TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ሂርጳ 'ዳግም' ሞቱ‼️

ከሁለት ወራት በፊት የሞትን ብርቱ ክንድ አሸንፈው ተነሱ የተባሉት አቶ #ሂርጳ_ነገሮ ሞተው ሳሉ የገጠማቸውን ለቢቢሲ አጫውተው የነበረ ሲሆን ከ70 ቀናት በኋላ ትናንት 'ዳግም' ማረፋቸውን ከሁለት ጊዜ ገናዣቸው ተሰምቷል።

መቃብር ፈንቅለው ከወጡ በኋላ ጤናማ የነበሩት አቶ ሂርጳ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ግን በፅኑ ታመው ከፈሳሽ ውጭ ምንም ነገር ይወስዱ እንዳልነበር BBC ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል። እሳቸው አይሆንም ቢሉም ቤተሰቦቻቸው ነቀምት ሆስፒታል ወስደዋቸው ነበር። ቤተሰቦቻቸው አቶ ሂርጳ ዳግም መቃርብር ፈንቅለው ይነሳሉ የሚል #ተስፋ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 1 ሚሊዮን 55 ሽህ 286 ብር በላይ ግብይት ይካሄድበታል ተብሎ የሚጠበቀው ሀገር አቀፍ አነስተኛና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽንና ባዛር ትናንት በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተመርቆ ተከፈተ፡፡ 129 አቅራቢዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ እንደገለጹት፤ በባለሥልጣኑ ቅጥር ግቢ የተከፈተው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ዙር ሀገር አቀፍ አነስተኛና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽንና ባዛር‹‹የተቀናጀ የገበያና የግብይት ድጋፍ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ውጤታማነት›› በሚል መሪ ቃል ከጥር 23 እስከ 30 ድረስ ይካሄዳል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴዎድሮስ በእስር ላይ ይገኛል‼️

#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ቴዎድሮስ አዲሱ ከሀምሌ 28-30 ቀን 2010ዓ.ም በጀጅጋ እና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ምርመራውን ስላላጠናቀቀ እና በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ #ፍትሃዊ አለመሆኑንና የግለሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጎዳ መሆኑን በማመን መዝገቡ እንዲዘጋ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በ80 ሺህ ብር ዋስ #እንዲወጣ ፈቅዶ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ግለሰቡ በሌላ ወንጀል ከቀድሞው የሱማሌ ክልል ምክትል የትምህርት ቢሮ ኃላፊና ከኒያላ ኢንሹራንስ የጅጅጋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ጋር በመመሳጠር #በተጭበረበረ የኢንሹራንስ ዋስትና አፈጻጸም የቅድመ ክፍያ ቦንድ ከኢንሹራንስ እንዲጻፍ በማድረግ በውሉ ላይ ከተጠቀሰው ቅድመ ከፍያ ላይ ብር 15,306,303.3 ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ወጪ በማድረግ የወሰደ በመሆኑ ለትምህርት ቤቱ መፀሐፍቱን ሳያቀርብ ገንዘቡን ከጥቅም ተጋሪዎች ጋር በመከፋፈል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

መርማሪ ፖሊስ በቴዎድሮስ አዲሱ ላይ #በከባድ የሙስና ወንጀል የጀመረውን ምርመራው ለማከናወን የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት ተጠርጣሪው በእስር ቤት እንዲቆይ እና ለየካቲት 5 ቀን 2011 እንዲቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ለሚያልፉ ዐለም ዐቀፍ መንገደኞች #የነጻ ጉብኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ በአውሮፕላን ማረፊያው እስከ ከ6 እስከ 8 ሰዓታት ቆይታ ላላቸው መንገደኞች አየር መንገዱ ከነገ ጀምሮ በራሱ አስጎብኝ ድርጅት አማካኝነት አዲስ አበባ ከተማን በነጻ ያስጎበኛል፡፡ ብሄራዊ ሙዚዬም ለጉብኝቱ ከተያዙት ቦታዎች ቀዳሚው ነው፡፡

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዘርፍ ማህበር እና #የሰላም_ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የሰላም ሚዲያ ህብረት ትስሰር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ዛሬ ማምሻውን አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሐረሪ ክልል የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ #መሻሻል ማሳየቱን የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ  አስታውቋል። በፍቅርና በመቻቻል በምትታወቀው ጥንታዊቷ ከተማ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሕግና ሥርዓት የማይከበርባት፣ ሥርዓተ አልበኝነትና መንግሥት አልባ ተደርጋ በነዋሪዎቿና በጎብኚዎቿ ስትቀርብም ነበር።

via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪ- ኢብራሂም ደደፎ አብደላ
ድሬ ፖሊስ‼️

#ብሄሬን መሰረት ተደርጎ ጥቃት ተፈፅሞብኛል በሚል በሀሰት የሽንት መሽኛ #ብልቱን በፋሻና ፕላስተር በመጠቅለል ግጭት ለመቀስቀስ የሞከረው ግለስብ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ተጠርጣሪ #ኢብራሂም_ደደፎ_አብደላ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት ሆን ብሎ ብሄሬን መሰረት አድርገው በቢላዋ የሽንት መሽኛ ብልቴን ቆርጠው ጉዳት አድርሰውብኛል በሚል ድርጊቱን ያልፈፀሙ ግለሰቦችን ስም በመጥቀስ ለፖሊስ አቤቱታ ያቀረበው።

ፖሊስ የቀረበውን አቤቱታ ተቀብሎ ሁኔታውን ለማጣራት ተከሳሽን ወደ ህክምና የላከ ሲሆን በተደረገ የህክምና ምርመራ ግለሰቡ ላይ ምንም አይነት ጥቃት #እንዳልተፈፀመበት ማረጋገጥ መቻሉን ተናግሯል።

#ተጠርጣሪው አሁን ላይ #በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ጨምሮ ገልፆ ማንኛውም ሰው በዜጎች መካከል ግጭቶችና አለመግባባቶች እንዲፈጠሩ ከሚያደርጉ ተግባራት ሊቆጠብና ሊርቅ እንደሚገባ አሳስቧል::

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ኢንሳ የሀገሪቱንና የሕዝብ #ደህንነትን የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮምቦልቻ🔝

የጉዞ አድዋ ተጓዦች ኮምቦልቻ ከተማ ቆይታ አድርገዋል። #ኤርሞን_መኮንን ሰላም እንደሆነ እና መጓዝ እንደሚችል ገልጿል። ከደሴ በኃላ ጫማ ተጫምቶ በእግር ይጓዛል የተባለውም ከእውነት የራቀ እንደሆነ ገልፆ፤ ጉዞውን በእግሩ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

©ዮሴፍ አለማየሁ(TIKVAH-ETH ኮምቦልቻ ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopia @tsegabwolde
Audio
ሃላሌ!! #ይርጋለም!!

የአገር ሸማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ #በይርጋለም ከተማ ተካሂዷል፡፡

ወጣቶች ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ የሲዳማ "ሃላሌ" ባህላዊ ስርዓት ተከትለው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠይቁ የሲዳማ አገር ሸማግሌዎች አሳስበዋል፡፡

"ኤጄቶዎች" ወይም የሲዳማ ወጣቶችና አገር ሸማግሌዎች የጋራ የሰላም ኮንፈረንስ ማካሄድ ከጀመሩ በኋላ ለውጥ መታየቱን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ አስታውቋል፡፡

"ኤጄቶዎች" የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የሚረጋገጥበትን ህዝበ ውሣኔ እንዲያስፈፅም የክልሉ ምክር ቤት ለምርጫ ኮሚሽን ቢስታውቅም ዘግይቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴፒ‼️

በደቡብ ክልል በቴፒ ከተማ #ለተቃዉሞ አደባባይ በወጡ ወጣቶች ላይ ፀጥታ አስከባሪዎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ አራት ሰዎች ተገደሉ። ሌሎች ሰባት ቆሰሉ። የዐይን ምስክሮች እንዳሉት ከሟቾቹ አንዱ የአስራ ሶስት ዓመት ታዳጊ ወጣት ነዉ ተብሏል። የጀርመን ድምፅ ራድዮ የከተማይቱን ነዋሪዎች ጠቅሶ እንደዘገበዉ ከግጭቱ በኋላ የከተማይቱ የንግድ፣ የትራንስፖርትና የመንግሥት መስሪያቤቶች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ #ተቋርጧል። ፀጥታ አስከባሪዎች የከተማይቱን ዋና ዋና መንገዶችን በጥብቅ እየተቆጣጠሩ ነዉ። የቴፒና የአካባቢዋ ነዋሪዎች የራስ አስተዳደር ጥያቄ በማንሳት አደባባይ መዉጣት ከጀመሩ ካለፈዉ ጥቅምት ጀምሮ ነዋሪዎችና ፀጥታ አስከባሪዎች በተደጋጋሚ ይጋጫሉ። በየግጭቱ የሰዉ ሕይወት ይጠፋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ🗓ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ በነገው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ በነገው ዕለት እንደሚያካሂድ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ‼️

ባለፉት 6 ወራት በርካታ ሽጉጥ፤ ክላሽ፤ በርካታ ጥይቶች፤ቦንብ እና የቡድን መሳሪያ መትረጊስ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በደቡብ ሞያሌ፤ በምስራቅ ቶጎ ውጫሌ፤ በምዕራብ ጋንቤላ ሱዳን አዋሳኝ፤በሰሜን ከሱዳን መተማ ፤ እና በቤንሻጉል ጉምዝ አካባቢ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባና ቱርክ ሰራሽ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡

ይህ ህገ ወጥ መሳሪያም በፌደራል ፖለስ ኮሚሽን፤ የሀገር መከላከያ ሚንስቴር፤ የቢሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት እና ከጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም ከሰፊው ሰላም ወዳድ ህዝብ ጋር በመቀናጀት ከበፊቱ ጋር ሲነጸጸር ቀንሷል፡፡ሌላው ሊቀንስ የቻለበት ምክንያት ደግሞ በማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎትና በተቋሙ ሚዲየሞች አማካኝነት ህብረተሰቡ ስለ ህገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውር አስከፊነት በፌደራልና በክልሎች ደረጃ በማስተማር የህዝቡን ተሳትፎ በማሳደግ መቀነስ ተችሏል፡፡

በፍተሻ ኬላዎቹም ጥብቅ ፍተሻ ቢደረግም ከዋናው መንገድ ውጭ ባሉ መንገዶች በጋማ ከብትና በሞተር እያጓጓዙ ወደ አራቱም አቅጣጫዎች እንደሚያስገቡ ተገጸል። ይህን የሃገር ሰላም የሚያናጋ ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ግጭት እንዳይባባስ ህብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ያለውን ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ሰላም የሰፈነባትና #የተረጋጋች ኢትዮጵያን መፍጠር ይኖርበታል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ በዳቦ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ አግባብነት የሌለውና ህብረተሰቡን ያላማከለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰሙ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበኩሉ በዳቦ ዋጋ ላይ አግባብነት የሌለው ጭማሪ ባደረጉ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

ቢሮው በከተማዋ ባሉ ዳቦ ቤቶች ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ምንም አይነት እውቅና ያልተሰጠውና አግባብነት የጎደለው በመሆኑ ይሄንን አድርገው በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

የዋጋ ጭማሪውን አስመልክቶ ኢዜአ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ባደረገው ምልከታ በትክክል የዋጋ ጭማሪ መኖሩን አረጋግጧል።

በዚህም ባለ 100 ግራም ዳቦ በ2 ብር ከ50 ሳንቲም፣ ባለ 200 ግራም ዳቦ በ5 ብር እንዲሁም ባለ 300 ግራም ዳቦ በ7 ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሚገኝ ተመልክቷል።

አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የመዲናዋ ነዋሪዎችም የተደረገው የዋጋ ጭማሪ አግባብነት የሌለውና ህብረተሰቡን ያላማከለ ነው ሲሉም ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

በመሆኑም መንግስት ይህንን ተግባር በሚፈጽሙ አካላት ላይ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባውም አስተያየታቸውን ገለጸዋል።

አቶ አክሊሉ ቢንያ አንድ ብር ከሰላሳ ሳንቲም ይሸጥ የነበረው ዳቦ ዛሬ ሁለት ከአምሳ ገብቷል፡፡ ይህ ደግሞ አግባብ አለመሆኑን ነው የተናገሩትአቶ ጉታ አዱኛ በበኩላቸውየዳቦ ጭማሬው በጣም አስገራሚ እንደሆነ የከተማ አስተዳደሩ አስቸኮይ መፍቴህ ሊሰጠው እንደሚገባ ነው የተናገሩት “የዳቦ ጭማሪው አግባብነት የለውም፤ በአንድ ጊዜ የ1 ብር ከ20 ሳንቲም ጭማሪ እግባብ አይደለም፤ ሁለተኛ ነገር መንግስት ባለበት አገር እንደዚህ አይነት ነገር ሲፈጸም መንግስት ምን እየሰራ ነው? ምንድነው እያደረገ ያለው አፋጣኝ የሆነ እርምጃ ሊሰጠው ይገባል።” ያለው ወጣት ዘላለም ጤናው ነው።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ በበኩላቸው መንግስት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ 165 ሺህ ኩንታል በድጎማ ያቀርባል።

በዚህም በከተማዋ 1 ሺ 400 ከሚሆኑ ዳቦ ቤቶች ጋር ከ100 ግራም ጀምሮ በ1 ብር ከ30 ሳንቲም እንዲሸጡ የሚያደርግ ትስስር በመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ይሁንና በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ዳቦ ቤቶች ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ምንም አይነት እውቅና ያልተሰጠውና አግባብነት የጎደለው መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህም በተተመነላቸው ዋጋ መሰረት የማይሸጡና ከዚህ ዋጋ በላይ ጨምረው በሚሸጡ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም ጠቁመዋል።

በዚህም ቢሮው ባደረገው ክትልል በሁለት ቀናት ውስጥ በኮልፌ ክፍለ ከተማ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ አድርገው የተገኙ ሶስት ዳቦ ቤቶች እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ ዳቦ ቤት ላይ እርምጃ መውሰዱን ጠቁመዋል።

ሌሎችም ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠቡና ህብረተሰቡን በአግባቡ እንዲያገለግሉና የተጣለባቸውን ሃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

ህብረተሰቡም በሸቀጦች ላይ አላስፈላጊ ጭማሪን በሚመለከትበት ጊዜ ለሚያጋጥሙት ህገ-ወጥ ተግባራት በነጻ የስልክ መስመር 8885 ላይ ጥቆማ እንዲያደርግም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢ ዜ አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia