TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሱዳን ፖሊስ አባላት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ ታዘዙ‼️
.
.

የሱዳን ፖሊስ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወስድ አባላቱን አዘዘ።

ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ከአርብ ዕለት ጀምሮ በጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።
ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺር ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ ናቸው።

ቀደም ብሎ ከዋና መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውጪ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ የተሰማ ሲሆን ይህ የሆነውም ወታደሮች ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ላይ የመንግሥት የደህንነት ኃይሎች እንዳይተኩሱባቸው ሲከላከሉ እንደሆነ ተሰምቷል።

የፖሊስ ቃል አቀባይ ባወጣው መግለጫ "ሁሉንም አባላቱን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እንዳይተኩሱ ታዟል።" ብሏል።

"ፈጣሪ ሀገራችንን እንዲያረጋጋ እና ደህንነታችን እንዲጠብቅ .... ሱዳናውያን አንድ እንዲያደርገን....ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር መግባባት ላይ እንድንደርስ እንፀልያለን"ብለዋል በመግለጫቸው።

ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ለመበተን የሞከሩ የብሄራዊ ፀጥታና ደህንነት አባላት ከወታደሩ ጋር መጋጨታቸው ተዘግቧል።

የተቃውሞ ሰልፉ ከተጀመረ ቢያንስ ሁለት ወታደሮች ከዋና መስሪያ ቤቱ ውጪ መሞታቸው ተዘግቧል።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰባት ተቃዋሚ ሰልፈኞች መሞታቸውን 15 መጎዳታቸውን እና 42 የደህንነት ኃይሎች መጎዳታቸውን ገልፀው ነበር።

2ሺህ አምስት መቶ ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

ከተቃዋሚ ሰልፈኞቹ አንዱ ለቢቢሲ እንደገለፀው ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ፣ ጥይት በደህንነት ኃይሎች ተተኩሷል።

ወታደሮችም ተቃዋሚ ሰልፈኞችን በግቢያቸው እንዲደበቁ እንደረዷቸው ተናግሯል።

አክሎም "ኦማር አል በሺር ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን ከአደባባዮች ላይ ዞር እንዲሉ ለማድረግ መሞከራቸው እርባና ቢስ ነው ምክንያቱም የትም አንሄድም " ብሏል።

ሌላ ተቃዋሚ ሰልፈኛ በበኩሉ ሁሉም የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹን እንደማይደግፉ ገልጧል።
ከፍተኛ ሹማምንቶቹ አሁንም ፕሬዝዳንቱን የሚደግፉ ሲሆን አነስተኛ ማዕረግ ያላቸውና ተራው ወታደርና አባል ግን ከሕዝቡ ጋር ነው ሲል ለቢቢሲ አስረድቷል።

አሜሪካ፣ እንግሊዝና ናርዌይ ሱዳን የፖለቲካ ሽግግር ለማድረግ መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም...

ካለፈው አርብ ዕለት ጀምራ ላለፉት ሁለት ቀናት አንፃራዊ የሰላም እጥረት አጋጥሟት የነበረችው ደሴ ወደ ቀድሞ #ሰላሟ ተመልሳለች፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሕዝቡ ወደቀየው #መመለስ ጀምሯል፤ ግን ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡››

‹‹ችግሩን ለመፍጠር ካስፈለገው ምክንያት አንፃር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ሊሠራልን ይገባል፡፡›› የአጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራቆሬ ነዋሪዎች
.
.
.
ሰሞኑን በሰሜን ሽዋ ዞን አጣዬ፣ ማጀቴ እና ካራ ቆሬ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት እና ንብረት ጠፍቷል፡፡ በችግሩም ከቀያቸው ውጭ የተሰደዱ ዜጎች እንዳሉ አብመድ ከአካባቢዎቹ ነዋሪዎች አረጋግጧል፡፡

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊው አቶ ሰለሞን አልታየ ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ረፋዱ ድረስ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ዳግም በከተማዋ መኖሩን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በግጭት ስጋት ከቀያቸው ሸሽተው የነበሩ ወገኖቻችንም መመለስ ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ዜጎቹ ቢመለሱም ሀብት ንብረታቸው በመዘረፉ ለዕለት ሊበሉ የሚችሉት እንኳ ባለመኖሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታነቱን እንዲያሳይ እጠይቃለሁ ነው ያሉት፡፡ በአከባቢው የመከላከያ ሠራዊት ሰላም የማስጠበቅ ሥራ እየሠራ ነው፤ በዘላቂነት ከሚነሳው እና ከሚታየው ሐሳብ አንፃር የቀጠናውን ሰላም ለማስጠበቅ እና ከመሰል ድርጊቶች ለመጠበቅ የመከላከያ ሠራዊት ካምፕ በአቅራቢያው ሊኖር እንደሚገባም አቶ ሰሎሞን ተናረዋል፡፡

በማጀቴ ከተማ ውስጥ በሕመም ምክንያት ከመንደራቸው እንዳልወጡ የነገሩን ወይዘሮ ፋጤ ደሳለኝ ከትናንት ጀምሮ እስከ ርፋዱ ድረስ ያለው የአካባቢው ሁኔታ ሰላማዊእደሆነ ነግረውናል፡፡ ሕዝቡም ሰላማዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው የገለጹልን፡፡

የካራ ቆሬ ነዋሪው አቶ ደንበሬ ገብረማሪያም ደግሞ ‹‹ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ 5፡30 ድረስ አካባቢው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊትም እየተዘዋወሩ ሰላማችን እየጠበቁልን ነው፡፡ ሕዝቡም ስለ አጥፊዎቹ ሙሉ መረጃ ለመስጠት ዝግጁ ነው›› ብለዋል፡፡ አቶ ደንበሩ ከተለያዩ አጎራባች ከተሞች እና በየተራራው የነበሩ ዜጎች እየተመለሱ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን የተመላሾቹ መኖሪያ ቤት እና የንግድ ተቋማት ሙሉ በሙሉ በግጭቱ ቀናት በመዘረፉ እና በመውደሙ የዕለት ጉርስ የላቸውም፤ እነዚህን በዘላቂነት ለማቋቋም መንግሥት እና የኢትዮጵያ ሕዝብ አስቸኳይ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል›› ብለዋል፡፡

ችግሩን ለመፍጠር ካስፈለገው ምክንያት አንፃር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ሊሠራልን ይገባልም ብለዋል አቶ ደንበሩ፡፡

በከተማዋ ግጭት ለፈጠሩ ኃይሎች መረጃ አቀባዮች በመኖራቸው የአካባቢው ሕዝብ ወደመደበኛ ሥራው ለመመለስ በመቸገሩ አጥፊዎችን የመያዝ እና ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር የማድረግ ኃላፊነት ወስዶ መንግሥት ሊሠራ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ🚍በዚህ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ(ሚያዚያ 5 እና ሚያዚያ 6) #StopHateSpeech

ተዘጋጁ!!

#ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ ----- ሚያዚያ 12 እና 13
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቢሾፍቱ አቅራቢያ የዛሬ አንድ ወር በተከሰሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች ዛሬ የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ የተከናወነው በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ውስጥ ነው።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከባቲ- ከሚሴ በአንድ ግለሰብ ሲዘዋወር የነበረ 880 የክላሽ ጥይት ኮምቦልቻ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ያለለት ዘገዬ ለአብመድ እንደተናሩት ዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ረፋድ ላይ 880 የክላሽ ጥይቶችንና 400 ሺህ ብር የያዘ የባንክ ደብተር ይዞ ሲጓዝ የነበረ ግለሰብ መናኸሪያ ባሉ ተራ አስከባሪዎች እና የትራንስፖርት ባለሙያዎች ተይዞ ለፖሊስ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡

አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ደግሞ ግለሰቡ 8 ሺ 150 ብር በካሽ፣ የሞባይል ካርድና ፓስፖርት ይዞ መገኘቱን ተናግረዋል::

በአካባቢው ሰላም የሚያውኩ ድርጊቶች እንዳይፈጠሩ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ፀረ ሽምቅ፣ ሚሊሻ እና የአካባቢው ፖሊስ ተሰማርቶ እየጠበቀ እንደሆነም ኮማንደር ያለለት ተናግረዋል፡፡ ወደ አካባቢው የሀገር መካለከያ ሠራዊት እንደገባም ለአብመድ አስታውቀዋል፡፡

አካባቢው #ትልልቅ ድርጅቶች የሚገኙበት በመሆኑም ጥቃት እንዳይደርስባቸው ከወጣቱ እና ከአካባቢው ማኅረሰብ ጋር በመተባበር ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሆነ ነግረውናል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ኮማንደሩ አስታውቀዋል፤ ኮምቦልቻ እና አካባቢዋ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር ባይኖርም #ስጋት ለመቅረፍ #መከላከያ በአካባቢው መኖሩን ኮማንደሩ አመልክተዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ዳግም ያገረሸውን የእሳት ቃጠሎ በማስነሳት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንድ የአካባቢው ባለስልጣን ተናገሩ። ካለፈው ሰኞ አመሻሽ ጀምሮ እንደገና የተነሳው እሳት በፓርኩ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል።

በአማራ ክልል የደባርቅ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምርኩዝ ዋሴ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት በፓርኩ ላይ “ሆን ብለው እሳቱን ለኩሰዋል” የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ስለ ተጠርጣሪዎቹ ብዛትም ሆነ እንዴት ቃጠሎው እንደተነሳ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት የወረዳው አስተዳዳሪ በአሁኑ ወቅት በፓርኩ ውስጥ “እሳቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቀጣጠለ” እንዳለ አስረድተዋል።

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የህብረተሰብ እና ቱሪዝም ሀብት ኃላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው ቃጠሎው እንዴት ተነሳ የሚለውን ለማወቅ “አሁን ጊዜው ገና ነው” ብለዋል፡፡ ቃጠሎው በንፋስ ታግዞ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ እንዳለ እና እሳቱን ለማጥፋት በመረባረብ ላይ እንደሆኑም ገልጸዋል።

ባለፈው መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም በፓርኩ የተነሳው እሳት ለሳምንት ያህል ቆይቶ መጥፋቱ አይዘነጋም። በወቅቱም ከ342 ሄክታር በላይ የፓርኩ ክፍል ተቃጥሏል፡፡ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 30 አመሻሽ ላይ እንደገና ያገረሸው የእሳት ቃጠሎ ምን ያህል ውድመት እንዳደረሰ እስካሁን እንደማይታወቅ ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

Via #ዶቼ_ቨለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀጠሎ ወደ #ገደላማው የፓርኩ ክፍል በመግባት ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል፡፡ ከፓርኩ ግጭ አካባቢ የተነሳው እሳት በርካታ አካባቢዎችን እያዳረሰ ወደ ፓርኩ ሰሜን ምዕራባዊ አቅጣጫ ገደላማ ክፍል ወርዷል፡፡ አሁንም በሰው ኃይል ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ መንግስት ከኔዘርላንድ መንግስት ጋር በመተባበር በ877 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ በአለርቲ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በአይነቱ ልዩ እና የመጀመሪያ የሆነ አዲስ የህፃናት አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በሀገሪቱ በሚከሰተው የጸጥታና ተያያዥ ችግር ሣምንትን ያለ #ክፉ ዜና ማለፍ እየከበደ መጥቷል..." የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፅዳት ዘመቻ...

በኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ በሁሉም ከተሞች፣ መንገዶች እና ሰፈሮች የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በትናትናው እለት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ሚያዚያ 6 ቀን 2011 በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል፡፡

ይህ የፅዳት ዘመቻ በመላ ሀገሪቱ እሁድ ጠዋት 1፡ 30 ጀምሮ እስከ ሶስት እንደሚካሄደ የወጣው መርሃ ግብ ያመለክታል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ባስተላለፈው ጥሪ የምናጸዳው በክብርና በንጹሕ አከባቢ መኖር መብታችን እንደሆነ ስለምናምን ነው ብሏል፡፡

ፅህፈት ቤት የምናጸዳው ለጤናችን ነው፤ማጽዳትም ኃላፊነታችን ስለሆነ ሲል ጥሪ አቀርቧል፡፡

ለኢትዮጵያ ጽዳት በአንድነት እንነሳ በማለት ጥሪ ይስተላለፈው ፅህፈት ቤቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለአካባቢ ፅዳት በአንድነት መነሳት እንዳለባቸው ጠቁሟል፡፡

በትናትናው ዕለት መልካም አስተሳሰብን ለመስበክ የሚያግዝ የጽዳት ዘመቻ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሀገሪቱ በሚከሰተው የጸጥታና ተያያዥ ችግር ሣምንትን ያለ ክፉ ዜና ማለፍ እየከበደ መጥቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ችግሮችን ባሉበት ለማቆምና እንዳይዛመቱ ለማስቻል ቀና ማሰብ ስለሚያስፈልግ በመጪው እሁድ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የጽዳት ዘመቻ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia