TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ትላንት ምሽት በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ቁጥጥር ስር ውሏል። ትናንት ምሽት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ ጌትነት ይግዛው በተለይ ለኢቢሲ እንደገለፁት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስዔ ሰዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ምሽት በመሆኑ ቃጠሎውን የፈጸሙ ግለሰቦችን ለጊዜውም ቢሆን ቁጥጥር ስር ማዋል እንዳልተቻለ አቶ ጌትነት ተናግረዋል፡፡በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ባለፈው አመትም በከፍተኛ ደረጃ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበርና ይህንን ችግር በቋሚነት ለመፍታት መስሪያ ቤታቸው እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopi
ሞህ ፋራህ ...ተዘረፍኩኝ አለ!

እንግሊዛዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ሞህ ፋራህ ልምምድ ለማድረግ ባረፈበት ያያ አፍሪቃ የአትሌቲክስ መንደር መዘረፉን አስታወቀ። ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ የሚገኘው ያያ አፍሪቃ የአትሌት ሀይሌ ገብረስላሴና (ሸሪኮቹ) ንብረት የሆነ የአትሌቲክስ መንደር ነው።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያያ ቪሌጅ ሪዞርት ማናጀር ዛሬ ጠዋት በስልክ በአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ የሚከተለውን ብለዋል፦

"ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አምስት የሪዞርቱ ሰራተኞች በጥርጣሬ ተይዘዋል። እነዚህ በወቅቱ የሆቴል ክፍሎችን ቁልፎች ይዘው የነበሩ ናቸው። አሻራ እና ቃል ሰጥተዋል። ምን ያህል ብር እንዲሁም ምን አይነት የእጅ ሰአት እንደተሰረቀበት አላወቅኩም። ሆቴሉ ካሜራ የለውም ስለዚህ ሰራተኞቹ በጥርጣሬ ነው የተያዙት። ሞ ፋራህ አሁንም በሪዞርቱ ይገኛል። ነገር ግን ፌስቡክ ላይ እንደፃፈው ሳይሆን እኛ በጣም ተባብረነዋል። ሶስት እና አራት ግዜ በየቀኑ ፖሊስ ጣብያ እኔ እራሴ እየተመላለስኩ ነበር። የምርመራው ውጤት እስኪያልቅ ትብብራችንን እንቀጥላለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዋሳ ድምፅ FM 97.7‼️

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ በ‹‹ ትራንስሚተር ›› #ብልሽት ምክንያት #አስር_ወራትን ያለ ሥርጭት ማሳለፉን የዩኒቨርሲቲው የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ወይዘሮ #አርማዬ_አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ በ‹‹ ትራንስሚተር ›› ብልሽት ምክንያት ለአስር ወራት ያህል አገልግሎት እንዳልሰጠና መረጃዎችን በተገቢው ለማኅበረሰቡ ማድረስ ባለመቻሉ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ገልፀዋል፡፡ ጣቢያው ለረጅም ወራት አገልግሎት እንዳይሰጥ የተደረገውም የመሣሪያ ግዥ ሂደቱ ሰፊ ጊዜን በመውሰዱ ምክንያት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሯ ማብራሪያ፤ መሣሪያው ብልሽት በደረሰበት ወቅት በባለሙያዎች ተመርምሮ ሲጣራ መቀየር እንዳለበት ታምኗል፡፡ ማሣሪያውን ለመቀየር ዩኒቨርሲቲው ቀጥታ ግዥ ማድረግ ስለማይችል ሦስት ጊዜ ጨረታ ቢወጣም ብቸኛ የጨረታ አቅራቢ አንድ ሰው ብቻ ስለነበር እንዳይካሄድ ተደርጓል፡፡ በዚህም የግዥው ሂደት ጊዜ በመውሰዱ ጣቢያው ለረጅም ወራት አገልግሎት እንዲያቆም ተገልጿል፡፡

የማኅበረሰብ ራዲዮ ጣቢያው ያለ ሥርጭት መቆየቱ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ያሉት ወይዘሮ አርማዬ፤ ጣቢያው ሲቋቋም ዩኒቨርሲቲው እየሠራ ያለውን ጥናትና ምርምር እንዲሁም መሠረታዊ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ ለማድረስና ራሱን የሚያስተዋውቅበት መድረክ እንደመሆኑ አገልግሎት አለመስጠቱ መረጃዎችን በተገቢው ለማኅበረሰቡ ማድረስ ባለመቻሉ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም ተናግረዋል፡፡

የማኅበረሰብ ራዲዮ ጣቢያው ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ለጥናትና ምርምር፣ ለማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም ለመማርና ማስተማር ሥራዎች ድጋፍ ስለሚያደርግ ትኩረት ተሰጥቶት መሣሪያው መገዛት እንዳለበት ታምኖ ለግዥ ኤጀንሲ ደብዳቤ በመጻፍ በውስጥ ጨረታ እንዲገዛ ፈቃድ መሰጠቱን ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም አቅራቢ ድርጅቱ ውል መፈፀሙንና በቅርብ ቀናት ውስጥ ማሣሪያው ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደሚገባ፤ ለግዥውም ሦስት ሚሊዮን ብር ወጭ መደረጉን፤ የሥርጭት አገለግሎቱም በቅርቡ እንደሚጀመር ተናግረው፤ ከመሣሪያ ግዥው በተጨማሪ በቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ገብረጊዮርጊስ አብርሐ በበኩላቸው፤ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የማኅበረሰብ ራዲዮን በሚመለከት በ‹‹ ትራንስሚተር ›› ብልሽት ምክንያት አስር ወራትን ከአገልግሎት ውጭ መሆኑ በብሮድካስት ባለሥልጣኑ በኩል እንደሚታወቅ ገልፀዋል፡፡

የጥገናና ተከላው ሥራ የባለ ሥልጣኑ ድርሻ አለመሆኑንና፤ ነገር ግን የራዲዮ ጣቢያዎች እንዲህ ዓይነት እክል ሲያጋጥማቸው በውስጥ ሙያተኞች የሚስተካል ከሆነ ሥራውን ማከናወን የሚችሉ ባለሙያዎች እገዛ እንዲያደርጉላቸው፤ በሌላ መልኩ ሥራው በአገር ውስጥ ባለሙያዎች ብቻ የማያልቅ ከሆነ በተለይም መሣሪያዎች በጨረታ የሚገዙ ከሆነ ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ምክር እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድም ባለሥልጣኑ ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተኮር ራዮ ጣቢያ ድጋፍ ማድረጉን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

‹‹የአየር ሰዓት እንኳን አስር ወር ይቅርና አስር ሴኮንድም ቀላል አይደለም›› ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የተለመደ ሥርጭትና ህዝባዊ አገልግሎት ያለው ሚዲያ ከአገልግሎት ውጭ ሲሆን ተጽዕኖው ቀላል አለመሆኑን ጠቁመው፤ ህዝቡ የመረጃ ባለቤት መሆን እንዳለበትና የተቋቋመውን ማኅበረሰብ ተኮር ራዲዮ ጣቢያ ምንም እንኳን የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ በበላይነት የያዘው ቢሆንም፤ አገልግሎቱ የህዝብን የመረጃ ማግኘት ባለቤትነት ማረጋጋጥ ጉዳይ ስለሆነ፤ ፈልገው ያደረጉት ባይሆንም ይህን ያህል ጊዜ አገልግሎት አለመስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ አመላክተዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ የእኔም ናት- ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፦

"የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት 50 ላላነሱ ዓማታት በብዙ መከራና ስቃይን አይቷል የተሸለ የፖለቲካ ስርአትን ተመኝተህ፣ ከዛ የባሰ የፖለቲካ ስርአት እያገኘህ ፣መከራ ስታይ ፣ልጆችህ ሲጨፈጨፉና በየእስር ቤቱ ሲንገላቱ፣ በደምና በዕንባ ስትራጭ ኖረሃል፡፡ ስለዚህ ይህ ለውጥ የመጨረሻ እድላችን የተሸለ እንዲሆን፣ በሙሉ ልብህ፣ ከቀልባሽ ሀይሎችምና ለስልጣን ብለው ከሚልከሰከሱ ሀይሎችም፣ በመጠበቅ ትግሉን የተሸለ እንዲሆን ፣ ለነገው ትውልድ ነፃ ኢትዮጵያ እንድትፈጠር፣ ሁላችንም በእኩልነት የምንኖርባት ብቻ ሳይሆን ልጆቻችንም የሚኖሩባት፣ የተሸለች ኢትዮጵያን እንድትፈጠር፣ አንተም የፖለቲካ ሀይሎችም አቅጣጫ እንዲይዙ ፣ የመቻቻል ፖለቲካ እንዲፈጠር ፣ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫ በሀገራችን እዲሰፍን፣ በዚህ ነፃና ፍትሀዊ ምርጫም ድሞክራቲክ ኢትዮጵያ እንድትወለድ፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዚህ አስተዋፅኦ እንድታደርጉ አደራ እላለሁን፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake-photoshop‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአቶ በረከት ስምዖንና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ ሲደረግ የቆየው ምርመራ መጠናቀቁን የባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የክልሉ ፀረ-ሙስና መርማሪ እና ዐቃቤ ህግ ያቀረቧቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡ ዐቃቤ ህግ ክስ የመመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ የጠየቀ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ በበኩላቸው ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡ እንደ ኢቢሲ ዘገባ የፀረ-ሙስና ዐቃቤ ህግ በፈለገው ጊዜ ክስ መመስረት እንደሚችልም ችሎቱ አመልክቷል፤ ተጠርጣሪዎቹም የዋስትና መብታቸውን መጠየቅ እንደሚችሉም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

ትናንት ሌሊት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተነሳው እሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአካባቢ፣ ደን እና ዱር አራዊት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣን ከተናገረ በኋላ ዛሬ እንደገና አገርሽቷል፡፡ ቃጠሎው #እንደገና የተነሳው እሜትጎጎ በተባለ አካባቢ መሆኑን የአማራ መገናኛ ብዙኻን የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወርቁ ለምለሙን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ቃጠሎው በንፋስ ታግዞ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ነው፡፡ የክልሉ ልዩ ሃይል ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሷል፤ ወጣቶች እና አርሶ አደሮች እሳቱን በአፈር እና ቅጠል ለማጥፋት ጥረት ላይ ናቸው፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቃጠሎው ቀጥሏል🔝

ትናንት ምሽት የጀመረው የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቃጠሎ አሁንም ከቁጥጥር ውጭ ሐሆኑ ታውቋል። በፓርኩ በእሳት ማጥፋት ሲሳተፉ የዋሉ ወጣቶች እንደተናገሩት በእሜትጎጎ
አካባቢ ያለው እሳት ወደ ገደላማ አካባቢዎች በመግባቱ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል።

ወጣቶቹ ለአብመድ በሰጡት አስተያዬት "ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በአራት አይሱዙ ሄደን ለማጥፋት ጥረት አዶርገናል፤ ግን ወደ ረፋድ ተቆጣጥረነው የነበረ ቢሆንም ቀትር ላይ እንደገና ተነስቷል፤ ከድካም ጋር ተዳምሮም አይሎን ወደ ገደሉ ወርዷል"ብለዋል።

በአውሮፕላን የታገዘ የመቆጣጠር ሥራ ካልተሠራ እሳቱ የፓርኩን ኅልውና አደጋ ውስጥ እንደሚጥለውም ወጣቶቹ ተናግረዋል።የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ደግሞ እሳቱ በፓርኩ ላይ የከፋ አደጋ እያደረሰ በመሆኑ የመንግሥትን ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚሻ አስታውቀዋል።

እሳቱን ሳንቃ በር አካባቢ በሰው ኃይል ለመቆጣጠር እንደሚቻል የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው እሜትጎጎ አካባቢ ግን ከአቅም በላይ መሆኑን አስረድተዋል። የፌዴራል የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ግን አሁንም በሰው ኃይል ለመቆጣጠር መጣር የተሻለ አማራጭ መሆኑን ነው ያስረዱት።

"በአውሮፕላን ለመቆጣጠር መሞከር የተሻለ አማራጭ ነው፤ ግን እንደ ሀገር የእሳት መቆጣጠሪያ አውሮፕላን የለንም። ያላቸው ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ናቸው። የሚጠይቀውን ከፍተኛ ወጭ እንኳ ችለን ብንከራዬው ሂደቱ ቀናትን ይወስዳል። ስለዚህ በሰው ኃይል ለመቆጣጠር መሞከሩ ይሻላል" ነው ያሉት።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውሮፕላን ውስጥ መንትያ ልጆች የተገላገለችው ኢትዮጵያዊት አዲስ አበባ ገብታለች‼️
.
.
ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ በነበረ የሳውዲ ዓረቢያ አውሮፕላን ተሳፍራ እዛው አውሮፕላኑ ውስጥ መንታ ሴት ህፃናት በመውለዷ አስመራ ዓለምቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንድታርፍ የተደረገችው ኢትዮጵያዊት እናት ዛሬ አዲስ አበባ ገባች።

በሥራ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ መዲና ከተማ የምትኖረው የ35 ዓመቷ ወይዘሮ ጀነት ሁሴን የስምንት ወር ነፍሰ ጡር በመሆኗ አገር ቤት ለመዉለድ ነበር ባለፈው መጋቢት 13 ቀን 2011 ዓም በሳዑዲ አየር መንገድ የተሳፈረቸው።

ሆኖም እርሷ ያሰበችው ሳይሆን ቀረና ከጊዜዋ ቀድማ መንትያ ሴት ልጆቿን መንገድ ላይ ተገላግላለች።

ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው፦

አውሮፕላኑ በኤርትራ አየር ክልል ውስጥ እንደገባ ነበር ወይዘሮ ጀነት በድንገት ምጥ የያዛት።

እናም ፖይለቱ ከኤርትራ አየር ተቆጣጣሪዎች ጋር በመነጋገር አውሮፕላኑ አስመራ አየር ማረፊያ እንዲያርፍ ተደረገ።

አንዷ ህፃን ወደዚህ ምድር የተቀላቀለችው አውሮፕላኑ አየር ላይ እያለ ሲሆን ሁለተኛዋ ግን አውሮፕላኑ እንዳረፈ ነበር የተወለደቸው።

መንታ ልጆቿን ይዛ ዛሬ አዲስ አበባ የገባችው ወይዘሮ ጀነት ለጋዜጠኞች በሰጠችው ቃል አውሮፕላን ውስጥ ከተሳፈረች በኋላ ባልጠበቀችው ሁኔታ ምጥ እንደጀመራት ነው የገለጸችው።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያዊያን መርማሪዎች ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከመከስከሱ በፊት MCAS የተሰኘው የበረራ ተቆጣጣሪ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ ውሎ እንደነበር ጊዜያዊ ድምዳሜ ላይ እንደደረሱ ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል፡፡ መረጃው ትክክል ከሆነ አውሮፕላኑ አፍንጫን ዘቅዝቆ እንዲከሰከስ ያደረገው ይሄው ሶፍትዌር ይሆናል፡፡ በሌላ ዜና አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በብልሹ ሶፍትዌር ሳቢያ ነው በማለት ቦይንግ ኩባንያ በአሜሪካ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ከሳሾቹ በአደጋው የሞተው የሩዋንዳዊው ጃክሰን ሙሶኒ ቤተሰቦች መሆናቸውን ጋርዲያን አስነብቧል፡፡ የአደጋው ተጎጅ ቤተሰቦች በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች በኩባንያው ላይ ክስ መመስረት እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Ethiopia_ጀዋር_እና_እስክንድር_በDW_የአዲስ.mp3
14.9 MB
ጀዋር መሀመድ እና እክንድር ነጋ በDW የአዲስ አበባ የባለቤትነት ዉዝግብ፦

«እኛ የምንለዉ ሕጉ የሚለዉን ነዉ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሕግ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ነች ይላል። የፌደራሉ ሕገ መንግሥትም ኦሮሚያ (ከአዲስ አበባ) ልዩ ጥቅም እንዳለዉ ያስቀምጣል------»የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅና የመብት አቀንቃኝ #ጀዋር_መሐመድ

«የአዲስ አበባ ጉዳይ የዜግነት ጥያቄ ነዉ-----ሕገ መንግስቱ ከየት መጣ? ማን አወጣዉ? ምንስ አላማ ነበረዉ?------» ጋዜጠኛና የመብት አቀንቃኝ #እስክንድር_ነጋ

«እንዴ!! ምነዉ እባክሕ? እስክንድር ነጋ እኮ የመብት ታጋይ ነዉ----ልንቃወመዉ፣ ልንተቸዉ እንችላለን፣ ከዚያ ባለፈ ግን ዛሬ እስክንድርን ያስፈራሩ ነገ ጀዋርን #ያስፈራራሉ-----እስክንድር ብቻዉን ሳይሆን ሁላችንም አብረነዉ ተሰልፈን እንታገላለን----»ጀዋር መሐመድ

ጀዋር ያለዉን «የምጠራጠርበት ምንም ምንም ምክንያት የለኝም። #አመሰግነዋለሁ።-------»እስክንድር ነጋ።

«በግሌ ከጠይቀከኝ ከእስክንዳር ጋር አይደለም ከማንም ጋር በማንኛዉም ሰዓት በዚሕ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላም ጉዳይ ላይ ለመወያየት ዝግጁ ነን----»ጀዋር መሐመድ

«ለመወያየት መቶ በመቶ ዝግጁ ነኝ። እምንፈታዉም በድርድርና ዉይይት ነዉ።----ብስለቱም አለን» እስክንድር ነጋ።

Via የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia