#EthiopianCoffee☕️
11 ሺህ ከረጢት የኢትዮጵያ 🇪🇹 ቡና በአምስት ሰከንድ ውስጥ ተሸጠ።
በቻይና በተካሄደ የቀጥታ ሽያጭ ስነስርዓት 11 ሺህ ከረጢት የኢትዮጵያ ቡና በአምስት ሰከንድ ውስጥ መሸጡን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
በሚኒስቴሩ የአፍሪካ ጉዳይ ጀኔራል ዳይሬክተር ዉ ፔንግ በትዊተር ገጻቸው ፤ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በተገኙበት የተካሄደው የቀጥታ ሽያጭ ሂደት ውጤታማ ነበር ብለዋል።
የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ውስጥ ፍላጎቱ እያደገ መምጣቱን የገለጹት ዉ ፔንግ፤ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ከጥር እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ወደቻይና የገባው የኢትዮጵያ ቡና መጠን ቀደም ካለው ጊዜ አንጻር በ196 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።
በመጪዎቹ ዓመታት ቻይና ከአፍሪካ የግብርና ምርቶችን በስፋት እንደምታስገባም ጠቁመዋል።
#ENA
@tikvahethiopia