TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዶክተር #ኤልያስ_ገብሩ የፌስቡክ ገፅ!
.
.
"የሚጓዙት በዝናብ ነው!
የሚጓዙት በምሽት ነው!
የሚጓዙት ለሰላም ነው!
የሚጓዙት ለፍቅር ነውና በውሽንፍሩ መሐል ነጩን የሰላም አርማ ከፍ አድርገው ይዘዋል። ለኢትዮጵያ ለአንድነት እንጓዛለን! እኛ ልጆቿ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም ብለው የተነሱትን የTIKVAH ቤተሰቦች እናመሰግናለን። በሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ሲመጡ የጀግና አቀባበል ይደረግላቸው። ትላንት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ደስ የሚል የአንድነት መንፈስ ፈጥረው ተመልሰዋል። ቀጣይ መዳረሻቸው የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ እንደሆነም አሳውቀዋል።
#ጀግኖቻችን_ናችሁ!
#Keep_Walking #My_Generation"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኤልያስ_ገብሩ

ሰኔ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡40 ሰዓት ላይ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውሎ በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛና የባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ተብሎ የሚጠራው ምክር ቤት ጸሐፊ ኤልያስ ገብሩን፣ ፖሊስ ለምን እንዳሰረውና ከእስር እንደማይለቀው ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ትዕዛዙን የሰጠው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ሲሆን፣ ለትዕዛዙ መሰጠት ምክንያት የሆነው የታሳሪው ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጉ አካልን ነፃ የማውጣት (Habeas Corpus) አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡ጠበቃው የፍትሐ ብሔር ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 177 እና 205 ድንጋጌ መሠረት አድርገው ባቀረቡት አካልን ነፃ የማውጣት አቤቱታ እንዳብራሩት፣ ማንንም ሰው አስሮ ምርመራ የማድረግ ሥልጣን ለማንኛውም አካል የሚሰጠው በግልጽና በሕግ ብቻ ነው፡፡

ጋዜጠኛው ታስሮ የሚገኘውና ምርመራ እየተደረገበት ያለው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሲሆን፣ የተጠረጠረበት የወንጀል ድርጊት ደግሞ የሽብር ወንጀል ነው፡፡ ይህንን የወንጀል ድርጊት ለማጣራት ኮሚሽኑ በሕግ የተሰጠው ሥልጣን ስለሌለ፣ ድርጊቱ ሕገወጥ መሆኑን ጠበቃው ገልጸዋል፡፡ ከፖሊስና ከደኅንነት የተውጣጣና በሕግ ተቋቁሞ ሰው አስሮ የመመርመርና የማጣራት ሥልጣን የተሰጠው አካል እንደሌለ የተናገሩት ጠበቃው፣ ጋዜጠኛው የታሰረው ያለ ሕግ ድግፍ በተደራጀው ግብረ ኃይል በመሆኑ ድርጊቱ ሕገወጥ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Via reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia