TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HARAR

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዛሬው ዕለት "ሂላል" በሚል ስያሜ የሸርዓ መርህን መሠረት በማድረግ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ በሐረር ከተማ ከፍቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በሐረር ከተማ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን ከፍቶ ሥራ መጀመሩን አስታውሰው፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ የሸርዓ መርህን መሠረት አድርጎ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ መክፈቱን ገልፀዋል፡፡

(CBE)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ኡቡንቱ - 'እኔ ነኝ ምክንያቱም እኛ ነን'

ቲክቫህ ቤተሰቦች - አርባ ምንጭ❤️

ኡቡንቱ - እኛ አንድ ሰብዓዊ ቤተሰብ መሆናችን ላይ የተመሠረተ የአፍሪካ ጥንታዊ ፍልስፍና ነው። እኛ ወንድምና እህት ነን። እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን፡፡ አንድ ሰው የሚበላው ሲያጣ ሁሉም ሰዎች በዚህ ረሃብ ይሰቃያሉ። አንዱ ሲበደል ሁላችንም ህመሙን ይሰማናል፡፡ አንድ ልጅ በሚሰቃይበት ጊዜ እንባዎች በሁሉም ሰው ጉንጮዎች ላይ ይፈስሳሉ፡፡ የእኛን ተቀዳሚ ሰብአዊነት በመገንዘብ፣ እኛን አንድ የሚያደርግ ጠንካራ ትስስር፣ የሰው ልጆችን በሙሉ የሚያስተሳስር የማይጠፋ ቦንድ ነው።

#Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ #Day2

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ጋሞዞን #ፒስሞዴል

(AFRIKHPRI FOUNDATION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day2 #Ubuntu #ኡቡንቱ #አርባምንጭ

በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከናወነ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል፦ የሃሳቡ ደጋፊዎች፣ ተካፋዮች ፣ አስተባባሪዎች የሆኑ እጅግ የምናከብራቸው የሀገራችን ወጣቶች በተለያዩ የከተማው ክፍሎች በመዘዋወር ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ብሮሸሮችን በመበተንና ስለ ዓላማው በማስረዳት ስራቸውን ሲሰሩ ውለዋል። ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና ለአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልዩ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

ነገ የ3ኛው ቀን ስራ ይቀጥላል!

ሃሳብ፣ መልዕክት የላችሁ፣ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ ልታግዙን የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት ካላችሁ እነዚህ አድራሻዎች ተጠቀሙ፦ @tikvahethiopiaBot @tsegabwolde 0919743630

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል
"የትራፊክ አደጋ እየገደለን ነው፣ ቀስ ብለን እናሽከርክር፣ #እንደርሳለን"
“ወጣቶች ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚያበረክቱትን ግንባር ቀደም ሚና አጠናክረው መቀጥል ይገባቸዋል” - ዶክተር ዳንኤል በቀለ

ወጣቶች ራሳቸውን ከአፍራሽ ድርጊቶች በመቆጠብ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ያላቸውን ሚና አስጠብቀው መቀጠል እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገለጹ፡፡

በመጪው ማክሰኞ ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም በዓለም ለ71ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀን አስመልክቶ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወጣቶች በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ታሪካዊ ሽግግሮች ውስት ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

የበዓሉ ዋነኛ ዓላማም ከህበረተሰቡና እርስ በእርስ እንዲወያዩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የወጣቶችን አዎንታዊ ሚና ለማጎልበት መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ “አሁንም ወጣቶች ራሳቸውን ከአፍራሽ ድርጊቶች በመቆጠብ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ያላቸውን ሚና አስጠብቀው መቀጠል ይገባቸዋል” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Audio
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ “ከመቼውም ጊዜ በላይ የተወሳሰበ ነው” ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አጠቃላይ የሃገራዊ ንግግር መድረክ እንዲጠራ ጠይቋል። ግንባሩ ህዳር 16/2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ “ችግሩን ይበልጥ በማስፋፋት ወደ ህዝቦች ግጭት ለመቀየር ሲሞክር እየታየ ነው” ብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዘንድሮው የ2019 CNN HEROES ውስጥ የተካተተችው ፍሬወይኒ መብርሃቱን የተመለከተውን ተከታዩን የCNN AFRICA ዘገባ ተመልከቱት!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
100 MOST INFLUENTIAL AFRICANS...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በኒው አፍሪካን መጋዚን ከ100 አፍሪካውያን ተፅእኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

(የኢትዮጵያአየርመንገድ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ዩኒቨርሲቲዎች የሥርዓተ አልበኞች መፈንጫ አይሁኑ!
.
.
.
...ዩኒቨርሲቲዎችን የግጭት የስበት ማዕከል በማድረግ አገሪቱን ቀውስ ውስጥ ለመክተት የሚደረገው አደገኛ እንቅስቃሴ በፍጥነት ካልተገታ፣ አንፃራዊ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር በፍፁም አይቻልም፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሒደቱ በሰላማዊ መንገድ መከናወን አቅቶት የተማሪዎች፣ የመምህራንና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ሕይወት ለአደጋ ተጋልጧል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ የሚፈጸሙ ጥቃቶችም ሆኑ የሚቀሰቀሱ ግጭቶች በእነ ማን እንደሚከናወኑ የማይታወቅ ይመስል፣ ሀቁን ፍርጥርጥ ለማድረግ ለምን እንደማይፈለግ ያስገርማል፡፡ ‹ፀረ ሰላም ኃይሎች› የሚባሉት እነ ማን ናቸው ቢባል መልሱ የዩኒቨርሲቲዎች ማኅበረሰቦች በሚገባ ያውቋቸዋል ነው፡፡

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማሩ ሒደት የማይመለከታቸው ሲገኙ ለምን ዝም ይባላል? ማንንም ሳይፈሩ የሚያስፈራሩና ጥቃት የሚፈጽሙ በግልጽ እየታዩ ዝም የሚባለው እስከ መቼ ነው? ዩኒቨርሲቲዎች የሥርዓተ አልበኞች መፈንጪያ እየሆኑ በዝምታ ማለፍ ተባባሪ ከመሆን አይተናነስም፡፡

More👇
https://telegra.ph/REPORTER-12-05

(ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ይዞት ከወጣው ርዕሰ አንቀፅ የተወሰደ ፅሁፍ))

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአሲምባ ፍቅር ፊልም!

በእውነተኛ የህይወት ታሪክ እና ገጠመኞሽ ላይ ተመርኩዞ በደራሲ ካሕሳይ አብረሃ የተፃፈው "የአሲምብም ፍቅር" መፅሃፍ ወደፊልም ስራ ለመቀየር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተሰምቷል። መፅሃፉ በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ባለው ኢሕአፓ ወታደራዊ ክንፍ ኢሕአሠ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሰሆን ደራሲው በአሲምባ ተራራ ላይ በነበረው ቆይታ የገጠመውን የጦርነት እና የፍቅር ታሪኩን አጣምሮ የፃፈበት ነው። "የአሲምባ ፍቅር" ፊልም የሚሰራው ታሪኩ በተከናወነበት ቦታና እቅድ ሲሆን ከ500 በላይ ተዋንያንም ይሳተፉበታል ተብሏል። እስካሁን ባለው ሁኔታ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚጠይቅ ለማወቅ ተችሏል። ከዚሁ ፊልም ጋር በተያያዘ ባለፈው ሳምንት በግራድ ኤሊያና ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአሲምባ ፍቅር ፊልም ስራ...

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ!

ከሶስት ሺህ በላይ ተማሪዎች የተመዘገቡበት የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት የፊታቸን ቅዳሜ በይፋ እንደሚጀመር ዩንቨርሲቲው አስታወቀ። ዩንቨርሲቲው ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳስታወቀዉ ለጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት 3 ሺህ 200 ተማሪዎች በፍቃደኝነት ተመዝገበዋል ብሏል፡፡

የዩንቨረሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሥራት አፀደወይን እንዳስታወቁት ፕሮጀክቱ በመጪዉ ቅዳሜ በይፋ ይጀመራል፡፡ አዲስ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸዉ እና ከአካባቢያቸዉ ተለይተዉ ዩንቨርሲቲን ሲቀላቀሉ የቤተሰብነት ስሜት እንዲሰማቸዉ በሚል የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት እንደተቀረፀ ፕሬዝዳንቱ የተናገሩ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት የተማሪዎቹን የዩንቨርሲቲ ቆይታ የተሳካና እና ከግጭት የፀዳ እንዲሆን ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረዉም ታምኖበታል፡፡ በተለይም ደግሞ አሁን ላይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚታየዉን አለመረጋጋት ለማስቀረት የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት ይረዳል ብለዋል፡፡

የጎንደር ቤተሰብ ፕሮጀክት አንድ ተማሪ በራሱ ምርጫ መሰረት በጎንደር ከተማ ለሚኖሩ ወላጆች የሚሰጥ ሲሆን ይህም ተማሪው የቤተሰብነት ስሜት እንዲኖረዉ ለማስቻል ነዉ ተብሏል፡፡ ተማሪዎቹ በተለይም የኢኮኖሚም ሆነ ሌሎች ችግሮች ሲገጥሟቸዉ ከነዚህ ወላጆች ጋር ተማክረዉ ችግሮቻቸዉን እንዲፈቱ እና በበዓላት ወቅትም በጋራ እንዲያሳልፉ የሚያደርግ እንደሆነ ታዉቋል፡፡

(ETHIO FM 107.8)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ኮሚሽን ጋር በሠላምና ፀጥታ ሪፎርም ትግበራ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት አካሄደ። ለሁለት ቀናት በተካሄደው አውደ ጥናት ላይ ከሠራዊቱ የተወጣጡ ጄኔራል መኮንኖችና ሌሎች መኮንኖች መካፈላቸውን ከመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia