TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
''ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው'' ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
_______________________________________________

ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 9 ሺህ 637 ተማሪዎች ዛሬ ባስመረቀበት ወቅት ነው።

በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩ ተመራቂዎች የአንዱ ክልል ነዋሪ በሌላኛው ክልል ለመኖር የምትመች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መስራት አለባቸው ብለዋል።

ተመራቂዎቹ እዚህ ለመድረስ ሳይማሩ ያስተማሯቸው ቤተሰቦቻቸው፣ በብዙ መስዋእት ያስተማሯቸው አስተማሪዎቻቸው እና ከበጀቷ ትልቁን በጀት የመደበችላቸው ሀገራቸው ብዙ ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ እንደከፈለችላቸው ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኑሮ ቀንበር ሳይደናገጡ የተከፈለላቸውንም ዋጋ ዋጋ ሳያሳጡ እዚህ መድረሳቸው ለትውልድ መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደሚቻል ማሳያም ነው ብለዋል፡፡

ትልቁ እውቀትን መሸመቻ መድረክ ትምህርት ቤት ቢሆንም ተመራቂዎች ከዩኒቨርስቲ ለቀው ቢውጡም ትምህርት እንደማያቆም የተናገሩት ዶክተር አብይ ተማሪዎቹ ለትዳር፣ ለስራ እንዲሁም ለህይወት ፈተናና ትምህርት እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በቂ ናት ሲሉም ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሀላፊ እና የዑለማ ሀላፊ ለሆኑት ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለሆኑት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷቸዋል፡፡ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና አቶ ተወልደ ገብረማርያም የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን ከጠ/ሚር አብይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደብረ_ብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

ተመራቂዎች በኢትዮጵያ እየታዬ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና ዘረኝነት እንዲታገሉ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳሰበ፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተከታታይ ሶስትና ከዚያ በላይ ዓመታት ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 64 ተማሪዎች ማስመረቁ ታውቋል፤ 1 ሺህ 226 የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ አንዳርጌ ተመራቂዎች ያካበቱትን እውቀት ተጠቅመው ሕዝባቸውን እና ሀገራቸውን በታማኝነት እና በቅንነት እንዲያገለግሉ መልዕክት አስተላፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየታዬ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና ዘረኝነት ለመታገልም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮውን ሳይጨምር ከ26 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋቻሞ_ዩኒቨርሲቲ

ከ23,500 በላይ ተማሪዎችን በዋናው ግቢ፣ በዱራሜ፣ በንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ሆስፒታል እያስተማረ የሚገኘው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ 3,144 ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰላሌ_ዩኒቨርሲቲ

የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ፕሮግራሞችና ሰባት የትምህርት አይነቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ሰለጠናቸውን 198 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነስርዐቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ‘’ተመራቂዎች የሀገራችሁና የራሳችሁ ህይወት ብሩህ እንዲሆን በሀገርና ወገን ፍቅር በማስተዋልና በስራወዳድነት እንዲሁም በማንበብና በመማር ራሳችሁን በማነፅ እንድትኖሩ’’ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በ2009 ዓ.ም የማስተማር ስራውን የጀመረው ዩኒቨርሲቲው በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት እንዲሁም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን አስተምሯል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ መርሃ ግብሮች ከመጀመሪይል እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ9 ሺ800 በላይ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት በዩኒቨርሲቲው ስታዲየም በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከል 28.4% የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ ተነግሯል። በዘንድሮ ዓመት በዩኒቨርሲቲው ለነበረው ፍፁም ሰላማዊ የመማር ማስተር ሂደት የከተማ ማህበረሰብ እንዲሁም አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ላደረገው አስተዋፆ ምስጋና ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

የወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ11ኛው ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4000 በላይ ተማሪዎችን በድምቀት አስመርቋል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በመስጠት ሲሳተፉ ለነበሩ ሁለት ኢትዮጵያዊያን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ክቡር ዶክተር ዘብዲዮስ ጨማ ላለፉት 40 ዓመታት በወላይታ ባህል፣ ቋንቋ፣ እና በወላይታ ታሪክ ላይ በስፋት ለሰሯቸው ስራዎች የእውቅናና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል። ሌላኛው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላቸው ኢትዮጵያዊ ደጃዝማች ወልደሰማያት ገ/ወልድ ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ወልደሰማያት ገ/ወልድ 7ቱን የወላይታ ወረዳዎች በመቆርቆር የሚታወቁ የልማት አርበኛ እንደሆኑ ተነግሮላቸዋል። ህይወታቸውን በሙሉ በወላይታ ውስጥ ሲሰሩ በነበሩ የልማት ስራዎች ላይ ላደረጉት ትልቅ አስተዋፆ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት 4 ሺህ 44 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል👇
___ https://telegra.ph/WSU-07-13 _____
#update የኢፌደሪ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኢንስቲትዩት በማስተርስ ዲግሪና በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 454 ተማሪዎችን አስመረቀ። ኢንስቲትዩቱ  በዕለቱ 218 ሴትና 1ሺህ 236 ወንድ ተማሪዎችን በማስተርስ ዲግሪና በመጀመሪያ ዲግሪ አሰልጥኖ አስመርቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቅድመና በድህረ ምረቃ መርሀ ግብሮች ያስተማራቸውን ዘጠኝ ሺህ 860 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/HU-07-13-2
#Congratulations

በሐረር ከተማ የሚገኘው የሰዎች ለሰዎች የእርሻና የቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ለስድስተኛ ጊዜ #ያሰለጠናቸውን 198 ተማሪዎችን በመጀመርያ ድግሪ ዛሬ አስመርቋል። የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አትሌት ሻለቃ ሐይሌ ገብረስላሴ በምረቃው ስነስርዓት ወቅት “ተመራቂ ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃን በመተውና የበለጸገ አስተሳሰብን በማጎልበት እራስን በስራ የመለወጥ ስራ ላይ ትኩረት መስጠት ይገባቸዋል” ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መሐዲ ጊሬ የአስተዳደሩ ካቢኔ እና የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) አመራሮች ከሥልጣን ሊያፈናቅሉኝ ሞከሩ ሲሉ ወነጀሉ። «እኔ ለሥራ ጉዳይ ከሐገር በወጣሁበት ማግሥት ከሌሎች አካላት ድጋፍ ያገኙ የድርጅታችን አመራሮች የድርጅቱን ውስጠ ደንብ ባልተከተለ መልኩ እኔን ለማፈናቀል ሞክረዋል» ሲሉ ተናግረዋል። አቶ መሐዲ ከሽፏል ላሉት ሙከራ «በጎሳ ግፊት ወደ ሥልጣን የተመለሱ» ያሏቸውን አካላት ተጠያቂ አድርገዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ጉዳዮች ኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ግን ምክትል ከንቲባው ከሥራቸው አለመነሳታቸውን እና አለመታገዳቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። አቶ እስቅያስ እንደሚሉት የአስተዳደሩ ካቢኔ የምክትል ከንቲባውን ጨምሮ የአስተዳደሩ የሥራ አፈፃጸም እንዲገመገም ጠይቋል።

አቶ መሐዲ እንደሚሉት ባለፈው ሳምንት ለሥራ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ውጪ በተጓዙበት ወቅት እርሳቸው አባል የሆኑበት የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች እና የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ከሥልጣን ሊያወርዷቸው ሞክረዋል። «የመሻርም የመሾምም ሥልጣን የሌለው አስፈፃሚ አካል ጋ ቀርቦ ውሳኔ እስከ ማስወሰን ድረስ» ደርሰዋል ሲሉ ከሰዋል።

ከሥልጣን ሊያወርዷቸው የሞከሩት «ከአሁን በፊት ከተማውን ሲያበጣብጡ የነበሩ ከጸጥታ ዘርፍ የተነሱ አካላት፤ በጎሳ ግፊት ወደ ሥልጣን የተመለሱ፣ የከንቲባ ወንበር ይገባኛል የሚሉ እንዲሁም በአመራር ላይ ያሉ ሰዎች» ናቸው ብለዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አምቦ_ዩኒቨርሲቲ

#Congratulations የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺ 600 በላይ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። #AmboUniversity

@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ካንቤቢበእናቶች ዙሪያ የሚያጠነጥን የቴሌቪዥን ሾው ሊጀምር ነው፦

ዝርዝሩን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/C-07-13-8
#አምቦ_ዩኒቨርሲቲ🎓

#Congratulations የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺ 600 በላይ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። #AmboUniversity

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶስተኛው ሀገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ዛሬ ተካሂዷል፡፡ በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር በጋራ ፅዳት በማናወን ችግኝ ተክለዋል። በፅዳት ዘመቻው በተለያዩ አካባዎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የህብረተሰበ ክፍሎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ ከፅዳት ዘመቻው በተጨማሪም የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድምፃዊ ጃሉድ በማረሚያ ቤት የሙዚቃ ኮንሰርት አቀረበ። ድምፃዊ ጃሉድ ከአደንዛዝ እፅ ጋር በተያያዘ የ 6 ወር የእስር ቅጣት ተጥሎበት በማረሚያ ቤት እንደሚገኝ ይታውቃል።

ድምፃዊ ጃሉድ ሸዋሮቢት የሚገኝው የህግ ታራሚዎች ቤት ሲታረም ቆይቷል። ባሳለፍነው ሳምንት በርከት የተለያዩ ሙዚቃዎችን ለታራሚዎች አቅርቧል። ጃሉድ የእስር ጊዜውን ጨርሶ ውጥቷል።

Via @AccessAddis
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert

"ከሆሳዕና አዲስአበባ የሚሄድ መኪና ላይ የደረሰ ግጭት ነው። መንገዱ ተዘግቷል።" #sami

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉበኤውን እያካሄደ ነው፡፡ጨፌ ኦሮሚያ በዚህ ጉባኤው በክልሉ የ70 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ያጸደቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ በተለያዩ ኮሌጆች በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ያሠለጠናቸውን 8 ሺህ 492 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ነው፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia