TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
*አስቸኳይ የሰብዓዊነት ተግባር ላይ ይሳተፉ*

(ሼር ይደረግ!)

ከቤኒሻንጉል #ለተፈናቀሉ ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በህይወት ለመድረስ የአዲስ አበባ እና የአካባቢው ነዋሪዎች የእርዳታ ማስተባበሪያ መርሐ ግብር በመልካም ሁኔታ እየሔደ ነው።

የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ መስከረም 28 እና 29 በሀገር ፍቅር ቴአትር ከሚሰበሰበው እርዳታ #በተጨማሪ ቅዳሜና እሁድ ብቻ ለሚመቻቸው ወገኖቻችን ከዚህ በታች ባሉ ግዚያዊ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች ያዘጋጃችሁትን እርዳታ እያስመዘገባችሁ መለገስ ትችላላችሁ።

ለማስታወስ ያህልም የእርዳታ አይነቶቹን በድጋሚ እናስታውቃለን።

#የማይበላሹ_ምግቦች
መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች
ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት
ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ
የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)
በመሆኑም ከዚህ በታች በተቀመጡት ተጨማሪ አድራሻዎች ቅዳሜና እሁድን ብቻ የቻሉትን በአቅራቢያዎ መለገስ ይችላሉ።

🔹ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ ~0911219235 ቦሌ ኤድና ሞል ዝቅ ብሎ ምስራቅ በር ስጋ ቤት @Blen Sahlu

🔹ኮልፌ እና 18 ማዞሪያ ፍቅሩ አብጤ +251911319571

🔹ሰባተኛ የአማኑኤል ታክሲ መያዣ 0911793475 ደንበል ጀርባ ከ ላፓሪዝያን ፊት ለፊት ሶሎሞን ሞባይል +251912634363 @Solomon Mengesha

🔹ፒያሳ ማስታወቂያ ሚንስቴር አካባቢ ተስፋዬ ለማ ~+251912914748
ለበለጠ መረጃ መሐመድ ካሳ ወይንም ያሬድ ሹመቴን በ0930 36 52 44 ማግኘት ይችላሉ።

ጫካ ያደሩ ህፃናትና እናቶች፤ አረጋውያንና ደካሞች ከምንም በላይ "የኢትዮጵያዊያን ያለህ!" እያሉ ነው።

#ሰብዓዊነት_ይቅደም !!

(ከአንድ ግዜ በላይ ሼር በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ!)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
EiTex⬆️የባህርዳር EiTex የመግብያ ላልተወሰነ ግዜ መራዘሙ ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዮን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ኤርትራ እንደሚጓዙ ተሰማ። በቆይታቸውም ከኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ ኤርትራ ፕሬስ
@tsegabwolde @tikvahethiopi
#update ስድስተኛው ዓለም አቀፍ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ የሚያጠነጥን ጉባኤ #በባሕር_ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሰላም በአጠገባችን ያለ ግን የማንገዛው፤ ካልጠበቅነው ግን የሚጠፋ ነው፡፡ በመንግሥት በኩል ትኩረት ሰጥተን ሰላምን ለመጠበቅ እንሠራለን፡፡ ግን ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች፣ በጋራ #ሰላምን እንድንጠብቅ ጥሪየን አቀርባለሁ››

▪️▪️ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ - ሀዋሳ▪️▪️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለBiT ተማሪዎች‼️

ቀን 26/01/2011 ዓ.ም

በባህር ዳር ዩንቨርስቲ ለባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ #ማራዘሙን የገለፀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በ2010 ዓ.ም ማጠቃለያ ፈተና ላልወሰዳችሁ ( ለ1ኛ፤2ኛ እና የ3ኛ ዓመት Holistic ፈተና ተፈታኝ ) የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች #የማይመለከት መሆኑን አውቃችሁ ኢንስቲትዩቱ ባወጣላችሁ የመግቢያና የፈተና መርሃ ግብር መሰረት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ምንጭ፦ የBiT የፌስቡክ ገፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ጥቆማ‼️

ከአዲስ አበባ ወደ ሱሉልታ በሚወስደው መንገድ ሚዛን ጋር የመኪና ግጭት አደጋ ደርሷል። የሚመለከተው አካል ወደስፍራ እንዲሄድ ከቦታው ጥሪ ቀርቧል።

ቻናላችን የደረሰውን ጉዳት አጣርቶ ያሳውቃል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ⬆️የተማሪዎች የመግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጎንደር⬆️

"ዛሬ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 127 ወንድ እና 31 ሴት ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ እና ክቡር ዶ/ር አርቲስት መሃሙድ አህመድ በክብር እንግድነት ተገኝተው ነበር። ተማሪ ፍሬህይወት በከፍተኛ ነጥብ የወርቅ ተሸላሚ ሆናለች። "

©Dave ከጎንደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ማርቆስ⬇️

"በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በከሠዓቱ መርሃ ግብር የአመቱን የስራ ሪፖርት የሚያቀርብ ሲሆን አጠቃላይ የተቋማት የተማሪዎች ህብረት አዲስ የምርጫ ደንብ ውይይት ተደርጎበት ከተወሰነ በኋላ MoE ከፍተኛ ትምህርት ድኤታ ይፀድቃል። ጎን ለጎንም በሰላማዊ መማር ማስተማር፣ መልካም አስተዳደር፣ ልዩ ድጋፍ ስለሚሹ ተማሪዎችን በተመለከተ እና ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ለተማሪዎች ህንረት ተልዕኮ የሚሰጥ ይሆናል። ጉባኤው "እኛ ተማሪዎች ሀገራችን በምታደርገው የላውጥ ጉዞ ሚናችን የጎላ ነው!" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።"

©መሌ ከWKU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ‼️ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ተራዝሟል። ነገእ ግን 2ኛ አመት እና ከዚያ በላይ የመደበኛ ጤና ተማሪዎች ጥቅምት 1 እና 2 ወደተቋሙ እድትገቡ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia