TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Congratulations ወደበኃላ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርቃት ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን አቀርባለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የመከላከያ አዛዥነት ስታፍ ኮሌጅ ለ13ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 100 ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በተከናወነ ስነ ስርዓት የተመረቁት 100 ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ 92 ፖስት ስታፍ እና ስምንት የሁለተኛ ድግሪያቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥም 21 ተመራቂዎች ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ተገልጿል። እነዚህ ተመራቂዎችም ከጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የተውጣጡ መሆናቸው ነው የተመለከተው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አህመድም ለተመራቂዎች ዲፕሎማ ከሰጡ በኋላ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። ተመራቂዎች በስነ ምግባር፣ በወታደራዊ ጥበብ፣ በሙያዊ ብቃት እና በላቀ ዝግጅት የሰራዊት አባላትን ለመምራት እና ለድል ለማብቃት የሚያስችላቸውን እውቀት እና ከህሎት ለማግኘት ለአንድ ዓመት ትምህርታቸውን መከታተላቸውን አንስተዋል።

በመሆኑም በትምህርት የገበዩትን እውቀት ከዚህ በፊት ካገኙት ልምድ፣ በንባብ ከሚያገኙት እና በተፈጥሮ ከያዙት እውቀት ጋር በማዋሃድ በትጋት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ነው ያሳሰቡት።

ወታደራዊ ተቋማት በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ መሪዎች፣ በስነ ምግባር አርኣያዎች፣ ሀገርን እና ወገንን በመጠበቅ አኩሪዎች፣ ህግና ስርዓትን በማክበር እና በማስከበር ተምሳሌት እንዲሆኑም ያስፈልጋል ብለዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸አቶ ለማ መገርሳ/የመከላከያ ሚኒስትር/፣ ዶ/ር አብይ አህመድ/የኢፌዴሪ ጠ/ሚ/፣ጀነራል አደም መሃመድ/የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅማ_ዩኒቨርሲቲ

ዛሬ የጅማ ዪኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ለአርንጓዴ አሻራ ከ5 መኪና በላይ ወደ ግልገል ጊቤ በመሄድ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

ASTU 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ!

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ/ASTU/ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 353 ሴት ተማሪዎችን ጨምሮ 1859 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም በዩኒቨርስቲ የሚታዩ #በዘርኝነት የሚከሰቱ #መጠፋፋቶች ኋላ ቀር አስተሳሰብ በመሆናቸው ይህ ትውልድ መፍቀድ የለበትም ብለዋል፡፡ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም በበኩላቸው ተማሪዎች በተማሩበት መስክ ጠንካራ ሰራተኛ በመሆን የአገልጋይነት ስሜት በመላበስ የተጣለባቸውን አደራ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ ከ25 አመታ በፊት የተቋቋመው ዩኒቨርስቲው በልዩ የመግቢያ ፈተና በዓመት 5ሺህ የሚሆኑ ለፈተና ቢቀርቡም 1500 ብቻ ናቸው ዕድሉን የሚያገኙት ተብሏል፡፡ ዩኒቨርስቲው የምርምር እና የጥናት የልህቀት ስራዎችን የሚያካሂድበት 8 የልህቀት ማዕክል አሉት፡፡

በዩኒቨስቲው የሚገኘው ላብቶሪ ለዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር አገልግሎቱን እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡ ሙህራን በዘርፉ ላይ ምርምር እና ጥናት ሊያካሂዱበት የሚችል በአይነቱ ለየት ያለ የምርምር ማዕከል በዩኒቨርስቲው ውስጥ እየተገነባ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፦

በሀገር ደረጃ የሚስተዋለው የብሄር ፅንፈኝነት ለሀገራዊ አንድት ተግዳሮት በመሆኑ መታገል እንደሚገባ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

የብሄር ፅንፈኝነት ለሀገራዊ አንድነት እና ለፌደራላዊትና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ተግዳሮት እንደሆነ በውይይቱ በማንሳት መታገል እንደሚገባ ኮሚቴው ተመልክቷል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያዊ ማንነትን አስታርቆና አቻችሎ ማስኬድ እንደሚገባ መነሳቱንና በማህበራዊ ሚዲያው ከሚንፀባረቁትና አመራሩም ከሚገዛቸው ፅንፈኝነት በመውጣት መታገል እንደሚገባ ዝርዝር ግምገማ ማካሄዱን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/EPRDF-08-10
ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ ኢህአዴግ ወሰነ!

ምርጫ 2012 በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንደወሰነ ተገልጿል። ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከነሀሴ 2 እስከ 3/2011 ስብሰባውን አካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስተር

#በትምህርት_ሚኒስቴር ስር የተደራጀው የ’#እኛ_ለእኛ’ የወጣቶች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ክረምት ጀምሮ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግረኛ ተማሪዎችን ለመርዳት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ወራት በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን በማስመልከት ወጣቶቹንና የተሻለ አበርክቶ የነበራቸውን አካላት አመስግኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ #ጽዮን_ተክሉ እንዳሉት የእኛ ለእኛ የወጣቶች በጎ ፈቃደኞች ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣችን አቅፎ ላለፉት ሁለት ወራት በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ችግረኛ ተማሪዎችን መርዳት፤ በዚሁ መሰረት ፕሮጀክቱ አስካሁን ለተፈናቃይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በቁጥር ረገድ በደቡብ፣ በሱማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ነው ያሉት።
ከዚሀ ጎን ለጎን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሳይካትሪስቶች ማህበር ጋር በመተባበር ለተፋናቃይ ተማሪዎች የስነ ልቦና የህክምና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

በቀጣይ ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባላቸው ሙያ ፕሮጀክቱን ተቀላቅለው ድጋፉን እንዲያበረክቱም ወይዘሮ ፅዮን ጥሪ አቅርበዋል።
ትምህርት ሚኒስተር

በትምህርት ሚኒስቴር ስር የተደራጀው የ #እኛ_ለእኛ’ የወጣቶች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ክረምት ጀምሮ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግረኛ ተማሪዎችን ለመርዳት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ። ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት ወራት በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን በማስመልከት ወጣቶቹንና የተሻለ አበርክቶ የነበራቸውን አካላት አመስግኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ #ጽዮን_ተክሉ እንዳሉት የእኛ ለእኛ የወጣቶች በጎ ፈቃደኞች ፕሮጀክት በመላ አገሪቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ወጣችን አቅፎ ላለፉት ሁለት ወራት በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ችግረኛ ተማሪዎችን መርዳት፤ በዚሁ መሰረት ፕሮጀክቱ አስካሁን ለተፈናቃይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በቁጥር ረገድ በደቡብ፣ በሱማሌ እና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ በቀጣዩ ዓመት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ነው ያሉት።
ከዚሀ ጎን ለጎን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሳይካትሪስቶች ማህበር ጋር በመተባበር ለተፋናቃይ ተማሪዎች የስነ ልቦና የህክምና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። በቀጣይ ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ባላቸው ሙያ ፕሮጀክቱን ተቀላቅለው ድጋፉን እንዲያበረክቱም ወይዘሮ ፅዮን ጥሪ አቅርበዋል።

ተጨማሪ👇
"በእኛ ለእኛ" ሀገር አቀፍ ስራ ላይ ማገልገል የምትፈልጉ ሁሉ ከታች በተጠቀሱት ፕሮግራሞች ማለትም፦

1. ዛሬ ቅዳሜ ነሀሴ 4 ቀን 2011 ዓም
ከጠዋቱ በ2:30 ጀምሮ፣ እስከምሽቱ፡ 10:30

2. ሰኞ ነሀሴ 6 2011 ዓም
ከጠዋቱ በ2:30 ጀምሮ፣ እስከምሽቱ፡ 10:30

በነዚህ ፕሮግራሞች የሚመቻችሁ በጎ ፈቃደኞች የሚመቻችሁን ቀንና ሰአት ከስምና ስልካችሁን ጋር በ 📞0911 485705 በመደወል ወይም በስልክ ቁጥሩ ቴሌግራም ላይ በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ።

አሊያም፣ በአራት ኪሎ በሚገኘው በትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

#ሼር #share

via ከትምህርት ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኛ ለእኛ"

ሀገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተመዝገቡ👇

0911 485705
@Egnalegnareg


የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ችግረኛ ተማሪዎችን መርዳት፤ በዚሁ መሰረት ፕሮጀክቱ አስካሁን ለተፈናቃይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና የመማሪያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል።

ትምህርት ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
2 ሚሊዮን የሚደርሱ የሃጅ ተጓዦች!

ሳዑዲ አረቢያ ከዕቅዷ በላይ #የሀጅ ተጓዦችን እያስተናገደች መሆኗ ተዘገበ፡፡ ሀገሪቱ ኢቦላን በመስጋት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጓዦችን እንደማትቀበል አስታውቃለች፡፡

2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች በሃጅ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ለመሳተፍ ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል፡፡ የሳዑዲ ሃጂ ሚኒስቴር እንደጠቆመው 1 ሚሊዮን 843 ሽህ 961 የኃይማኖቱ ተከታዮች በሀይማታዊ ክዋኔው ለመታደም ወደ ሀገሪቱ ደርሰዋል፡፡ እንደ ሀገሪቱ ብዙኃን መገናኛ ከሆነ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን አማኞች በሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቱ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ነው የታቀደው፡፡

በምዕራብ ሳዑዲ አረቢያና በሀገሪቱ ቅዱስ ከተማ ከአምስት ቀናት በላይ ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስርዓቶች ይከወናሉ፡፡ በየዓመቱ ከአፍሪካ ሀገራትም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ወደ ሳዑዲ ይጎርፋሉ፡፡ ከሰሜን አፍሪካ ሀገራት ግብፅ፣ አልጄሪያና ሞሮኮ ከፍተኛ ተጓዦች አሏቸው፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ናይጄሪያ ከፍተኛውን የተጓዦች ቁጥር ትይዛለች፡፡ እ.አ.አ በ2017 ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር 79 ሺህ ተጓዦች ወደ ሳዑዲ አቅንተዋል፡፡ በተጠቀሰው ዓመት የአፍሪካ ሀገራት በርካታ ተጓዦችን በመላክ ከ1 እስከ10 ያለውን ደረጃ ይዘው እንደነበርም ይታወሳል፡፡

በዚህ ዓመት የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተጓዦች ወደ ሳዑዲ እንዳይገቡ እገዳ ተጥሏል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢቦላ በሽታ ስለተከሰተባት ነው፡፡ በጣም በፍጥነት ተላላፊው ኢቦላ ለነዋሪዎቿ እና ለምዕመናኑ ሥጋት እንዳይሆን፣ ጤናቸውንም ለመጠበቅ በማሰብ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!

ሕዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ አረፋን በዓል ሲያከብር በወቅታዊ ችግር ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖቹን በማሰብ እንዲሆን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አሳሰበ።

ጉባዔው መላውን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 440ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል አደረሳችሁ ሲል መልዕክት አስተላልፏል። መልካም ምኞቱን ባስተላለፈበት መግለጫም ሙስሊሙ ህብረተሰብ በዓሉን ማክበር ያለበት በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብና ያለውን በማካፈል እንዲሆን አስገንዝቧል።

በተለይም በወቅታዊ ችግር ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ወገኖችን በማሰብ እንዲሆን ነው ያሳሰበው። በዓሉ ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በማጠናከርና ተፈጥሮ የነበረውን መከፋፈል በመፍታት ሁሉን ያካተተ ጠንካራ መጅሊስ እንዲኖር የሚያስችል ስራ በተጀመረበት ወቅት መከበሩ ከቀደሙት ዓመታት የተለየ እንደሚያደርገው ገልጿል። ይህም በመጅሊሱ ታሪክ የነበሩ ክፍተቶችን በመፍታት ለህዝበ ሙስሊሙ ሁለንተናዊ አገልግሎት የሚሰጥ ኢስላማዊ ተቋም እንዲፈጠር የሚያስችል መሆኑን እንደሚገነዘብ ጉባዔው አስታውቋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የታሰሩት የመስጅዱ ወጣቶች ተፈተዋል!

በዛሬው እለት ኢንጂነር ታከለ ዑማ በፈረሰው የአሊፍ መስጂድን በመጎብኘት ቀድሞ መስጊዱ ከነበረበት የ200 እስከ 400 ካሬ ሜትር ስፍራ ምትክ ከአስር እጥፍ በላይ በሆነ በ4ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እንዲሰራ መሬቱን ለአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማንና ለአከባቢው ህብረተሰብ አስረክበዋል። በአዲሱ ስፍራ ላይ ዘመናዊ መስጊድ እስኪሰራ ድረስ መስጊዱ በነበረበት ስፍራ ጊዜያዊ መስጊድ በቆርቆሮ ተሰርቶ ይሰገድበታል። መስጂዱን በህገወጥ መንገድ ያፈረሱት መታሰራቸው እና መስጂዳቸው እንዳይፈርስ ተከላከላችሁ ተብለው የታሰሩት የመስጊዱ ወጣቶች መፈታታቸውን ኢንጂነር ታከለ ዑማ ገልፀዋል። በስፍራውም ህዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ ጠይቀው ህዝበ ሙስሊሙና መንግስትን ለማጋጨት የሚጥሩት እንደማይሳካላቸው ገልፀዋል።

Via አህመዲን ጀበል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰመራ

የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እስላሚክ ሪሊፍ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የአረፋን በዓል ምክንያት በማድረግ 1ሺህ 500 በግና ፍየሎች ለአቅመደካሞች እያከፋፈለ መሆኑን አስታወቀ። ሙስሊሙ ህብረተሰብ የአረፋ በአልን ሲያከብር እርስ-በርሱ በመረዳዳትና ወንድማማችነቱን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ መሳተፍ እንደሚገባው የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዩች ጽህፈት ቤት አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የአብዲ ኢሌ የፍርድ ሂደት!
#አብዲ_ኢሌ

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጉዳያቸውን የሚመረምረውን ፍ/ቤት ነፃም #ገለልተኛም አይደለም ሲሉ ተናገሩ፡፡ የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከዚህ በኋላ ጠበቆቻቸውን እንዳሰናበቱና እንደማይከራከሩ ቢገልፁም ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ቆርጧል፡፡

Via #VOAአማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

1440ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡ በሶላት ወቅትም ሆነ ከሶላት መጠናቀቅ በኋላ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ፖሊስ ኮሚሽኑ ፣ ከከተማው አስተዳደር እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

የዘንድሮው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር ኮሚሽኑ ለወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ስራው ልዩ ትኩረት በመስጠት አብዛኛውን የሰው ኃይሉን በወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከለካከል ተግባር ላይ ማሰማራቱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ከፍተኛ አስተዋእፆ ማበርከቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ የዘንድሮ የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ በተለይ ለሶላት የሚመጡ የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓሉ በሰላም እንዲከበር ለፍተሻ ትብብር እንዲያርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዝግ የሚሆኑ መገዶች!

በአዲስ አበባ ስታዲዬም የሚደረገውን የሶላት ሥነ-ሥርአት ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከቦሌ---ፍላሚንጎ---መስቀል አደባባይ፣ ከባምቢስ ወደ መስቀል ከአደባባይ፣ ከብሄራዊ ቤተ-መንግስት ወደ እስጢፋኖስ፣ ከብሄራዊ ቲያትር-በለገሃር ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል--በጋንዲ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ኮሚሽኑ አሳውቋል።

በመሆኑም ከቦሌ ወደ አራት ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች በኡራኤል--በካሳንቺስ--አራትኪሎ፤ ከመገናኛ ወደ ጦርኃይሎች መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ደግሞ በኡራኤል--ካሳንቺስ--ታላቁቤተ-መንግስት--እሪበከንቱ--ቴዎድሮስ አደባባይ--ኤክስትሪ ምሆቴል--ተክለሀይማኖት--ጣርሀይሎች እንዲሁም ከሳሪስ አቅጣጫ ወደ አራትኪሎ እና ፒያሳ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች ደግሞ ጎተራ--ወሎሰፈር--አትላስሆቴል--ኡራኤል--ካሳንቺስ--አራት ኪሎ ያሉመንገዶችን በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ከበዓሉ ዋዜ ምሽት ጀምሮ የሶላቱ ስነ-ስርዓቱ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ በስታዲዬም ዙሪያ እና አካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም የሚችል መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ለስራው ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...የሀሰት ወሬ ነው!" አቶ ንጉሱ ጥላሁን

"በብሄራዊ ምርጫ ቦርድና በጠ/ሚር አብይ አስተዳደር መሀል ውዝግብ ተፈጠረ" ብሎ Ethio 360 Media ያወጣውን ዘገባ ከእውነት የራቀ መሆኑን ምርጫ ቦርድ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ገልፀዋል።

የምርጫ ቦርድ ቃል-አቀባይ #ሶልያና_ሽመልስ በጉዳዩ ላይ ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ተከታዩን ብለዋል፦

"እንዲህ አይነት ንግግር ምንም የለም፣ አልነበረምም። ሁለት አመት አራዝሙ የሚል ንግግር በመሀከላችን ሊኖር አይችልም። እኛ እንደውም የቀረበ እና ቀጥተኛ ግንኙነት ያለን ከፓርላማው እና ቋሚ ኮሚቴው ጋር ነው እንጂ ከስራ አስፈፃሚው ጋር አይደለም፣ ስለዚህ ሀሳቦች ቢመጡ እንኳን ከፓርላማው ነው እንጂ ከጠ/ሚሩ አይደለም።"

በተጨማሪ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የሰጡት የጠ/ሚሩ ቢሬ ፕረስ ሰክረታሪ አቶ #ንጉሱ_ጥላሁን ይህን ብለዋል፦

"ይህ የሀሰት ወሬ ነው። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ትናንት የወሰነውን ሁሉም ያቀዋል። ጠ/ሚር ቢሮ ምርጫ ይካሄድ ወይም አይካሄድ ብሎ አቅጣጫ አያስቀምጥም። መንግስት ምርጫ እንዲካሄድ እየተዘጋጀ ነው እንጂ እንዲራዘም አቅጣጫ እያስቀመጠ አይደለም።"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia