TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች:

•Doctors are naive:talented:symbolic: over all jewel to our society —
No More
*Disregarding
*ExploItation
*Abuse
*Insult

#stop_modern_slavery

•Treat us like human so that we can treat humans.
#Stop Mistreating Medical interns & Medical Students

•Medical Interns are not #machine can’t function 36 HRs sleeplessly!!

We should be Paid what we deserve!!

ተማሪዎቹ እያነሱት ባለው የመብት እና ደህንነት ጥያቄዎች ላይ ምላሽ የሚሰጥ አካል ካለ ሊያነጋግረን ይችላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳውን እሳት ለመቆጣጠር የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ከኬኒያ ለማስመጣት ሂደት መጀመሩ ተነግሯል፡፡

የእሳት ማጥፊያ ሂሊኮፕተር ከኬኒያ የሚያስመጣው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ነው ተብሏል።

ሂሊኮፕተሩን በቶሎ ወደ ሀገር ቤት ለማስመጣት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከኬንያ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከሳምንት በፊት በፓርኩ በተነሳው እሳት ከ342 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል እንደተጎዳ ይታወሳል።

ምንጭ - አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እሳት የተነሳባቸው አካባቢዎች ዋሊያዎች የሚኖሩበት ቦታ አለመሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ከኬንያ ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። ኬንያ ፈቃደኛ መሆኗንና የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተሩን በቶሎ ለማስመጣትና ቃጠሎውን ለመቆጣጠርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከኬንያ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑም ታውቋል።

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት...

"አሁን በደረሰኝ መረጃ መሰረት ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር እንዲገዛ #ትእዛዝ ሰጥተው የሚመለከተው አካል ግዢውን ለመፈፀም እየተነጋገረ ነው፡፡ "የሂሊኮፕተሩ ግዢ ተጠናቆ በቅርቡ ወደ ሀገር እንደሚገባ ተስፋ ተደርጓል" ብለው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰብ ከደቂቃዎች በፊት ነግረውኛል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኦሮሚያ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ ለሚገነባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ። በ20 ሚሊየን ብር ሚከናወነው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ግንባታ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ🗓 የፊታችን እሁድ በመላ ኢትዮጵያ የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል፡፡ እሁድ ሚያዚያ 6/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡ 30 ጀምሮ የሚካሄደውን የጽዳት ዘመቻ የጠሩት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ናቸው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ስልጣን መልቀቃቸው ተገለፀ።

የሀገሪቱ ጦር አሁን ላይ ባወጣው መግለጫ ሱዳንን ለሶስት አስርት አመታት ሲያስተዳደሩ የነበሩት ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን መውረዳቸውን አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም ሀገሪቱን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድር የሽግግር መንግስት መቋቋሙን ጦሩ አስታውቋል።

በሱዳን ከወራት በፊት በዳቦ ዋጋ መጨመር ምክንያት የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ በቅርቡ አድማሱን አስፍቶ ፕሬዚዳንት አል በሽር ከስልጣን እንዲወርዱ መቀየሩ ይታወሳል።

በዛሬው ዕለትም የአልበሽርን ከስልጣን መው ረድ ተከትከሎ ዜጎች በተለያዩ የሀገሪቱ ከተማዎች በአደባባይ በመውጣት ደስታቸውን እገለፁ ይገኛሉ።

ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1989 ጀምሮ ላለፉት 30 ዓመታት ሀገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል።

ምንጭ ፦ አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia