TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዩጋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ዶ/ር አብይ የዩጋንዳን ጉብኝታቸውን እንደጨረሱ ወደ ግብፅ ያቀናሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትማሩ እና ትላንት ምሽት ላይብረሪ ውስጥ የነበራችሁ ተማሪዎች የተፈጠረውን በአይናችሁ ያያችሁትን እንድትነግሩን በትህትና እንጠይቃለን።

@tsegabwolde
ባህርዳር! ተማሪዎችን ቅር ያሰኘው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ማስታወቂያ። ተማሪዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይዘው ዛሬ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ነግረውኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ማርስ! ናሳ በማርስ ላይ ህይወት እንደነበር የሚያመላክት መረጃ እንዳገኘ ተሰማ።

የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ማዕከለ 3 ሚሊዮን ዓመት ካስቆጠረ የማርስ አለት በተገኘ መረጃ መሰረት ህይወት ያላቸው አካላት በፕላኔቱ ይኖሩ እንደነበር አመላካች መረጃ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ መረጃው ለተጨማሪ ምርምራ የሚጋብዝ እንጂ ማረጋገጫ የሚሰጥ አይደለም ተብሏል፡፡

ግኝቱ በማርስ ያለው የከባቢ አየር እና ተፈጥሮአዊ ነገር ህይወት ማኖር የሚያስችል እንደሆነ አመላካች ሆኗል፡፡

በማርስ ላይ የሚገኘው ሮቦት መሰል ተሽከረካሪ በላከው መረጃ መሰረት ማርስ ከቢሊዮን ዓመት በፊት ህይወት ማቆየት የሚችል የውሃ ክፍለ ነበራት፡፡

በመሆኑም አዲስ ጥልቅ ምርምር በማድረግ በማርስ ህይወት ያላቸው አካላት እንዲኖሩ ለማድርግ እየሰራ መሆኑን ናሳ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ ኦክስጅን እና ናይትሮጅን በስፍራው መገኘታቸው እስካሁን አልተረጋገጠም፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ እና ናሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የልማት ድርጅቶቹ! በቅርቡ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብት እንዲሸጡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኪሚቴ የወሰነው ውሳኔ በበቂ ጥናትና ዝግጅት ላይ ተመስርቶ የተካሄደ መሆኑን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡

አቶ አህሙድ ሽዴ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ውሳኔው የሀገሪቱን ፈጣን ልማት ለማስቀጠል ታልሞ የተደረገ
ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሁን ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ! የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።

.ጥያቄዎቻቸው ምን እንደሆኑ መረጃው ሲላክልኝ አቀርባለሁ።

ምንጭ፦ ኢ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዲላ ዩኒቨርሲቱ! ከ100 በላይ ተማሪዎች መረጃ እንዳደረሱኘ ከሆነ በትላንትናው ዕለት ምሽት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ቤተ መፅሀፍ ውስጥ ቦንብ ፈንድቷል። ጉዳዩንም ፖሊስ ይዞታል ብለውኛል።

.ጥቂት ተማሪዎች ደግሞ ነገርየው ባንብ ሳይሆን ትራንስፎርመር ነው ብለውኛል። ነገር ግን የትራስፎርመር ፍንዳታ ቢሆን ማብራቱ ዘግይቶ አይጠፋም ነበር ሲሉ ገልፀዋል ፍንዳታው የቦንብ እንደሆነ የገለፁት ተማሪዎች።

.በድንገቱ 5 የሚደርሱ ተማሪዎች ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ተሰምቷል። ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም ሆስፒታል ገብተዋል። ይህንንም ተማሪዎቹን ሊጠይቁ ሆስፒታል ከሄዱት ተማሪዎች ማወቅ ችያለሁ።

*አዲስ ነገር ካለ አሳውቃለሁ ዩኒቨርሲቲው የሚያወጣው መረጃም ካለ እከታተላለሁ።

የተጎዱ ወንድሞቻችንን ፈጣሪ ይማርልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር! የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች ዛሬ ጥዋት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ኢንስቲትዩቱም ጥያቄዎቻችሁን እናያልን ብሎ ሰልፉ እንዲበተን አድርጓል። 8 ሰዓት ላይ ከተማሪዎች ጋር ውይይት ይኖራልም ተብሏል።

.ተማሪዎች በሆልስቲክ ፈተና እንዲሁም በሌሎች ያሳስቡናል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ግቢው የፊታችን ማክሰኞ የማጠቃላያ ፈተና መሰጠት ይጀምራል። (አብዛኛው የትምህርት ክፍል)

ምንጭ፦ Ye
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉት ወገኖች 11 ሰንጋዎችን የረመዳን ፆምን በማስመልከት አበርክቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
FM RADIO! አዲስ አበባ ሶስት አዳዲስ የFM ራድዮ ጣቢያዎችን ልታገኝ ነው።

እነዚህም...

FM 95.1 ~ አራዳ FM ~ ባለቤትነቱ የጋዜጠኛ ብርሃኔ ንጉሴ(ኢትዮፒካሊንክ) እና አዲካ

FM 93.8 ~ አፍሪ FM ~ ባለቤትነቱ ሜሎን ከበደ

FM 106.7 ~ J FM ~ ባለቤትነቱ የዮሴፍ ገብሬ(ጆሲ)(J TV) ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ! ለይስማይከ ወርቁ ህክምና አራት መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል።

ይህ የተነገረው ዛሬ በቤስት ዌስተርን የይስማእከ ወርቁ የህክምና ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ይስማእከ በአሁኑ ወቅት በተደረገለት የህክምና ምርመራ ውጭ አገር ሄዶ መታከም እንዳለበት የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሀኪሞች ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም መሰረት ይስማእከ የመጀመሪያው የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረግ የሚጠበቅበት ሲሆን የህክምና ማገገሚያ እና የንግግር ልምምድ ያስፈልገዋል። ይህ ህክምናም ከአንድ አመት በላይ ይፈጃል ተብሏል።

በዚህም መስረት በአገር ውስጥ ከተለያዩ ግለስቦችና ድርጅቶች ቃል የተገቡትን ገንዘቦች ሳይጨምር 600,000 ብር እስካሁን ለመሰብሰብ ተችሏል። ያም ሆኖ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ በተጠናከረ መልኩ የገቢ ማሰባሰብ ስራዎችን መስራት አስፈልጓል።

ለዚህ ይረዳ ዘንድም በአገር ውስጥና በውጭ አገር የተለያዩ
ድጋፍ ማሰባሰቢያ ስልቶች ተቀይሰዋል።

*በኦሮሚያ ኅብረት ስራ የባንክ አካውንት ቁጥር 1000047902804

*በሞባይል ባንኪንግ ሄሎ ካሽ

እንዲሁም በአርቲስት ታማኝ በየነ
አማካኝነት በተከፈተው
WWW.gofundme.com.Save Yesmake Worku አካውንቶች ደራሲና ገጣሚ ይስማእከ ወርቁን ለመርዳት የሚቻልባቸው አማራጮች ሆነው ቀርበዋል።

አስተባባሪ ኮሚቴው ለእርዳታ ማሰባሰቡ እገዛ ያደርጉና እገዛ ለማድረግ በመተባበር ላይ ለሚገኙ በሙሉ ምስጋናቸውን
አቅርበዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ምንም መናገር ባይችልም ደራሲ እና ገጣሚ ይስማእከ ወርቁ ታድሟል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የይስማእከ ወርቁን የጤንነቱን ደረጃ፣ የሀኪሞች ቦርድ ውሳኔና አስፈላጊ ማስረጃዎች ተያይዘው
ቀርበዋል።

ምንጭ፦ በፍቃዱ አባይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia