ዶ/ር የሺዋስ መኳንንት ምን ይላሉ፦
ዶክተር የሺዋስ መኳንንት እባላለሁ። የምሰራው ድሬዳዋ ድልጮራ ሆስፒታል ነው። ኮረና ቫይረስን ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል። 1000 አልጋ ያለው ግዙፍ ሆስፒታል በስድስት ቀን መገንባት የሚችሉ ኃያላን ሀገራት ሊቋቋሙት ያልቻሉት በሽታ ወደ እኛ ከመጣ ምን ሊዉጠን ነዉ? ባለፈዉ ክረምት ድሬዳዋ ላይ ብቻ ተከስቶ የነበረዉን ችኩንጉንያ መቆጣጠር ተስኖን ያ ሁሉ ሰዉ በትኩሳት ሕመም ሲረፈረፍ በአይናችን አይተናል። ያውም እኮ ችኩንጉንያ በፓራሲታሞል ብቻ የሚታከም ሆኖ ከተማዉ ላይ ግን ፓራሲታሞል ጠፍቶ እንዴት እንደተቸገርን እኛ ነን የምናዉቀዉ።
አሁን ማን ይሙት ኮረና ቫይረስ ከመጣ ስንኳንስ የጽኑ ህሙማን ክፍሎች፣ የመተንፈሻ መሣሪያዎች ... ይቅርና በትንሹ በቂ የዉኃ አቅርቦት እንኳን አለን ወይ? በጽኑ ህሙማን ክፍሎችና በመተንፈሻ መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት በየቀኑ የሚሠረዙትን ቀዶ ሕክምናዎች እና የሚሞቱትን ወገኖቻችንን ግን አስበን እናውቃለን? አብዛኞቹ (ምናልባትም ሁሉም) ሆስፒታሎቻችን እኮ በቂ የንጽሕና መጠበቂያ እንኳን የሌላቸዉ ናቸው /ውኃ፣ አልኮል፣ ጓንት/።
በሚያሳዝን ሁኔታ ሆስፒታሎቻችን አንዲት የኦክስጅን ሲሊንደር ለሁለት ታማሚዎች ሰንጥቀን የምንጠቀምባቸው ምስኪን ተቋማት ናቸው። የብዙዎቹ ሆስፒታሎቻችን ድንገተኛ ክፍሎች እንኳን 24 ሰዓት ክፍት ነው (24 hour open) የሚባለው በራቸው ነው እንጅ አገልግሎታቸው አይደለም። እንተዋወቃለን።
ታዲያ እነአሜሪካ እንኳን ስጋት ሆኖባቸው ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ከሰረዙ ለእኛ ስጋት የማይሆነው በምን ቀመር ነው? እባካችሁ ተረዱን። ኮረና ከገባ አንችለውም።
https://telegra.ph/TIKVAH-02-02
#TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ካሱ የስፖርት መገልገያ መሸጫ!
በተለይ በእድሜ ለገፉ ለሚወዱት ወላጅ ቤተሰብዎ፤ ከምንም በላይ በስጦታ በማበርከት ቀናቸውን ፤ ዘመናቸውን፤ ንቁ ! ሁነው እዲገፉ የሚያስችል እና ለርስዎም ቢሆን ያሻዎትን ስፍራ እደ አስፈላጊነቱ በዲፕ ቲሹ ማሳጅ (በጫና) እየተጠቀሙ ይህን 6 ደረጃ ከፍተኛ የማሸት ሀይል የተጨመረለትን ፣ 4 የተለያዩ መቀያየሪያ የያዘን ፤ የትም ይዘውት የሚንቀሳቀሱትን ፣ ከፈለጉ ለህክምና (ቴራፒ ) አገልግሎት የሚጠቀሙበት ሲያሻዎ ዘና ለማለት ለ (Relaxation) አልያ በማናቸውም ጊዜ ጡንቻዎትንና ጅማቶችን በማሸት፤ ነርቭን በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት የደም ዝውውርን በማፋጠን ዘርፈ ብዙ የጤና በረከቶችን የሚያላብሰንን አዲሱን GUN MASSAGER ይሸምቱ። ቪዲዮው ይመልከቱ ! ጤናዎን ካስቀደሙ Gun massager ይጠቀሙ! ዋጋ 3,400 ብር። ወስነው ይደውሉ። ያሉበት ስፍራም መላክ እንችላለን። ለማንኛውም ጥያቄ ዋና➙ አድራሻ፦ ቃሊቲ ካፍደም ህንፃ 2ኛ ፎቅ
0906 252525... 0911 042543

#Election2012
ወጣቶች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑና በቀጣይ በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ [ምርጫ 2012] ላይ በንቃት እንዲሳተፉ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ወጣቶች ሰላምና ብልጽግና ተልእኮ አስታውቋል፡፡
በነሀሴ 2011 ዓ.ም በሲቪክ ማህበራት ኤጀንሲ እውቅና የተሰጠው ይህ የወጣት አደረጃጀት አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ በኦሮሚያ ፤ በሶማሌ እና በአማራ ክልሎች እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ በሰጠው መግለጫ ላይ ጠቅሷል፡፡
በሰላም እጦት ምክንያት ሰለባ የሚሆነው ወጣቱ ነው የሚለው ህብረቱ ወጣቱ መብትና ግዴታውን አውቆ ለሰላም የበኩሉን እንዲወጣ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የህብረቱ ፕሬዝዳንት ወጣት ብርሀኑ በቀለ ተናግሯል።
ህብረቱ ለቀጣዩ ምርጫ በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች 40 ሺህ የምርጫ ታዛቢዎችን እንደሚያሰማራም ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገረው፡፡
ህብረቱ የጎዳና ወጣቶችን የማንሳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በከተማ ጽዳት ወጣቶችን የማሳተፍ ተግባር እንደሚያከናውን የተናገረው ወጣት ብርሃኑ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም ህብረቱ ጠንክሮ እንደሚሰራ ጠቁሟል፡፡
[አዲስ ቴሌቪዥን]

TIKVAH-ETHIOPIA
"አየር መንገዱ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ያቁም" - የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በ10 ሺህ የሚቆጠሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ [TIKVAH-ETH] ቤተሰቦች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና ከተሞች የሚያደርጋቸውን በረራዎች በአስቸኳይ እንዲያቋርጥ እየጠየቁ ይገኛሉ። በ @tikvahethiopiaBot በኩል መልዕክት እየላኩ የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ለቻይና ያልተቀመሰው ይህ አደገኛ በሽታ ድሃዋ ሀገራችን…
የኮሮና ቫይረስ ስጋት...
የሀገራችን ከፍተኛ መኮንን ነኝ ያሉ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል አየር መንገዱ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንዲያቆም የግል ምክረ ሃሳባቸውን አቅርበዋል።
ከፍተኛ መኮንኑ የኮሮና ቫይረስ እየሠፋ በመሄዱና ለታዳጊ ሃገራት ሊኖረዉ ከሚችለዉ ከፍተኛ ተጽኖና የመቆጣጠር አቅም አኳያ እንደ ታዳጊ ሃገር ኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ካለው የፖለቲካ ሰጣገባን ጨምሮ በሽታዉ ሀገሪቱ ውስጥ ቢገባ ለመቋቋም የሚኖረን ብቃት በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዳይሆንብን ስጋቱ አለኝ ብለዋል።
ከምናገኘዉ ገቢ [ዶላር] ይልቅ የምናተርፈዉ የሰዉ ልጆች ህይወት ስለሚበልጥ፤ ይህን አድርገን ቢሆን ብሎ ከመፀፀትና ከመወነጃጀል ከወዲሁ ቢታሰብበት፤ አየር መንገዱም ለጊዜው በረራውን ቢያቆም የተሻለ እንደሚሆን የግል ምክረ ሃሳባቸውን አቅርበዋል።

#UPDATE
ዛሬ በዮድ አቢሲኒያ የባህል አዳራሽ ፍቅር ያሸንፋል የሲቪክ ማህበር ከኃይማኖት አባቶች፣ ከአባገዳዎችና ከፓለቲካ ፖርቲ ተወካዮች ጋር ስለ ማህበሩ እንቅስቃሴና በቀጣይ የካቲት 15 በሚደረገው 'ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ ' የጎዳና ሩጫ አስመልክቶ ባሰናዳው መድረክ የድርጅቱ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚፍታ ከድር የተናገሩት፡-
በእስር ቤት በቆየንበት ወቅት እኛ ላይ ግፍ ሲፈጽሙ የነቀሩት የሁሉም ብሔረሰቦች አባላት ነበሩበት ግን እነሱ የስርዓቱ ሎሌዎች ነበሩ ስርዓቱ እንጂ ህዝቡ አልበደለንም፡፡ እነዛም ቢሆኑ ሁሉም ወንድሞቻችን ናቸውና ከልባችን ይቅር ብለን ፍቅር ያሸንፋል ብለን ለፍቅር እየሰራን እንገኛለን፡፡
ማህበራችንን ከመሰረትን በኀላም 'ደሜ ብሔር የለውም ደሜ ቋንቋ የለውም ደሜ ለወገኔ' በሚል የደም ልገሳ መርኃግብር አካሂደናል፡፡ በተለያዩ ክብረ በዓላት ጊዜም ሳንከፋፈል የጽዳት ሥራዎችን ሰርተናል፡፡
የካቲት 15 ደግሞ ለፍቅር እንሩጥ በሚል ርዕስ 40,000 ሰዎች የሚሳተፉበት የሩጫ መርኃግብር አዘጋጅተናል፡፡ ውድድሩን የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ሁሉም በጋራ ያስጀምሩታል ብለን አቅደናል፡፡ ከዛም ባለፈ በአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ የሚመዘገብ ሰፊ እንጀራ ተጋግሮ ሁሉም የፓርቲ አመራሮች ከአንድ መአድ እንዲቋደሱ ይደረጋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የኦነግ መግለጫ፦
በኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመ ያለዉ የሰብዓዊ መብት ረገጣ በነፃ እና ገለልተኛ አካል ምርመራ ልደረግበት ይገባል!
ከምዕራብ ኦሮሚያ (የወለጋ ዞኖች) ቴሌፎንና ኢንተርኔትን የመሳሰሉት የመገናኛ አገልግሎቶች በመንግስት ከተቋረጡ 1 ወር ኣለፈ። ከዚህም የተነሳ የዕለት ተዕለት ክስተቶችን በጊዜዉ ከነበቂ መረጃ ጋር ማግኘት አዳጋች ብሆንም እንኳ የመንግስት ወታደሮችና ታጣቂዎች በሰላማዊ (ትጥቅ-ኣልባ) ዜጎች ላይ እያካሄዱ ባሉት ግድያ የሰዎች ህይወት እንደቅጠል እየረገፈ መሆኑ መተለያየ መንገድ እየተሰማ ነዉ።
በተለይም በሁለት ዞኖች (ምዕራብ ወለጋ እና ቄሌም ወለጋ) ዉስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች በሕዝቡ ላይ እየፈጸሙ ያሉትን ግድያና ጭፍጨፋ በቃላት መግለጽ እንኳን ይከብዳል። የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀል የሚሉት ቃላቶችም በትክክልና በበቂ ሁኔታ ልገልጹት ኣይችሉም።
በደቡብ ኦሮሚያ (በጉጂ ዞኖች) ያለዉ ሁኔታም እምብዛም ከዚህ የተለየ አይደለም። በዚህ መልኩ ከአንድ ዓመት በላይ በወታደራዊ አስተዳደር (ኮማንድ ፖስት) ሥር በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ያለዉን እሮሮና ስቃይ በተለያዩ ጊዜያት ገልጸን መፍትሄ እንድፈለግለት ብንወተዉትም እስካሁን የሕዝባችን ኡኡታና ችግሩ ተገቢዉን ተሰሚነት ሊያገኝ አልቻለም።
More https://telegra.ph/OLF-02-02

ፍልስጤም ከአሜሪካ እና እስራኤል ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግነኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዘመናት የቆየውን የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ብሎም የቀጠናውን ሰላም በዘላቂነት መፍታት ያስችላል ያሉትን የሰላም እቅድ በቅርቡ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም የዓረብ ሊግ ሀገራት በትናንትናው ዕለት በጉዳዩ ዙሪያ የሚመክር አስቸኳይ ጉባኤ በግብጽ ካይሮ አካሂደዋል። ሀገራቱ ባካሄዱት ስብሰባም ትራምፕ ይፋ ያደረጉት የሰላም እቅድ የፍልስጤማውያንን መብት በዘላቂነት የማያስከብር በማለት ውድቅ አድርገውታል።
የፍልስጤም ፕሬዚዳንት መሃሙድ አባስ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሀገራቸው ከአሜሪካ እና እስራኤል ጋር የነበራትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይፋ ያደረጉትን የሰላም እቅድ የፍልስጤማውያንን ጥቅም እና መብት የማያስከበር ከመሆኑ ባሻገር ዓለማቀፋዊ ህግን ያልተከተለ የፖለቲካ ሴራ ሲሉ አጣጥለውታል።
[ፕሬስ ቴሌቪዥን, ኤፍ ቢ ሲ]

የትራምፕ የሰላም እቅድ ምንድነው?
የፕሬዚዳንት ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም እቅድ የእስራኤልና ፍልስጤም የዘመናት ግጭት መንስኤ የሆነችው እየሩሳሌም ከተማን የእስራኤል ግዛት ስለመሆኗ እውቅና ይሰጣል። ዌስት ባንክ የእስራኤል ሉዓላዊ ግዛት መሆኗን ያረጋግጣል።
የሰላም እቅዱ ፥ ፍልስጤማውያንም ሆኑ እስራኤላውያን አሁን ላይ ከሚኖሩበት ስፍራ የማይለቁ መሆኑንም ያብራራል። በሌላ በኩል የሰላም እቅዱ ለፍልስጤም ሉዓላዊ ሀገር ምስረታ እውቅና የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል።

ሀገራት ዜጎቻቸውን ከቻይና እያስወጡ ነው...
የ11 ሚሊዮን ነዋሪ ያላት ዉሃን ከተማ እስከ አሁን 31 ሰዎች ሞተውባታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ አገሮች ዜጎቻቸውን ከቻይና የማስወጣት ሂደት ላይ ናቸው።
ለአብነትም ሳውዲ አረቢያ 10 ተማሪዎቿን ከዉሃን ከተማ እንዲወጡ አድርጋለች። ደቡብ ኮሪያ፣ ህንድና ባንግላዲሽም በተመሳሳይ ዜጎቻቸውን እያስወጡ ነው።
ኢንዶኔዥያ እና ቱርክም ዜጎቻቸውን ለማስወጣት የራሳቸውን አውሮፕላን ወደ ቻይና መላካቸው ተገልጿል። በነገው ዕለት ደግሞ ራሺያ ዜጎቿን ለማስወጣት የጦር አውሮፓላኗን ወደ ቻይና ትልካለች ተብሏል።
የኢትዮጵያ ዜጋ የሆኑ ተማሪዎች በቻይና [ዉሃን ከተማ] እንደሚገኙ ይታወቃል ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ከቻይና ለማስወጣት የጀመራቸውን ስራዎች ግን እያየን አይደለም።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች በቻይና እየተስፋፋ ከመጣው የኮሮና ቫይረስ ስጋት አንፃር ወደ ሀገራቸው በአፋጣኝ መመለስ እንደሚፈልጉ ከሰሞኑን ለቲክቫህ ኢትዮ. ሲገልፁ እንደነበር አይዘነጋም።
[ENA, TIKVAH, BBC]

ኢንዶኔዥያ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ ወደ ቻይናና ከቻይና ወደ ኢንዶኔዥያ የሚደረጉ በረራዎችን ለተወሰኑ ቀናት ልታቋርጥ እንደተዘጋጀች ሮይተርስ ዘግቧል።

#nCoV
የቬይትናም አየር መንገድ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን በጊዜያዊነት ሊያቆም እንደሆነ ተሰምቷል። ወደ Beijing, Shanghai, Guangzhou, Shenzhen ከማክሰኞ ጀምሮ በረራዎች ይቋረጣሉ። ወደ Chengdu ከረቡዕ ጀምሮ እንዲሁም ወደ Macau ከሀሙስ ጀምሮ በረራዎች እንደሚቋረጡ ተሰምቷል።
[TNT]

አጫጭር መረጃዎች ለቲክቫህ ቤተሰቦች፦
• ዛሬ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የታገቱ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይለቀቁ የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ። ሰልፎች ከተካሄዱባቸው ከተሞች መካከል፦
- ጎንደር፣
- ሰቆጣ፣
- ደብረታቦር፣
- ኮምቦልቻ፣
- ላሊበላና ሌሎችም ይገኙባቸዋል፡፡
ሰልፎቹ በዋናነት የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ የሚጠይቁ ሲሆን ክልሉን የሚመራው የፖለቲካ ፓርቲም ተማሪዎቹን እንዲያስለቅቅ የሚጠይቁ መልዕክቶች መተላለፉ ተገልጿል።
• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በየካቲት ወር የመጀመሪያ ሳምንት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በዱባይ ከተማ በመዘጋጀት ላይ በሚገኘው መድረክ ላይ በመገኘት ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ፡፡
• ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ።
• የኢንተርኔት ማቆም፣ መረጃን አጣርቶ ማውጣትና መዝጋት በተመለከተ በአገር ደረጃ የወጣ ህግ ባለመኖሩ ተገቢው መረጃ ለተገቢው አካል እንዳይደርስ ሆኗል። በዚህም ይህንን ለማረም በኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ ለማካተት ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑን የብሔራዊ ህግና ፍትህ አማካሪ ምክርቤት አስታውቋል።
• የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ በባቱ ከተማ ከሚገኙ ደጋፊዎቹ ጋር በዛሬው ዕለት ተገናኝቷል። በሺዎች የሚቆጠሩ የባቱ ከተማ ነዋሪዎች ለፓርቲው አመራሮች አቀባበል አድረገዋል።
[የጀርመን ድምፅ፣ኢቢሲ፣ኦኤምኤን፣ኢ.ፕ.ድ]

#UPDATE የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤርትራን ጨምሮ ለስድስት ሃገራት ዜጎች የሚሰጠውን የስደት ቪዛ አገዱ። እገዳው ኤርትራ፣ ናይጀሪያ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን ኪርጊዝታን እና ማይንማር ዜጎች ላይ የተጣለ ነው። አዲሱ መመሪያ የሃገራቱ ዜጎች አሜሪካ የምትሰጠውን የስደት ቪዛ እንዳያገኙ የሚከለክል ሲሆን፥ የጎብኝ ቪዛ ግን ይፈቅድላቸዋል። ይህን ተከትሎም የናይጄሪያ፣ ኤርትራ፣ ኪርጊዝታን እና ማይንማር…
#UPDATE
አሜሪካ ከሰሞኑ ኤርትራን ጨምሮ ለስድስት (6) አገራት ዜጎች የምትሰጠው የስደት ቪዛ ላይ እገዳ መጣሏን ተከትሎ የኤርትራ መንግሥት አግባብነት የሌለውና ውሳኔው ወዳጅነትን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው ብሎታል።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በውሳኔው ቅሬታውን ገልፆ "ውሳኔው አሉታዊ መልእክት የሚያስተላልፍ ነው ብሎታል።
መግለጫው እንዳተተው ባለፉት 20 ዓመታት የኤርትራን ህዝብ ''በተቀናጀ ሁኔታ ለመቀነስ ድብቅ ፍላጎት ያላቸው ሀገራት'' የጥገኝነት ጥያቄዎችን ያለቅድመ ሁኔታ በመቀበል እና በተሳሳቱ መረጃዎች ላይ በመመስረት የሚወስዱትን እርምጃ በተደጋጋሚ ሲቃወም እንደነበር ጠቅሷል።
More https://telegra.ph/BBC-02-02-2
[BBC]

ሶማሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች...
የአንበጣ ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ ሰብል እያወደመብኝ ነው ያለችው ሶማሊያ ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር ቀድሞውንም ፈተና ውስጥ ያለው የሀገሪቱ የምግብ ዋስትና አሁን ይበልጥ አደጋ ላይ ወድቋል ብሏል። በቀጣዩ ሚያዚያ ወር ሰብል ከመሰብሰቡ በፊት በሀገሪቱ የአንበጣ ወረርሸኑ ሊቆም እንደማይችል ተገምቷል።
[አል-ዓይን]

አውስትራሊያ ከቻይና ተመላሽ ዜጎቿን ራቅ ወዳለች ደሴት ማጓጓዝ ጀመረች። ከቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተነሱት የአውስትራሊያ ዜጎች የስደተኞች ማቆያ ቦታ ተደርጋ ወደምትታወቀው ክርሲማስ ደሴት እየተጓጓዙ ነው።
ደሴቷ ከአውስትራሊያ በ2700 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ደሴቷ ጥገኝነት የጠየቁ ስደተኞች ለማቆያ ስፍራነት አገልግሎት ስትሰጥ ነበር።
በአሁኑ ወቅት 4 የሴሪላንካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ብቻ ናቸው በደሴቷ ላይ እየኖሩ የሚገኙት። ከቻይና እየተጓጓዙ ያሉት አውስትራሊያውያን ለሁለት ሳምንት በደሴቷ ላይ ይቆያሉ። 89 ታዳጊዎችን ጨምሮ ዛሬ ጠዋት 243 ዜጎች እና የአውስትራሊያ ቋሚ ነዋሪዎች ወደ ደሴቷ ለመጓዝ አውሮፕላን መሳፈራቸውን የአውስትራሊያ መንግሥት አስታውቋል።
ከ600 በላይ የአውስትራሊያ ዜጎች ቫይረሱ በተከሰተበት ሁቤይ ግዛት ውስጥ ይኖራሉ። የተቀሩ ዜጎችን ለማጓጓዝ ተጨማሪ በረራዎች እንደሚዘጋጁ መንግሥት አስታውቋል። የህክምና መስጫ ስፋራዎች ቀደም ብለው በክሪስማስ ደሴት ላይ ተዘጋጅተዋል።
የአውስትራሊያ መንግሥት ስደተኞች ለማቆያ በሚጠቀምበት ደሴት ላይ ዜጎቹን ለይቶ ለማቆየት መወሰኑ ከበርካቶች ትችት ተሰንዝሮበታል። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥት በደሴቱ ላይ ያዘጋጀው የህክምና መስጫ ስፍራዎች ደረጃ ዝቅ ያለ ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው።
መንግሥት ግን 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ማስማራቱን እና ከዚህ ቀደም እያንዳንዱ ከቻይና የሚጓጓዝ ዜጋ ወይም ቋሚ ነዋሪ እንዲከፍል ተጠይቆ የነበረው 1ሺህ የአውስትራሊያ ዶላር እንዲቀር ተወስኗል ብሏል። 24 ዶክተሮችን እና ነርሶችን ወደ ደሴቷ መሰማራታቸውን መንግሥት አስታውቋል።

#UPDATE በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 305 ደርሷል። 14,559 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተሰምቷል። #nCoV @tikvahethiopia @tikvahethiopia
#UPDATE
- የሟቾች ቁጥር 369 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 17,408 ደርሰዋል
በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 369 መድረሱ ተሰምቷል። ውድ ቤተሰቦቻችን ትላንት በሰጠናችሁ መረጃ የሟቾች ቁጥር 305 እንደነበር ታስታውሳላችሁ፤ በአንድ ቀን 64 ሰዎች ህይወታቸው አልፎ አጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 369 ደርሷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
- የሟቾች ቁጥር 369 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 17,408 ደርሰዋል
በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 369 መድረሱ ተሰምቷል። ውድ ቤተሰቦቻችን ትላንት በሰጠናችሁ መረጃ የሟቾች ቁጥር 305 እንደነበር ታስታውሳላችሁ፤ በአንድ ቀን 64 ሰዎች ህይወታቸው አልፎ አጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 369 ደርሷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በወደ ቻይና በረራ እንዲቆ ዛሬም የተጠየቀ ነው...
በሻንዶንግ ሃይዌይ የሚባል የቻይኖች ድርጅት እንደሚሰራ የገለፀልን የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የድርጅታቸው HO የሚገኘው ሻንዶንግ ከዉሃን 9 ሰአት በረራ ያህል ርቆ ቢሆንም - ድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ወደሀገራቸው መመለስ የነበረባቸው የቻይና ዜጎች እንኳን አገራችን አንሄድም ብለው እዚሁ ተቀምጠዋል ሲል ገልጾልናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ አልሰርዝም ማለቱ እና ዉሃን ያሉ ተማሪዎችንንም ሆነ ሌሎችን አልማስወጣቱ እጅግ እንዳሳዘነውና መንግስት የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብሏል።
መንግስት የህላፊነት ስሜት ይሰማው፤ ከህዝቡ ጤንነት ይልቅ ለቻይና አጋርነት እና ታማኝነት ለማሳየት የሚደረግ ጥረት ፍፁም ተገቢ አይደለም፤ ዜጎቻችን ሳይውል ሳያድር በአስቸኳይ ወደሀገራቸው ይመለሱ ሲልም ጥሪ አቅርቧል። ይህ ፖለቲካ አይደለም ጉዳዩ የህልውና ጉዳይ ነውና ሁሉም ድምፁን ሊያሰማ እንደሚገባም ጠቁሟል። #StopFlyingToChina

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ፦
[ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም]
የዓለም ጤና ድርጅት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ ከታሕሳስ 21, 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በቻይና ዉሃን (Wuhan) ግዛት የተከሰተ መሆኑን አሳውቋል፡፡ በድርጅቱ ሪፖርት መሰረት ይህ በሽታ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 24, 2012 ድረስ ከ 23 ሀገራት በጠቅላላ 14, 557 ታካሚዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን ከቻይና ውጪ ያሉ አገራት 146 በቫይረሱ የተጠቁ ታካሚዎችን ሪፖርት አድርገዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ታይላንድ፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ፣ አውስትራሊያ፣ ሲንጋፖር፣ ፈረንሳይ፣ ኔፓል፣ ካናዳ፣ ማሌዥያ፣ ቬትናም፣ ካምቦዲያ፣ ፊሊፒንስ፣ ሲሪላንካ፣ ፊንላንድ፣ ህንድ፣ ጀርመን እና ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ ይገኙበታል፡፡
ሌሎች የመረጃ ምንጮች (የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮኖና ቫይረስ ኬዞች) እስከ ጥር 25 ድረስ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 17,373 ሰዎች የደረሰ ሲሆን 362 ታካሚዎች ህይወታቸው ማለፉን ዘግበዋል፡፡
◾️የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስትር እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለኖቬል ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
More https://telegra.ph/MoH-02-03

ከጤና ሚኒስቴር መግለጫ የተወሰደ፦
"በአሁኑ ወቅት አራት ሰዎች በበሽታው ተጠርጥረው፤ አንድ ቻይናዊ እንዲሁም ሶስት ኢትዮጵያዋን፤ አንድ በአክሱም እና ሶስቱ በቦሌ ጨፌ በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን ናሙናቸው ተወስዶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡"

#LteAdvanced
ኢትዮ ቴሌኮም የLte advance 4G አገልግሎት በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል። የ4G ኔትወርክ አገልግሎት ማብሰሪያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ፍሬህይወት በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ እንዳሉት በጣም ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ልታገኙ ስለሆነ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
የዚህ ኔትወርክ ማስፋፊያ ግንባታ የቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ የተከናወነ ሲሆን ይህ ግንባታ 170 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ ተገልጿል። ወይዘሪት ፍሬህይወት እንደገለጹት የደንበኞች እየጨመረ ያለ ፍላጎት ለዚህ እንዳበቃቸው ገልጸው በቀጣይ ከፍተኛ የኢንተርኔት ፍላጎት ያላቸውን የኢትዮጵያ ከተሞች በጥናት እየለየን Lte Advance 4G ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል።
ይሄ የኔትወርክ ማስፋፊያ ያለምንም ዕዳ በመንግስት ወጪ የተገነባ ሲሆን አገልግሎቱ ከዛሬ በመላ አዲስ አበባ አገልግሎት ይጀምራል። ይህ የ4G Lte አገልግሎት በ 50 የተመረጡ የመዲናዋ ቦታዎች ላይ የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ከዚህ በኋላ አገልግሎት የሚሰጠውም የኢንተርኔት ፍላጎት ከፍተኛ በሆኑባቸው አካባቢዎች ብቻ ነው ተብሏል። አዲሱ አገልግሎት በአንዳንድ አፕሊኬሽኖች ላይ፣ advanced Lte ከ4G አራት ዕጥፍ ከ 3G ደግሞ 14 ዕጥፍ እንደሚፈጥን ወይዘሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል።
[ETHIO FM 107.8]