TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 164 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 164 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6,630 የላብራቶሪ ምርመራ 164 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,670 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 117 ወንድ እና 47 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 92 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 163 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዱ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 104 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 26 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 22 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 1 ሰው ከሐረሪ ክልል እንዲሁም 1 ሰው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሰላሳ ሶስት (33) ሰዎች (32 ከአዲስ አበባና 1 ከአማራ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 434 ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 40 ደረሰ!

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአምስት (5) ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ92 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

2. የ58 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘባቸው።

3. የ80 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

4. የ36 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

5. የ70 ዓመት ወንድ የሱማሌ ክልል ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Oromiyaa

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 293 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሆለታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 2 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊት የሰበታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

ዛሬ በአማራ ክልል በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 22 ሰዎች ሲሆኑ ሃያ (20) ሰዎች ከመተማ፣ አንድ (1) ሰው ከወልዲያ እንዲሁን 1 ሰው ከአብርሃጅራ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

ከፆታ አኳያ ሲታዩ ሃያ (20) ወንድ እና ሁለት (2) ሴት ሲሆኑ ከ18 እስከ 35 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

የተገላጭነት ሁኔታ ፦

• የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው - 21
• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 1

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦

• ምዕ/ጎንደር - 139 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 4 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 6 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች፦

ታማሚ 1 - የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 2 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 3 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው።

ታማሚ 4 - የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ የሌላቸው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው።

ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጠው አራቱ (4) ሰዎች መካከል ሶስቱ (3) ይርጋለም ህክምና ማዕከልና አንድ ሰው ሀዋሳ ህክምና ማዕከል እንዲቆዩ ተደርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SRHB

በሱማሌ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሃያ ስድስት (26) ሰዎች ሲሆኑ ሁሉም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ (ጅቡቲ) ያላቸውና ከደዋሌ ለይቶ ማቆያ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#THRI

ዛሬ በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ አራቱ (4) ሰዎች መካከል ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የተቀሩት ሁለቱ (2) ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኑነት ያላቸው እንደሆኑ ከትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ሰምተናል።

በትግራይ ክልል ደረጃ በአጠቃላይ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 92 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 8 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አግግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሐረሪ ክልልና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ፦

- በሐረሪ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠው የሀኪም ወረዳ ነዋሪ የሆነች የ37 ዓመት ሴት ስትሆን በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ናት።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኮቪድ-19 የተያዘው ግለሰብ ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ በተደረገው በረራ በአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት በተወሰደው የናሙና ምርመራ የተገኘ ሲሆን ግለሰቡ የጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለሌው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከትምህርት ሚኒስቴር ለሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች የተሰጠ ማሳሰቢያ!

(የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር)

የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመቋረጡ ሀገር አቀፍ የብሔራዊ ፈተና /ምዘና/ የሚሰጥበት ጊዜ በትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም በኤጀንሲው አለመገለፁ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የተለያዩ አካላት ሀሰተኛ ማህበራዊ ድረገፆች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስምና ሎጎ ተጠቅመው ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን እያሰራጩ እንደሚገኙ ተደርሶበታል።

ስለዚህ ውድ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትምህርት የሚጀመርበትን እና ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና /ምዘና/ የሚሰጥበትን ጊዜ ወደፊት የሚገልፅ መሆኑን እያሳወቀ ተማሪዎች ከወቅታዊው በሽታ ለራሳችሁ እና ለቤተሰባችሁ ጥንቃቄ በማድረግ የመማሪያ መፅሀፍትንና ደብተሮቻችሁን እያነበባችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrEbbaAbate

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ቢቀመጡም ወረርሽኙ 'ወደ ህብረተሰቡ' ውስጥ መግባቱ በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMatshidisoMoeti 

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ '#አፍሪካ' ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሞዌቲ እንዳሉት በቂ ምርመራ እየተደረገ ባለመሆኑና የመከላከያ አቅርቦቶችም በቂ ባለመሆናቸው ቫይረሱ ከዋና ዋና ከተማዎች አልፎ በገጠር አካባቢዎችም ስሩን እየሰደደ ነው።

ነገር ግን የቫይረሱ ስርጭት አሁንም ቢሆን ከቁጥጥር ውጭ እንዳልሆ እና የሚመዘገቡ ሞቶች በመንግሥታት ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ዶክተር ማሺዲሶ ሞዌቲ መናገራቸውን #BBC ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ምርመራ ትላንት በይፋ ጀምሯል።

ምርመራው የትግራይ ክልል የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት የሚላክን ሳምፕል ብቻ ስለሚሰራ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ በአካል ወደ ዓይደር መምጣት እንደማይችል ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,946 ደርሰዋል! 

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 4/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,946 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 87 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው 2 ሰዎች፣ 4 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 81 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 23 ሰዎች
• ቦሌ - 3 ሰዎች
• ጉለሌ - 14 ሰዎች
• ልደታ - 5 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 10 ሰዎች
• የካ - 8 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 6 ሰዎች
• አራዳ - 8 ሰዎች
• ቂርቆስ - 7 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 2
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 1

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,946 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 490 ሰዎች
• ቦሌ - 290 ሰዎች
• ጉለሌ - 251 ሰዎች
• ልደታ - 208 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 177 ሰዎች
• የካ - 114 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 95 ሰዎች
• አራዳ - 94 ሰዎች
• ቂርቆስ - 88 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 66 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 73 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia