TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሱማሊያ ተጨማሪ 47 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 47 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,502 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስራ አምስት (15) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 178 ደርሷል።

በተጨማሪ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሃምሳ ዘጠኝ (59) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክያት የተዘጋው የአሜሪካ እና የካናዳ ድንበር እስከ ሰኔ 14/2012 ዓ/ም ድረስ ተዘግቶ እንደሚቆይ ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ ገልፀዋል።

- ብሪታኒያ ሰዎች ራሳቸውን ችለው እንዲገለሉ ከሚያደርጉ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ማሽተት አለመቻል ወይም ጣዕም ማጣትን አካታለች - #BBC

- 2ተኛ ቀኑን በያዘው የWHO 73ኛ ዓመታዊ የቪዲዮ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ አባል ሃገራት ድርጅቱ /WHO/ እና በስሩ ያሉ ኤጀንሲዎች ለኮሮና ወረርሽኝ የሰጡት ምላሽ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተስማምተዋል - #AlAin

- የቻይና ሳንቲስቶች ኮቪድ-19ኝን የሚያቆም መድሀኒት አግኝተናል እያሉ ነው። ወረርሽኙን ክትባት ያቆመዋል ተብሎ ይገመት ነበር የሚሉት የቻይና ላብራቶሪ ተመራማሪዎች የኮሮናን ስርጭት በፍጥነት የማቆም ኃይል ያለው መድሀኒት እያዘጋጀን ነው ብለዋል - https://telegra.ph/EthioFM-05-19-2

- በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ100,000 በላይ ሆኗል። የሟቾች ቁጥር ከ3,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።

- በብራዚል የኮሮና ቫይረስ እየበረታ ነው፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከUK፣ ከጣልያን፣ ከፈረንሳይ በልጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 261,567 ደርሷል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 162 ሰዎች ሞተዋል፤ 813 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በማዳጋስካር ሁለተኛው (2) ሞት በትላትናው ዕለት ምሽት ተመዝግቧል። በሌላ በኩል በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 326 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DonaldTrump

"የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ቻይና በአፍሪካዊያን ላይ የፈጸመችውን ዘረኛ ድርጊት ችላ ብሏል" - ዶናልድ ትራምፕ

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይናዋ ደቡባዊ ከተማ ጉዋንዡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መቀስቀሱን ተከትሎ በአፍሪካዊያን ላይ ሲፈጸም ለነበረው ዘረኛ ድርጊትና መድልዎ የዓለም ጤና ድርጅት ጠንካራ ምላሽ አልሰጠም ሲሉ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ትራምፕ ለድርጅቱ ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በጻፉት ደብዳቤ ላይ አፍሪካዊያን በግድ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ፣ ከመኖሪያቸው እንዲባረሩ ፣ እንዲሁም አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግን ጨምሮ ዘረኛ እና አድሎአዊ ድርጊት ደረሰብን ቢሉም፤ ድርጅቱ በቻይና #ዘረኛ ድርጊት ላይ አስተያየት አልሰጠም ሲሉ ከሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SouthSudan

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል እንደሚገኙበት #SSNN ይፋ አድርጓል።

2ቱም ሚኒስትሮች ባለፈው ወር ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር የተባለ ሲሆን በዚህ ወር ግን ምርመራ ሲደረግላቸው ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን #SSNN ስማቸው ካልተገለፀ 'የኮቪድ-19 ታስክ ፎርስ' አባል መረጃ ማግኘቱን ገልጿል።

ሌላ አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ምንጭ ደግሞ ሁለቱም (2) ሚኒስትሮች ጤናቸው ጥሩ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ምልክት እንደማይታይባቸው አሳውቀዋል ሲል #SSNN ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የእኔ ውጤት #ኔጌቲቭ ነው!" - ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ

የደቡብ ሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ውጤታቸው #ፖዘቲቭ ነው ተብሎ በሚዲያዎች ላይ መነገሩ ሀሰት ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ "በትላንትናው ዕለት የደቡብ ሱዳን ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ እንዳረጋገጠልኝ የናሙና ውጤቴ #ኔጌቲቭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስትር ከቫይረሱ #ነፃ ናቸው!

የደቡብ ሱዳን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤልዛቤት አቾዪ ዮል በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ #ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ሚኒስትሯ ያለፈው ሳምንት ነው የኮቪድ-19 ምርመራ የተደረገላቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ግብፅ ውስጥ በአንድ ቀን 720 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የግብፅ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት ሰባት መቶ ሃያ (720) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13,484 ደርሷል።

በተጨማሪ በሀገሪቱ የሟቾች ቁጥር 659 ደርሷል ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የአስራ አራት (14) ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በስፔን ለ3ተኛ ቀን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዝግቧል!

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ስልሳ ዘጠኝ (69) ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ በሀገሪቱ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 27,778 ከፍ ብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢትዮጵያና የጎረቤት ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 2,591፣ ሞት 105፣ ያገገሙ 247

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,618 ፣ ሞት 7 ፣ ያገገሙ 1,033

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 1,502፣ ሞት 59 ፣ ያገገሙ 178

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 963 ፣ ሞት 50 ፣ ያገገሙ 358

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 365፣ ሞት 5 ፣ ያገገሙ 120

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 347 ፣ ሞት 6፣ ያገገሙ 4

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 39

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 137 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተረጋገጠ!

የሱዳን ጤና ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ተጨማሪ 137 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 39 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,728 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 111 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 286 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸዉ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ የኮቪድ-19 ስርጭት ካለፉት 2 ወራት ይበልጥ ባለፉት 2 ሳምንት ውስጥ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 63 በመቶ ድርሻ እንዳለው ገልጿል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው አጠቃላይ ቁጥር 228 የሚሆኑት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መሆናቸውን አሳውቋል።

የልደታ ክ/ከተማ 40 በመቶ የሚሆነውን ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ቁጥር ሲይዝ አዲስ ከተማ ክፍለከተማ በሁለተኛነት ድርሻውን መያዙን ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

ይህም ቫይረሱ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን የሚያመላክት እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እንዲሁም ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 በመቶ መድረሱንም ዶ/ር ሊያ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrEbbaAbate

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ቅኝት የማድረግ ስራ ዋነኛ ተግባር መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተደረገ ቅኝት ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ከነበረው አንድ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ በወረዳው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በተደረገ ድንገተኛ ምርመራ አርባ (40) 'የህግ ታራሚዎች' ይገኙበታል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 365 ሰዎች 56ቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ከበሽታው ተጠቂ ግለሰብ ጋር ንክኪ #ያልነበራቸው መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ከእነዚህ ውስም 48 በመቶ ' በአዲስ አበባ ከተማ ' ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthSudan የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል እንደሚገኙበት #SSNN ይፋ አድርጓል። 2ቱም ሚኒስትሮች ባለፈው ወር ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር የተባለ ሲሆን በዚህ ወር ግን ምርመራ ሲደረግላቸው ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን #SSNN ስማቸው…
ሚካኤል ማኩዪ በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጠዋል!

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የሆኑት ሚካኤል ማኩዪ በተደረገላቸው የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራ #በቫይረሱ መያዛቸውን በይፋ አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ለቪኦኤ እንደተናገሩት የቀድሞ 'የኮቪድ-19 ታስክ ፎርስ' አባላት በሙሉ በኮሮና ቫይረስ ስለመያዛቸው መረጃው እንዳላቸው ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,460 የላብራቶሪ ምርመራ ሃያ አራት (24) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 389 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 18 ወንድ እና 6 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ4 እስከ 57 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 9 ሰዎች ከአዲስ አበባ (5 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና 4 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 7 ሰዎች ከትግራይ ክልል (4 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና 3 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ከነዚህም ውስጥ 1 መቐለ ለይቶ ማቆያ ያለ ሲሆን ስድስቱ (6) ማይካድራ ለይቶ ማቆያ ያሉ ናቸው) ፣ እንዲሁም 8 ሰዎች ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው እና መተማ ለይቶ ማቆያ ያሉ) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 12

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 8

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 4

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 2 ሰዎች ከአማራ ክልል ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ሁለት (122) ደርሷል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#MutahiKagwe

በኬንያ በአንድ ቀን 66 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተረጋገጠ!

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። እስካሁን ከተመዘገቡት የአንድ ቀን ኬዞች #ከፍተኛው ነው። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,029 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!

TIKVAH-ETHIOPIA እንኳን ለሲዳማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን!

ይህን ዓለምን ያስጨነቀ ወረርሽኝን አሸንፈን የዓለም ቅርስ የሆነውን 'ፊቼ ጨምባላላ በዓል' በአደባባይ ተሰባስበን የምናከብርበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን #ተስፋ እናደርጋለን!!

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ለ1 አመት ያህል ትምህርት በርቀት እንዲሆን ወሰነ!

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

በዓለም ላይ ካሉት እውቅ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ለአንድ (1) አመት ያህል በክፍል ውስጥ የሚኖር ትምህርት #እንደሌለ አስታውቋል።

ሆኖም ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉም ትምህርቶች በ 'ኦንላይን' የሚሰጡ ሲሆን " ከተቻለም የተወሰኑ ተማሪዎችን በቡድን አንድ ቦታ ላይ በማድረግ መማር የሚችሉበትን መንገድ ልናመቻች እንችላለን ብሏል።

ዩኒቨርስቲው 'ይህ መሆን የሚችለው ግን ጥቂት ተማሪዎች ቢሆኑም አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ ሲችሉ ነው' በማለት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማዳጋስካር ውስጥ የኮሮና ስርጭት እየጨመረ ነው!

በማዳጋስካር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ አርባ አምስት (45) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከአርባ አምስቱ መካከል ሶስት (3) ሰዎች ከአንታናናሪቮ እንደሆኑ ተሰምቷል።

አጠቃላይ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 371 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 131 ሰዎች በተደርገላቸው ህክምና አገግመዋል፤ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia