TIKVAH-ETHIOPIA via @like
ETV Zena Live! የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች አቀባበል ከአዲስ አበባ ስታዲየም በቀጥታ በመተላለፍ ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ተጠናቋል📌ዛሬ በአዲስ አባባ ከተማ የተደረገው የአርበኞች ግንቦት 7 አቀባበል ፍፁም #ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወሊሶ⬆️
"የወሊሶ ከተማ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ከተማቸውን ሲያጸድ ውለዋል። አክሊሉ ከወሊሶ"
መልካም ስራ ሲበራከት ምንኛ ደስ ይላል!
መልከም አዲስ አመት!

#update አርበኞች ግንቦት 7⬇️
አርበኞች ግንቦት 7 ወደ ሰላማዊና ህጋዊ ፓርቲነት የመጣው በሀገሪቱ የተጀመረውን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ለማጠናከር መሆኑን የድርጅቱ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።
በዛሬው እለት ወደ ሀገር ለተመለሰው አርበኞች ግንቦት 7 በአዲስ አበባ ከተማ ስታዲየም አቀባበል ተደርጓል።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የድርጅቱ ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ የድርጅቱ አባላት እና አመራሮች ተገኝተዋል።
በአቀባበሉ ላይ የተገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም፥ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸው የአዲስ አበባ እና አካባቢው ህዝብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ አክለውም፥ ለዛሬዋ ቀን እንድንበቃ መስዋእትነት ለከፈሉ መላው የሀገሪቱ ህዝብ፤ እንዲሁም መብታችን ይከበር ብለው እጃቸውን ባዶ በሰላማዊ መንገድ ለመብታቸው ታግለው ለተሰው ወጣቶችም ምስጋና አቅርበዋል።
እንዲሁም የህዝቡን ትግል በመረዳት እና ትልቅ ሀላፊነት በመውሰድ በኢህአዴግ ውስጥ የለውጥ ሀይል ለሆኑት እንዲሁም የእርቅና የአንድነት መንፈስ ይዘው ለመጡ አመራሮችም ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ አሁን በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ሀገሪቱን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ከመሆን ውጭ ሌላ መደራሻ የለውም ሲሉም ተናግረዋል።
አርበኞች ግንቦት 7 ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ሰላማዊ እና ህጋዊ ፓርቲ ለመሆን የወሰነውም በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የተጀመረውን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ለማጠናከር እንደሆነም ገልፀዋል።
“በቀጣይ ሁላችንም ቂምና በቀል አርቀን፤ ሁላችንም ተጋገዘን ሀገራችንን ወደ ተሻለች ደረጃ እንውሰዳት” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ለፖለቲካ ፓርቲዎች ባስተላለፉት መልእክት፥ በአመለካከት ከምንስማማቸው ጋር እየተዋሃድን ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ መፍጠር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
በአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ አመራሮቹ እና አባላቶቹን እንኳን በሰላም ወደ ሀገራችሁ መጣችሁ ብለዋል።
በመላው ሀገሪቱ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ የለውጥ ስራዎች እየተሰሩ ባለበት ወቅት እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ለውጡን የበለጠ ለማስቀጠል ይረዳል ሲሉም ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በከተማ አስተዳደሩ ሰፋፊ #የለውጥ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ፥ በምንሰራው ስራ የሚያግዙን ከሆነ ዝግጁ ነን ሲሉም ተናግረዋል።
ኢንጂነር ታከለ፤ በመካከላችን ያለው ግንብ ፈርሷል ያሉ ሲሆን፥ አሁን አንድ ሆነን ከተማችን እና ሀገራችንን በጋራ እንገንባ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ዋና ፀሃፊ አቶ #አንዳርጋቸው_ፅጌ በበኩላቸው፥ በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው፤ ይህንን ያስተተባበረውን አካል አመስግነዋል።
አቶ አንዳርጋቸው አክለውም፥ ኢትዮጵያ የወጣቱ የስራ አጥነት ችግር እስኪቀረብ እና ሁሉም ተደላድሎ የሚኖርባት ሀገር እስክትሆን ድረስ ትግላችን ይቀጥላል ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የሚመራውን መንግስት ጨምሮ ለህዝቡ ለውጥ ከሚታገሉት አካላት ጋር በሙሉ በትብብር እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል።
©FBC
@tikvahethiopia @tsegabwolde

#update የአዲስ አበባ ፖሊስ⬇️
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመጪው አዲስ ዓመት ህብረተሰቡ በተረጋጋ ሁኔታ በዓሉን እንዲያከብር ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ለወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ አባላትን በልዩ ልዩ ስፍራዎች ማሰማራቱን ገልጿል፡፡
የ2011አዲስ ዓመት “በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር” በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ኮሚሽኑ አስታውሶ በዓሉን ምክንያት በማድረግም ጳጉሜን አምስት በሚሊንየም አዳራሽ
ከሚዘጋጀው ፕሮግራም በተጨማሪ በልዩ ልዩ ስፍራዎች የመዝናኛ ዝግጅቶች ስለሚኖሩ ድንገተኛ #አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡
📌ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ጥቆማ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ
መስመሮችን እና 011 1 11 01 11፣ 011 8 69 88 23 በመደወል ማሳወቅ ይችላል ተብሏል፡፡
©የአዲስ አበባ ፖሊስ

አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ጥናት⬇️
የደቡብ ክልል አዳዲስ #የዞንና #የወረዳ አወቃቀር ምክረ ሐሳብ የያዘ ጥናት አጠናቅቆ ለአመራሮች ውይይት እንዳዘጋጀ ታወቀ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሊቀመንበርና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ #ሙፈርያት_ካሚል ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ ክልሉ አዲስ አወቃቀር እንደሚኖረው የመንግሥት አገልግሎትን ለወረዳ ማዕከላት ቅርብ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ ገልጸው ነበር፡፡
አፈ ጉባዔዋ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ ‹‹በጥናት የተለየና ሕጋዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ወደ ተግባር የሚገባበት የመዋቅር ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡን ባወያየንበት ወቅት የነበረው ዋናው ጥያቄ የአገልግሎት ጥያቄ ነው፡፡ በጥናት አገልግሎት ወደ ኅብረተሰብ ማቅረብ አቅደናል፤›› ብለው፣ ‹‹በመንግሥታዊ መዋቅሩ ይኼንን በሕግ አግባብ ዳር ለማድረግ ምላሽ መስጠት ጀምረናል፤›› ሲሉም የደረሰበትን ደረጃ ማስረዳታቸው ይታወሳል፡፡
በዚህም መሠረት ካሁን በፊት #ልዩ ወረዳ የነበረው አላባ ወደ ዞንነት ሲያድግ ዌራ ዙሪያ፣ ድጆ ዌራና ድጆ የተባሉ ወረዳዎች ይኖሩታል፡፡ የወረዳዎቹ ማዕከላት በቅደም ተከተል ቁሊቶ፣ ጉባና የቤሻኖ ከተሞች እንዲሆኑ ጥናቱ ያሳያል፡፡
በሌላ በኩል ካሁን በፊት ከነበረው ጋሞ ጎፋ ዞን፣ ጎፋ ራሱን ችሎ በመውጣት ዞን በመሆን በሥሩ ስምንት ወረዳዎች እንዲኖሩት የሚል መዋቅር ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም መሠረት ጎፋ ዞን ዲምባ ጎፋ፣ ባዜ ጎፋ፣ ዛላ፣ ኡባ ደብረ ፀሐይ፣ አይደ ወረዱ፣ ሳውላ ከተማ፣ መለኮዛና ጋደ የተባሉ ወረዳዎች እንዲኖሩት በጥናቱ ተመልክቷል፡፡
ለብቻው እንደ አዲስ የተዋቀረው ጋሞ ዞን ደግሞ 13 ወረዳዎች እንዲኖሩት እንደሚደረግ የሚጠቁመው ጥናቱ፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ዲታ፣ ካምባ፣ ምዕራብ አባያ፣ ጨንቻ፣ ደራማሎ፣ ቁጫ፣ ቦንኬ፣ ቦረዳ፣ አርባ ምንጭ ከተማ፣ ምዕራብ ቁጫ፣ ሰሜን ቦንኬና ጋርዳ ማርታ የተባሉ ወረዳዎችን ያቀፈ ሆኖ እንዲቋቋም ሐሳብ ቀርቧል፡፡
በተመሳሳይ ኮንሶ ከሰገን ሕዝቦች ዞን ወጥቶ በዞንነት እንዲደራጅ በጥናቱ የተመለከተ ሲሆን፣ በሥሩም ካራት ዙሪያ፣ ከና፣ ሰገን ዙሪያና ካራት ከተማ አስተዳደር የሚሉ የወረዳ መዋቅሮች እንደሚኖሩት ተጠቁሟል፡፡
ጥናቱ ካሁን በፊት የሰገን ሕዝቦች ዞን አስተዳደር በሚል ስያሜ ተዋቅሮ የነበረው አደረጃጀት ወደ ቀድሞው ተመልሶ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣ የዴራሼ ልዩ ወረዳና የአሌ ልዩ ወረዳዎች ተብለው እንዲቋቋሙ የሚል ይዘት አለው፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር

#update የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤና ሀገራዊ ለውጡን #ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ በመምከር መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጅማ⬆️
"ለቀናት በፀሃይ በብርድ ለአቅመ ደካሞች ጧሪ ለሌላቸው አዛውንቶች ለህፃናት ከመንግሰት የቀረበልን ጥሪ በመቀበል የበኩላችንን ለመወጣት ያረግነው ርብርብ በመጨረሻዎ ቀን ማለትም ከ በጎ ሰዎች የተቀበልናቸውን አልባሳት ደብተር ብዕር እና የተለያዩ ቀሶች በማስረከቢያ ጊዜ የደረሰብን ነገር #አሳምሞናል ወጣቶቻችን የ ሠደፍ ሰለባ ሆኖዎል ጥይት ተተኩሶብናል፤ እናቶች አልቅሰዎል፤ አባቶች አዝነዎል ከምንም በላይ ደግሞ የጋሽ አዛዥ የጋሽ ባለስልጣን ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ የሆኑት ምክንያት ያሳፍራል መንገድ ተዘጋብኝ በሚል የግል ምክንያት ነው። ሀገር ይፍረደን ጅማን ይሄ አይወክልም
ሀገር ይፍረደን!!!"