TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአርባ ምንጭ🔝

"የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውይይት በሰላማዊ መልኩ አልቋል። ግቢው ወደ ሰላማቂዊ መማር ማስተማር የስራ ሂደት ተመልሷል። የሀይማኖት አባቶች እና የጋሞ ሽማግሌዎች ላደረጉት ተግባር ሊመሰገኑ ይገባል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ‼️

በአሁን ሰዓት ተማሪዎች ከከፍተኛ የፌደራል የስራ ሀላፊዎች ጋር በግቢው ስለተፈጠረው ችግር በመምከር ላይ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከሰማያዊ፣ ከኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና ከቀድሞው አንድነት ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ።

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሚሊዮን ማትዮስ...

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ:

• አሁን ባለው ሁኔታ እንደከዚህ ቀደሙ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ አፍኖ ለመቀጠል አዳጋች ነው፤

• የደቡብ ክልል ከአምስት ወደ አንድ ሲጠቃለል በዴሞክራሲያዊ መልኩ ህዝቦች ተወያይተውበት፤ ቋንቋዬንና ባህሌን ለማሳደግ ይመቸኛል በሚል አይደለም፤

• ደኢህዴን ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የወሰነው ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አንፃር ህዝቦች ያዋጣል የሚሉትን ሃሳብ ማዳመጥ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱም ጭምር ነው፤

• የሲዳማ ክልል መሆን የክልሉን #አደረጃጀት ይቀይረዋል፤ አደረጃጀቱ ሲቀየር ደግሞ በጥናት ላይ ተመስርቶ የህዝቦች ትስስርና ጥቅም ጥናት ላይ የተመሰረተውን መነሻ ከህዝቦች ጋር ውይይትና ምክክር በማድርግ መፈፀም እንዳለበት ይታመናል፤

• ሃዋሳ ከተማን አሁንም ቢሆን የሲዳማ ዞን ዋና ከተማ ናት፡፡

#ሲዳማ_ክልል ከሆነ #ሃዋሳ የሲዳማ ክልል ዋና ከተማ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው፤

• በሃዋሳ የሚኖሩ የተለየዩ ብሄር ብሄረሰቦችን በሚመለከት የሃገሪቱ ህግና ህገመንግስት በሚፈቅደው መሰረት ዜጎች የመኖር የመስራት መብታቸውን የሚያግድ ነገር ይኖራል ብለን አንገምትም።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታሕሳስ 13, 2011 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት #ሳሕለወርቅ_ዘውዴ መላው ህዝብ ለሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋት በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዚዳንቷ በትላንትናው እለት ከ9 ክልሎችና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የሰላም አምባሳደር እናቶችን በቤተ መንግስት አነጋግረዋል። በዚህ ወቅትም በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ በጋራና በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሊበን ወረዳ‼️

ከተፈቀደለት ስምሪት ውጪ  46 ሺህ 516 ሊትር ነዳጅ ጭኖ ሲጓጓዝ ተደርሶበታል የተባለው የቦቴ አሽከርካሪ በገንዘብ #እንዲቀጣ መወሰኑን በጉጂ ዞን የሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የፍርድ ቤቱ ዳኛ በለጠ ታዬ እንደገለጹት ውሳኔው የተላለፈው ለአማራ ክልል ደጀን ከተማ ከጅቡቲ የተጫነ ቤንዚልና ናፍጣ ወደ ሶማሌ ክልል ፊልቱ ከተማ ሲጓጓዝ በመያዙ ነው

ነዳጁ የተጫነው የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3  57142 ኢት ቦቴና ተጎታቹ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ  የቀረበው የክስ ማስረጃ ጠቅሰው አስረድተዋል፡፡

በቦቴውና በተጎታቹ ተጭኖ የተገኘው 24 ሺህ 363 ሊትር ቤንዚልን እና 22 ሺህ 153 ሊትር ናፍጣ ህዳር 28ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት 2.ሰዓት በህዝብ ጥቆማ ነገሌ ከተማ ውስጥ መያዙን  ዳኛው አስታውቀዋል።

ፍርድ ቤቱ #በነገሌ ከተማ በዋለው ችሎት አሽከርካሪው ሞገስ አሰፋን  በ13 ሺህ ብር እንዲቀጣ እንዲሁም የተጫነው ቤንዚልና ናፍጣ ለመንግስት ውርስ እንዲሆን መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

“ጥፋቱ ከ10 እስከ 50 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ቢሆንም አሽከርካሪው ከዚህ በፊት የክስ ሪከርድ ስለሌለበት ቅጣቱ ቀሎለታል” ብለዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡት የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ገመዳ ቱሉሳ ቅጣቱ ፍትሐዊ፣ ትክክልና አስተማሪ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢኮኖሚ አሻጥር የኑሮ ውድነትን ለማባባስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ  ለማጋለጥ የዞኑ ህዝብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰሞኑን   በተፈጠረ የቤንዚል እጥረት በነገሌ ከተማ አንድ ሊትር  እስከ 80 ብር እየተሸጠ ሲሆን  የታክሲ ክፍያም ከሁለት ብር  ወደ አምስት ብር ከፍ ማለቱን ቀደም ሲል ኢዜአ  ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅሬታ‼️

"በአማራ ክልል ዞኖች ውስጥ የምንገኘው በውሃ መስኖና ኢነርጅ መምሪያ የመስኖ ቡድን ሰራተኞች መዋቅሩ ይስተካከላል እየተባልን ከ3 ዓመታት በላይ ያለስራ በነፃ ደሞዝ እየተከፈለን ቆይተናል። በተደጋጋሚ ለአማራ ውሃ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ብናመለክትም ምላሽ የሚሰጠን አላገኘንም፡ በሰራተኞችም ሆነ በመምሪያ ሃላፊዎች የመስኖ ቡድንን ወይ መዋቅሩን አስተካክሉት ካለበለዚያ ቡድኑን አጥፉት የሚል ጥያቄ በየመድረኩ ቢነሳም ይሄ ከእኛ አቅም በላይ ነው የሚል ምላሽ ነው የሚሰጠው፡፡ ይህ የመስኖ ቡድን በውሃ መስኖና ኢነርጅ ቢሮ በኩል እስከ ዞን ብቻ የተዘረጋ ሲሆን በግብርና በኩል ግን የሰው ሃይሉን በዛ አድርጎ እስከ ወረዳ ድረስ መዋቅር ተሰርቶለታል፡፡ እንደዚህ አይነት መዋቅር በአማራ ክልል ብቻ የሚገኝ ሰራተኞችን እንደ ጡረተኛ በባዶው ደሞዝ ከመክፈሉ በተጨማሪ የእኛን /የሰራተኞቹን/ ስን ልቦና እየጎዳን ይገኛል፡፡ ይሄን ጉዳይ ርዕሰ መስተዳድሩ የሚያቁት ቢሆንም እስከ አሁን የተሰጠን ምላሽ የለም። እናም መስራት የሚችልን ጉልበት እና ጭንቅላት ተጠቀሙት፡ አትቀልዱበት። እባካችሁ፡ እባካችሁ የሚመለከታችሁ የፈደራልም ሆነ የክልል ባለስልጣናት መፍትሄ ስጡን እያልን እንገኛለን በየዞኑ የምንገኝ በውሃ መስኖና ኢነርጂ መምሪያ ውስጥ የምንገኝ የመስኖ ቡድን ባለሙያዎች! __ነኝ ከአዊ ዞን ውሃ መስኖና ኢነርጅ መምሪያ፡ እንጅባራ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 22ዐ የጤና ባለሙያዎችን በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩጋንዳ‼️

የዩጋንዳ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ከጉልበት በላይ ጉርድ ቀሚስ እንዳይለብሱ፣ ኩል እንዳይኳኳሉ እና ጌጥ #እንዳያደርጉ እገዳ አስተላለፈ፡፡

በዩጋንዳ የቡጋሜ ዩኒቨርሲቲ ነው የሞራል እሴቶችን በአስገዳጅነት ለመጠበቅ በሚል ነው ክልከላውን ያስተላለፈው፡፡ የጆሮና የአንገት ጌጥ፣ የእጅ አምባርና ሌሎች ጌጣ ጌጦችን እንዲሁም ሱሪዎችን አጫጭር ጉርዶችን እንዳይለብሱ ነው ዩኒቨርሲቲው የከለከለው፡፡ በቀጣዩ ወሰነ ትምህርት ማንም ተማሪ የተከለከሉትን አለባበሶች ተግብሮ እንዳይመጣም ማስታወቂያ ተነግሯል፡፡

ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ በዩኒቨርሲቲው የሥነ-ምግባር ኮሚቴ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ነው የተጠቆመው፡፡

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ጆርጅ ሙፓጋሃሲ በእነዚህ ደንቦች ውስጥ ተማሪዎች እንዲያልፉ እያደረግን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል🔝

ጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር #ዓብይ_አሕመድ በዛሬው ዕለት  ከሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት ጋር ተገናኝተዋል።

የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል የአገሪቱን ህገ መንግሥትና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በአዲስ የተቋቋመ የደህንነት መሳሪያ አካል መሆኑ ተገልጿል።

የሪፑብሊክ የጥበቃ ኃይል አባላት የመንግስት ባለስልጣናትንና እና ቤተሰቦቻቸውን የጥቃት ዓላማን አንግበው በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከሚሰነዘር ጠለፋና እንግልት ለመከላከል የተቋቋመ ነው።

ይህ የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል በከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ያሉትን ኃላፊዎች ከማንኛውም ስጋት እና ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዘዴ መጠቀም ዋነኛ ተግባሩ ነው ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥበቃ አባላቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይም የሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል አባላት የተሰጣቸውን ሃለፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የሚያሳይ ትርዒት አቅርበዋል።

ባለፉት ስደስት  ወራትም ይህ ሃይል እራሱን በሰለጠኑ የደህንነት ባለሙያዎችና በተገቢው መንገድ ተግባሩን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን እያደራጀና ስልጠናዎች እያደረገ መቆየቱን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

“አባ ቶርቤ” በሚል መጠሪያ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድብቅ በመንቀሳቀስ ሰዎችን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በዛሬው እለት ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ “አባ ቶርቤ” (ባለሳምንት) በሚል መጠሪያ በመደራጀት ሰላማዊ ዜጎችን፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና የፀጥታ ሀይሎችን #ሲገድሉ እና #ሲያስገድሉ ነበር በሚል ነው ተጠርረው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የተጠርጣሪዎቹን ማንነትና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰው ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia