋም በመስራት ላይ እንደሆም ነው የተገለፀው።

የኬንያ የፓርላማ አባላት ያለፈው ሐምሌ ወር አየር መንገዱን ከኪሳራ ለመታደግ ድጋፍ ማድረግ እንደሚስፈልግ ድምጽ መስጠታቸውን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

አቃቤ ህግ ፦

- እጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ የሚልና ለውጡን ተቃርኖ “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ርእስ የተሰጠው የፖለቲካ ይዘት ያለውና ህገ መንግስቱን ለመናድ አልሞ የተዘጋጀ ሰነዶችን ተከትሎ ክስ ለመመስረት እየመረመርኩ ነው ብሏል።

አቶ ልደቱ አያሌው ፦

- የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ በመንግስት ደረጃ አስገብቼው ተቀባይነት የለውም ተብዬ ያስቀመጥኩት ነው፤ ተጠያቂነት ቢኖረው ኖሮ መንግስት ተቀባይነት የለውም ብሎ ዝም አይለኝም ነበረ ብለዋል።

- “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚለውም ቢሆን በረቂቅ ላይ ያለ ያልታተመ ነው፤ ልከሰስ የምችለው ሰነዱን አሳትሜ አሰራጭቼ ቢሆን ነበረ ፤ በዚህች ሀገር ላይ ሳንሱር የለም ስለዚህ ሀሳቤን ነው እየገለፅኩ ያለሁት፤ ፍርድ ቤቱ ይህንን ሊረዳልኝ ይገባል ብለዋል።

- ውጭ ሀገር ሄጄ የታከምኩት ሀብታም ነጋዴ ሆኜ ሳይሆን ፤ ህክምናው እዚህ ስለሌለ ነው፤ ይህንን ፍርድ ቤቱ ከግምት ያስገባልኝ” ሲሉ ጠይቀዋል።

የአቶ ልደቱ አያለው ጠበቃ ፦

- ለደንበኛቸው ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል።

የሁለቱን ክርክር የተከታተለው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Via Tarik Adugna (FBC)

@tikvahethiopiaBOT
የአርቲስት ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ ታስረው የነበሩት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ከሁለት ወር እስር በኋላ ተፈቱ!

ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት አራት ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት የኢትዮጵያውያን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ (ኢሃን) ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ከእስር መለቀቃቸውን ፓርቲው ለአል ዓይን አስታውቋል።

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል ምዕራፍ ይመር እንደገለጹት ኢንጅነር ይልቃል ዛሬ በዋስትና ከእስር ተለቀዋል፡፡

ከሁለት (2) ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩት ፖለቲከኛው ዛሬ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለምዶ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ ከሚጠራው ማረሚያ ቤት በዋስ ተለቀዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ሀይሌ ሪዞርት አዳማ' ዛሬ ተመረቀ!

የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ድርጅት በ500 ሚሊየን ብር በአዳማ ከተማ ያስገነባው 7ኛው የሀይሌ ሪዞርት ዛሬ መመረቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በሪዞርቱ የምርቃት ስነስርዓት ላይ ሻለቃ ሀይሌን ጨምሮ የሪዞርቱ የስራ ሃላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

ዛሬ የተመረቀው ሪዞርት ሰፋፊና ምቹ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በአዳማ የተገነባው ሰባተኛው ሪዞርት በ 500 ሚሊየን ወይም በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ መሆኑን ሀይሌ በመግለጫው ገልጿል።

ከዚያም ባለፈ 300 ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠሩን ተናግሯል።

ሪዞርቱ በግንባታ ሆነ በአገልግሎቱ ከሌሎች ሪዞርቶች ለየት ባለ መልኩ መቅረቡን የተናገረው ሻለቃ ሀይሌ ÷ ከባለ 4 እና 5 ኮኮብ ደረጃን የሚያሟሉ አገልግሎቶችን እንደሚሠጥ ገልጿል።

ግንባታውን ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን የፈጀ ሲሆን በአዲሱ ዓመት እየተገነቡ ያሉ ሶስት (3) ሪዞርቶችእንደሚጠናቀቁ ከኤፍቢሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የእስራኤል ጦር አባል ለተቃውሞ የወጡት ፍልስጤማዊ አዛውንት አንገትን በጉልበቱ አፍኖ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ከወጣ በኋላ ቁጣ መቀስቀሱን BBC አስነብቧል።

ካሂሪ ሃኑን የተባሉት ዝነኛው ተቃዋሚ አዛውንት እጆቻቸው ወደኋላ ታስሮ ፤ ፊታቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ የእስራኤል ወታደር አንገታቸው ላይ በጉልበቱ ቆሞ የሚያሳየው ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቷል።

ምስሉ የተቀረጸው ትናንት ፍልስጤማውያን በዌስት ባንክ ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት ነው።

ወታደሩ በጉልበቱ የካሂሪ ሃኑን አንገት ላይ ለ50 ሰከንዶች ያክል ተጭኖ ቆይቷል። ይህም በፍልስጤማውያን ዘንድ ሌላ ታቃውሞን ቀስቅሷል።

የእስራኤል ጦር የጦር አባላቱ የነበረውን ሁኔታ ለመቆጣጠር ተመጣጣኝ እርምጃ ነው የወሰዱት ብሏል።

ተንቀሳቃሽ ምስሉም የግጭቱን ሙሉ ምስል አያሳይም፤ በጦር አባላቱ ላይ ሲደርስ የነበረውን ጥቃትም አያስመለክትም ብሏል።

ጦሩ ጨምሮ ወደ 200 ሰዎች ግጭት በተስተዋለበት የተቃውሞ ስልፍ ላይ መሳተፋቸውን እና በጦሩ አባላት ላይ ድንጋይ መወርወሩን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት! አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል። አቃቤ ህግ ፦ - እጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ የሚልና ለውጡን ተቃርኖ “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ርእስ የተሰጠው የፖለቲካ ይዘት ያለውና ህገ መንግስቱን ለመናድ አልሞ የተዘጋጀ ሰነዶችን ተከትሎ ክስ ለመመስረት እየመረመርኩ ነው ብሏል። አቶ ልደቱ አያሌው…
#UPDATE

የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በዋለው ችሎት አቃቤ ህግና ፖሊስ በ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ቢጠይቅም አቃቤ ህግና ፖሊስ ማስረጃውን እንዳላቀረቡ የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለነገ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ በጠዋቱ ቀጠሮው ማስረጃውን አይቶ ከሰዓት 8 ላይ ውሳኔ እስጥበታለሁ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2.7 ሚሊዮን ሕዝብ ድምፅ ይሰጥበታል የተባለው የትግራይ ክልል ምርጫ ስድስት (6) ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ዛሬ በክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ የመጨረሻ ቀጥታ የቴሌቪዥን ክርክር መከናወኑን ዶቼ ቨለ (DW) ዘግቧል።

የዛሬው የምርጫ ክርክር ትኩረት የነበረው በጤናና ትምህርት ዘርፍ አማራጭ ፖሊሲዎች ዙሪያ እንደነበር ተገልጿል።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፣ ባይቶና ፣ ዓሲምባ ዴሞክራስያዊ ፓርቲና የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በቀጥታ የቴሌቪዥን ክርክሩ መሳተፋቸውን ከዶቼ ቨለ (DW) የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ (COVID- 19) የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት ለተመርማሪዎች በ8335 በእጅ ስልካቸው የጽሁፍ መልዕክት እንዲደርሳቸው የሚያስችል ስራ መጀመሩ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

EPHI ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የላቡራቶሪ ናሙና የተወሰደላቸው ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ የናሙና ምርመራ ውጤት ከተረጋገጠ በኋላ ከሶስት (3) ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በ8335 በጠቀም ተመርማሪዎች ውጤቱን በSMS እንዲደርሳቸው እየተደረገ ይገኛል።

ውጤቱ በትክክል መድረሱን የሚያረጋግጥ የአሰራር ዘዴ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እየተሰራ ሲሆን ፣ ተመርማሪዎች ግን ትክክለኛ የስልክ ቁጥራቸውን ማስመዘገብ እንዳለባቸው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ የተመረቀው ኃይሌ ሪዞርት አዳማ ፦

- 500 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል

- ግንባታውን ለማጠናቀቅ 2 ዓመታትን ወስዷል

- ለ300 ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል

- የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን አካቷል

- ባለ 4 እና 5 ኮኮብ ደረጃን የሚያሟሉ አገልግሎቶችን ይሰጣል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 28/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 600 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 32 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,021 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 142 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 35 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 14 ከአዳማ ከተማ
- 12 ከምስራቅ ሸዋ
- 9 ከነቀምቴ ከተማ
- 6 ከሞጆ ከተማ ይገኙበታል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 449 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው (የባምቢስ ወረዳ ነዋሪ) በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 7,176 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 12 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 11 ከሰ/ወሎ ዞን
- 7 ከደሴ ከተማ
- 7 ከጎንደር ከተማ ይገኙበታል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 594 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot
በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ20 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 20,778 የላብራቶሪ ምርመራ 804 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 380 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 55,213 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 856 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 20,283 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia