የኦነግ እና ኦፌኮ ቅሬታ!
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በአንዳንድ ዞኖች ጽ/ቤታቸዉ በመዘጋቱ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና አደጋ ላይ መዉደቁን ማስታወቃቸውን ዶቼ ቨለ/DW ዘግቧል።
የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የፓርቲ አባላት እስራት ከአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በፊትም ነበረ ሲሉ ተናግረዋል።
በተለይ በወረዳ የሚገኙ ጽ/ቤቶቻችን ተዘግተዉብናል ያሉት ፕ/ር መረራ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የታሰሩ አባላቶቻችን ጉዳይ ይጣራልን ብለን ደብዳቤ አስገብተናል ብለዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ቃለ አቀባይ የሆኑት አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው የኦነግ ዘጠኝ የሥራ አስፈፃሚ አባልት በመታሰራቸዉ ሳቢያ ፓርቲዉ በሙሉ አቅሙ እየተንቀሳቀሰ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የOMN ሰራተኞች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ!
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ እና ሌሎች 2 ሰራተኞች በሶስት ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ መስጠቱን 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ጠበቃቸውን አቶ ከዲር ቡሎን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳ እና ሌሎች 2 ሰራተኞች በሶስት ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ መስጠቱን 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ጠበቃቸውን አቶ ከዲር ቡሎን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደ/አፍሪካ 24ሺህ የጤና ባለሞያዎች በኮሮና ተይዘዋል!
የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኮቪድ-19 ወደ ሀገሪቱ ከገባ ጊዜ አንስቶ በትንሹ 24 ሺ የሚሆኑ የጤና ባለሙያወች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አሳውቋል።
በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ከ24 ሺህ በላይ የጤና ባለሞያዎች አንድ መቶ ሰማንያ አንዱ (181) መሞታቸው ተገልጿል።
በኮሮና የተያዙት የጤና ባለሙያዎች በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ከተያዙ ሰዎች ውስጥ 5 በመቶ አንደሚሸፍኑ ከአል አይን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደቡብ አፍሪካ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኮቪድ-19 ወደ ሀገሪቱ ከገባ ጊዜ አንስቶ በትንሹ 24 ሺ የሚሆኑ የጤና ባለሙያወች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አሳውቋል።
በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ከ24 ሺህ በላይ የጤና ባለሞያዎች አንድ መቶ ሰማንያ አንዱ (181) መሞታቸው ተገልጿል።
በኮሮና የተያዙት የጤና ባለሙያዎች በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ከተያዙ ሰዎች ውስጥ 5 በመቶ አንደሚሸፍኑ ከአል አይን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በአቶ ጆምባ ሁሴን መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ስድስት (6) ተከሳሾች በ4 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ማዘዙን ጠበቃቸውን አቶ ከዲር ቡሎ ዋቢ በማድረግ 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ዘግቧል።
ፖሊስ ዛሬ በነበረው ችሎት ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት ቢጠይቅም ችሎቱ ውድቅ ማድረጉን አቶ ከዲር ተናግረዋል።
ዛሬ በፍርድ ቤት በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ጆምባ ሁሴን ፣ ኢብሳ ጅማ ፣ መሐመድ ጅማ ፣ ኢብራሂም አብዱልጀሊል፣ ኪያር መሐመድ እና አለማየሁ ገለታ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው።

#UPDATE
በሊባኖስ (ቤሩት) የደረሰው ፍንዳታ 300,000 ሰዎችን ቤት አልባ ማድረጉንና እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት ማድረሱን የቤሩት ገዢ ማርዋን አቡውድ ተናግረዋል።
በሌላ መረጃ ደግሞ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በነገው ዕለት ወደ ሊባኖስ (ቤሩት) ይጓዛሉ ፤ ማክሮን በቤሩት ቆይታቸው ከሀገሪቱ የፖለቲካ አመራሮችና መሪዎች ጋር ይገናኛሉ።

TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ጉማ ሰቀታ በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ! ዛሬ (ሃምሌ 28/2012 ዓ/ም) ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ጉማ ሰቀታ በ7,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ጉማ ሰቀታ ከእስር ተፈቱ!
ትላንት ሃምሌ 28/2012 ዓ/ም ፍርድ ቤት በ7,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ የወሰነላቸው አቶ ጉማ ሰቀታ ዛሬ ከሰዓት ከእስር ተፈተዋል - 📸#ShiferawLegesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትላንት ሃምሌ 28/2012 ዓ/ም ፍርድ ቤት በ7,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ የወሰነላቸው አቶ ጉማ ሰቀታ ዛሬ ከሰዓት ከእስር ተፈተዋል - 📸#ShiferawLegesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፍርድ ቤቱ ሂሩት ክፍሌ ከእስር እንዲፈቱ አዘዘ! የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። የፖሊስን የይግባኝ አቤቱታ የሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ትላንት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ሂሩት የዋስትና መብታቸው ተከብሮ…
ሂሩት ክፍሌ ከእስር ተፈቱ!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ከእስር መለቀቃቸውን ፓርቲው አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ከእስር መለቀቃቸውን ፓርቲው አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ20 ሺህ አለፉ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,319 የላብራቶሪ ምርመራ 459 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 358 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 20,336 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 356 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 8,598 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,319 የላብራቶሪ ምርመራ 459 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 358 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 20,336 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 356 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 8,598 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦
- በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 55 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ከነዚህ መካከል 18 ሰዎች ከለገጣፎ፣ 14 ሰዎች ከምስራቅ ሸዋ ይገኙበታል።
- በትግራይ ባለፉት 24 ሰዓት 37 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 18ቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 12 ሰዎች ንክኪ ያላቸውና 7 ሰዎች የውጭ የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 115 ምርመራ ተደርጎ 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል ፤ አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 292 ደርሰዋል።
- በደቡብ ክልል ከተደረገው 578 የላብራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጣል ፤ ከነዚህ መካከል 13 ሰዎች ከወላይታ ዞን ናቸው።
- በሱማሌ ክልል ከተደረገው 42 የላብራቶሪ ምርመራ 19 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ፤ 10 ከጅግጅጋ እንዲሁም 9 ከጎዴ ናቸው።
- በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሃያ (20) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከነዚህ መካከል 9 ሰዎች ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ናቸው።
#CARD #TIKVAH

በቤሩት ኢትዮጵያውያን ጉዳት ደርሶባቸዋል!
በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ኃላፊ የሆኑት ተመስገን ኡመር በትላንቱ ፍንዳታ በቆንስላውና በኢትዮጵያ ማህበረሰብ በኩል ጉዳት እንደደረሰባቸው የተረጋገጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር አስር (10) መሆኑን ገልፀዋል።
ከእነዚህ ውስጥ 2 መካከለኛ ጉዳት 7 ደግሞ ቀላል ጉዳት ሲደርስባቸው 1 ግለሰብ መሞቱ ቢነገራቸውም ከሚሰራበት ተቋምም ሆነ ከሊባኖስ መንግሥት በኩል የተጣራ መረጃ አልደረሰኝም ብለዋል።
አቶ ተመስገን መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸው 2 የኢትዮጵያ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ የሚታከሙበት ሆስፒታል ድረስ በመሄድ መመልከታቸውን ገልፀው ሁለቱም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል ፤ 7 ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ህክምና አግኝተው ወዲያው ወደ መኖሪያቸው መሄዳቸውን አስረድተዋል።
በሊባኖስ (ቤሩት) የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ፅ/ቤት ወደ ቆንስላውም ሆነ ወደ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ያልመጡ ሌሎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሊኖሩ እንደሚችሉ ለቢቢሲ ገልጿል።

የሊባኖስ ጤና ሚኒስትር ሃማድ ሃሳን በትላንቱ ከባድ ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 135 መደረሱንና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከ5,000 ማለፉን አሳውቀዋል።
የጤና ሚኒስትሩ ሃማድ ሃሳን አሁንም በርካታ የጠፉ ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን ገልፀዋል።
ከቬኦኤ (VOA) ባገኘነው መረጃ ደግሞ የቤሩት ነዋሪዎች ከፍርስራሾች ውስጥ የጠፉባቸውን ቤተሰቦቻቸውን እየፈለጉ መሆናቸውን ይገልፃል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች የአደጋው ሰለባ የሆኑትና ፍንዳታውን ተከትሎ የገቡበት የማይታወቁ ሰዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ናቸው።

የአሥራት ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ታሰሩ!
የአሥራት ቴሌቪዥን [ASRAT MEDIA] ጋዜጠኞች የሆኑት በላይ ማናዬና ሙሉጌታ አንበርብር ዛሬ ሐምሌ 29/2012 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ የፌደራል ፖሊስ አባላት 'ትፈለጋላችሁ' በሚል እንደወሰዳቸውና እስካሁን የታሰሩበት ቦታ እንደማይታወቅ የቴሌቪዥን ጣቢያው በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ በተረኛ ችሎት በልደታ አዳራሽ አቶ ሃምዛ ቦረናን ጨምሮ የአቶ ጃዋር ስምንት (8) ጠባቂዎች ቀርበው ነበር።
ፖሊስ በተጨማሪ ጊዜ የሰራው ስራ ለችሎቱ ይፋ አድርጓል፤ የምርመራ መዝገበ እንዲዘጋለትና ጠቅላይ አቃቤ ህግ በከፈተው የቅድመ ምርመራ መዝገብ እንዲቀጥል ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች በኩል የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ሃሙስ ሃምሌ 30/2012 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በዛሬው ዕለት በነበረው የአራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት በሚዲያ ላይ አቤቱታ ባልቀረበበት ሁኔታ ማንኛውም የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሚዲያዎች የምርመራ ውጤቱና የክርክር ሂደቱን እንዳይዘግቡ/ለህዝብ እንዳይቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
Via Tarik Adugna

Attention Hawassa!
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠው አርባ አንድ (41) ሰዎች መካከል ሰላሳ ስድስቱ (36) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በከተማይቱ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከዕለት ወደዕለት እጅግ በአደገኛ ፍጥነት እየጨመረ በመሆኑ 'ከፍተኛ ጥንቃቄ' አድርጉ።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሰላም ዋጋ ስንት ደረሰ?
ሠላም ዋጋው ምን ያህል ነው ? እንገምት እንበል። ማልዶ ወጥቶ ፣ አምሽቶ ገብቶ ያለአንዳች እንከን ተግባርን ከውኖ መመለስ በምን ያህል ይለካል?
በምን ይመዘናል ? ልጅ ወልዶ ፣ አሳድጎ ፣ አስተምሮ እና ለወግ ማዕረግ አብቅቶ ተመስገን ብሎ አምላክን ለማመስገን መታደል ዋጋው ስንት ይሆን? የሰላም ዋጋ ስንት ደረሰ ?
መረዋ ኳየር : https://youtu.be/T40xBK66FsM
ከላይ በሊንኩ የምታገኙት (ቪድዮ የምትመለከቱት) በ'መረዋ ኳየር' የተዘጋጀው የክቡር ዶ/ር አርቲስት መሀሙድ አህመድ 'ሰላም' የተሰኘው ስራ ነው።
የሙዚቃ ቡድኑ ለቲክቫህ ኢትዮ. በላከው መልዕክት ስራው ብዙ ተደክሞ እንደተሰራበት ፣ ለሰዎችም ጥሩ ትምህርት ሊሰጥ በሚችል መልኩ የተዘጋጀ እንደሆነ አሳውቆናል።
📹25 MB (WiFi ተጠቀሙ)

ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደረሰን መረጃ ከትላንት በስቲያ በቤሩት በደረሰው ከባድ ፍንዳት የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉንና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጾልናል።

#MoHEthiopia
ከነገ ነሐሴ 1/2012 ዓ/ም እስከ ነሃሴ 17/2012 ዓ/ም ‹‹ማንም›› የተሰኘ የኮቪድ-19 ምርመራ ዘመቻ ይካሄዳል።
የዚህን ዘመቻ ምርመራ ውጤት ተከትሎ በኢኮኖሚው በኩል አገልግሎት የሚሰጡ የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፎች ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሳሕርላ አብዱላሂ ለኢዜአ ተናግረዋል።
የበሽታው ስርጭት በማያስፋፋ መልኩ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ ብለው ባለሙያዎች በሚሰጡት መመሪያ መሰረት ወደ ስራ የሚገቡት የአገልግሎት ዘርፎች እንደሚሊዩ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

#ATTENTION
ባለፉት 5 ወራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ #ወጣቶች ቁጥር በሶስት እጥፍ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት አሳውቋል። የዚህ ምክንያት አካላዊ ርቀትን መጠበቁ ላይ ችላ መባሉ እንደሆነ አስረድቷል።
ካለፈው የካቲት ወር መጨረሻ እስከ ሃምሌ ወር አጋማሽ በነበረው ጊዜ ከተመዘገቡት 6 ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ ተጋላጮች ውስጥ 15 በመቶው ከ15-20 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው ተብሏል። ድርጅቱ እንደንፅፅር ከዚያ በፊት የነበረው 4.5 በመቶ ብቻ እንደነበር አንስቷል።
ወጣቶች ከሁሉም ሲነፃፀር አፍና አፍንጫ ማሸፈኛ ማድረግ ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ችላ የሚሉ መሆኑ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ።
ስራ መሄድ ያለባቸው እነሱ፣ ወደ ባህር ዳርቻ ለማዝናናት የሚሄዱት እነሱ፣ ወደ መጠጥ ቤትም የሚሄዱት፣ ሱቅ የሚያዘወትሩትም እነሱ ናቸው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል።
ወጣቶች በብዛት በኮሮና ቫይረስ እየተያዙ ካሉባቸው ሀገራት መካከል አሜሪካ ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ጀርመን እና ጃፓን ይጠቀሳሉ።
የጃፓን ቶኪዮ ባለስልጣናት በከተማዋ የሚገኙ ወጣቶች በሚያዘወትሯቸው የመዝናኝ መንደሮች ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማካሄድ እቅድ ማውጣታቸውን ከቪኦኤ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#PASSPORT
ኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከመስከረም ወር ጀምሮ ፓስፖርት በኦንላይን መስጠት እንደሚጀምር ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል።
ኤጀንሲው ከኢትዮጲያ አየር መንገድ አይቲ ክፍል ጋር ውል በመፈፀም ፤ የፓስፖርት ፣ የቪዛ ማራዘም ፣ የትውልድ መታወቂያ እና የመኖሩያ ፍቃድ እድሳት ኦንላይን እንዲከናወን እየተሰራ ነው ብሏል።
ፖስፖርትም ሆነ የኤጀንሲውን ሌሎች አገልግሎት ፈላጊዎች ቀድመው በኦንላይን ሲስተም ቀጠሮ አስይዘው ወደ ኤጀንሲው በቀጠሯቸው በመሄድ አገልግሎት የሚያገኙበት ስርዓትም እየተዘረጋ እንደሆነና አገልግሎቱ ከ1 ወር ከ15 ቀን በኃላ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጿል።
ኦንላይን አገልግሎትን ማግኘት ለማይችሉ ሰዎች በተቋሙ በሚኖረው መጨናነቅ ሳቢያ ለኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጡ አማራጭ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ለመክፈት ግንባታ መጀመሩን ኤጀንሲው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል።
ኤጀንሲው አዲስ አበባ ላይ ሁለት ቅርንጫፎች እንዲሁም በክልል ከተሞች ኦሳዕና ፣ ጋምቤላ ፣ አሶሳ ላይ የቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ ተጀምሯል፤ በሌሎች ክልሎች ላይም ይህ ሂደት ይቀጥላል ብሏል።

በኮሮና የተያዘው ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ኢቲቃ!
(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት የተዘጋጀ)
በአፋን ኦሮሞ የፖለቲካ ዘፈኖቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ በኮሮና ቫይረስ መያዙን ካወቀ/ከተረጋገጠ ሳምንታት መቆጠሩን ለቢቢሲ ተናግሯል።
ድምጻዊው "በሽታው እንዲህ አይነት ቦታ ያዘኝ ብዬ መናገር አልችልም" ካለ በኋላ የሚጠረጥረው ስፍራ እንዳለ ግን ገልጿል።
ድምጻዊው ሃጫሉ ሁንዴሳ በተገደለበት እለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርግ ከጓደኞቹ ጋር በሆስፒታል ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ሲሯሯጡ እንደነበር ያስታውሳል።
አምቦ በነበረው የሃጫሉ ቀብር ስነስርዓት ላይም አብዛኛው ሰው በሐዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አልተጠቀመም ነበር።
ትልቁ ጥርጣሬው ይህ እንደሆነ የሚናገረው ድምጻዊ ሂቲቃ ፣ ከአምቦ ከተመለሰ በኋላ የሕመም ስሜት ተሰምቶት ወደ ግል ጤና ጣብያ ቢሄድም ሌላ በሽታ ነው ተብሎ መርፌና ኪኒን ታዘዘለት።
ይሁን እንጂ በራሱ ላይ የተመለከታቸው የሕመም ስሜቶች የኮሮና ቫይረስ ነበሩ ይላል ድምጻዊ ሂቲቃ። 'ሰውነቴ በጣም ይደክማል ፤ ደረቅ ሳል ሳያቋርጥ ለሶስት ሰዓት ያስለኝ ነበር' በማለት ይናገራል።
ከዚያ በኋላ ለጤና ቢሮ በመደወል ምርመራ እንደተደረገለት እና በኮሮና መያዙ ሲረጋገጥም ወደ ሚሊየም አዳራሽ የኮሮና የህክምና ማዕከል ተወስዶ ሕክምናና እንክብካቤ ሲደረግለት መቆየቱን ገልጿል።
ድምፃዊ ኢቲቃ ተፈሪ ከቢቢሲ ጋር ያደረገውን ሙሉ ቆይታ በ :https://telegra.ph/BBC-08-06 ገብታችሁ ማንባብ ትችላላችሁ።