TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቀኑ በመስከረም 7/2012 ይስተካከል⬆️

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችና ከኢትዮጵያ እስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2012 ጠዋት ተገናኝተው ተወያይተዋል። አባላቱ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቻቸውን ለማክበር ከመስቀል በዓል በፊት በሚደረግ ጽዳት ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሦስተኛው ጣና ማህበራዊ ሚዲያ አዋርድ!

የዘንድሮው የጣና ሽልማት ወደ 21 ዘርፍ ከፍ ማለቱ ታውቋል፡፡ የሽልማቱ ዓላማ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር ለሚጠቀሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና መስጠት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በ16 ዘርፎች ነበር ሽልማት የሰጠው፡፡

ዘንድሮ ዘርፉን አስፍቶ በ21 መስኮች ሽልማት እንደሚሰጥ የዘመራ ማስታወቂያ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ እና የሽልማት ሥነ ስርዓቱ አስተባባሪ አቶ ደምስ አያሌው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ሽልማቱ ጥቅምት 1/2012 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጧል፡፡

ለተሸላሚዎች ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዓመት ለሚከናወነው የሽልማት ሥነ ስርዓት በየዘርፉ ለመጨረሻ ዙር የተመረጡት እጩዎች 68 መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በቀጣይ ዓመት መርሀ ግብሩን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር መታሰቡን አቶ ደምስ ተናግረዋል፡፡ የጣና ሽልማት በ2009 ዓ.ም ነው መሰጠት የተጀመረው፡፡

Via #AMMA

የ3ኛው የጣና ሽልማት እጩዎችን ይህን በመጫን ማየት ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/TANA-AWRD-09-18
#JIMMA_UNIVERSITY

"...ለተማሪዎች ትምህርት ሲሰጥ የቆየው በህጋዊ መንገድ መሆኑን እያረጋገጥን ይህንኑ በህግ የተሰጠውን ሥልጣን በመጋፋት ኤጀንሲውና የሥራ ኃላፊዎቹ በማድረግ ላይ ያሉት አግባብ የሌለዉ እንቅስቃሴ ህዝብና መንግስት እንዳይረጋጋ የሚያደርግ በመሆኑ በፅኑ የምናወግዘው ነው"
___________________________________

ለጅማ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ አበባ ካምፓስ ተማሪዎች በሙሉ!

ጉዳዩ፡- ተገቢነት በሌላቸው ጽሁፎችና መግለጫዎች እንዳትደናገሩ ስለማሳሰብ

ዩኒቨርሲቲያችን መንግስት የከፍተኛ ትምህርትን ለማዳረስ የሚያደርገውን ጥረት በማሳካት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ያለው መሆኑ ከሁላችሁም የተሰወረ አይደለም፡፡ የመንግስትን የትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊነት ከማረጋገጥ አኳያ ዩኒቨርሲቲያችን በተለያዩ ደረጃዎች የሚሰጠውን ትምህርት አድማስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሰፋ መምጣቱ የቁርጠኝነቱ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ይኸውም ዋና መቀመጫው ጅማ ከተማ ሆኖ በአገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎችና ከአገር ውጪም በሐርጌሳ ጭምር ካምፓሶችንና የትምህርት ማዕከሎችን ከፍቶ ትምህርቱን በማስፋፋት ላይ የሚገኘውም በዚሁ አግባብ ነው፡፡

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዩኒቨርሲቲያችን የሚያደርገውን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍና ለማስቆም የሚሞክሩ አካላት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተገንዝበናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-18-2
ጅማ ዩኒቨርሲቲ⬆️

በአዲስ አበባ ካምፓስ የሚማሩ ተማሪዎቹን ተገቢነት በሌላቸው ፅሁፎችና #መግለጫዎች እንዳይደናገሩ አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ተጠሪነቱ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሆን ተወሰነ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ሲመራ የነበረው የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ተጠሪነቱ ለፌዴራል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

በተለያዩ የትምህርት መስኮች የሚያስተምሩ መምህራንና የስፖርትና የሰውነት ማጎልመሻ ባለሙያዎችን በብቸኝነት በማፍራት ይታወቅ የነበረው የዛሬው ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ስራውን የጀመረው በ1951 ዓ ም በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ነው፡፡

በኋላም የአዲስ አበባ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በሚል ስያሜ ሜክሲኮ አካባቢ ባሁኑ ተግባረ ዕድ ግቢ በርካታ መምህራንን በማሰልጠን ለመላው ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶቸ አበርክቷል ። በ1967 ዓ.ም አሁን ወደሚገኝበት ኮተቤ ተዛውሮ ሲሰራ ከቆየ በኋላ በ1990 ዓ.ም ተጠሪነቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ለከተማው ትምህርት ቤቶች መምህራንን ሲያሰጥን ቆይቷል፡፡ ከዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ባሁኑ ወቅት በመምህራን ስልጠናና ሌሎችም መስኮች ከ14 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል። ተቋሙ ስር ሶስት ኮሌጆች እና አራት ፋኩልቲዎች እንዲሁም 26 የትምህርት ክፍሎች አሉት።

Via Ministry of Science and Higher Education
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#share #ሼር

በ2012 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርሲቲ ለሚመደቡ ተማሪዎች በሙሉ፦

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በ2012 የትምህርት ዘመን የሚካሄደው የተማሪዎች/ተፈታኞች ዩኒቨርሲቲ ምደባ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በማህበራዊ ሳይንስ እና በመምህርነት የሚካሔድ መሆኑን እያሳወቀ፣

1. ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስክ መቀየር የተፈቀደ ሲሆን ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ መቀየር የሚቻለው ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች /ተፈታኞች የተዘጋጀውን መቁረጫ/ማለፊያ/ ነጥብ ለሚያሟሉ ተማሪዎች ብቻ መሆኑን

2. የትምህርት መስክ ምርጫ፣
• ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች (ተፈታኞች) ፣ ተፈጥሮ ሳይንስና መምህርነት
• ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች (ተፈታኞች) ደግሞ ማህበራዊ ሳይንስና እና መምህርነት ብቻ እንዲሆን መወሰኑን

3. ተማሪዎች/ተፈታኞች ውጤታችሁን መሰረት በማድረግ የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን ማስተካከል (መቀየር) የምትችሉ መሆኑን እየገለፀ

የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን #ማስተካከል ሆነ የትምህርት መስክ መቀየር (ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ) የሚቻለው በተማራችሁበት ትምህርት ቤት (ፈተና በወሰዳችሁበት የፈተና ጣቢያ) በኩል መሆኑን እያሳወቀ የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያና የፊልድ መቀየሪያ ቀናት እስከ መስከረም 12/2012 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ነው፡፡ የመሰናዶ ትምህርት ቤቶችም የተማሪዎችን ምርጫ ማስተካከልና የትምህርት መስክ ቅየራ/ ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ/ ጥያቄ በመቀበል እንዲታስተናግዱ ያሳስባል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

📝የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መግቢያ ተልኮልናል።

📝የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ከሉ ምርጥ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል 13ኛ ደረጃ ማግኘቱን በፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።

📝የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የዝግጅት ስራዎችን ለማጠናቀቅ የምዝገባ ቀን ለውጥ ማድረጉ አሳውቋል።

📝2012 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርሲቲ ለሚመደቡ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መልዕክት አሰስተላልፏል።

📝የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ተጠሪነቱ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሆን ተወስኗል።

@tikvahethmagazine

ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን በTIKVAH-MAGAZINE ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#update ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ያቀረበችው ምክረ-ሀሳብ ከእስካሁኑ ሂደት ያፈነገጠ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ተገለጸ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በቅርቡ በግብጽ የቀረበው ምክረ-ሀሳብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል።

ምክረ ሀሳቡ የግብፅን ጥቅም ብቻ ያማከለ እና የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ግብፅ ከግድቡ የአሞላል ሂደት እና በግድቡ አሰራር ላይም የግብፅ ባለሞያዎች እንዲሳተፉ የሚሉ እና ሌሎችም ምክረ ሀሳቦችን ነው ያቀረበችው፡፡

ለዚህ ምክረ-ሀሳብ ምላሽ የሚሆን ሌላ ምክረ-ሀሳብ በኢትዮጵያ በኩል እንደሚዘጋጅም ሚኒስትሩ አስረድተዋል። በተጨማሪም ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በቅርቡ ለጋዜጠኞች ክፍት ተደርጎ ግንባታው የደረሰበት ሁኔታ እንደሚጎበኝም ገልጸዋል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ በመላ አገሪቷ ሶስተኛ ወገን የመድን ዋስትና ሳይገቡ እንዲሁም ውላቸውን ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ3 መቶ በላይ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የፋይናንስ ድጋፍ ጥያቄዎቻቸውን አቀረቡ!

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ እና አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ያቀረበውን የመጀመሪያውን ዙር የስራ ምክረ ሃሳብ (ፕሮጀክት ፕሮፖዛል) ጥሪ ተከትሎ ሦስት መቶ የሚሆኑት ፕሮፖዛሎቻቸውን አቅርበው የገንዘብ ድጋፍ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ኮምኒኬሽን ኃላፊ ሀና አጥናፉ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደተናገሩት የቀረቡት የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ከተጠበቀው በላይ ቁጥራቸው ከፍ ያለ እንደሆነና ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት የሚታየው አንገብጋቢው ድህነት ትረስት ፈንዱ የሚያደርገው ጥረት በሀገር ውስጥም ሆነ በዉጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ሁሉ የተጠናከረ ድጋፍ እና ርብርብ እንደሚያስፈልገው በማያወላዳ ሁኔታ የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከተመሰረት አንድ አመት ያስቆጠረው ትረስት ፈንዱ በሰባ ሰባት አገራት ውስጥ ከሚገኙ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት ካሰባሰበው ብር ውስጥ ከአንድ መቶ አስራ ስድስት ሚሊዮን ብር በላይ መድቦ አንገብጋቢ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ በትጋት እየሰራ ይገኛል።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰሚ ያጣው የኮፈሌ - ቆሬ መንገድ⬆️
በመከላከያ ካምፕ ላይ በተወረወረ ቦምብ አንድ ሰው ሲገደል በርካቶች ቆሰሉ!

በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ በሚገኝ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ካምፕ ላይ የተወረወረ ቦምብ አንድ ሰው ሲገድል በርካቶችን አቁስሏል። የመንዲ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለሙ ጉዲና ለቢቢሲ እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት (ማክሰኞ) የተወረወረው ቦምብ የአንድ ሰው ህይወት ከመቅጠፉም በላይ በርካቶችን አቁስሏል።

የመንዲ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አዳም ኦልጂራ "በቅድሚያ ሶስት ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታላችን መጡ። ከዚያ ደግሞ ህይወቱ ያለፈ ሌላ ሰው መጣ" በማለት ይናገራሉ። "ህይወቱ ያለፈውም ሆነ ጉዳት የደረሰባቸው ከቦምብ ፍንጣሪ ይመስላል" ያሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ቆስለው ወደ ሆስፒታሉ የመጡት ህክምና ተደርጎላቸው ከሆስፒታል እንዲወጡ ተደርጓል።

ከቦምብ ፍንዳታው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለ ተጠርጣሪ እንዳለ የተጠየቁት አቶ አለሙ "እስካሁን አልታወቀም። እያጣራን ነው።'' ሲሉ መልሰዋል። በምዕራብ ወለጋ የምትገኘው የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ተካልኝ እሁድ ዕለት ማታ በመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ ላይ በታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-18-3
"...የጥላቻ ሀሳብ ንግግር መሆን የሚጀምረው በተለያዩ ሚዲያዎች #መሰራጨት ሲጀምር ነው። ንግግሩ ቀስ እያለ #ወደመጠፋፋት ደረጃ የመራል። የቃላት ጉልበት የሚገለጠውም እዚህ ደረጃ ላይ ነው። ቃላት እንደሚያድኑት፤ እንደሚያፅናኑት ሁሉ ቃላት ለማጥፋትም ስሜትን መቀስቀስ ይችላሉ። ስለዚህ በእኔ እሳቤ መዋጋትና ማስቆም ካለብን የጥላቻን ሀሳብ ነው፤ የጥላቻ ንግግር ተብሰልስሎ ወደ ውጪ የወጣ የጥላቻ ሀሳብ መገለጫ ነው።" ዶክተር ፀደይ ወንድሙ /በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH መድረክ ላይ የተናገሩት/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዛሬ በተካሄደ የህገ-ወጥ ንግድ ድንገተኛ አሰሳ በ26 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ የነበረ የአትክልትና ኢንዱስትሪ ምርት መያዙን የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስታወቀ። በግብረኃይል የተወሰደው የኦፕሬሽን ስራ ያለደረሰኝ ግብይት በሚፈፅሙ፣ያለንግድ ፍቃድ የሚነግዱ፣ ከአድራሻና መደብር ውጪ በሚነግዱ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላቸው የዋጋ ጭማሪባደረጉ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ መሆኑም ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
«ግብፆች የኅዳሴ ግድብ በየአመቱ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሐ የመልቀቅ ስምምነት እንዲደረስ ይፈልጋሉ። ይኸ ደግሞ ተገቢ አይሆንም። ያንን ያህል ውሐ ወደ ታች የማስተላለፍ ግዴታ ልንስማማ አንችልም» የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር #ስለሺ_በቀለ

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሀዋሳ ከተማ ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ ደርሷል!" የሆቴል ባለሀብቶችና ስራ አስኪያጆች
.
.
የሀዋሳ ከተማ #ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ በመድረሱ ተጠቃሚነታቸው እየጨመረ መምጣቱን በሀዋሳ የሆቴል ባለሀብቶችና ስራ አስኪያጆች ገለፁ።

በቱሪስት አገልግሎት ዘርፍ የሚስተዋሉ #ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ የሆቴል ባለሀብቶችና ስራ አስኪያጆች ጋር በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡

የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በመሩት በዚህ መድረክ የተሳተፉት የሆቴል ባለሀብቶች እና ስራ አስኪያጆች ቀድሞ የነበረውን የከተማዋን ሰላም ጠብቆ የማቆየት እና አስተማማኝ ደረጃ የማድረስ ኃላፊነት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ህብረተሰብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለቱሪዝም ዘርፉ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በጋራ ለመፍታት እንሰራለን ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች የከተማዋ ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ ተጠቃሚነታችን ተረጋግጧልም ብለዋል፡፡

አቶ ጥራቱ በየነ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ በበኩላቸው አስተዳደሩ ሰላምን በማረጋገጥ እና ሁሉን አቀፍ ለውጥ በማምጣት የከተማዋን የቱሪስት መስህብነት ከምንጊዜውም በላይ እውን ለማድረግ እንደሚሰራም አመላክተዋል፡፡

Via Hawassa City Administration Public Relation Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GrandEthiopianRenaissanceDam

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ግንባታን በተመለከተ አንዳንድ የውጪ ሚዲያዎች የተዛባ መረጃ እያቀረቡ መሆናቸውን የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ እነዚህ ሚዲያዎች ግድቡን በተመለከተ ያለበቂ መረጃ የሚሰሯቸው ዘገባዎች ህብረተሰቡን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዝ የሚያደርጉ እንደሆነም በመግለጫው ተጠቁሟል።

የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተን ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ አንዳንድ የውጪ ሚዲያዎች ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባ እያሰራጩ ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዳይኖረው ማድረጋቸው ሃላፊነት የጎደለው አሰራር ነው።

በተለይ በአንዳንድ የግብፅ ሚዲያዎች ላይ የሚተላለፉ ዘገባዎች የተዛቡ መሆናቸውን የጠቀሱት ኢንጅነሩ አሁን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ሚዲያዎችን በማስተባበር ታላቁን የህዳሴ ኃይል ማመንጫ ግድብን ቦታ ድረስ ተገኝተው እውነታውን እንዲረዱ ለማድረግ የመስክ ምልከታ ፕሮግራም ያዘጋጃል ብለዋል። እንደሚኒስትሩ ገለጻ የመስክ ምልከታ ፕሮግራሙ ዋንኛ ዓላማ ጋዜጠኞች እውነታ ላይ ተመስርተው መረጃን ለህዝብ ማድረስ እንዲችሉ ለማድረግ በመሆኑ ሁሉም ሚዲያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ።

Via ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በTIKVAH-ETHIOPIA|ተስፋ ኢትዮጵያ| ስር የሚገኙ ሌሎች ትክክለኛ ቻናሎች እኚህ #ብቻ ናቸው፦

•ለዓመታት የቆየው የቤተሰባችን የመተጋገዣ መድረካችን-- የታመሙትን የምናግዝበት፤ ጠያቂ ያጡትንም የምንጠይቅበት TIKVAH-AID https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFL4FSDwsNhb0sVn3Q

•በዋናው ቻናል ብዙም የማይዳሰሱ የቱሪዝም፣ የባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች፣ የተማሪዎች፣ የወላጆች፣ የመምህራን ጉዳዮች የሚዳሰስበት TIKVAH-MAGAZINE https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

•ስፖርታዊ ጉዳዮች TIKVAH-SPORT https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

•ይህ ደግሞ የቤተሰባችን አባላት የአፋን ኦሮሞ የመረጃ መለዋወጫ ቻናላችን ነው TIKVAH-AFAAN OROMOO https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFEzH7Ywz6n7V8mzcQ

•ይህ የቋንቋ መማማሪያ ቻናላችን ብዙ ለመስራት የታቀደበት ነገር ግን ከሁኔታዎች አለመመቻቸት ጋር እንደታሰበው ያልተገለገልንበት ቻናላችን ነው። በቅርቡ ግን የዩኒቨርሲቲ መምህራን እንዲሳተፉበት በማድረግ የቆሙት የትግርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ የግዕዝ ትምህርቶች እንዲቀጥሉ ለማድረግ ይሰራል። ተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎችን ለማስተማር መምህራኖችን ካገኘን ተጨማሪ ትምህርቶች ይካተቱበታል TIKVAH-EDUCATION -- https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEWA_-Jt2zIM5COJqw

#ማሳሰቢያ፦ ከላይ ከተገለፁት ውጭ TIKVAH-ETH ሌላ ምንም ቻናል የለውም፤ በተጨማሪ TIKVAH-ETH ፌስቡክ ላይ ምንም ገፅ የለውም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia