TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከቤንሻንጉል ሕዝቦች ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2011 በጽ/ቤታቸው በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያዩ። በውይይታቸውም የክልሉን የአስተዳደርና የልማት ችግሮችንና የግጭትና አለመረጋጋት መንስኤዎችን ለመቅረፍ የተጠናከረ እርምጃን አስፈላጊነት አንስተዋል። በሌሎች ክልሎች እንደታየውም አመራሮቹ የለውጥ እንቅስቃሴዎቹ ሰፊውን የክልሉን ነዋሪ በተለይም የክልሉን ወጣት አቅም በመጠቀም ወደ ክልል ደረጃ ለማውረድ ቃል ገብተዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ‼️

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተቻችለው ለሀገራቸው ሰላምና አንድነት የበኩላቸውን እንዲወጡ የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተርና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ጠየቁ፡፡

አቶ ኦባንግ ሜቶ በሀገራዊ  አንድነት ፣ ሰላምና መቻቻል ዙሪያ ትላንት ከአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

”በሀገራችን  በአሁኑ ጊዜ እየተስተዋለ ያለው ግጭት ባለፉት 27 ዓመታት ለኢትዮጵያዊ አንድነት ትኩረት አለመስጠታችን ነው፣ ይህ ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ የነገይቱ ባለራዕዮችን እየተፈታተነ ይገኛል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ወደዚህች ምድር ብሔርን ምርጫ አድርጎ የመጣ ማንም እንደሌላ የተናገሩት አቶ ኦባንግ ሰው ማየት የሚገባው ሰው  መሆኑ እንጂ በዘርና በብሔር መሆን እንደማገባም አመልክተዋል፡፡

በሀገሪቱ የህግ የበላይነት እንጂ የዘር የበላይነት ሊኖር እንደማይገባ ጠቁመው ኢትዮጵያ እንድትለወጥ እያንዳንዱ ዜጋ ከብሔር አመለካከት ነፃ መሆን እንዳለበት አስረድተዋል ፡፡

”በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች የኢትዮጵያ እንጂ ተዋጽኦ አይደሉም፣ ደግሞ አንዳችን ያለአንዳችን መኖር አንችልም ስለዚህ ተማሪዎች የጥላቻ ሳይሆን የአንድነት ነፀብራቅ ልሆኑ ያገባቸዋል” ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ የተለያዩ ግጭቶች ቢኖሩም የዴሞክራሲ መሠረት እየተጣለ መሆኑን የገለጹት  አቶ ኦባንግ የተፈጠረው በነፃነት የመናገር ዕድል  በመጠቀም ለሀገሪቱ አንድነት፣ ለሰላምና መቻቻል ሞጋቾች እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ባለቤት እንደመሆኗ ባለፉት ጊዜያት በአንድነት ሳይሆን በልዩነት ላይ ትኩረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

”ቀደምት አባቶቻችን በአንድነት ወግ ያደጉ በመሆናቸው የተለያዩ የሀገራችን ፈተናዎችን በድል ተወጥተው ለእኛ አስረክበዋል” ብለዋል፡፡

ወደ ቀድሞ የአንድነት ታሪክ ለመመለስ የመሪነት ሚና መጫወት ያለባቸው  የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ መሆናችንን መዘንጋት እንደሌለባቸውም አመልክተዋል፡፡

”ብሔራዊ መግባባትና አንድነት ላይ ባለመሠራቱ በክልል የታጠሩ ነፃ አዉጪ የፖለቲካ ድርጅቶች እየተፈጠሩ እንጂ ብሔራዊ አመለካከት ያላቸው ጥቂቶች ናቸው”  ያለው ደግሞ በዩኒቨርስቲው የፕሮዳክሽን ምህንድስና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ግሩም አጅሬ ነው፡፡

ተማሪ ግሩም እንዳለው የዘር ፖለቲካ ባመጣው ጠባብ አመለካከት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተቻችሎ ለመኖር እየከበዳቸው ይገኛል፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ፣ ሰላምና መቻቻል አቶ ኦባንግ ገለፃ መስጠታቸው ራሱን እንዲያገኝ ያስቻለው መሆኑን ተናግሯል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ ምህንድስና የአራተኛ ዓመት ተማሪ ሪሐና ኑሩ በበኩሏ “ሀገራችን በዘርና በብሔር በሽታ የታመመችው ከእኛ የተነሳ ነው ” ብላለች፡፡

ሆኖም አቶ ኦባንግ በአንድነትና ሰላም ዙሪያ ያደረጉት ገለጻ በካምፓስ ህይወታችን አንድነት በመፍጠር ተባብረው ለመኖር እንደሚያግዝ ተናግራለች፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኛ ሸሽተን የወጣነውን ትግል ባዶ እጁን ታግሎ ነፃ አውጥቶን ወደአገር የመለሰንን ህዝብ ትግል አስተምራለሁ ማለት #ውርደት ነው። ትግልን እንማርበት ከሆነ እንጂ።" ኦቦ ሌንጮ ለታ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢሉአባቦር ዞን‼️

በኢሉአባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 43 #ክላሽንኮቭ ጠመንጃና 44 የጥይት ካዝና መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለፁት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተያዙት ከትላንት በስቲያ ሲሆን ከጋምቤላ ክልል በኮድ 3 -92943 ኢትዮጵያ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ወደ መሀል ሀገር በመጓጓዝ ላይ እያለ በህብረተሰቡ ተሳትፎ በቡሬ ወረዳ ሲቦ ቀበሌ በተደረገው #ፍተሻ ነው።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም #የሁሉም_ነገር_መሰረት ነው!!
.
.
ሰላም ከሌለ ወጥቶ መግባት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ሰርቶ መብላት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ መማር አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ልጅ ወልዶ ማሳደግ አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለሀገር አንድነት መነጋገር አይቻልም።

ሰላም ከሌለ እንቅልፍ ሊኖረን አይችልም።

ሰላም ከሌለ ስለሀገር ማሰብ አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለፖለቲካ ማውራት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለብሄር ማውራት አይቻልም።

ሰላም ከሌለ ስለነገ ማሰብ አይቻልም።

TIKVAH-ETH ሠላም የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን ስለሚየምን ዘውትር ስለሰላም ይሰብካል!!

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአምቦ መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር ዛሬ ጠዋት ተወያዩ። አምቦ የኦሮሞ ነፃነት ሀዉልት ናት ያሉት ጠ/ሚሩ ተማሪዎቹ እምቅ ችሎታቸውና የወደፊት እድሎቻቸውን በመገንዘብ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አበረታች መልእክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update “አባ ቶርቤ” በሚል መጠሪያ በድብቅ ሰዎችን በመግደልና በማስገደል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር 15 ደርሷል።
Via~Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ በመቀጠልም የጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢሮ ሀላፊ (Chief of Staff) ከዛም እንደገና የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር የተደረጉት አቶ ፍፁም አረጋ አሁን ደግሞ በአሜሪካ የኢትዮጵያ #አምባሳደር ሆነው ሊሾሙ መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፦ ኤልያስ መሰረት(ENF)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
4 ሺ ሊትር የምግብ ዘይት ተያዘ‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ4 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት መያዙን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአለፋ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ.ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር አብራራው አበጀ እንደነገሩን 4ሺህ 3መቶ 44 ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡ ተጭኖ የነበረውም የሰሌዳ ቁጥሩ አ አ 44 822 በሆነ አይሱዙ የጭነት መኪና ነው፡፡

መነሻውን ከባህር ዳር ያደረገው ተሽከርካሪ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ ላይ ነው የተያዘው፡፡ የወረዳው የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር ያዋሉትም የአካባቢው ህብረተሰብ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት መሆኑን ኢንስፔክተር አብራራው ተናግረዋል፡፡

ከሁለት ወራት በፊትም ከ45 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ተይዞ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል የፖሊስ ጽ.ቤት ኃላፊው፡፡

ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን የመግታት ስራው ለፀጥታ አካላት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ህብረተሰቡም የተለመደ ድጋፉን እንዲደርግ አሳስበዋል፡፡ ህብረተሰቡ ህገ ወጦችን በማጋለጥ እያሳየው ላለው ትብብርም አመስግነዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

ህግን በመተላለፍ የክልሉን ሰላምና ደህንነት በሚያደፈርሱ አካላት ላይ #እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል #ጥብቅ ትዕዛዝ ለሁሉም ዞኖች መተላለፉን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በምዕራባዊ የክልሉ አካባቢዎች ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር በውይይትና በትዕግስት ለመፍታት ሞክሬያለሁ ያለው ኮሚሽኑ እስከ ህይወት መስዋዕትነት የደረሰ ዋጋ አስከፍሎኛል ሲልም ገልጿል።

ትዕግስቱ የበዛ ነበር ያሉት ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ በቄለም ወለጋ የተገደሉትን 2 የዞን ፖሊስ አመራሮችን ጨምሮ የ12 ፖሊስ አባላት ህይወት ማለፉንና 77 ፖሊሶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ አያይዘውም የሚሊሻ አባላትን ጨምሮ በ40 የፀጥታ አካላት ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል ያሉ ሲሆን፣ የ29 ነዋሪዎች ህይወት ማለፉን ገልፀዋል።

በቄለም ወለጋ፣ በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በሆሮጉዱሩ አካባቢዎች የመንግስት መዋቅር ስራ መስራት ካለመቻልም በላይ እንዲፈርስ ተደርጓል ያሉት ኮሚሽነሩ በቄለም እና በምዕራብ ወለጋ አካባቢዎች የመንግስት ንብረት በኦነግ ታጣቂዎች መዘረፉን አስታውቀዋል።

በአካባቢው የሚደርሰው ጉዳት ከዚህም በላይ ነው ያሉ ሲሆን የግለሰቦችን ሳይጨምር ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከባንክ መዘረፉን ገልፀዋል።

ታጣቂዎቹ በአካባቢው ካለ ፖሊስ ጣቢያ 2072 ክላሺንኮቭ ጦር መሳሪያ መዝረፋቸውም ነው የተገለፀው።

ትዕግስቱ ከአንድ ወገን መሆኑ ዋጋ አስከፍሎኛል ያለው ፖሊስ ኮሚሽኑ ህግን የሚያውኩ አካላትን ለህግ የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥሏል ብሏል። ለዚህም ለሁሉም ዞኖች ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል ያለ ሲሆን የህዝቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ‼️ዛሬ ጥዋት በሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት አለመረጋጋት ተፈጥሮ ነበር። አለመረጋጋቱን የፀጥታ ሀይሎች ተቆጣጥረውታል። የአይን እማኞች እንደገለፁልን ከተፈጠረው ችግር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሲያውል አይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫ‼️

(15.04.2011ዓ.ም የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ)

ወቅታዊ የሀዋሳ ከተማን #ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በከተማው አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የተሰጣዊ ዜጣዊ መግለጫ፦

ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን ፖለቲካዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆኗ በግልፅ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ በከተማችን ሀዋሳም አልፎአልፎ አሉታዊ ክስተቶች ይስተዋላሉ፡፡

ከእነዚህ አሉታዊ ክስተቶች መካከል ከሰኔ 10/2010 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶችና የፀጥታ መናጋት በቀዳሚነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ይህን አልፎ አልፎ የሚከሰተው ግጭት ሀዋሳ ከተማ የምትታወቅበትን ነዋሪዎቿ ለዘመናት ያዳበሩት የመከአበክሮ የመፈቃቀድ እና አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር መንግስት አበክሮ በመስራት ላይ ነው፡፡

በከተማዋ ለዘመናት የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት ለማጠልሽት፣ ቅሬታ ለመፍጠርና የጥላቻ ጥቁር ነጥብ ጥለው ለማለፍ የሚዳክሩ አካላትን ጥረት ለማክሸፍና የህግ የበላይነትን ለማስፈን ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ ግጭቶች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ የጥፋት ሀይሎችን ለህግ በማቅረብ ባጠፉት ልክ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ቀጥላል፡፡

ይሁንና ፀረ-ሰላም ሀይሉ ከድርጊቱ ባለመቆጠብ የተሳሳተ የትግል ስልቱን በመቀያየር የእውቀት መገበያያ የሆነውን ትምህርት ቤት የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በሀዋሳ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በሚገኘው አዲስ ከተማ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት
ቤት ሁከትና እረብሻ በመፍጠር 12 ወጣቶች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ ተማሪ ያልሆኑ መሆናቸው ተለይቷል፡፡

በግጭቱም እርስበእርስ ድንጋይ በመወራወር በአስሩ ላይ ቀላል ጉዳት እንዲሁም ለፀጥታ ሀይሉ ባለመታዘዝ በሁለቱ ላይ ደግሞ ከባድ አደጋ ደርሷል፡፡

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ ወጣቶች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

የረብሻው መንስኤ ገና በፀጥታ ሀይሉ #በመጣራት ላይ ያለ ቢሆንም በርካታ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አካላት ያልሆኑ ነገር ግን እራሳችውን ከተማሪ ጋር ያመሳሰሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ተማሪዎችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ከተዋል፡፡

ክስተቱን #የብሔር_ግጭት ቅርፅ ለማስያዝ ጥረት ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገው የከተማው ነዋሪ ግን አልተባበራቸውምና ልፋታቸው ሳይሳካ #መና ሆኖ ቀርቷል፡፡

በዚህ ድርጊት #ጠንሳሽነትና ተሳታፊነት የተጠረጠሩ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ስራ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም
ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በፀጥታ ሀይሉና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት የከተማው #ፀጥታ_ሁኔታ ወደነበረበት የተመለሰ ሲሆን ለከተማው ሰላም ወዳድ ህዝብ የከተማው አስተዳደር ያለውን ክብርና አድናቆት እየገለፀ በቀጣይም ነዋሪው ከመንግስት ጎን በመቆም የከተማውን ሰላም ለማደፍረስና አብሮ የመኖር እሴትን ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላትን አጋልጦ በመስጠት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪውን እያቀረበ የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ሰላም እና ፀጥታ የማስጠበቅ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia