#update ኦቦ ዳውድ ኢብሳ⬇️
በሀገሪቱ አየታየ ያለው ለውጥ እንዳይደናቀፍ ጥያቄዎች #በሰላማዊ መንገድ ሊቀርቡ አንደሚገባ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ገልጸዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ ከfbc ጋር በነበራቸው ቆይታ ለውጡ እንደዚህ ቀደም ለውጦች በጅምር እንዳይቀር ሁሉም የየበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
በተለይም ወጣቱ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችንም ሆነ ቅሬታዎች ሲገልጽ፥ ህግና ስርዓትን በተከተለና የሌሎችን መብት በማክበር ብቻ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ይህ ካልሆነ ብዙ #መስዋትነት የተከፈለበት ለውጥ ከግቡ ሳይደርሰ ሊጨናገፈና ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊወስድ እንደሚችል ነው አቶ ዳውድ የተናገሩት።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወደ ሀገር የገባውም #ልዩነትን ለማጥፋት እንዳልሆነ የገለጹት ሊቀመንበሩ የሰው ልጆች እስካሉ ድረስ ልዩነቶች መኖራቸውንም አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ልዩነቶን #ለማጥበብ በተረጋጋ መንፈስና በሰከነ አካሄድ ውይይቶችን ማድረግ እደሚየስፈልግ ተናግረዋል ተናግረዋል።
ሰውን #በመግደልና ንብረትን በማውደም ልዩነት ይሰፋል እንደሆነ እንጂ የማይጠብ መሆኑንም ያመላከቱት የግንባሩ ሊቀመነበር ይህንን አይነት ድርጊት መቼም ቢሆን ድርጅታቸው የማይደግፍና የማይቀበል መሆኑን አስገንዝበዋል።
አብዛኛው ህዝብ ለውጡን እንደሚፈልገው የተናገሩት የኦሮሞ ነጻነት ግናባር የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
እንደ አቶ ዳውድ ገለጻ አብዛኛው ህዝብ ለውጡን እንደሚፈልገው ሲሆን፥ የኦሮሞ ነጻነት ግናባር እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
መስዋትነት የተከፈለውም የሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበርና ለመስጠበቅ መሆኑንም አመላክተዋል።
©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ⬇️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈናቀሉ ዜጎችን #እየጎበኙ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ቀትር ላይ በአዲስ አበባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ መድሃኃኒያለም ትምህርት ቤት ተገኝተው በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተፈናቀሉ ዜጎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ #ቡራዩ አቅንተውም በተመሳሳይ መልኩ በመጠለያ ውስጥ ካሉ ዜጎች ጋር ተመሳሳይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ
ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፈናቃዮችና ተጎጂዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችና የችግሩን ስፋት ለማጤን ነው በአካል ተገኝተው ጉብኝት እያደረጉ ያሉት፡፡
በበጎ ፈቃደኞችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተፈናቃዮቹ እየተደረገ ያለውን ድጋፍንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመልክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በተደራጁ ኃይሎች በርካታ ዜጎች ለሞት፣ ለጉዳት፣ ለንብረት ውድመትና መፈናቀል መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡
እነዚህን ችግሩን የፈጠሩ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑንም መንግስት መግለፁ ይታሳል፡፡
©etv

#update የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት እየተራዘመ ይገኛል የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚይደርጉትን ጥሪ እንደደረሰኝ አቀርባለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዛሬው ዕለት ይጀምራል ተብሎ የነበረው 9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ ለነገ #መራዘሙ ተገልጿል። ለዚህም ተሳታፊዎችና የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በጅማ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ በዘጠነኛው የኦህዴድ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የቀረበ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሪፖርት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
📌ነገ በሚጀመረው ድርጅታዊ ጉባኤ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
📌ነገ በሚጀመረው ድርጅታዊ ጉባኤ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 02 እና 03 ነው።
©የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ፦
ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት በ08/01/2011 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በአገራችን እየተስተዋሉ ያሉ ህገ-ወጥና የስርዓት አልበኝነት እንቅስቃሴዎችን ገምግሞ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።
ባለፉት አምስት ወራት የዴሞክራሲ ምህዳርን ለማስፋት በርካታ ስራዎች ተከናውነው ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል። በዚህም መላው ህዝባችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአገሩ ተስፋ እንዲሰንቅና በሃገሩ መጻዒ እድል ላይ የራሱን አስተዋፅኦ ለማበርከት እንዲነሳሳ አድርጓል።
ሆኖም ግን የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከህግ የበላይነት ውጭ #የሚታሰብ አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
በለውጥ ውስጥ እንደመሆናችን መጠን መንግስት ችግሮችን በሀይል ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ሆደ ሰፊነትን ቢያሳይም ይህን እንደ አቅመ ቢስነት የተመለከቱ የጥፋት ሀይሎች #የወጣቱን ስሜት በማነሳሳት የሚፈፅሟቸው ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየተበራከቱ
መጥተዋል።
ሰሞኑን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በተከሰቱ ግጭቶች በርካታ ዜጎች ውድ #ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህን ብጥብጥ በተለያዩ አካባቢዎች
ለማስቀጠል፣ በሱማሌ ክልልና በሌሎች አካባቢዎች የከሸፈባቸውን የጥፋት አቅድ በሌላ ሙከራ ለመቀጠል እንዲሁም በመስከረም መጨረሻ የሚካሄደውን #የኢህአዴግ ጉባኤ ለማደናቀፍ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።
#ሁከቱ ከላይ እንደሚመስለው በትናንሽ ችግሮችና ልዩነቶች የሚነሳ ሳይሆን በታቀደ መልኩ የሚከናወን፣ ድብቅ ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው፣ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት ወይም ግጭቶች ሲከሰቱ እነሱን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የማባባስ እና ሃገራችንን የማያባራ ግጭት ሰለባ በማድረግ ለውጡን ለማሽመድመድና ለመቀልበስ የሚደረግ ሴራ አካል ነው።
በመሆኑም መንግስት ያለበትን የህግ የበላይነትና የዜጎችን #ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት ለመወጣት ማንኛውንም ህጋዊ፣ #የማያዳግምና
ተገቢ #እርምጃ ለመውሰድ በሙሉ ዝግጅትና አቋም ላይ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ስርዓት አልበኝነትን ከዚህ በኋላ የምንታገስበት ልብ፣ የምንሸከምበት ትከሻ የለንም። በመሆኑም ለዜጎች ህይወት ዋስትና ለመስጠት መንግስት ማንኛውንም ህጋዊና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ የጀመረ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
#ወጣቱም በስሜት እየተገፋፋ፣ የፖለቲካ ነጋዴዎችና ዘራፊዎች መሳሪያ እየሆነ አፍራሽ ወደሆነ ድርጊት መምጣቱን መረዳት ይኖርበታል፡፡
በመሆኑም አውቆም ይሁን ሳያውቅ በህገ-ወጥ ድርጊት ላይ የሚሳተፍ ወጣትና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ህጋዊ እርምጃ #የሚወሰድበት መሆኑን አውቆ ከጥፋት ተግባሩ #እንዲሰበሰብ መንግስት ያሳስባል፡፡
የጥፋት ሀይሎች በሚያደርጉት የመጨረሻ መፍጨርጨር ለጊዜው የታወከው የህዝብ #ሰላም ወደ ነበረበት እንደሚመለስ መንግስት እያረጋገጠ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ የደህንነት ስሜት ተሰምቶት መንቀሳቀስና መኖር እስከሚችል ድረስ፥
መንግስት ሰላምና መረጋጋትን የማስከበር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል።
በዚህ ሂደት ውስጥ ወንጀሎቹን #በማቀነባበር ደረጃም ሆነ ለተቀነባበሩ ወንጀሎች መሳሪያ ሆኖ የተገኘ ሰው፣ በማንኛውም ደረጃ ወንጀል ላይ የተሳተፈ አካል ከህግ-ሊያመልጥ አይችሉም፤ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በህግ ተጠያቂ ይሆናል። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ #ልዩነትን በሚያሰፉና ብጥብጥን በሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ #አክቲቪስቶችና የፖለቲካ #ፓርቲዎች እጃሁን መሰብሰብ ይኖርባችኋል፡፡
በመጨረሻም፥ አሁን ከጀመርነው የሰላምና የዴሞክራሲ የለውጥ መንገድ ማንም ሀይል ሊያደናቅፈን እንደማይችል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ #ኢትዮጵያ

#update የ2011 የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ #መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ለኢቲቪ እንዳስታወቁት አዲስ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት ባለው ረቂቅ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ ተጨማሪ የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ስለሚደረግ ወደ የዩኒቨርሲቲዎች ቀደም ብሎ ተላልፎ የነበረው ጥሪ ወደ ጥቅምት ተሸጋግሯል፡፡
በመሆኑም ዩኒቨርሲቲዎች ከመምሀራኖቻቸው እና ከአስተዳደር ሰራተኞቻቸው ጋር በረቂቅ ፍኖተ ካርታው ላይ ውይይት ካደረጉ በኃላ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ እንደየ ዩኒቨርሲቲዎቹ መርሃ ግብር የተማሪዎች መግቢያ የጥሪ መርሃ ግብር እንደሚቀርብ ወ/ሮ ሀረጓ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ሰፊ ውይይት ሲደረግበት የቆየው የፍኖተ ካርታ ረቂቅ ጥናት ግብዓት ማሰባሰብ ሂደት ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ አበላት ጋርም በዛሬው ዕለት በመላ አገሪቱ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ማስጠንቀቂያ‼️
ልዩነትን የምታሰፉ እና ብጥብጥ በሚፈጥሩ እንቅስቃሴዎች የምትሳተፉ፦ #አክቲቪስቶች እና #የፖለቲካ_ፓርቲዎች ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ካልሆነ ግን የማያድግም #እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል በዶ/ር ዐብይ የሚመራው መንግስት‼️
#ETHIOPIA

ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች‼️
ከትናትና በስቲያ ጀምሮ የመጠጥ ውሃ ተበክሏል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የአስተዳደሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አወቀ ሀይለማሪያም ለfbc እንደተናገሩት፥ በመዲናዋ ባለው የመጠጥ ውሃ ስርጭት ምንም አይነት የውሃ መበከል አልተከሰተም።
የስም #ማጥፋት አድማው አንዳንድ የታሸገ ውሃ አምራቾች ያለ አግባብ ገቢያውን ለመቆጣጠርና ለፓለቲካ ፍጆታ የሚጠቀሙ አካላት የሚያሰራጩት መሆኑን ገልፀዋል።
ህብረተሰቡም በእንደዚህ አይነት ሀሰተኛ መረጃ ስጋት ሊፈጠርበት እንደማይገባ ነው ዋና ስራ አስኪያጁ ያስታወቁት።

ASTU⬆️የመደበኛ እና የአዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል። የመግቢያ ቀናቱ ወደፊት እንደሚገልፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኦህዴድ/ኢህአዴግ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት 9ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ #ጅማ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጅማ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች #አቀባበል አድርገውላቸዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር በመተባበር በበጎ ፎቃደኛነት #ፀጥታ የማስከበር ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
©የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tiovahethiopia
©የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tiovahethiopia
ማሳሰቢያ‼️
በህገ-ወጥ ድርጊት ላይ የሚሳተፍ #ወጣትና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ህጋዊ #እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አውቆ ከጥፋት ተግባሩ #እንዲሰበሰብ መንግስት ያሳስባል፡፡
©የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በህገ-ወጥ ድርጊት ላይ የሚሳተፍ #ወጣትና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ህጋዊ #እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን አውቆ ከጥፋት ተግባሩ #እንዲሰበሰብ መንግስት ያሳስባል፡፡
©የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ምስጋናና አክብሮቱን ገልጿል።
"Galata Manguddootaa fi Jiraattota Magaalaa Arbaa Minciif /ምስጋና ለአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች/"
@tsegabwolde

#update ቡራዩ⬇️
በዛሬው እለት ቡራዩ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አከባቢዎች ወደ ሰላምና #መረጋጋታቸው ተመልሰዋል።
የኦሮሚያ ክልል ኮሙዪኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት መግለጫ፥ ችግሩን በመፍጠር ህዝብን #ለአደጋ በማጋለጥ የፖለቲካ አላማቸውን ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ከአዲስ አበባ ጀምሮ የተንቀሳቀሱ ካላት መኖራቸውን አስታውቀዋል።
የዚህ ጥፋት ሀይል አካል የሆነ 99 አባላት ካለው ቡድን ውስጥ ስድስት ሰዎች የጦር መሳሪያ ማለትም፥ 3 ክላሽ እና 8 ሽጉጥ ሁለት መኪና፣ የባንክ እንዲሁም ደብተር እና የቡራዩ ከተማ መሬት አስተዳደር #ሀሰተኛ ማህተም ይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ያስታወቁት።
የሀሰት ገንዘብን ጨምሮ መጠኑ ከፍ ያለ ገንዘብ መያዙን እና በተጨማሪም በተያዙት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ውስጥ 8 ሚሊየን ብር ተገኝቷል ብለዋል።
በዛሬው ዕለትም የቀሩትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየተከታተለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት እስካሁን ከ300 በላይ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው አንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቀዋል።
የቀሩትንም ለመመለስ አስፈላጊው ድጋፍ የፌደራል መንግስትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የክልሉ መንግስት በጋራ እየሰሩ ይገኛሉም ብለዋል።
በግድያና ዝርፊያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት 200 ሰዎች መካከል በ23 ሰዎች ላይ መረጃ ተመርምሮ እየተጠናቀቀ በመሆኑ
ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ዶክተር ነገሪ ተናግረዋል።
ንብረታቸው የተዘረፈ ሰዎች ንብረታቸው ከዘራፊዎች ተሰብስቦ ተመልሷል ያሉት ሀላፊው፥ የክልሉ መንግሰት አስፈላጊውን ድጋፍ አድርጎ የተዘረፈውን ንብረት በቦታው ለመመለስ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

#update ዛሬ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር ውይይት አድርገዋል።
©Wi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©Wi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
etv! በጋሞ ሽማግሌዎች እርጥብ ሳር የከሸፈው የአርባምንጭ አመጽ🕊
በአዲስ አበባ ዙሪያ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ የደረሰዉን አደጋ ተከትሎ በጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ #ወጣቶች በስሜት ተነሳስተዉ በንብረት ላይ ሊያደርሱ የነበረዉን ጥቃት የአካባቢዉ ሽማግሌዎች እርጥብ ሣር በመያዝ መስቆም መቻላቸዉ ተገለጸ፡፡
በአርባ ምንጭ የተቆጡ ወጣቶች በኦሮሞ ተወላጆች ንብረቶች ጥፋት እንዳያደርሱ የጋሞ ሽማግሌዎች እንደ ባህላቸው ቅጠል ይዘው በመማጸን ሀላፊነታቸውን መወጣታቸውን የጋሞ ጎፋ ዞን ኮሙኒኬሽን ባለሙያ አብዮት አባይነህ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
ለሀዘን መግለጫ ተብሎ በተደረገዉ ሰልፍ የድንጋይ መወርወር ቢኖርም በንብረት ላይ የደረሰ አደጋ አለመኖሩን የኮሙኒኬሽን ባለሙያው ገልጸዋል፡፡
በትላንትናው ዕለት የዞኑ ህዝብ ሀዘኑን ለመግለጽ በአርባምንጭ ከተማ በወጣበት ወቅት የተደራጁ ሀይሎች ሰልፉን ወደ አመጽ ለመቀየር ሙከራ ማድረጋቸውን የጋሞ ጎፋ ዞን ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ቤታ አንጁሎ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
ህግን ለማስከበር በተደረገ ጥረት ከፖሊስ ጋር በተወሰነ መልኩ ግጭት ተፈጥሮ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ገልጸዋል፡፡