TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሸዋሮቢት~መንገዶች ተከፍተዋል‼️

በሸዋሮቢት ከተማ የተከስቶ የነበረው #አለመረጋጋት በአሁኑ ሰዓት ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የሸዋሮቢት ከተማ ከንቲባ አቶ #አካሉ_ወንድሙ ተናገሩ።

እንደ ከንቲባው ገለጻ በአሁኑ ሰዓት የተዘጉ መንገዶች #ተከፍተው የጸጥታ ሀያሉ እና የአካባቢው ማህበረሰብ መንገደኞችን #በመሸኘት ላይ መሆናቸውን ተናግረው የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ #መቻቻልና #መረዳዳት ባህሉና ወጉ የሆነው ህዝባችን ድርቶችን ሁሉ በተለመደውን የችግር መፍቻ መንገዶችን፣ ህግን በማክበርና በማስከበር ስራ ላይ #ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የጸጥታ ሀይሉ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሀገር ሽማግሌዎች ከተማውን #ለማረጋጋት ላያደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። በአሁኑ ሰዓት ሽዋሮቢት ወደነበረችበት #ሰላምና መረጋጋት እየተመለሰች መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።

Via Shewa Robit City Administration Kentiba office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሸዋሮቢት ከተማ ፖሊስ‼️

ትላንት በሸዋሮቢት ከተማ ተፈጥሮ የነበረው #አለመረጋጋት ሙሉ በሙሉ ተወግዶ ዛሬ ሸዋሮቢት ወደነበረው ሰላሟ ተመልሳ ማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆኑን #የሸዋሮቢት_ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር #ሞገስ_ባየህ እንደገለፁት ማህበረሰቡ በአሁን ሰአት በተሰማራበት የስራ መስክ በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቅሰው በከተማው አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ #ከጉዳት_መጠን ጋር ተያይዞ #የሚናፈሱ አሉባልታዎች መሰረተ-ቢስ ናቸው በሰው ህይወት ላይም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት #የለም ስለዚህ ማህበረሰቡ ከአሉባልታ በፀዳ መንገድ የተለመደ ተግባሩን ማከናወን እንዳለበት ፖሊስ አስታውቀዋል፡፡

Via Shewa Robit City Administration Kentiba office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቬንዙዌላ ድንበሯን ዘጋች‼️

የቬንዙዌላ ፕሬዘዳንት #ኒኮላስ_ማዱሮ #በሰብዓዊነት ስም በተቃዋሚ ፓርቲዎች አማካኝነት ከአሜሪካ የሚደረገውን እርዳታ ለማስቆም አገራቸው #ከብራዚል ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷን አስታወቁ፡፡

በዚህ ምክንያትም በርካታ ተሽከርካሪዎች በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ ቆመው እንዳሉም ተገልጿል።

ፕሬዘዳንቱ በአገራቸው ከመንግስት አቅም በላይ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ እንደሌለና ምንም አይነት የእርዳታ ጥሪም እንዳልተደረገ ገልፀዋል፡፡

በአገሪቱ በተፈጠረው #አለመረጋጋት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ግራ ዘመሙ መሪ #ማዱሮ በአገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ ወጥተው እንደገለፁት የተቃዋሚ መሪዎች በሰብዓዊ እርዳታ ስም ከአሜሪካና ሌሎች አጋሮቿ የሚላከውን ለማስቆም የኮሎንቢያ ድንበርንም ጨምረው እንደሚዘጉ ገልፀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ጁዓን ገይዱ በበርካታ አውቶቡሶችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ታጅቦ ከቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ ወደ #ኮሎንቢያ ድንበር ማቅናታቸው ተገልጿል፡፡

በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በአገሪቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት መፈጠሩ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል‼️

መንግስት የጦር መሳሪያ ሊያስፈታ ነው የሚለው ቅስቀሳ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች አንፃራ ሰላም መስፈኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው በሁለቱ ዞኖች አንፃራዊ ሰላም መታየቱን ያስታወቀው፡፡ በአካባቢው የነበረውን #አለመረጋጋት ወደ #ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልከላ እና ሌሎች እገዳዎች ከተላለፉበት ቀን ጀምሮ በሰውም ይሁን በንብረት ላይ ይደርስ የነበረው ጉዳት መቀነሱን ገልፃል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም እንደጠቆሙት የፌደራል እና የክልል የፀጥታ ሀይሎች ከህብረተሰቡ ጋር እየሰሩት ባለው ተግባር በቡድን ሲፈፀሙ የነበሩ የግድያ እና የንብረት ማጥፋት ወንጀሎች ቀንሰዋል፡፡

ከእገዳው በኋላ በጥምረት በተሰራው ስራም 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል። አሁንም አልፎ አልፎ በግለሰብ ደረጃ የሚፈፀሙ ወንጀሎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
ከአሁን ቀደም ታግተው የነበሩ ግለሰቦችም ሙሉ በሙሉ መለቀቃቻን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል፡፡

ከጎንደር መተማም ይሁን ከጎንደር ሁመራ የተሽከርካሪ መጓጓዣ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ በጎንደር ከተማ ከአሁን ቀደም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር ያሉት ኮሚሽነር ዘላለም እገዳው ከተደረገ ወዲህ መቀነሱን አመላክተዋል፡፡

ይህ ደግሞ የፀጥታ ሀይሉ ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ ሆኖ በመስራቱ የመጣ ነው፤ የጎንደር ከተማ ወጣቶች ለሰላም እያሳዩ ያሉት ትብብርም የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

ወንድማማች ህዝቦቹ ካለፈው ጥፋት ተምረው በጋራ ችግሮቻቸውን ለመቅረፍ እየተወያዩ መሆናቸውም ታውቋል።

እገዳ በተደረገባቸው አካባቢዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ መከልከሉን ምክንያት አድርገው መንግስት የጦር መሳርያ #ሊያስፈታ ነው እያሉ ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላት አሉ፡፡ "ቅስቀሳው ከእውነት የራቀ ነው፤ #ብጥብጥ በመፍጠር ክልሉን ለማዳከም የታለመ ሀሳብ በመሆኑ ማህበረሰቡ በአሉባልታዎች እንዳይታለል" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ...

በተቋሙ ውስጥ በተፈጠረ #አለመረጋጋት ሳቢያ ለሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው ዕለት #ተጀምሯል። በትላንትናው ዕለት በግቢው ውስጥ የእርቅ ስነ ስርዓት መካሄዱ ይታወሳል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል የጎብኚ ቁጥር አሽቆልቁሏል!

በደቡብ ክልል #የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው #አለመረጋጋት የጎብኚዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የስራ ሃላፊ እንዳሉት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ክልሉን የጎበኙ የውጭ አገር ጉብኚዎች ቁጥር አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ አየለ እንዳሉት በክልሉ የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው አለመረጋጋት በጎብኚዎች እንቅስቃሴ ላይ የራሱን ተፅህኖ አሳድሯል።

ለአብነትም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ወደ ክልሉ የመጡ የውጭ አገር ጎብኚዎች አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶ መገኘቱን ነው የቢሮ ሃላፊዋ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ የጠቀሱት። የቱሪዝም ዘርፈ ጥንቃቄ የሚያሻው በትንሽ ስጋት ሊደናቀፍ የሚችል መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ በቀጣይ መስህቦችን መልሶ የማስተዋወቅ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።

በደቡብ ክልል የሆቴሎች ህብረት ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ ጌታቸው በከተማው ተፈጥሮ በነበረው ሁከት የጎብኚዎች ቁጥር አስከመቆም በመደረሱ በከተማው በሆቴል ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች ላይ የገበያ መቀዛቀዝ ማጋመጠሙን ተናገረዋል። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ መንግስት ባከናወናቸው የማረጋጋት ስራዎች ዘርፉ አንፃራዊ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን ነው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ የገለጹ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ገለቱ ገረመው በበኩላቸው የአስተዳደሩ የፀጥታ መዋቅር ከጊዚያዊ ኮማንድ ፖስትና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ከጀመረ ወዲህ ከተማዋ ወደ ነበረ ሰላሟ እየተመለሰች ትገኛለች ብለዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia