TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዳማ ከተማ የሚገኘው ብራዘርስ የዱቄትና ብስኩት ፋብሪካ ከ700 ለሚበልጡ የችግረኛ ልጆች ዛሬ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የፋብሪካው ባለቤት ሃጂ አህመድ በሽር እንደገለጹት ድጋፉን ያደረጉት በድርጅቱ ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ ቤተሰብ ልጆች ነው። ከ300ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው ቦርሳ ፣ ደብተርና ሌሎችንም የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም በክልሉ መንግስት ያወጣውን የዜግነት አገልግሎት ስራ በመደገፍ የድርሻቸውን ለመወጣት አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመው በተጨማሪም 100 ለሚሆኑ አረጋዊያን የምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች መስጠታቸውን አስረድተዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰሜን ወሎ ወጣቶች በበጎ ተግባር!

"ከሰሜን ወሎ #መርሳ ከተማ ነው፤ በክረምት በጎ አድራጎት እኛ ደስ በሚል ሁኔታ እየሰራን ነው። በከተማችን ያሉ አረጋዋያንን ቤት በመጠገን፣ አልባሳታቸውን እና ንፅህናቸውን በመጠበቅ እንዲሁም ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፍ እያደረግን ሲሆን አሁን ደግሞ የትምህርት ቁሳቁሶችን እየሸከፍን እንገኛለን" #ደሳለኝ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር ፈተና ሆኗል!

”እራሳችንን ጠቅመን አገራችንና ህዝባችንን ለማገልገል የገነባናቸው ፋብሪካዎች በኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር ምክንያት ወደ ማምረት ተግባር መግባት አልቻሉም ” ሲሉ በደሴ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች ቅሬታ አሰሙ።” በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደሴ ዲስትሪክት በበኩሉ በአሁኑ ጊዜ የሃይል እጥረት በማጋጠሙ ችግሩ ከአቅሜ በላይ ነው ብሏል።

https://telegra.ph/ETH-09-01-4

Via #ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋሞ አባቶች የልዩ ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ!

#TIKVAH_ETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ⬆️ድንቅ የሆኑት የጋሞ አባቶች እና የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬም ክብር ይገባቸዋል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋሞ አባቶች ተሸለሙ!

"ተንበርክከው #ከጥፋት ከታደጉን የጋሞ ሽማግሌዎች ብዙ ልንማር ይገባል" አቶ ለማ መገርሳ/የዛሬ አመት የተናገሩት/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ስራ! በህይወት ሳለን የመረዳጃ እድር ከሌሎች ማህበራት ጋር በመተባበር 90ሺህ ብርና የትምህርት ቁሳቁስን አሰባስቦ ረዳት ለሌላቸዉ አረጋዊያንና ተማሪዎች ደጋፍ አበረከተ። 90ሺህ ብር፤ ብርድ ልብስና ሳሙና ለአረጋዊያን ድጋፍ የተደረገ ሲሆን እንዲሁም ቦርሳ፣ ደብተር፣ እስክርቢቶና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች መበርከቱ ተገልጿል። ይህ ድጋፍም ለ20 #አረጋዊያንና 300 ለሚሆኑ ህፃናት ተማሪዎች መሆኑም ታውቋል። በዚህ በጎ አድራጎት ስራም ተስፋ ልማት አቀፍ ማህበር፣ ቦኤዝ ምግብ ኮምፕሌክስ፣ ይቻላል ፋውንዴሽን፣ አስቴር ቤተ ፍቅርና ያጅቡሻል የመድሃኒት መደብር የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸዉ ተገልጿል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
7ኛው የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች፦

1. መምህርነት ዘርፍ ህይወት ወልደመስቀል፣

2. ሳይንስ (ህክምና፣ ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ምህንድስና፣ ኬሚስትሪ፣ አርክቴክቸር፣ ወዘተ) ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው፣

3. በኪነ ጥበብ/ሥነ-ጥበብ፣ (በፎቶ ግራፍ ዘርፍ) አቶ በዛብህ አብተው፣

4. በበጎ አድራጎት (እርዳታና ሰብዓዊ አገልግሎት) ዘርፍ ዶክተር አብዱላዚዝ ኢብራሂም፣

5. በቢዘነስና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ አቶ ነጋ ቦንገር፣

6. መንግሥታዊ የሥራ ተቋማት ኃላፊነት አቶ ግርማ ወንዳፍራሽ፣

7. በቅርስና ባህል ጥበቃ ዘርፍ አቶ አብደልፈታህ አብደላ፣

8. በሚዲያና ጋዜጠኝነት አቶ አማረ አረጋዊ፣

9. ለኢትዮጵያ እድገት አስተዋጽዖ ያበረከቱ ዳያስፖራዎች አቶ ኦባንግ ሜቶ፣

💫እንዲሁም የዓመቱ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚዎች የጋሞ ሽማግሌዎች በጋራ ተሸላሚ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል።

በመድረኩ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት መልእክት አገር በትውልድ ቅብብሎሽ እንጂ ባንድ የተወሰነ ቡድን ወይም ግለሰብ ብቻ አትገነባም፤ ተገንብቶ ያለቀ አገርም የለም ብለዋል። በመሆኑም ዛሬ የምንሰራቸው ስራዎች ለአገር ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ ነውና በጎውን እንስራ ብለዋል ፕሬዝዳንቷ።

@tsegabwolde @tikvagethiopia
#ሰሜን_ተራሮች

የዋልያን ቁጥር #ለመጨመር ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በትብብር የተጀመረው ፕሮጀክት በውቢቷ የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ተጀምሯል። በመጀመሪያው እርምጃ #ዋልያ የሚመገባቸውን አገር በቀል #ተክሎች ችግኝ በማፍላትና በመትከል እንዲሁም እንስሳው እንዳይታደን ጥበቃ ለሚያደርጉ ስካውቶች የደምብ ልብስ ማልበስ ተጀምሯል። ኤቨረስት ተራራ ላይ በመውጣት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ሲራክም ከቡድኑ ጋር ተጉዟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ ሽልማት ተበረከተላቸው!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአሸንዳ በዓል በአዲስ አበባ ደረጃ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉት አስተዋፅኦ ከትግራይ ሴቶች ማህበር አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA "የአሸንዳ በዓል #የኢትዮጵያውያንን አንድነትና ሰላም በማጠናከር ጉልህ ሚና አለው" የበዓሉ ተሳታፊዎች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የአዲስ አበባ አዴፓ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ፦

እኛ በየደረጃው የምንገኝ የአዲስ አበባ አዴፓ አመራሮች ከነሐሴ 25 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በ2011ዓ.ም መደበኛ የድርጅትና የፖለቲካ ስራዎች አፈፃፀም እንዲሁም በከተማዋ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እንቅስቅሴ ዙሪያ የከተማችንን ህዝብና ወጣት መሰረታዊ ፍላጎቶች ለመመለስ፣ ባከናወናቸው ተግባራት የነበሩንን ጠንካሬና ጉድለቶች በዝርዝር ገምግመናል፡፡

#AddisAbebaEPRDF

ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-01-5
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ #አልተደረገም፤ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲም መቼ ይፋ እንደሚደረግ #አላሳወቅም። በተመሳሳይ ስለዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ የሚዋራው ሀሰት ነው። መቁረጫ ነጥብ ይፋ አልተደረገም።

ውድ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በተለያዩ ሀሰተኛ ገፆች እንዳትታለሉ! ተማሪዎች እና ወላጆች አጠቃላይ ስለፈተናችሁና ውጤታችሁ ትክክለኛ መረጃን ልታገኙ የምትችሉት በዚህ መንገድ ብቻ ነው፦

1. https://m.facebook.com/neaea.nae/ ይህ ትክክለኛው የኤጀንሲው የፌስቡክ ገፅ ነው። አዲስ መረጃ ካለ በዚህ በኩል ይገልጻሉ።

2. https://app.neaea.gov.et/ ይህ የኤጀንሲው ድረገፅ ነው። አዲስ መረጃ ካለ በዚህ በኩል ይገልጻሉ።

3. በተለያዩ የመንግስትና የግል የቴሌቪዥንና ሬድዮ ጣቢያዎች በኤጀንሲው በኩል የሚሰጠውን መረጃ ብቻ ተከታተሉ።

4. ህጋዊ በሆኑና በቴሌቪዥንና በሬድዮ ጣቢያዎች ቁጥጥር ስር ባሉ ህጋዊ✔️የፌስቡክ ገፆች ላይ ስለውጤታችሁ የሚወጣ መረጃ ካለ #ተመልከቱ፤ አረጋግጡ።

📌ከዚህ ውጪ በትኛውም አይነት መንገድ የሚሰራጩ መረጃዎች #እንዳታምኑ። በሚሰራጩ ሀሰት ወሬዎችም #እንዳትጨነቁ። የምታዩትን ነገር ሁሉ ሼር እንዳታደርጉ በቅድሚያ አረጋግጡ!!

💫ኤጀንሲው ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል የለውም! ሁሉም በኤጀንሲው ስምና በትምህርት ሚኒስቴር ስም የተከፈቱት ቻናሎች ህጋዊ እውቅና የሌላቸው ናቸው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በዋጋ ንረት ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር እየተወያየ ነው። ውይይቱ በዋናነት በአገልግሎት እና በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ በሚታየው የዋጋ ንረት ላይ ነው እየመከረ ያለው። በመድረኩ የዋጋ ንረትን እና ህገ ወጥነትን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልበት አግባብ ዙሪያም ምክክር እየተደረገ ነው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
💫በአዲስ አበባ የአርሰናል ደጋፊዎች ትላንት አርሰናል ከቶትነሀም ባደረጉት የፕሪሚየር ሊግ ጨወታ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተገኝተው የታደሙ ሲሆን በጎ አላማ ያለውን ስራንም አሳክተዋል፡፡ ደጋፊዎቹ ከ10:00 ሰአት ጀምሮ ችግርተኛ ተማሪዎችን ለመርዳት ከበርካታ ተመልካች የመማሪያ ደብተር እና ቁሳቁስ ለመለገስ የመሰብሰብ ስራን ሰርተዋል መልካም ተግባር ፈፅመዋል፡፡

Via Teddy Soccer
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ስራን ሰርተን እንለፈ!

"እኛ እዚህ አዲስ አበባ የምንኖር የተወሰንን የጭሮ ተወላጆች በ26/12/2011 ዓ.ም. በጭሮ ከተማ የሚገኝ ቁጥር 4 ት/ቤት አቅም ላነሳቸው ተማሪዎች የደብተር፣ የብእርና አርሳስ እርዳታ በቦታው በመገኘት አድርገናል። ይህንን አስመልክቶ ከወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት የምስጋና ደብዳቤ ተሰቶናል። ለቀጣም አጠናክረን እንቀጥላለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለ10 ቀናት ሥራ ማቆሙ ተገለጸ!

የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት አስር ቀናት ያህል ሥራ የተቋረጠ ሲሆን አንድ ድርጅት የጄነሬተር ኃይል በመጠቀም ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል።

የፓርኩ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ መሐመድ ሃጂ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ፓርኩ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኘው ከአዋሽ መልካሳ የኃይል ማመንጫ ሲሆን፣ ለፓርኩ ኃይል የሚያቀብለው ትራንስፎርመር በመቃጠሉ ምክንያት ሥራቸው መስተጓጎሉን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሰኞ ነሐሴ 20/2011 አዲስ ትራንስፎርመር ተገዝቶ ወደ አዋሽ መልካሳ መላኩን የነገሩን መሐመድ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ጥገናው ተጠናቆ የኃይሉ ችግር እንደሚቀረፍ ተናግረዋል።

በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ለችግር የተጋለጠው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ አለመሆኑን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኮንን ኃይሉ ገልጸዋል። ብዙዎቹ ፓርኮች ሥራቸውን ባቀዱት መጠን እንዳይሠሩ የኃይል መቆራረጡ እቅፋት እንደሆነባቸውም ኃላፊው ተናግረዋል።

#AddisMaleda

https://telegra.ph/ETH-09-02
ከበዓል በፊት ደሞዛችን ይከፈለን!

ከአደረጃጀት ጋር በተያያዘ የኛ #የዶክተሮች ክፍያ አልተፈፀመም ሲሉ በቀድሞው የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን "ሰገን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል" የሚሰሩ ዶክተሮች ቅሬታ አቅርበዋል። የህክምና ባለሞያዎች ለሰሩበት እና ላገለገሉበት ክፍያ ካልተፈፀመላቸው ለምን መጥተው ያገለግላሉ ሲሉም ይጠይቃሉ? ከአደረጃጀት ጋር በሚያያዙ ጥያቄዎች የኛ ለሁለት ወር የደሞዝ አለመከፈል እጅጉን ቅሬታ ፈጥሮብናል፤ ይህ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ጤና መግባት የለበትም ያሉት ዶክተሮቹ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ከላይ ያሉት አመራሮች ትኩረት ሰጥተውበት እንዲሰሩ ጠይቀዋል አዲሱ ዐመት ከመግባቱም በፊት ተገቢው ክፍያ እንዲከፈላቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ...

የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ የሆኑት ዶክተሮቹ በአሁን ሰዓት የሚገኙት በጉማይደ/ሰገን/ ከተማ ሲሆን አከባቢው #በወታደር ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልፀዋል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢዜማ በደሴ ከተማ ውይይት አደረገ!

ለኢትዮጰያ ጠንካራ አንድነት፣ሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት አበክሮ እንደሚሰራ የኢትዮጰያ ዜጎች ማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ገለፀ ። ኢዜማ ከደሴና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር በለውጡና በቀጣይ የሰራ እቅዶቹ ዙሪያ ትናንት መክሯል፡፡

የኢዜማ ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ የአገሩን ዳር ድንበር አስከብሮ፣ ተከባብሮና ተቻችሉ ክፉ ደጉን አሳልፏል፡፡ ይህን ከአባቶች የተገኘውን የረጅም ዘመን አንድነት፣ ሰላምና የመቻቻል ባህልና እሴት ለማጎልበት ኢዜማ አበክሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ከተደቀነባት አደጋ ለማውጣት በየደረጃው ጠንካራ መሪና ህዝብ ያስፈልጋታል ያሉት አቶ አንዷለም ከዚህ ችግር እንድትወጣ ከመንግስትና ከሌሎች ተፎካካሪ ፓሪቲዎች ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን ብለዋል፡፡ እንደ አቶ አንዷለም ገለጻ ከማንኛዉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በፊት አገር፣አንድነትና ሰላም መቅደም እንዳለበትም አብራርተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-02-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደህና መጣችሁ!

በሞሮኮ አስናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት አይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ ገብቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

በሞሮኮ አስናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት አይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይፋዊ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል፡፡

በአቀባበል ስነ-ስርአቱ ላይ የኢትዮጵያ ስፖር ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን የተውጣጡ አካላት ተሳታፊ ናቸው፡፡

የስፖርት ልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ የገባበት ሰአት ለአቀባበል ምቹ ስላልነበረ የአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ለዛሬ መተላለፉ ተገልጿል፡፡ 250 አባላትን የያዘው የስፖርት ልኡካን ቡድኑ በሞሮው መድረክ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 12 የነሃስ ሜዳሊያዎች በማስመዝብ ከአፍሪካ 9ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

Via ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia