TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Breaking

የሶዳን ጦር የሀገሪቱን ብሄራዊ ራዲዮ ጣቢያ መያዙ ተሰምቷል።

የሀገሪቱ ጦር በብሄራዊ ራዲዮ ጣቢያው መግለጫ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።

ከዚያ በተጨማሪም የካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዝግ መደረጉ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ብሄራዉ የቴሌቪዥን ጣቢያም የሀገሪቱ ጦር በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወሳኝ የሆነ መግለጫ ይሰጣል ሲል አስታውቋል።

በርካታ የሱዳን ጦር ተሽከርካሪዎችም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የሚገኙበት ቤተ መንግስትን ከበው መቆማቸውን ነው ምንጮች የገለፁት።

ለወራት ፕሬዚዳንት አልበሽር ስልጣን እንዲለቁ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ በርካታ ሱዳናውያን የሀገሪቱ ጦር እየወሰደ ያለውን እርምጃ ተከትሎም አደባባይ ላይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ነው የተነገረው።

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተደረገባቸው እንደሆነ ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.aljazeera.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይና አቶ ለማ🚁ነቀምት🔝

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ነቀምቴ ከተማ ገብተዋል። በነቀምቴ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም የወለጋ ስታዲየምን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መርቀው እንደሚከፍቱ ይጠበቃል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝

የመብት እና ደህንነት ጥያቄዎች አሉብን ያሉት የጅማ ዩኒቨሲቲ የህክምና ተማሪዎች ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ::

ዘርዝር መረጃዎች ይኖረናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስብሰባውን ጥለው ወጥተዋል...

ጥያቄዎቻችን በአግባቡ እየተመለሱ አይደሉም ያሉት የህክምና ተማሪዎቹ ስብሰባውን ጥለው ወጥተዋል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነቀምቴ ከተማ ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነበው የወለጋ ስታዲየም የምረቃ ስነ ስርዓት እየተከሄደ ነው፡፡ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ተገኝተዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia