TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ዘይት መጭመቂያ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ጤፍን ከባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል እንጀራ በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ በህብረተሰቡ #ጥቆማ በቁጥጥር
ስር ውሏል፡፡

ወ/ሪት ወርቄና ትዕግስት አዳነ እንጀራ በመጋገር ለአንድ ወር ሰርተዋል፡፡

በቆይታቸውም 45 ኪሎ ግራም ጤፍን 100 ኪሎግራም ጀሶ ጋር በመቀላቀል ለባለሱቆች ያከፋፍላሉ፡፡

የማይሸጥና የተበላሸ እንጀራን #ጀሶ ከተቀላቀለበት ጤፍ ጋር እንደገና
በመቀላቀል ለጥቅም እንደሚውል የታዘቡትን ያስረዳሉ፡፡

በህብረተሰቡ ላይ ብዠታ የሚፈጥሩ ነገሮችን ለፖሊስና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ለዳት ሳጅን ተክሌ በቀለ ጠቁመዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ የምግብና መድሀኒትና ጤና እንክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በሐይሉ ዘለቀ በተገኘው ጥቆማ መሰረት ወደ ቦታው ከባለድርሻ አካላት ጋር ወደ ቦታው በመሄድ እንጀራ ጋጋሪዎች የንግድ ፍቃድና የብቃት ማረጋገጫ የሌላቸው መሆኑን ጠቅሰው ለእንጀራ የሚውል ሶስት ኩንታል #ባዕድ ነገር ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው በሚሸጡ ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ: የክ/ከተማውን ኮምኒኬሽን ቢሮ
@Ttsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ‼️መንግስት ወደሀገር ያስገባቸውን እና ሀገር ውስጥ ያሉትን #ሁሉንም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ክትትል ሊያደርግባቸው ይገባል። ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት አሁን እያታዩ ያሉ መስመር የለቀቁ ከስነ ምግባር የወጡ እቅስቃሴዎች ከወዲሁ ሊገቱ ይገባል።

‼️የሩዋንዳውን እልቂት ማስታወስ ተገቢ ነው‼️

ነፃነት ማለት እንደፈለጉ መሆን፤ ህግ መጣስ፤ ከስነ ምግባር ውጭ መሆን አይደለም። ሁሉም ነገር ገደብ እና ልክ አለው። አሁን መሬት ላይ ያለው ጥብቅ #እርምጃዎችን የመውሰድ እንቅስቅሴ ይበረታታል።


የመንግስት ተቀዳሚ ስራው ህግ እና ስርዓትን ማስከበር ነው‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ📌ከአዲሱ የትምህርት ፎኖተ ካርታ ጋር ተያይዞ የ2011 ዓ.ም. #ተመራቂ የለም እተባለ የሚሰራጨው መረጃ የሀሰት መሆኑ ልታውቁት ይገባል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ⬇️

በድሬደዋ አስተዳደር ባሳለፍናቸው ጥቂት ቀናት በከተማው ግጭቶችና ሁከቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችና የተለያዮ የህ/ብ ክፍሎች #የስጋት ሀሳቦች መመንጨታቸውን ተከትሎ ፖሊስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠቱ የሚታወቅ ነው::

ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና መላው ህብረተሰብ ባከናወናቸው ተግባራት ስጋቶቹን #እያመከነ በከተማው አሁን ላይ ያለው አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲገኝ ያደረገ ሲሆን ይህው የፀጥታ ሀይልና ህብረተሰብም ይህንኑ ሰላምና ፀጥታ አጠናክሮና የበለጠ አስጠብቆ በማስቀጠል ላይም ይገኛል። በዚህም ፖሊስ ለመላው የአስተዳደሩ ነዋሪና ወጣቶች ምስጋናውንም ያቀርባል።

ይህ ይሁን እንጂ ከፀጥታ ማስፈንና የህግ የበላይነት ከማረጋገጥ ተግባር ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ያሉና ሊታረሙ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉም ልብ ሊባል ይገባል።

በመሆኑም አሁን ላይ ያለውን ሰላምና ፀጥታ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የተጀመሩ የለውጥ ሂደቶች ለማስቀጠል ብሎም የትርምስና የብጥብጥ አላማ ያላቸውን ሀይሎች ከምንጫቸው ለማድረቅና እኩይ ተግባራቸውን ለማምከን ትኩረት መስጠትና ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፖሊስ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ክልከላ የተደረገ መሆኑን ያሳውቃል።

1ኛ:- ለፖሊስና ለፀጥታ ሀይሉ አሳዉቆ ተገቢውን ባጅና መለያ ሳያደርጉና ሳይዙ በቡድን ተደራጅቶ የጥበቃ እገዛ ሰጪነን ብሎ መንቀሳቀስ

2ኛ:-በተናጥልም ይሁን በቡድን የስለት መሳሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ

3ኛ:-ከአስተዳደሩ የፀጥታ ምክር ቤትና ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኙ ህዝባዊ ስብሰባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን #በጥብቅ ያሳስባል።

መላው የአስተዳደራችንም ነዋሪ ይህንኑ በመገንዘብና በመረዳት ለሰላሙና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ እያደረገ ያለውን አስተዋፆና እያሳየ ያለውን እጅግ ከፍተኝ ትብብርና እገዛውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጨምሮ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም
የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶ/ር #አብይ_አህመድ በመጨረሻ ሰአት በተደረገ የጉዞ #ለውጥ ምክንያት በሚቀጥለው ሳምንት የአለም መሪዎች ከሚገናኙበት የተ.መ.ድ ስብሰባ #መቅረታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያለው ግለሰብ ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገልጿል። ዶ/ር አብይ በዘንድሮው ስብሰባ ከፍ ባለ ሁኔታ ከሚጠበቁት የአለም መሪዎች አንዱ እንደሚሆኑ ተገምቶ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ድፍድፍ ነዳጅ⬇️

በኢትዮጵያ ለሙከራ የወጣው ድፍድፍ ነዳጅ ለኤክስፖርት የሚውል አለመሆኑን የመአድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በማዕድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ #አሰፋ_ኩምሳ ድፍድፍ ነዳጁ ለኢንዱስትሪዎች በግብአትነት የሚውል
መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድፍድፍ ነዳጁን የማውጣት ስራ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል ከወራት በፊት በሶማሌ ክልል ድፍድፍ ነዳጅ በሙከራ መልክ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Haramaya University⬇️

"To all HU, HiT (HU,Haramaya instititute of Technology)senior students the registration date is postponed to tikimt 1&2 and for fresh students tikimt 6&7. Hunde Tilahun HIT students union president."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሀዋሳ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች በመኖሪያ ቤቶች ላይ ልዩ ምልክት እየተደረገ እንደሆነ እና ይህም ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

📌መንግስት በዚህ አይነት ህዝብን የማሸበር ድርጊት ውስጥ ያሉ አካላትን ከከተማው ህዝብ ጋር በመሆን ሊለይ እና ለህግ ሊያቀርብ ይገባል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

"በአዲስ አበባ በምንገኝ የአልማ አባላትና ደጋፊዎች የተገዙ አስር አምቡላንሶች ለአማራ ልማት ማህበር (አልማ) አስረክበናል። ከአማራ ክልል ውጪ የምንገኝ የክልሉ ተወላጆች በአካል ከክልላችን ብንርቅም ልባችን፣ ሃሳባችንን እና መንፈሳች ክክልላችን ህዝቦች ጋር መሆንን ከመናገር ባለፈ በተግባር ያረጋግጥንበት ተግባር ነው።"

©ወ/ሮ ዳግማዊት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶማሌ ክልል⬇️

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውና በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይፈጸምበት ነበር የተባለውን ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራው #ማእከላዊ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት #ተዘጋ

የሶማሌ ክልል መንግስት በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ እየወሰደ ከሚገኘው የለውጥ እርምጃዎች መካከል ባለፉት አመታት በክልሉ ህዝብ ላይ ሲፈጸሙ የነበሩትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ዋነኛው ነው፡፡

የክልሉ መንግስት ካቢኔ ከትላንት ወዲያ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ ባለፉት አመታት በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች የሚታጎሩበትና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸምበት የነበረ ነው በሚል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውን ማእከላዊ ማረሚያ ቤት እንዲዘጋ ወስኗል፡፡

በዚህ መሰረት በዛሬው እለት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፤ ታዋቂ ግለሰቦች ፤ ሙሁራን እንዲሁም ለረጅም አመታት በተለያዩ የአለም ክፍሎች በመዟዟር በክልሉ የሚፈጸሙትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችን ሲቃወሙና ሲታገሉ የቆዩት አክቲቪስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ አብዱላሂ ሁሴንና አክቪስቲስት አብዱረሺድ አሊ ሸአ በተገኙበት ማረሚያ ቤቱ በዛሬው እለት በይፋ ተዘግቷል፡፡

በዛሬው እለት የተዘጋው የጅግጅጋ ከተማ ማእከላዊ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ህጉን መሰረት በማድረግ እንደሚለቀቁም ከክልሉ መንግስት ለኢቢሲ የተላከው መግለጫ ያለክታል፡፡

የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርም በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የማሰቃያ ማዕከሉን መንግስት ለመዝጋት መወሰኑ መልካም እርምጃ ሲል በትዊተር ገፁ አወድሶታል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ📌የከተማይቱ ሰላም እንደከዚህ ቀደሙ ነው። በከተማይቱ ውስጥ ምንም አይነት የተፈጠረ ችግር የለም። ህብረተሰቡን በሰላም እና በፍቅር የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን እያደረገ ነው የሚገኘው። በተለይም በአሁን ሰዓት ውቢቷ ከተማ የ"ኢህአዴግ"ን ድርጅታዊ ጉባኤ ለማዘጋጀት ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ጥበቃውም ጠንከር ያለ ነው።

📌ከሰሞኑን የአንዳድ ሰፈር ነዋሪዎች ቤታችን ላይ ሳናውቀው ምልክት ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል። በርግጥ ከዚህ ቀደም በየቤቱ ለተለያዩ ምክንያቶች ምልክት ተደርጎባቸዋል። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ምልክት የተደረገቸው ቤቶች እንዳሉ ለመስማት ተችሏል። ይህም ከሰሞኑ በድሬዳዋ ከተማ የሚወራውን ነገር በመስማት ስጋት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።(የፌስቡክን ተፅዕኖ ማንሳቱ ተገቢ ነው)

📌እንዲህ አይነት ነገሮች ሲፈጠሩ የቀበሌ አመራሮች ለህብረተሰቡ በቂ መረጃ ሊሰጡ ይገባል። ሁሉም ህብረተሰብ ግን ከፖሊስ፣ እንዲሁም ከከተማይቱ ወጣቶች ጋር በመሆን ሁሌም ለሰላም ሊሰራ ይገባል።

▪️በነገው ዕለት የከተማውን አስተዳደር ስለጉዳዩ ጠይቄ በቂ እና ታአማኝነት ያለው መረጃ አደርሳችኋለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስፖርት📌 በ2010 ሳይጠናቀቅ ወደ 2011 የተሻገረው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በዛሬው እለት ቀጥሎ ተካሂዷል። በዛሬው እለትም #በሀዋሳ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሲዳማ ቡና መካከል ቀጥሎ ተካሂዷል። በዛሬው እለት የተደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡና ጨዋታም በመደበኛ ሰዓት ያለምንም ግብ 0ለ0 መጠናቀቁን ተከትሎ በመለያ ምት አሸናፊው ተለይቷል። በዚሀም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን በመለያ ምት 7ለ6 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችሏል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ⬇️

"ሀይ ፀግሽ በዛብህ ነኝ ለሀዋሳ ዛሬ በሀዋሳ ስታዲየም በሲዳማ ቡና እና በቅዱስ ጊርጊስ መካከል የተደረገ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በሰላም ተጠናቋል። በጨዋታ ውስጥ ምንም አይነህ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ኤጄቶዎች ከፖሊስ ጋር በመተባበር ብዙ ዝግጅት አድርጎ ነበር። ዛሬ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ጨዋታ በ9:00 ስዓት ላይ ተጀምሮ የመደበኛ ሰዓት ያለምንም ጎል ተጠናቋል። በመጨረሻም ቅዱስ ጊዮርጊስ 7 ለ 6 በሆነ ውጤት በፍፁም ቅጣት ምት ማሸነፍ ችሏል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚኒሊኒየም ሜደካል ኮሌጅ፦

የ2011 ዓ.ም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን የሪዝደንስ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ለስፔሻላይዜሽን ትምህርት በኮሌጃችን ለተመደባችሁ በሙሉ:- መስከረም 28 እና 29/2011 ዓ.ም ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

©ሪጅስትራር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማንነቱን መግለፅ አልፈልግም...

"ፀጋ በቅድሚያ ለሰላም ያለህን አቋም እና ለህዝቡ ትክክለኛና እውነተኛ መረጃ ለማድረስ የምታደርገውን ጥረት ሳላደንቅ አላልፍም። መንግስት ከመቼውን ጊዜ በላይ የሀገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል። የሰላም እና የህግ የበላይነት ጉዳይ መንግስት ለድርድር የሚያቀርበው ባለመሆኑ ዜጎች ያለምንም ስጋት እና ፍራቻ የሚኖሩባትን ሀገር ለማስቀጠል ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ህብረተሰቡም የህግ የበላይነት እና አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ ከመንግስት እና ከፀጥታ ሀይሉ ጎን እንዲቆም መልዕክቴን አስተላልፍልኝ። አመሰግናለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia