TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢንትሮዳክሽን ቱ ገዳ!

ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የትምህርት ዘመን ስለ ገዳ ስርዓት የሚያስተምር ‘’ኢንትሮዳክሽን ቱ ገዳ ሲስተም ‘’ የተሰኘ አዲስ ትምህርት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ሴት ማህበር የፓናል ውይይት አ/አ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አማራ ሴት ማህበር የአሸንድዬ፣ ሻደይና ሶለል የልጅ አገረዶች በዓልን በማስመልከት በዛሬው እለት በሆፕ ዩኒቨርሲቲ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ የተገኙትና ጥናታዊ ፅሑፍ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ እንዳሉት፣ ባህላዊ እሴቶቻችንን ከትውልድ ትውልድ ማስተላለፍ እና አዲሱ ትውልድም በራሱና በባህሉ ሊኮራና ሊተማመን እንደሚገባ አሳስበዋል። በዚህ ኘሮግራምም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አማራ ሴት ማህበር አባላት፣ የክፍለ ከተማው የአማራ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በፓናል መድረኩ ታድመዋል።

Via #EPRDF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከወረዱ ዘረኞች፣ ደካማዎች ጋር ሳትወርዱ ባላችሁበት ከፍታ የወደቀን የምታነሱ እንጂ ከወደቀ ፖለቲካ ጋር ወድቃችሁ የምትንኮታኮቱ እንዳትሆኑ’’
.
.
-‘’የአንድ ወታደር መለኪያው በጀግንነት ለለሀገሩ ክብርና አንድነት መሰዋቱ ነው።’’

-‘’ወታደር የሚሞትለት ነገር ካላገኘ የሚኖርበት ምክንያት የለውም።"

- ‘’ወታደር የሚሞትለት ሀገርና ህዝብ ስላላው አላማ ሰንቆ ለአላማ የሚኖር በዚያልክ መኖር ሲችል ወታደር ሆኖ ኖሮ፣ ወታደር ሆኖ ይሞታል።’’

- ‘’ወታደር መሆን በራሱ ከባድ ነገር ነው፤ የወታደር መኮንን መሆን ደግሞ ድርብ ሀላፊነት ነው።’’

- ‘’እናንተ የኬንያ፣ የደቡብ አፍሪካ እና የናይጄሪያ መኮንኖች አይደላችሁም እናንተ የኢትዮጵያ መኮንኖች ናችሁ።’’

- ‘’ጀግንነታችሁ ሰብአዊነትን የተላበሰና ለወገን ክብር የሚንገበገብ መሆን አለበት።’’

- ‘’ወታደር የሚዋጋውም፣የሚገለውም፣የራሱን ህይወት አሳልፎ የሚሰጠው ባላንጣውን አጥብቆ ስለሚጠላ ሳይሆን ወገኑን አጥብቆ ስለሚወድ ነው።’’

- ‘’ወታደር ከወደቀ ጋር የማይወድቅ፣ ነገር ግን የወደቀችን ሀገር የሚያነሳ ነው።’’

(የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ኮሌጅ ለ13 ኛ ዙር ከፍተኛ መኮንኖችን በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ባስመረቀበት ወቅት ተገኝተው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወታደር የሚዋጋውም፣ የሚገለውም፣ የራሱን ህይወት አሳልፎ የሚሰጠውም ባላንጣውን አጥብቆ ስለሚጠላ ሳይሆን ወገኑን አጥብቆ ስለሚወድ ነው።’’ ዶክተር አብይ አህመድ - የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"መከላከያ የሰራዊቱን ተልዕኮ የመፈፀም አቅም እና ብቃት ለማሳደግ የሚያስችለው #የሪፎርም ሥራ ይገኛል። ዛሬ የተመረቁ ከፍተኛ መኮንኖችም የተጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም ከግብ ለማድረስ ሚናቸው የጎላ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም።" (የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም - ጄነራል አደም መሀመድ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations #Somaliland Military Officers graduate from #Ethiopian Military Academy, Won medals!

Via Horn
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዛይራይድ

የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ እሰራለሁ የሚለው ዛይራይድ የተሰኘው ድርጅት ማህበራዊ ሃላፊነቱ ለመወጣት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል። በዛሬው ዕለትም በካንሰር ህፃናት ህሙማን ማዕከል የምሳ ማብላትና ለተማሪዎች የደብተርና የእስክሪብቶ ስጦታ የማበርከት ስነ ስርዓት ማከናወኑን ለTIKVAH-ETH በላከው መልዕክት አሳውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ያገባኛል #ይመለከተኛል የመዝሙር ኮንሰርት
#LIVE on etv, ebs, FANA, addis tv

ገቢው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ማህበራዊ ትረስት ፈንድን ለመደገፍ ይውላል!
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ "በያገባኛል ይመለከተኛል" የገቢ ማሰባሰቢያ የመዝሙር ኮንሰርት ላይ ንግግር እያደረጉ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ልመና ባህሪያችን አይደለም፣ ልመና #የማንነታችን መገለጫ አይደለም፤ ...መስጠት ትውልድን የማይገነባ ከሆነ፣ መስጠት ሀገር መቀየር ካልቻለ ባንሰጥ ይሻላል" ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"Our beloved Muslim brothers and sisters, may the peace and love of Allah embrace your life. Wishing you and your family a very Happy Eid. Eid Mubarak!" #Ethio_telecom #ኢትዮ_ቴሌኮም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የእስልምና እምነት ተከታዮች #ሙስሊሞች የተራበውን ለማብላት፤ ለተቸገረው ለመድረስ ይሰራሉ!" ሼህ ጣሂር አብዱልቃድር /#ሚሊኒየም_አዳራሽ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ትልቅነታችንን በመስጠት እናሳይ...መስጠትን የምንማረው ከተፈጥሮ ነው...እኛ ያለሌላው ሙሉ ልንሆን አንችልም" አባ ጴጥሮስ/ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
6400 ላይ 'A' ብለው በመላክ #የጎዳና ልጆችን መልሶ ለማቋቋም የድርሻዎትን ይወጡ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia

ልመናና የጎዳና ኑሮ በህግ ሊከለከል ነው!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የጎዳና ላይ ኑሮና ልመናን በህግ እስከመከልከል የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ። የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው “የያገባኛል ይመለከተኛል” የገቢ ማሰባሰቢያ የመዝሙር ኮንሰርት ላይ ነው ይህን ያሉት፡፡

በአዲስ አበባ ከየትኛውን የአገሪቱ ክፍል መጥቶ ሰርቶ መኖር ይችላል፣ ጎዳና ግን መኖርም ሆነ መለመን የማይቻልበት ሁኔታ እንዳይፈጠር እስከመድረስ ለመስራት እንገደዳለን ብለዋል፡፡

“ሰርተን መለወጥ የምንችል ሆነን እያለን ከልመና ለመውጣት የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል” ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡ በተናጠል ከምንሰጥ መንግስት በዘረጋው አሰራር ስር በመስጠት ጎዳና ላይ የወጡ ወገኖችን በዘላቂነት አሰራር መቀየር እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ የኮንሰርቱ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ሊደርስ ፌሎውሺፕ 100 ሚሊዮን ብር አሰባስቦ ለትረስት ፈንዱ ገቢ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

የፌሎውሺፑ ሊቀመንበር ሐዋሪያው ዮሃንስ ዜጎችን ከጎዳና ላይ ለማንሳት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ገቢው የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ጎዳና ላይ የወጡ ዜጎችን ለማንሳት የተመሰረተውን ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ለመደገፍ ይውላል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ወንጌላውያን ህብረት መሪዎችና የሌሎች ሐይማኖት መሪዎችም ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት የየእምነቱ ተከታተዮቻቻቸው እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ከመግቢያው በተጨማሪ በ6400 የአጭር የፅሁፍ መልዕክት ገቢ የማሰባሰቢያ መርሃ ግብርም ተካሂዷል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸"በያገባኛል ይመለከተኛል"የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፣ ኢ/ር እንዳወቅ አብቴ ፣ ከተለያዩ ቤተ-እምነት የመጡ የሃይማኖት አባቶች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ70_እንደርታ #ፋሲል_ከነማ

የመቐለ 70 እንደርታ ቡድን በካኖ ስፖርትስ አካዳሚ በፓብሎ ቦያስ ደሳምፓካ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን ትላንት አድርጓል ። የቡድኑ ተጨዋቾች #በጥሩ_ጤንነት መሆናቸውን ተሰምቷል።

በሌላ ዜና...

የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ እግር ኳስ ውድድር ፋሲል ከነማን ከታንዛንያው አዛም ክለብ ጋር ያገናኛል፡፡ ጨዋታው ነገ እሁድ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ይደረጋል፡፡ የፋሲል ከነማ ምክትል አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ እንደተናገሩት አፄዎቹ ለማሸነፍ የሚያስችል መልካም የስነ ልቦና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ እንደ ምክትል አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ ገለጻ ተጫዋቾቹ ለማሸነፍ የሚያስችል ልምምድ በባሕር ዳር ከተማ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አፄዎቹ የመጨረሻውን ልምምድ ትናንት አድርገው ዛሬ ዕረፍት ላይ ናቸው፡፡ ጉዳት የደረሰበት ምንም ተጫዋች እንደሌለ እና የተሻለ የስነ ልቦና መነቃቃት እንደሚታይባቸውም ነው የተናገሩት፡፡

Via #AMMA & #ethiokickOff

የስፖርት ጉዳዮችን ብቻ ትከታተሉ ዘንድ👇
@tikvahethsport

⛹‍♀🏋‍♀🏂🏄‍♂🚴‍♀🥊🥋🏇🤼‍♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
#NewsAlert

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ንግሥት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አሥፈፃሚነት ራሷን #አገለለች። በደብረብርሀን እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ የ2012 እቅድ አፈፃፀም ድምፅ ሊሰጥ ሲቃረብ ደራርቱ" በቃኝ ከፍተኛ #መገለል እየደረሠብኝ ነው። ወደዚህ ጉባኤ እንኳን ስመጣ በግል እንጅ እንደሌላው ምንም መጥሪያ አልደረሠኝም ብላለች። ሁላችሁንም እወዳችኋላሁ ያለችው ደራርቱ ሥፖርቱ እንዲያድግና የሀይሌ ራእይ እንዲቀጥል ነው ፍላጎቴ አሁን ግን ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አሥፈፃሚነት ይበቃኛል በማለት ተናግራለች።

ዶ/ር አሸብር በበኩላቸው ያለደራርቱ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ማሠብ ከባድ ነው ጉዳዩን ቁጭ ብለን እንፈታዋለን ብለዋል። ደራርቱ የተከፋችበት ጉባኤ መሆኑ አሳዝኖናል ደራርቱ ትመለሳለች፤ ትመለሳለች፤ ትመለሳለች ሲሉም ተናግረዋል። ቀጣዩ የ2012 ጠቅላላ ጉባኤ ትግራይ የ2013 ደግሞ አማራ ክልል እንዲያዘጋጁ ተወሥኗል። ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክሥ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ም/ፕሬዝደንት ሥትሆን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ አባል ነች።

Via ግርማቸው እንየው/ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
69 ሚሊዮን ኮንዶም እንዳይሰራጭ ታግዷል!

"በጥራት ጉድለት ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ 69 ሚሊዮን ኮንዶም ወደ ገበያ እንዳይሠራጭ ታግዷል" አቶ ኃይሉ ታደግ፣ የፕሮሞቲንግ ዘኳሊቲ ኦፍ ሜዲሲን ፕሮግራም ኃላፊ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ አዲስ እንቁጣጣሽ ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ