TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.7K photos
1.56K videos
216 files
4.28K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

አውረስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ምክንያት ሰው እምደሞተባት አሳውቃለች። ግለሰቡ በዳይመንድ ፕሪንሰስ መርከብ ውስጥ የነበረ የ78 ዓመት አዛውንት ነው ተብሏል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ትላንት በአሜሪካ የሞተው ግለሰብ በ50ዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝና ሌሎች በሽታዎች ያሉበት ሰው ነው። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሟቹ የቫይረሱ ስጋት ወዳለበት አካባቢ አልተጓዘም ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ የዋሽንግተን አገረ-ገዥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ካሊፎርኒያ፣ ኦሬጎን እና ዋሽንግተን ግዛቶች ውስጥ የቫይረሱ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች ያልሄዱ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ስጋት አድሯል።

ዋሽንግተን ውስጥ በሚገኝ አንድ የአዛውንቶች መንከባከቢያ ክበብ ሁለት ሰዎች የቫይረሱን ምልክት አሳይተው ወደ ጤና ጣብያ ተወስደዋል። ሌሎች በርካታ የክበቡ አባላት ምርመራ እየተደረገላቸው ነው።

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት በሰጡት መግለጫ ላይ ምንም እንኳ ቫይረሱ አገራቸው ቢገባም 'የሚያስደነግጥ ነገር የለም' የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ደግሞ ኢራን ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እግድ እንደሚቀጥልና ባለፉት 14 ቀናት ኢራንን የጎበኘ ማንኛውም የውጭ ዜጋ ወደ አገራቸው እንደማይገባ አሳውቀዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KFO #OFC #ADAMA

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] በአዳማ ሊያደርግ የነበረው ህዝባዊ ውይይት በፀጥታ ኃይሎች መከልከሉን የአዳማ ቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀውናል።

ውይይቱ ለምን? በማን? ሊከለከል እንደቻለ ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ቤተሰቦቻችን ተናገረዋል። ውይይቱ ለመካፈል መጥተው የነበሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውም ተገልጾልናል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADWA124

የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ 124ኛውን የዓድዋ በአል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ “ከ124 አመታት በፊት በሩቁ፣ በአሻጋሪ ተመልክተው በጨለማ የምንኖር ደካሞች አድርገው ለቆጠሩን በኅብረት፣ በእውቀት ብርሃን የምንኖር ፅኑ መሆናችንን በአድዋ አስተምረናል” ብለዋል።

ዓድዋ የፍቅር ፣ የመተባበር ፣ በጋራ የማደግ፣ የለጋስነት ፣ ጎረቤትን እንደራስ የመውደድ ትምህርት ኢትዮጵያውያን ሁሌም የሚያስተምሩት የእውነት መንገድ መሆኑንም ነው ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የገለፁት።

ም/ከንቲባው “የሀሰት፣ የትዕቢት፣ የመጠቃት ደንገርጋራ መንገድን ኢትዮጵያውያን እንጠላለን፣ ጠልተንም በአድዋ መንገድ እንድንፃረረው ሆነን አድገናል” ማለታቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KFO #AWADAY #OFC

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ላይ ተፈጽሟል ያለውን ኢ ሰብዓዊ ድርጊት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አጣርቶ ውሳኔ እንዲያስተላልፍበት ኦፌኮ ጠይቋል።

የኦፌኮ ለፓርላማው በጻፈው የአቤቱታ ደብዳቤው የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ለማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውና ዜጎች እየተቀባበሉ ስለተመለከቱት በአወዳይ ከተማ ማህበረሰብ ላይ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ሲፈጽሙት የሚታየውን ጭካኔ የተሞላበት ደብደባና ግድያ ጉዳይ እንዲጣራ ነው የጠየቀው፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው የድምጽ ምስል መረጃ በቀላሉ የምንመለከተው አይደለም ያለው ኦፌኮ ድርጊቱም እጅግ አሳዝኖኛል ብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ሐምሌ 30/2008 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የፀጥታ ሀይሎች በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲፈጽሙ ከሚታየው ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን የጠቀሰው ኦፌኮ ም/ቤቱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡

በአወዳይ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትም ፓርላማ አስቸኳይ ምርመራ አድርጎ እንዲወያይበትና ውሳኔ እንዲሰጥበት ኦፌኮ ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Mekelle

የስላሴ ጨለቖት ዘውድ ትላንት በመቐለ ራስ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ የተደረገው ደማቅ አቀባበል።

PHOTO : ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀነኒሳ የሞ ፋራህን የግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰበረ !

በለንደን ከተማ በተካሄደው የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን፤ ቀነኒሳ በቀለ ክብረ-ወሰን በመስበር አሸንፏል።

የ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ በዚህ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው።
1:00:22 በሆነ ሰዓት የገባው ቀነኒሳ፤ በእንግሊዛዊው ሯጭ ሞ ፋራህ የተያዘውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰብሯል።

ከቀነኒሳ ጋር ይፋጠጣል ተብሎ የተጠበቀው ሞ ፋራህ ከጥቂት ቀናት በፊት በህመም ምክንያት እንዳይማሰተፍ ማሳወቁ አይዘነጋ።

Join @tikvahethsport

@tikvahethsport @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኢትዮጵያ መንግሥት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን የተመለከተ ሰነድ አዘጋጅቶ ለድርድር እንደሚያቀርብ ሪፖርተር ጋዜጣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገለፁልኝ ብሎ ዘግባል።

በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ አመቻችነት የግድቡን የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ የቆየው ድርድር ውጤት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ጥቅም የሚያስከብር የድርድር ሰነድ እንዲያዘጋጅ በመንግሥት ታዞ ሰነዱን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከተደራዳሪ ቡድኑ በተጨማሪ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዓለም አቀፍ ሕግ ስምምነት ባለሙያዎች፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ሰነዱን በማዘጋጀት ሒደት ላይ ሌት ተቀን እየሠሩ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል።

More https://telegra.ph/reporter-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የእኔ ነው!

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መላው ኢትዮጵያውያን ከጉድለታቸው በመቆጠብ በጥረታቸው እና በላባቸው ዕውን ያደረጉት ነው።

አንድ የሃይማኖት አባት በግድቡ መጀመር ሰሞን ይህን ብለው ነበር፦ “በማህጸን ካለ ሕፃንና በመቃብር ካለ አስክሬን ውጪ” ሁሉም ኢትዮጵያውያን የቆሙለትና የደገፉት ታሪካዊ ፕሮጀክት ነው።

#ኢትዮጵያፕሬስድርጅት
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ወቅታዊ መግለጫ፦

የኢፌዴሪ የሚነስትሮች ምክር ቤት በትላንትና ውሎው አዲስ የቋንቋ ፖሊሲ ማፅደቁን ተናግሯል። በዚህ አዲሱ የቋንቋ ፖሊሲ በአፋን ኦሮሞና ሌሎች ቋንቋዎች የፌደራሉ መንግስት የስራ ቋንቋ መሆን የሚያስችል ነው ተብሎ ተናግሯል። ይህ የቋንቋ አጀንዳ በርካታ ጊዜያት ተነስቶ መልሶ የጠፋ፣ የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ ሲንከባለል ዛሬን ደርሷል። አሁንም ይህ ውሳኔ በስራ ስለሚተረጎበት ሁኔታ የሚታወቅ ነገር የለውም።

ስለሆነም ኦነግ የዚህ ውሳኔ ስራ ላይ መዋል በጥርጣሬ አይን ያያል። ይህ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተረጋገጠው ውሳኔ ስራ ላይ እንዲውል፦

1. ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንዲፀድቅ እንጠይቃለን።

2. የፊንፊኔና ድሬዳዋ በህግ አግባብ፣ በታሪክ እንዲሁም መሬቱ የኦሮሞ ህዝብ ሀብትና የኦሮሚያ አካል ስለሆኑ የነዚህ የሁለቱ የኦሮሚያ ከተሞች ጉዳይ በአስቸኳይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኝ እንጠይቃለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/NAMA-03-01

ኢዜማ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/EZEMA-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam

ትለንት ምሽት የውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በቀለ 'ታዲያስ አዲስ' ከተሰኘ የሬድዮ ዝግጅት ጋር የስልክ ቆይታ አድርገዋል። ሚኒስትሩ በቆይታቸው አሁን ስላለው ሁኔታ፣ በድርድሩ ዙሪያ ስለሚነገሩት ብዥታዎች፣ ስለኢትዮጵያ አቋም፣ ሂደቱ ከመነሻው ምን እንደሚመስል፣ የአሜሪካ ተሳትፎ እንዴት እንደመጣ፣ ስለ ህዳሴው ግድብ ቀጣይ እጣፈንታ በጥልቀት እና በግልፅ አብራርተዋል።

📹8 MB
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam

የህዳሴው ግድብ ቀጣይ እጣፈንታ ...

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፦

"የህዳሴ ግድብ እጣፈንታ ምንም ሚለወጥ ነገር የለም፤ ግንባታውም እየተካሄደ ነው፤ የኮንስትራክሽን ሂደቱ የውሃ ሙሌት ደረጃ ላይ ሲደርስ መሙላት ይጀምራል። ድርድሩም ይቀጥላል፤ ድርድሩን የሚያቆም ምንም ምክንያት የለም።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2010 እና 2011 ዓ.ም. ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ 8 ሺሕ ወጣቶችን መቅጠሩን አስታውቋል። ከ20 ሺሕ ተመራቂዎች መካከል በመመዘኛ ፈተና የተመረጡት ወጣቶች በዜሮ አመት የሥራ ልምድ በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት መመደባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። አስተዳደሩ እንዳለው ምሩቃኑ ባለፉት ቀናት በሥልጠና ላይ ነበሩ።

#MayorOfficeOfAA #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በወላይታ በከባድ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓጓዝ የተገኘ 120 ኩንታል ካናቢስ ተወገደ!

በወላይታ ዞን በከባድ ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር የዋለ 120 ኩንታል ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕጽ እንዲወገድ መደረጉን ፖሊስ አስታውቋል።

በዞኑ የዳሞት ጋሌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢኒስፔክተር ያሊሳ ጋጋ እንደገለጹት አደንዛዥ ዕፁ ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ተይዞ አስፈላጊው የምርመራ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት ትናንት እንዲቃጠል ተደርጓል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

በድህረ ምርጫ ለሚያጋጥሙ ችግሮች የዲጂታል መፍትሄዎችን ለማበጀት በአዲስ አበባ የተሰባሰቡ ወጣቶች፤ በ48 ሰዓታት ውስጥ ያዘጋጇቸውን የ"አፕልኬሽን እና ሃርድዌር" ስራዎቻቸውን ዛሬ በወመዘክር ግቢ በሚገኘው የአሜሪካ ማዕከል አቅርበዋል።

አስር ቡድኖችን ባሳተፈው "የድህረ ምርጫ የዲጂታል መፍትሄ ውድድር" ያሸነፉት ወጣቶች፤ የድምጽ ቆጠራ እና የምርጫ ውጤቶች የማሳወቅ ሂደትን ለማሳለጥ የሚያስችል አፕልኬሽን የሰሩ ናቸው። ወጣቶቹ ለስራቸው የሚረዳ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia