TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጀነራል ሰዓረ መኮንን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ
ኢታማዡር ሹም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Fiker Assefa
ዛሬ የተሰሙ የሀገር ውስጥ ስፓርት ዜናዎች

1⃣የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ አሰልጣኝ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

2⃣የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከነበረችበት በአምስት ደረጃዎች ዝቅ ብላለች 151 ላይ ተቀምጣለች።

3⃣ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት መሀበር ለኢ.እ.ፌ ጅማ ላይ በድጋፊውና በክለቡ ላይ ለደረሰው በደል የቅሬታ ደብዳቤ ላከ።

4⃣ዲሲፕሊን ኮሚቴ የጊዮርጊስና መከላከያ

🔴ተጨዋቾችን ቀጣ🔴

መከላከያ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ እርስ በርስ የተደባደቡት የመከላከያው አዲስና የጊዮርጊሱ አዳነ እንዲሁም በጨዋታ እንቅስቃሴ ላይ
የተጋጣሚን ተጨዋች ላይ ጉዳት ያደረሰው የመከላከያው ዳዊት እስጢፋኖስ እያንዳንዳቸው ላይ
የ 4 ጨዋታ እገዳ ተላልፎባቸዋል።

ከቀሪ 5 ጨዋታ አራቱ ላይ ሁለቱን ወሳኝ ተጨዋቾቹን የሚያጣው መከላከያ ይግባኝ መጠየቁ
ታውቋል። ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴም በቀናት ውስጥ ይግባኙን ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል።

5⃣በጋና አስተናጋጅነት በ2018 ለሚካሄደው የቶታል አፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻው የማጣርያ ዙር ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአልጄርያ ጋር ያደረገውን የመጀመርያ ጨዋታ 3-1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ከመረጃዋቹ ጋር ፍቅር አሰፋ ነበርኩ ለስፓርት መረጃ Join
Forwarded from Fiker Assefa
የሀገር ውስጥ የስፓርት ዜናዎች።

1⃣የመቐለ እና ፋሲል ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ይደረጋል።
2⃣የመከላከያ እና የጅማ ጫወታ ትራዝሟል ምክንያቱም ከቀናት በፊት ጅማ ከተማ ከጊዮርጊስ ጋር ባደረገበት ጫወታ ላይ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ነው ተብሏል።
3⃣ጥረት ኮርፖሬት የሴቶች ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ዲቪዝዮን ቻምፒዮንነቱን አረጋገጠ

💫ከውጪ የዝውውር ዜናዎች💫

1⃣ደሊ አሊ በክረምቱ ቶተንሃምን ይለቃል የሚባለውን ወሬ አስተባብሎታል።የ22 አመቱ አማካይ በማንቸስተር ዩናይትድ፣ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና ይፈለጋል።(ኢኤስ መጋዚን)
2⃣ማንቸስተር ሲቲዎች ለዮርጊንሆ አማራጭ የሳውዝሃምፕተኑን ማሪዮ ሌሚና እና የሪያል ማድሪዱን ማቲዮ ኮቫቺች ይዘዋቸዋል።(ስካይ ስፖርት)
3⃣ የሙሃመድ ሳላህ ወኪል የሊቨርፑሉ አጥቂ ወደ ባርሴሎና የመዛወር ፍላጎት አለው የሚባለውን ወሬ አስተባብሎታል።(ስካይ ስፖርት)
4⃣ ማንቸስተር ዩናይትዶች ከአሜሪካው ድርጅት ኮህለር ጋር የእጅጌ ስፖንሰርሺፕ ስምምነት አደረጉ።ስምምነቱ በአመት 10 ሚሊዮን ፓውንድ ያስገኝላቸዋል።(ጎል)

ከመረጃዎቹ ጋር ፍቅር አሰፋ ነበርኩ ለስፓርት መረጃዎች የኔስፓርት Join Join ያድርጉ
ሹመት! ጀነራል አደም መሐመድ የኢትዮጵያ ደኅነት መሥሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ። የቀድሞው ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሥልጣናቸው
ተነስተዋል። አባዱላ ገመዳ እና ግርማ ብሩ በጡረታ ተሰናብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንጋፋዎቹ የኢህአዴግ ሰዎች በጡረታ እንዲያርፉ ተደርገዋል! የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጄኔራል አደም መሐመድን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾሙ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጄኔራል አደም ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የተሾሙ ሲሆን፥ ያላቸው የስራ ልምድ ከግምት ውስጥ መግባቱ ተመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በጥር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ወታደራዊ ማዕረጎችን በሰጡበት ወቅት ለሌ/ጀኔራል አደም መሐመድ የጀኔራልነት ማዕረግ መስጠታቸው ይታወሳል።

ከዚህ በፊትም በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ማዕረግ መሾማቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል በመንግስት የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሁለት የሥራ ኃላፊዎች በጡረታ ተሰናብተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፥ ለረጅም ዓመት በተለያየ የመንግስት ኃላፊነት ያገለገሉ ሁለት የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ ተሰናብተዋል።

በዚሁ መሰረት በጡረታ የተገለሉት በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔነታቸውን ያስተላለፉት አቶ አባዱላ ገመዳ እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ግርማ ብሩ ናቸው።

አቶ አባዱላ ገመዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል። ቀደም ብሎም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው መስራታቸው ይታወሳል።

በአሜሪካ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ ደግሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታና በሽግግሩ ወቅት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

መንግሥት በቅርቡ ለረጅም ዓመት ያገለገሉ አምስት የስራ ኃላፊዎች በጡረታ ማሰናበቱ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት በጡረታ እንዲያርፉ የተደረጉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ ዶክተር ካሱ ኢላላ ከፖለሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ አቶ በለጠ ታፈረ ከተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም፣ ዕቅድና ፖሊሲ ዝግጅት ፕሮጀክት፣ አቶ ታደሰ ኃይሌ ከንግድና ኢንዱስትሪ የፖሊሲ ዕቅድ አፈጻጸምና ክትትል፣ እና አቶ መኮንን ማንያዘዋል ከፖሊሲ ምርምር ማዕከል መሆናቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️የጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ውሎ በፎቶ...

ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊያቀርቡ የወጡት ወጣቶች በእስለቃሽ ጭስ እና በፌደራል ዱላ ድብደብ እንዲበተኑ መደረጉን የአይን እማኞች ተናግረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ገብቷል! በህክምና ስህተት የአልጋ ቁራኛ የሆነው መሀመድ አብዲላዚዝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ተሰማ።

መሀመድ አብዲላዚዝና እናቱ ወ/ሮ ሃሊማ ሙዘሚልንም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቦሌ አለምዓቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡

በቀጣይም መሀመድ አብዲላዚዝ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍል በመግባት አስፈላጊው የህክምና
እንክብካቤ ይደረግለታል፡፡

መሀመድ አብዲላዚዝና እናቱ ወ/ሮ ሃሊማ ሙዘሚልንም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስርያ ቤት እንኳን ወደ አገራችሁ ኢትዮጵያ በሰላም ገባችሁ ብሏቸዋል፡፡

መሀመድ አብዲላዚዝ ለረጅም አመታት በሳዑዲ አረቢያ በህክምና ስህተት ያልጋ ቁራኛ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️ታዳጊው ወደ ሀገሩ ገብቷል።

ከፌደራል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዘንድሮ የ1ዐኛ እና የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በተሰካ ሁኔታ መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በፈተና ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳዩት ርብርብ የሚበረታታ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እጣው ነገ ይወጣል! የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ ከአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ጽህፈት ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በነገው እለት ከ2 ሺህ 500 በላይ ቤቶች እጣ እንደሚወጣባቸው አስታውቋል።

የ1997 ዓ.ም ነባር ተመዝጋቢ ሆነው ምዝገባቸውን በ2005 ዓ.ም ያደሱና መቆጠብ ያለባቸውን ያህል ገንዘብ የቆጠቡ ተመዝጋቢዎችም በዕጣው ይካተታሉ ተብሏል።

የእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በተገኙበት የሚካሄድ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia