TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በእንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ከነገ ዓርብ 12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከAAU ቲክቫህ ቤተሰቦች...

"አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ (AAU 6 ኪሎ) ተማሪዎችን ሰብስበው ካናገሩን በኃላ ሁሉም ነገር ተረጋግቶ ወደ ዶርም ተመልሰናል። የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከዛ ውጪ እንደሚባለው #የተጋነነ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም። ፕሬዝዳንቱም የሚያረጋጋ ንግግር አድርገዋል። ለተፈጠረውም ነገር ተማሪዎችን ይቅርታ ጠይቀዋል። በአሁን ሰዓት ተዘግተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው በሮች በሙሉት ተክፍተዋል። L(Tikvah Family-AAU)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ውብ ምስል ከሸገር ደርቢ . . .

ከሸገር ደርቢ በፊት ሁለቱ የሜዳ ላይ ተፎካካሪዎች ደጋፊዎቻቸው በአንድነት ከጨዋታው በፊት አንድ መሆናቸውን በስታዲየም ዙሪያ እየተጨዋወቱ የሚያሳይ ምስል!

TIKVAH FAMILY ( LEO )

በስታዲየም መግባት ላልቻላችሁ እንዲሁም በስራ ጫና በቴሌቪዥን መከታተል ያልቻላችሁ ቤተሰቦቻችን ጨዋታውን በፅሁፍ ከቲክቫህ ስፖርት መከታተል ትችላላችሁ👇
@tikvahethsport https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
በአዳማ ከተማ ተከስቶ የነበረው ግጭት ባስከተለው ጉዳት የተጠረጠሩ 179 ግለሰቦች ለህግ ቀረቡ!

በአዳማ ከተማ ሰሞኑን በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም የተጠረጠሩ 179 ግለሰቦች ለህግ መቅረባቸውን የከተማዋ አስተዳደርና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሁባድ ጂና እንደገለጹት ለህግ የቀረቡት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ሰላማዊውን የወጣቶችን ተቃውሞ በመጠምዘዝ ወደ ግጭት እንዲያመራ ምክንያት የሆኑ ናቸው ብለዋል።

ጉዳዩን በማስተባበር፣በመምራትና በመሳተፍ ለሰው ህይውት መጥፋትና በንብረት ማውድም የተጠረጠሩ 179 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ተናግረዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-21-2

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል!

ውጤቱ የሲዳማ ዞንን ወደ ክልልነት የሚመራ ከሆነ ከዚህ በኋላ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደሕዴን) ጋር ግንኙነት አይኖረንም ብለዋል፡፡

- የአዲሱ የብልፅግና ፓርቲ አባል እንሆናለን፣ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱንም በክልላችን እንከፍታለን ብለዋል፡፡

- በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የጣቢያው ውጤቶች ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ተለጥፈዋል፡፡

- ዛሬ እና ነገ አጠቃላይ ጊዜያዊ ውጤቱ ይደርሳል ተብሏል፡፡

- ምርጫ ቦርድ በ7 ቀናት ውስጥ አጠቃላይ ውጤቱን አሳውቃለሁ ብሏል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekdelaAmbaUniversity

ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በስጋት ምክንያት ከግቢ የወጡ ተማሪዎች እስከ ህዳር 15/2012 ዓ/ም ድረስ ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰው ትምህርታቸው እንዲከታተሉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቀረበ። በተጠቀሰው ቀን ለማይመጡ ተማሪዎች ኃላፊነቱን አለወስድም ሲል ዩኒቨርስቲው ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የዩኒቨርሲቲው ሁለቱም ካምፓሶች በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፤ መደበኛው የመማር ማስተማር ስራም እየተከናወነ ይገኛል ብሏል ተቋሙ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቡጁምቡራ ውስጥ ካረፈ በኋላ በሽብር ድርጊት የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የቡሩንዲ ባለስልጣናት አረጋገጡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን አንድ ተሳፋሪ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት በሰነዘረው ማስፈራሪያ አውሮፕላኑ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ወደሚያርፉበት የቡጁምቡራ አየር ማረፊያ እንዲቆም መደረጉም ተነግሯል። አውሮፕላኑ ዛሬ በቀጥታ በረራ ከአዲስ አበባ ወደ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ እየበረረ ሳለ ነበር ችግሩ የተከሰተው ተብሏል።

More👇
https://telegra.ph/BBC-11-21

(BBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
70 ክላሽንኮቭን ጨምሮ ሌሎች የጦር መሳሪያዎች በቡኖ በደሌ ዞን በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ በተለምዶ ቦቴ ተብሎ በሚጠራው የፈሳሽ ጭነት ተሽከርካሪ ውስጥ በድብቅ ተጭነው በመጓጓዝ ላይ እያሉ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። በተደረገው ፍተሻም 70 ክላሽንኮቭን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ቶሎሳ ሙሉጌታ መናገራቸውን ኦ.ቢ.ኤን ዘግቧል።

(OBN)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰበር ዜና!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመራለትን የፓርቲውን ውህድ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

(EBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት ተከባበረው፣ ተዋደውና ተደጋግፈው የኖሩ ህዝቦች ናቸው" - የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች

የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚጥሩ ሃይሎች ምክንያት የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ጠብና ጥላቻ ውስጥ እንደማይገቡ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ-ገዳዎችና የአገር ሽማግሌዎች ገለጹ። የአማራና ኦሮሚያ ክልሎችን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም የምክክር መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በሰላም ውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት የሃይማኖት አባቶች፣ አባ-ገዳዎችና የአገር ሽማግሌዎች የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት ተከባበረው፣ ተዋደውና ተደጋግፈው የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይሁንና በአንዳንድ የፖለቲካ ትርፍ ፈላጊዎችና በማህበራዊ የትስስር ገጾች ሳቢያ በመካከላቸው “ቁርሾ እንዳለ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ከወሬ የዘለለ አይደለም” ብለዋል። በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች መነሻን በማወቅ ችግሩን ከምንጩ መፍታት ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

ቤተክርስቲያንና መስጊድ ማቃጠል ከየትኛውም የሃይማኖት አስተምህሮ ውጪ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ፤  እንዲህ አይነት እኩይ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች የትኛውንም ብሄርና ሃይማኖት የማይወክሉ በመሆናቸው ሊወገዙ እንደሚገባም አሳስበዋል። በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር የማድረግ ሃላፊነትም የእነርሱ ቢሆንም ተሳታፊዎቹ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ አለመወጣታቸውን ተናግረዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአማራና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ምን መከሩ?

"እንዴት ነው የነበረን ድርሻ የጥላቻ ንግግር፣ የጥላቻ ፅሁፍ በቪድዮም በፅሁፍም የሚደረገው ነገር ቆሞ፤ ወደ አንድነት እና ወደ መቀራረብ ወደ ሰላም የሚያመጣ ፅሁፎች እየፃፍን ያለውን ውጥረት ማርገብ አለብን በሚለው ላይ ተስማምተን ነው 10 ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ ያወጣነው" አቶ ሃምዛ ቦረና (አስተባባሪ)

(BBC RADIO)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉም በሀገር ነው!

ጥሩ ልብስ ለብሰን...አምሮብን ተውበን የምንታየው፤
ሰዎች እንረዳ ቢገባን ትርጉሙ...ሁሉም በሀገር ነው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ሂደት ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደተከናወነ ይታወቃል፡፡ በድምጽ መስጫው ቀን ማምሻ ላይ ቆጠራው ተጠናቆ የህዝበ ውሳኔው ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

በትላንትናው እለት የሁሉም ምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ተጠናቀው ወደ15ቱም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች የገቡ ሲሆን በዛሬው እለት የዞን ማስተባበሪያ ጣቢያ ላይ ውጤቱን የማጠቃለል ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ ውጤት የሚያሳውቀው ነገ ቅዳሜ ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትእግስት እንዲጠብቁ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ!

በትላንትናው ዕለት በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የጽዳት ዘመቻ ለሰላም እና አብሮነት በሚል መሪ- ቃል ተካሂዷል፡፡ የጽዳት ዘመቻው በዩኒቨርርሲቲው ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች መካከል ያለውን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴት ለማዳበር ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የአስተዳደር ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የጸጥታ አካላት እና ተማሪዎች ተሳተፈዋል፡፡ ከጽዳት ዘመቻው በኋላም ተማሪዎችን የሚያዝናኑ ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች በዋልያ የባህልና የኪነ-ጥበብ ቡድን ቀርበው ነበር።

(ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቤጉህዴፓ አስቸኳይ የመሸጋገሪያ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) ወደ ሀገራዊ ብልጽግና ፓርቲ የሚያደርገውን ውህደት ለማስፈጸም አስቸኳይ የሽግግር ጉባኤውን ሊያካድ ነው፡፡

የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሀቅ አብዱልቃድር እንዳስታወቁት ኢህአዴግ ወደ  ውህድ ፓርቲ ለመሸጋር መወሰኑን ተከትሎ ቤጉህዴፓ በመጪው ሕዳር 15 እና16 ቀን 2012 ዓ.ም አስቸኳይ የሽግግር ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡

ወደሀገራዊ ፓርቲ የሚደረገውን ውህደት ለማስፈጸም ለሚካሄደው የሽግግር ጉባኤ ከወዲሁ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

(ENA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በድርጊቱ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው!

በባህርዳርና አዲስ አበባ ከአማራ ክልል አመራሮችና ከእነ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው። የጀነራል ሰዓረ ጥበቃ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡን ጨምሮ 13ቱም ተከሳሾች ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እየተነበበላቸው ነው።

ተጠርጣሪ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍንት ችሎቱ የሚጠይቀውን ምላሽ መስጠት እንዳልቻለና “እሺ” እና “አዎ” የሚሉ ምላሾችን ብቻ እንደሚሰጥ ኢቢሲ ከችሎቱ ቦታ ዘግቧል።ችሎቱ “መናገር ካልቻልክ ሀሳብህን በፅሁፍ ግለፅ” ቢለውም ተከሳሹ ይህንንም አለመቻሉ ተመልክቷል።

ከሰኔ 15ቱ ወንጀል ጋር በተያያዘ ባህርዳር ላይ የአማራ ክልል አመራሮች አቶ አምባቸው መኮንን፣ አቶ ምግባሩ ከበደና አቶ እዘዝ ዋሴ ሲገደሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ መገደላቸው ይታወሳል።

ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ከተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ይገኙበታል። ዓቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ " ህገ መንግስትን በኃይል ለመናድ" በሚል ነው ክሱ የመሰረተባቸው።

(EBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
ህወሓት የአዲሱ ፓርቲ ውህደት አባል አልሆንም...

ኢህአዴግ ባለፈው ቅድሜ ሕዳር 6/ 2012 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ የፓርቲው የውህደት ሃሳብና ውሳኔ አስመልክቶ ህወሓት በስብሰባው ወቅት ያነሳቸው ጥያቄዎችና እንዲሁም ውህደቱን የተቃወመበት ምክንያት የህወሓትና የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና የህወሓት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

ኢትዮጵያ በመጪው ታህሳስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ህዋ ታመጥቃለች። ቻይና የተሰራችውና 72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ሳተላይት በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና እና በአየር ሁኔታ መረጃ ትሰጣለች። ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከቻይና ቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትወነጨፈው የኢትዮጵያ ሳተላይት ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቃ ትቀመጣለች ነው የተባለው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በሶስት ቀናት ዉስጥ 487 ጥይትና 9 የቱርክ ሽጉጥ ተያዘ!

ሰሞኑን የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ባደርጉት ፍተሻ በቀን 09/03/2012 በአዋሽ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት አለበረከቴ ኬላ በተደረገ ፍተሻ በሶላር ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር የነበረ 218 ጥይት 126 የብሬን ና 92 የክላሽ ጥይቶች ከአራት ከተጠርጣሪዎች ጋርታርጋ ቁጥር ኮድ 3-62743 ኦሮ የህዝብ መመላለሻ መኪና ዉስጥ ተይዘዋል፡፡

በተመሳሳይ በቀን 09/03/2012 ዓ.ም በሞያሌ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ሞያሌ መ /ጣቢያ ኬላ በተደረገ ፍተሻ 9 የቱርክ ሹጉጥ 96 ጥይት የህዝብ ማመላለሻ FSR ታርጋ ቁጥር ኮድ-3 47008 ኦሮ ከኮንሶ ወደ ሞያሌ ከተማ ስገባ ተይዟል፡፡

በቀን 10/03/12 አ/ም ማታ 5 ሰዓት አከባቢ በአርበረከቴ ጉ/መቆ/ጣቢያ የሰ/ቁጥር ኮድ 3 67409 ኦሮ ሚንባስ ዉስጥ 173 የክላሽ ጥይት የረዳት መቀመጫ ኩርስ ዉስጥ በድብቅ አስቀምጦት በፍተሻ ተይዛል። ባጠቃላይም 487 ጥይትና 9 የቱርክ ሽጉጥ በሶስት ቀናት ዉስጥ መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(የገቢዎች ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጠናቀቀ!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቋል፡፡ በሁለተኛ ቀን ውሎው ዛሬ የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት ከመከረ በኋላ የተገኙት አባላት በሙሉ ድምጽ ማፅደቃቸው ነው የተነገረው፡፡ በመጀመሪያ ቀን ውሎው ምክር ቤቱ የፓርቲውን ውህደትና ፓርቲው ወደ ፊት የሚመራበት ፕሮግራም ላይ በመምከር አጽድቋል፡፡

(EPRDF)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia