ሲዳማ ቡና Vs ባህር ዳር ከተማ🔝
#አዲስ_ግደይ 14ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ በሲዳማ ቡና መሪነት እየተካሄደ ባለበት ሰዓት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በትሪቡኑ የቀኝ ቦታ አስለቃሽ ጪስ ተወርውሮ ጨዋታው ለደቂቃዎች ተቋርጦ ነበር። በአሁን ሰዓት ጨዋታው ካቆመበት ደቂቃ ቀጥሏል። በአሁን ሰዓት ጨዋታው #ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#Update በጣና ሐይቅ ብዝሃ ሕይወት ጥናትና ምርምር የሚያደርገው #የጎርጎራ የዓሣ ምርምር ማዕከል ዳግም ተከፍቶ በዚህ አመት አጋማሽ አገልግሎት ሊጀምር ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የግጭት ትርፉ፦
🔹ለቅሶ
🔹ስቃይ
🔹መከራ
🔹ረሀብ
🔹ስደት
🔹ሞት
🔹የሚወዱትን ማጣት
🔹ችጋር
🔹በሽታ
🔹እልቂት
ማስተዋል የሚችል ያስተውል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🔹ለቅሶ
🔹ስቃይ
🔹መከራ
🔹ረሀብ
🔹ስደት
🔹ሞት
🔹የሚወዱትን ማጣት
🔹ችጋር
🔹በሽታ
🔹እልቂት
ማስተዋል የሚችል ያስተውል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️
በሌብነትና በሙስና የተጠረጠሩ ዋና ዋና የመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይህን ያለው ከተያዘው ወር መጀመሪያ ጀምሮ ባለፉት 100 ቀናት አከናውናቸዋለሁ ያላቸውን ተግባራት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡
በየትኞቹ ተቋማትና ፕሮጀክቶች ላይ ምርመራ እንደተጀመረ ለመናገር አሁን ጊዜው አለመሆኑን የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ተናግረዋል፡፡
የሌብነት፣ የሙስናና የምዝበራ ተግባራት ተፈፅሞባቸዋል የተባሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በጥናት ተለይተው ምርመራ መጀመሩን አቶ ዝናቡ ተናግረዋል።
ህገወጥ የገንዘብና የጦር መሳሪያ ዝውውርን፣ የመንጋ ፍትህን እና ስርዓት አርበኝነትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ረቂቅ የህግ ማሻሻያዎች መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ተናገረዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ያለው የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ የተንዛዛ ምልልስ የበዛበትና ፍትሃዊነት የጎደለው በመሆኑ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ🔝
በተማሪዎች መካከል ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በሚያነሳሱ አካላት ላይ መንግስት አስፈላጊውን #እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠየቁ።
ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃን ሳያረጋግጡ ለሌሎች ከማስተላለፍ ተግባር መቆጠብ እንደሚገባቸውም የሐይማኖት አባቶች አስገንዝበዋል።
በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል ሰሞኑን በተፈጠረው አለመግባባት ዙሪያ ከተማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ትናንት በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በውይይቱ ከተሳተፉት መካከል የ2ኛ ዓመት የማኔጅመንት ተማሪ ሐና ይመር እንደገለፀችው በተቋሙ ሁከትና ግርግር የሚፈጥሩ አካላት የማንኛውንም ብሔር እይወክሉም፡፡
”የተከሰተው ችግርም የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ያሰቡ ሐይሎች ተግባር እንጂ የተማሪው ፍላጎት ባለመሆኑ ድርጊቱን እናወግዛለን” ብላለች።
በግቢው ጸብ ሲፈጠር ወደ ቡድንና #ብሔር የመቀየሩ ነገር እየጎለበተ ስለሚገኝ ተማሪው ከዚህ ዓይነቱ ተግባር #ሊቆጠብ እንደሚገባም ጠቁማለች፡፡
ተቋሙም በትምህርታቸው ተገቢውን ውጤት ሳያገኙ ተሰናብተው እያለ ተመዝግበው የሚገኙ ተማሪዎችና #በጥበቃ ስራ ላይ አድሏዊ አሰራር የሚፈጽሙ የጸጥታ ሐይሎችን ተግባር መገምገም እንደሚገባው ተናግራለች።
”ወንጀለኛ ተማሪ ብሔርን #አይወክልም፤ ጥፋት የፈጸሙ የየትኛውም ብሔር ተማሪዎች ለህግ መቅረብ አለባቸው” ያለው ደግሞ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ ፉዓድ መሀመድ ነው፡፡
ተማሪዎችም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላትን ተግባር ማውገዝና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራን ማጠናከር እንደሚገባቸው አሳስቧል፡፡
የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ ሙፍቲ መንዛ እንደተናገረው ተግባሩ በአገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ የታቀደ ሴራ በመሆኑ ተማሪው ተግባሩን ማውገዝ ይገባዋል፡፡
”ዩኒቨርሲቲውም አመራሩ፣ አገልግሎት ሰጪውና ሌሎች አካላት በተማሪዎች መካከል መከፋፈል እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆኑ አሰራሮችን ሊገመግም ይገባል” ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የሐይማኖት አባት መላዓከ ሰላም ማንደፍሮ በበኩላቸው “ተማሪው የሀይማኖት አባትና የአገር ሽማግሌዎች የሚያስተላልፉትን መልዕክት በተግባር ማዋል ይገባል፤ በተለይ ደግሞ ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃን ሳያረጋግጡ ለሌሎች ከማስተላለፍ መቆጠብ አለባቸው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
”በተማሪዎች መካከል ልዩነትን የሚፈጥሩ አካላት ተግባር የሐይማኖት አባቶች ያወግዛሉ” ያሉት ደግሞ ሼህ አብዱለጢፍ መታን ናቸው፡፡
ተማሪዎችም ቀያቸውን ለቀው ለመጡለት የመማር ማስተማር ዓላማ ቅድሚያ ሰጥተው እኩይ ተግባራትን በጋራ መዋጋት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድሩ የክልልና የፌዴራል ግንኙነት አማካሪ አቶ #ባዘዘው_ጫኔ እና የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ በተቋሙ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡
ድርጊቱ እንዳይባባስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የግቢው ማህበረሰብ፣ የጸጥታ አካላትና ተማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ተግባሩ የተማሪዎች አለመሆኑን በመረዳት ሁሉም የተቋሙ ተማሪ አንድነትን በማጠናከርና አኩሪ እሴቶችን በማጎልበት እኩይ ተግባሮች መታገልና የፍቅር መቻቻልና የይቅርታን ባህልን ማዳበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶክተር #ጀማል_ዩስፍ ችግሩ የተፈጠረው በአገሪቱ የተጀመረውን ለውጥ የማይፈልጉ አካላት በተማሪዎች መካከል ልዩነት በመፍጠር የራሳቸውን ዓላማ ለማሳካት ያቀዱት ሴራ መሆኑን ገልፀዋል።
ተማሪዎችም በአመራሩም ሆነ በጸጥታ አስከባሪ ሐይሎች ላይ ያነሷቸው ችግሮችን ለመፍታት ዩኒቨርሲቲው ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የጥፋቱ አካል የሆኑ ተማሪዎች በህግ እንደሚጠየቁም ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ የተቋሙ፣ የፌዴራልና የክልል ተወካይዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌሎች፣ የጸጥታ አካላትና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን በእለቱም እርስ በርስ ተጋጭተዋል የተባሉት ተማሪዎች #እርቅ ፈጽመዋል።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ ም ከምሽቱ 1 ሰዓት በተከሰተ አለመግባባት በአምስት ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

ብራዚል‼️
ብራዚል ውስጥ ሥራ ላይ የነበሩ 430 ሐኪሞች ሥራቸዉን አቋርጠዉ ወደ ሃገራቸዉ ወደ ኪዩባ ተመለሱ። በብራዚል በሕክምና ዘመቻ ላይ የነበሩት እነዚህ የኪዩባ የሕክምና ባለሞያዎች በድንገት ሥራችሁን አጠናቃችኋል የተባሉት በአዲስ ተመራጩ የብራዚል ፕሬዚዳንት #በዣር_ቦልዞናሮ እና በኩዩባ መንግሥት መካከል በተቀሰቀሰ #ግጭት መሆኑ ታዉቋል። 8300 የኪዩባ ሐኪሞች «ተጨማሪ የሕክምና ባለሞያ» «Mais Médicos» በተሰኘ የመንግሥት ስራ መርህ ግልጋሎት ለመስጠት ነዉ ወደ ብራዚል የመጡት። ኩባውያኑ የብራዚል ሐኪሞች ጋር የሕክምና ባለሞያ እጥረት በሚታይባቸዉ የብራዚል አዉራጃዎች ዉስጥ ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

ኮሎኔል ጉደታ ኦላና‼️
የዐቃቤ ህግን ስራ ለማደናቀፍ የሞከረው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ። የቀድሞው የኢትዮ ቴሌኮም የሴኪዩውሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል #ጉደታ_ኦላና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዉ የሙስና ወንጀልን እያጣሩ ባሉ ባለሙያዎች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በመፈጸም እና የፌደራል የዐቃቤ ህግን ስራ በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው መቅረባቸውን የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
በተጠርጠጣሪው በባለቤቱ ስም 438 ሺህ 222 ብር በኦሮሚያ ኢንትርናሽናል ባንክ አፍሪካ ቅርጫፍ መኖሩን እንዲሁም በ2010 ሚያዚያ ወር ሱሉልታ አካባቢ 550 ሺህ ብር በመንደር ውል መሸጣቸውን በማስረጃነት ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
ተጠርጣሪው በተከላካይ ጠበቃው አማካኝነት የቀረበበት የምርመራ መዝገብ ተገቢነት እንደሌለው በማስረዳት በዋስ ሊወጣ እንደሚገባ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ከተመለከተ በኃላ ፖሊስ ቀሪ የምርመራ ሰራዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ በማለት ተጨማሪ 7 የምርመራ ቀናትን በመፍቀድ ለህዳር 20 ቀን 2011ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ