ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...
የት ነው የምትኖሩት?? አካባቢያችሁ፤ ከተማችሁ ውስጥ ምን አይነት ተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሰራሽ መስዕብ አለ?? እናተ ያያችሁት የኢትዮጵያ ድንቅ ቦታዎች ሌሎች እንዲያዩት የምትጠቁሙት ይኖር ይሆን??
• 4 ምርጥ ፎቶዎችን ከአካባቢው ስም ጋር አድርጋችሁ በመላክ የምትኖሩበትን አስተዋውቁን። የሀገር ውስጥ እና የውጭ #ቱሪስቶችን ወደ አካባቢያችሁ ጋብዙ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ከስልጤ ዞን...
"ስልጤ ገርቤ በር የተጎዱ በርካታ #ፖሊሶች ጦራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም መተዋል፡፡ እዛው ነው ምሰራው!"
#ቲክቫህኢትዮጵያ #tikvahethiopia

የኮ/ሌ በዛብህ ጉዳይ...‼️
(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)
"ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስን ሰኔ ላይ ኤርትራ ውስጥ በአካል አግኝቻቸዋለሁ። በመጪው ሰኔ ላይ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ" -- ኢንጅነር #ታደሰ
"እኔ ምንም መረጃ የለኝም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ #ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው"-- ፕ/ር #በየነ_ጴጥሮስ
.
.
ኢንጅነር ታደሰ ይባላሉ። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ወደ ኤርትራ ተጉዘው እንደነበር እና በቆይታቸው ወቅትም በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበሩት ጀት ተመትቶ የተማረኩትን ኢትዮጵያዊውን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን እንዳገኟቸው ለጋዜጠኛ #አልያስ_መሰረት ተናግረዋል፤ አክለውም "በአሁን ሰአት እንደ ሌሎች የጦር ምርኮኞች በቀይ መስቀል ስር ይገኛሉ። እኔም እዛ አግኝቻቸዋለሁ። ትንሽ ከእድሜ መግፋት ውጪ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ሰኔ ወር ሲመጣ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ። ዝርዝሩን የመንግስት ሰዎች ያውቃሉ" ብለዋል።
የኮ/ሌ በዛብህ ጴጥሮስ ታላቅ ወንድም ወደሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ስለጉዳዩ በሰጡት ምላሽ፦ "እኛ ይህ መረጃ የለንም። እኚህ ያልካቸው ግለሰብ እንዴት access ሊኖራቸው እንደቻለ አላውቅም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው። ወንድሜ በህይወት አለ ወይስ የለም የሚለውን ለማረጋገጥ እንኳን ካደረግነው ጥረት አንፃር ሲታይ የዚህ ሰውዬ መረጃ በጣም extreme ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ሲጠቃለል በኮሎኔል በዛብህ ዙርያ መነጋገር አንፈልግም የሚል ነው። ከዚያም አልፎ ጉዳዩን sensitive አርጎ መናደድ አለ። እኛን አትጠይቁን አይነት ነገር ነው ያየነው። በህይወት ተይዞ የአስመራ መንገዶች ላይ parade የተደረገ ሰው ነው። የኛ አቋም ህይወቱ አልፏል ከተባለ ታውቃላችሁ እና አካሉ የት ነው እያልን ነው። ግን ይህንን ጉዳይ መወያየት አይፈልጉም። ከኢትዮጵያ መንግስት ወገን ደሞ አሁን የተጀመረውን ንግግር ያበላሽብናል የሚል ነገር አለ። ለማንኛውም ያልካቸውን ሰውዬ አገናኘኝ። ይህ ለኛ ትልቅ development ነው።"

#update የሰዎች ሕይወት ላይ እየደረሰ ያለው በደል እንዲቆም ምህላ እና ዱዓ እየተደረገ ነው። ምህላው እና ዱዓው እየተደረገ ያለው በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በሰዎች ሕይወት እየደረሰ ያለው ጉዳት ምሕረት እንዲያገኝ ነው፡፡ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሃይማኖት አባቶች በሁለቱ ዞኖች እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች ሕልፈተ ሕይወት፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት አውግዘዋል።
Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመምህራን...‼️
የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆናችሁ በሺዎች የምትቆጠሩ የመጀመሪያ ደረጃ፤ የሁለተኛ ደረጃ፤ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን እንዳላችሁ ይታወቃል።
ጥያቄያችን፦ ከቀለም ትምህርቱ ጎን በክፍል ውስጥ ለተማሪዎቻችሁ #ስለሰብዓዊነት፣ ስለሀገር ፍቅር፣ ስለአንድነት፣ ስለመከባበር ትነግሯቸዋላችሁ?? ከተማሪዎች ጋር ቀርባችሁ ትነጋገራላችሁ?? ወይስ አስተምሮ ብቻ መውጣት ነው?? ተማሪዎች ቀኑን ሙሉ አብረዋችሁ እንደሚውሉ አታውቁም?? ትልቅ የአስተሳሰብ ለውጥ ለመፍጠር ምን ሰራችሁ?
•መምህራን በሀገር #ሰላም እና #እድገት ላይ ያላችሁ ድርሻ እጅግ በጣም ትልቅ ሊሆን ይገባል።
አስተያየት መስጠት ይቻላል @tsegabwolde

#update የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ‹‹የሩሲያው ፕሬዝዳንት #ቪላድሚር_ፑቲን ዴሞክራሲ እንዳይዳብር በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት ሆነዋል›› አሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መካከለኛው አውሮፓን እየጎበኙ በሚገኙበት ወቅት ቻይናንም የአውሮፓን ፖለቲካ በፈለገችው መንገድ እየመራች ነው ሲሉ ወርፈዋል፡፡ በአውሮፓ የቻይናን እና የሩሲያን ፖለቲካዊ ተፅዕኖ መቀነስ ዒላማ ያደረገ ንግግርም አድርገዋል፡፡
ምንጭ፦ አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የባሕር ዳር ነዋሪዋ እና አደራ የተረከቡት አባት ለ20 ዓመታት #በአደራ የኖሩበትን ቤትና የቤት ኪራይ ለኤርትራዊ ባለቤቱ አስረከቡ!
.
.
የታሪኩ መነሻ ጊዜ 1991 ዓ.ም ነው፡፡ ቦታው ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ፡፡ ትውልድ ኤርትራዊው አቶ አብርሃም ደስይበለኝ በባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ነበር የሚሰሩት፡፡ በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ችግር ምክንያት ግን ከስራ እና ከመኖሪያ ቦታቸው ተነስተውና ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተደረጉ፡፡
ከአባቷ ጋር አብራ ወደ ኤርትራ እንድትሄድ የተደረገችው የዛሬዋ ባለታሪካችን ሰናይት አብርሃም በወቅቱ የትና ለምን እንደምትሄድ ባታውቅም ተወልዳ ያደገችበትን ቀየና ቤት እየተሰናበተች ነበርና ‹‹አደራ!›› ለባለአደራ ሰጠች፡፡
አደራው ደግሞ የአባቷ የስራ ባልደረባ ለነበሩት ለአቶ ተፈራ አባተ እና እነሰናይት ከሀገር ሲወጡ ግቢው ውስጥ ተከራይታ ለነበረችው ለወይዘሮ መዓዛ ሳሙኤል ነበር የተሰጠው፡፡ ወይዘሮ መዓዛ ለረዥም ዓመታት በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ውስጥ ሲሰሩ ቆይተው አሁን ላይ በጡረታ ከተቋሙ ወጥተዋል፡፡
እንደ ዋዛ ከሀገር እንደወጡ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት ሰናይት እና ቤተሰቦቿ አንድ ቀን ወደ ባሕር ዳር-ቀበሌ 8 እንደሚመለሱ እና ንብረታቸውን እንደሚያገኙ ተሰፋ ነበራቸው፡፡ ዘመን መመለሳቸውን ሲፈቅድ፣ ያለያያቸው የፖለቲካ ቁርሾ በፍቅር ሲሽር፣ ተስፋ ወደ እውነታ ተቀየረ፡፡
ሰናይት ያደገችበትን ቀየና ቤት ዳግም ለማየት በቃች፡፡ ‹‹አደራ የተሰጠን ቤቱን ጠብቆ ለማቆየት ቢሆንም በየጊዜው ከኪራይ የሚገኘውን ገንዘብ በተለያየ መንገድ ለባለቤቶቹ እንዲደርስ ስናደርግ ቆይተናል›› ያሉት አቶ ተፈራ ዛሬ ደግሞ ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ 18 ሺህ ብር ቀሪ ኪራይ እና ቤቱን ለባለቤቷ በአካል አስረክበዋል፡፡
‹‹ባለፉት ዓመታት በአስመራ በነበረኝ ቆይታ አንድ ሰው ‹ኢትዮጵያዊ ነው!› ሲባል ሀገሩን ብቻ ሳይሆን ታማኝነቱንም መግለጫ›› ነው ያለችን ሰናይት ከተቀበለችው ገንዘብ በላይ የግቢው እና የቤቱ አያያዝ ልዩ ስሜት እንደፈጠረባት ተናግራለች፡፡ ከ20 ዓመታት በላይ በኪራይ ቤት መኖር ያልተለመደ ነው ባይባልም እንግዳ ነገር ለመሆኑ ግን አጠራጣሪ አይደለም፡፡ ወይዘሮ መዓዛ ሳሙኤል ግን ከኪራይ ያለፈ ቃል እና እምነት ተጥሎባቸዋልና የእርሳቸውንና የሌሎችን ተከራዮች ወርሃዊ ኪራይ ለአቶ ተፈራ እየሰጡ ግቢውንም እንደ እራሳቸው ንብረት እየተንከባከቡ አደራቸውን ዛሬ ለሰናይት አስረክበዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ

#update ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ 106 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች መሰብሰቡን አስታውቋል። በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 38 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች በማግኘት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካት ችሏል። የዕቅድ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ11 ሺህ ከረጢት ደም ብልጫ አለው።
via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴዲ ማንጁስ‼️
በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩት አቶ #ቴዎድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ላይ ዐቃቤ ህግ የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ጠየቀ።
መርማሪ ፖሊስ በአቶ ቴዎድሮስ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ምርምራ አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ትላንት ለዐቃቤ ህግ አስረክቧል።
ዐቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት እንደገለጸው፤ ተጠርጣሪው አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ ባላቸው የህትመት ድርጅት ከኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና ከሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር የመማሪያ መጻህፍትን ለማተም ውል ፈጽመው እንደነበረ ገልጿል።
ሆኖም ተጠርጣሪው ከኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጋር በመመሳጠር በውሉ መሰረት መጽሐፉን ሳያስረክቡ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ቅድሚያ ክፍያ እንደተከፈላቸው ዐቃቤ ህግ ለችሎቱ አስረድቷል።
በዚህ መሠረት አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ በመንግስትና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ዐቃቤ ህግ አስረድቷል።
የተፈጸመው ወንጀል ውስብስብና ከባድ ከመሆኑም በላይ የተፈጸመው ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ስለሆነ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎችን አሳባስቦ በማጠናቀቅ በቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ክስ ለመመስረት የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ግለሰቡ የተጠረጠሩብት ወንጀል ከባድ የሙስና ወንጀል ሲሆን የዋስትና መብት የሚያስከለክል በመሆኑ የተጠርጣሪው የዋስትና መብት ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግለት ዐቃቤ ህግ ችሎቱን ጠይቋል።
ተጠርጣሪው አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ የህትመት ድርጅታቸው ለሰባት ወራት መታገዱንና ድርጅቱ መዘረፉን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።
የፍርድ ቤት እገዳ ሳይኖር ድርጅታቸው መታገድ እንደሌለበት ያመለከቱት አቶ ቴዎድሮስ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የህትመት ስራ አሰርቷቸው 7 ሚሊዮን ብር እንዳልተከፈላቸውም ተናግረዋል።
በሶማሌ ክልል ፍርድ ቤት የታገደው የአቶ ቴዎድሮስ የህትመት ድርጅት ፖሊስ ለተጠርጣሪው ማሳወቅ እንደነበረበት የገለጸው ችሎቱ ከዚህ በኋላም ተጠርጣሪው ማወቅ የሚገባቸውን መረጃዎች ፖሊስ በወቅቱ እንዲያሳውቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በተጠየቀው የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ከሰዓት በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ በሌላ መዝገብ ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በጅግጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ቢሆንም ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ የተጠርጣሪው ጠበቃ የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አመዛዝኖ የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ መጠየቁ ይታወሳል።
ፍርድ ቤቱም ከተጠርጣሪው ጠበቃ የቀረበውን የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪው በ80 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ መስጠቱ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ አቶ ቴዎድሮስ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው በመሆኑ ከእስር #አልተፈቱም።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#update የሕወሃት ሥራ አስፈጻሚ አባል #አስመላሸ_ወልደሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ውስጥ በአማካሪነት መመደባቸውን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪ ሚንስትር የነበሩት አስመላሽ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሃላፊታቸው እንደተነሱ ይነገራል፡፡ ምደባው በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ባዶ የነበረውን የሕወሃት ውክልና ይሞላል ተብሏል፡፡ አዲስ ዋና ተጠሪ እስኪመረጥ ድረስ በቅርቡ ምክትል ተጠሪ ሆነው የተመረጡት የኦዴፓው ጫላ ለሚ ተክተው ይሰራሉ፡፡
via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia