TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"በርከት ያለ አመራር የህወሓት ተላላኪ ነበርኩኝ ይላል ፤ እኛ ተላላኪ መሆናቸው ያወቅነው ሲናገሩ ነው። ለ27 ዓመታት የህወሓት ተላላኪ ነበርን ካሉ አሁንስ ተላላኪ አለመሆናቸው በምን እናረጋግጣለን? አብሮ ወስኖ አብሮ ሰርቶ በነጋታው ተላላኪ ነኝ ሲል በጣም ያሳፍራል እኔ በግሌ በጣም ይገርመኛል። ከደሙ ንፁህ ነኝ ለማለትና ሃላፊነት መውሰድ የማይወዱ ደካሞች ስለሆኑ ነው። " ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል (በመቐለ እየተካሄደ ባለው የፌዴራሊስት ኃይሎች መድረክ ላይ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#OFC #OLF

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በመቐለ ከተማ ፌደራል ስርዓቱንና ህገ-መንግሥቱን መጠበቅ በሚል በተካሄደው የውይይት መድረክ ጥቂት የማይባሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጥሪውን ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ከእነዚህ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ነው፡፡ የፓርቲው የወጣቶች ዘርፍ ተጠሪ አቶ አዲሱ ቡላላ ህውሐት ከዚህ በፊት የፌደራል ስርዓቱን በስርዓት ሲመራ ስላልነበር ዛሬ የፌደራል ስርዓቱ ተቆርቋሪ ነኝ ማለቱ የሚታመን አይደለም ይላሉ፡፡

በተመሳሳይ ጥሪውን ውድቅ ያደረገው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ነው፡፡ የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ደግሞ ከዚህ በፊት እኛን ሲያሳድድ ከነበረ ሃይል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን አይችልም ብለው ከመድረኩ ቀርተዋል፡፡ በትግራይ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ጥሪው ስላልተደረገላቸው ቀርተዋል ተብሏል፡፡

በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የአረና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ጥሪ እንዳልተደረገላቸው ለቢቢሲ ሬድዮ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ከትግራይ ክልል የተገኙት ሁለት ፓርቲዎች ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡ ህውሐት የፌደራል ስርዓቱና የህገ-መንግሥቱ ጠባቂ ነኝ የሚለው ሌሎች ላይ ጫና ለማሳደር እንደሆነም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

(AHADURADIO)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TANA #ABAY #GERD #ETHIOPIA

በዚህ ዓመት እምቦጭ ከጣና አልፎ አባይ ወንዝ ዳርቻዎች በሚገኝ 200 ሄክታር መሬት ላይ መንሰራፋቱ ተገልጿል። ባለፈው ዓመት በ34 ሄክታር መሬት ላይ የተከሰተው የአባይ እምቦጭ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 166 ሄክታር ጨምሮ ወደ 200 ሄክታር መስፋፋቱ ነው የተነገረው።

(በኩር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Day3 #አርባምንጭ #ኡቡንቱ

ዛሬ በአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"


ለሁሉም አካላት ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን!

#TIKVAH_FAMILY

#ፒስሞዴል #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ጋሞዞን #አርባምንጭፖሊቴክኒክኮሌጅ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Day3 በደም ልገሳ❤️

ዛሬ በአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃግብር ላይ የኡቡንቱ አስተባባሪዎች፣ ሃሳብ አመንጪዎች፣ አዘጋጆች የሆኑ የምናከብራቸው በጎፈቃደኛ የሀገራችን ወጣቶች በደም ልገሳ መርኃግብር ላይ በመሳተፍ ደም ለግሰዋል፡፡

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

ዛሬ ማለዳ የላዳ ታክሲ በመንገድ ፅዳት ላይ የነበረች የ40 ዓመት ሴት ገጭቶ መግደሉ ተሰማ። አደጋው የደረሰው በቦሌ ክፍለ ከተማ ደሳለኝ ሆቴል አካባቢ ማለዳ 12 ሰዓት አካባቢ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተሰምቷል፡፡ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የሚዲያ ዘርፍ ሀላፊው ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እንደተናገሩት በመንገድ ፅዳት ላይ እያለች በላዳ ታክሲ ተገጭታ ሕይወቷ ያለፈው ሴት የሁለት ልጆች እናት ናት ብለዋል፡፡ የላዳ ታክሲው አሽከርካሪ የመኪናው የኋላ መስታወት ተሰብሮ እንደወጣና በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“ሁሉም ሰው ለሰላም ዘብ መቆም አለበት” በሚል መሪ ቃል የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት እያካሄዱ ነው!

የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች ማህበር “ሁሉም ሰው ለሰላም ዘብ መቆም አለበት” በሚል መሪ ቃል ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በሰላም ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

የዚህ መድረክ ዋነኛ ዓላማ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም ሁሉም ዜጋ ሰላሙ የእኔ ነው የሚል ስሜት እንዲያድረበት ማድረግ እንደሆነ የሀገር ሽማግሌዎች ማህበር ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል፡፡

በመድረኩም ላይ የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን ያከናወኗቸውን ተግባራት የሚቀርቡበትና ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል። ከዚህም ባሻገር መድረኩ በማህበሩ የወደፊት ዕቅድ ላይም ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡

(EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EthioTelecom #EliasMeseret

ዛሬ ለበርካታ ደቂቃዎች ኢንተርኔት የተቋረጠበትን ምክንያት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለAssociated Press ጋዜጠኛው ኤልያስ መሰረት ተናግረዋል፦

"በመጀመርያ ለኢንተርኔት መቋረጡ ይቅርታ እንጠይቃለን። እኛ ሁል ግዜ የኔትወርክ ለውጥ የምናደርገው ብዙ ሰው ኢንተርኔት በማይጠቀምበት ሰአት ለሊት ላይ ነው። ዛሬ ላይ የተከሰተው የኢንተርኔት መቋረጥ ግን በእኛ ቁጥጥር ስር የነበረ አይደለም፣ አቅደነውም የነበረ አይደለም። በፋይናንስ ተቋሞቻችን ላይ ሊደርስ የነበረ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል INSA ኔትወርኩን ለማቋረጥ ተገድዶ ነበር። እኛም መቋረጡን ለደንበኞቻችን ለመንገር ግዜ አልነበረንም፣ ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አልነበረም። ለጥቂት ደቂቃ በማቋረጥ ጥቃቱን ለመከላከል ይቻላል ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነው። ከ INSA ጋር እየተነጋገርን ነው የምንሰራው። ዛሬ ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ችግር አጋጥሟቸው የነበረ ይመስለኛል። አሁን ጉዳዩ ላይ እየተነጋገርን ነው።"

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
የአፋር ከልል የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ!

የአፋር ከልል የመንግስት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እንዲያሳውቁና እንዲያስመዘግቡ  የፌዴራል ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን አሳሰበ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አያሌው ሙሉአለም የመንግስት ባለስልጣናት የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነትን የማረጋግጥ ግዴታ እንዳለባቸው በአዋጅ መደንገጉን ገልጸው፤ አትዮጵያ ከራሷ አዋጅ ባሻገር ዘርፉን የሚመለከቱ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችን ጭምር መፈረሟን ተናግረዋል። በመሆኑም በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናት ለሚመሩት ህዝብ ያላቸውን ታማኝነትና የአሰራር ግልጸኝነት ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰራበት ያለውን የሃብት ማሳወቂያ ምዝገባ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መንግሥት ምን እያደረገ ነው?

ብዙኃኑ ተማሪዎች በጥቂት ሥርዓተ አልበኞች ሲሰቃዩ፣ የመማር ማስተማሩ ሒደት ሲቃወስና ሕግ የማስከበር ተግባር ሲንቀረፈፍ ምንድነው የሚባለው? በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በአገር ሽማግሌዎች ጥረት ትምህርት ለማስጀመር ጥረት የተደረገ መሆኑ ሲሰማ፣ መንግሥት ምን እያደረገ ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

ተማሪዎች ከዕኩለ ሌሊት በኋላ በመኝታ ቤቶች አካባቢ ለምን ይዘዋወራሉ? የሌሎችን የፖለቲካ አጀንዳ የተሸከሙ በግላጭ ወጥተው ትምህርት ለምን ያስቆማሉ? ከዩኒቨርሲቲዎች ጥበቃ በላይ የሆኑ አደገኛ ድርጊቶች ከመከሰታቸው በፊት፣ የፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት እንዲደርሱ ለምን አይደረግም? ሥጋት የገባቸው ተማሪዎች የድረሱልን ጥሪ ሲያሰሙ ለምን ዝም ይባላል? በአንዳንድ አካባቢዎች የተደራጁ ኃይሎች ከውጭ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ሲታገሉ በግላጭ እየታየ ሕጉ የታለ? ሕግ አስከባሪውስ? ዩኒቨርሲቲዎችን በጊዜያዊ ሽምግልናና በማለባበስ ዕርቅ ወደ መደበኛ ተግባራቸው መመለስ አይቻልም፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተልዕኮ ተቀብለው የመሸጉ ኃይሎች ዋና ፍላጎት የብሔርና የእምነት ግጭት በመቀስቀስ አገሪቱን ትርምስ ውስጥ መክተት ነው፡፡ ይህንን እኩይ ዓላማ በመረዳት አስፈላጊውን ዕርምጃ መውሰድ ካልተቻለ፣ ለፀፀት የሚዳርግ አደገኛ ሁኔታ እንደሚፈጠር መጠራጠረ አይገባም፡፡ መሬት ላይ ያለው ዕውነት ይህንን ነው የሚያሳየው፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#AddisAbeba #Lyon

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#INSA

የዛሬው የኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት...

በሀገሪቱ የፋይናስ ተቋሞች ላይ ሊደርስ የነበረ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል በዛሬው ዕለት INSA ኔትዎርክ ለማቋረጥ ተገድዶ እንደነበረ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃኒ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገለፁ። ዛሬ የተከሰተው የኢንተርኔት መቋረጥ በኢትዮ ቴሌኮም ቁጥጥር ስር የነበረ እንዳልሆነና፤ ታቅዶም እንዳልነበር አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጥ አልነበረም፤እኛም መቋረጡን ለደንበኞቻችን ለመንገር ግዜ አልነበረንም፣ ለጥቂት ደቂቃ በማቋረጥ ጥቃቱን ለመከላከል ይቻላል ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነበር ብለዋል።

ከINSA ጋር እየተነጋገርን ነው የምንሰራው ያሉት ወ/ሪት ፍሬህይወት በዛሬው ዕለት ግን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ችግር አጋጥሟቸው የነበር ይመስለኛል፤ አሁን በጉዳዩ ላይ እየተነጋገርን ነው ብለዋል። ለኢንተርኔት መቋረጡ ይቅርታ ጠይቀዋል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot