#update ሀዋሳ⬇️
በሀዋሳ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ተገንብተው የነበሩ 214 ቤቶች እንዲፈርሱ መደረጉን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ ።
የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሱካሬ ሹዳ እንዳሉት የፈረሱት ቤቶች ባለፉት ሁለት ወራት በከተማዋ የነበረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የተገነቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ህገ ወጥ ተግባሩን በፈጸሙት ላይ ዛሬ የማፍረስ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡
የአስተዳደሩን እርምጃ ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ #ግጭት ለመቀስቀስ የሚጠቀሙበት በመኖራቸው የከተማው ነዋሪ #ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም አሳስበዋል።
በአሁኑ ወቅት ከተማዋ ወደ ሙሉ ሰላሟ የተመለሰች ሲሆን በግጭት ወቅት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችም ሙሉ ለሙሉ የማቋቋም ስራ መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።
©ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update⬆️ዛሬ ከጥዋት 12 ሰዓት ላይ ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረ ፒካፕ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ይመጣ ከነበረ የዳንጎቴ እቃ ጫኝ መኪና ጋር በመጋጨቱ የሹፌሩን ጨምሮ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የወገኖቻችንን ነብስ ይማርልን ለቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን እንመኛለን!
©BW
@tsehabwolde @tikvahethiopia

#update ኢንጂነር ታከለ ኡማ⬇️
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጀነር ታከለ ኡማ #በጎርፍ አደጋው ተከትሎ ህዝቡና ተቋማት ላደረጉት ህይወት የመታደግ ርብርብ #ምስጋና አቀረቡ፡፡
በአቃቂ ክፍለከተማ የደረሰው የጎርፍ አደጋ እጅግ ከባድና አሳዛኝ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ሆኖም ግን በክቡራን ወገኖቻችን ህይወት ላይ ምንም አይነት የህይወት አደጋ አለመድረሱ ለሁላችንም እፎይታ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ክቡሩን የወገንን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ ላደረጉት የኢ.ፌ.ድ.ሪ የአየር ሀይል፤ የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት፤ ለአዲስ አበባ አሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠር ባለስልጣን፤ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽንና ከምንም በላይ ደግሞ ለአከባቢው ነዋሪና ህብረተሰብ ያላቸውን ጥልቅ የሆነ አክብሮትና ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ኢንጀነር ታከለ እንደ አስተዳደር ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳይከሰቱ የጥንቃቄና የመፍትሄ እርምጃዎችን ጨምሮ የከተማውን የወንዝና ተፋሰስ ስራዎችን #በማልማት ከችግር ምንጭነት ይልቅ የከተማው የውበት ምንጭ እንዲሆኑ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
ምንጭ፦ አዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ

#update አዲስ አበባ ከተማ⬆️
በመሬት አስተዳደር ዘርፉ ላይ ዛሬ አዳዲስ #ሹመቶች ተሰጥተዋል፡፡
በመሬት አስተዳደርና ተያያዥ የስራ ዘርፎች ላይ የሚገኙ ሀላፊዎች በአዳዲስ አመራሮች ተተክተዋል በዚህም መሰረት፡
1. ወ/ት ሰላማዊት ሀዱሽ-የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
2. አቶ ባህሩ ግርማ-የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የካዳስተር መረጃና ቅየሳ ዘርፍ ም/ዳይሬክተር
3. አቶ ተስፋዬ አሰፋ-የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የኢንፎርሜሽን ሲስተም ልማት አስተዳደር ዘርፍ ም/ዳይሬክተር
4. አቶ ተሾመ ለታ-የመሬት ልማትና መልሶ ማደስ ዋ/ስራ አስኪያጅ
5. አቶ ሚሊዮን ግርማ-የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ም/ሀላፊ
6. ኢ/ር ኤልያስ ዘርጋ-የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ም/ሀላፊ
7. ወ/ሮ እየሩሳሌም ሽመልስ-የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ፅ/ቤት ሀላፊ
8. አቶ ሳህለ ፈርሻ-የተቀናጀ መሬት መረጃ ማእከል ዋና ዳይሬክተር
9. አቶ ለሙ ገመቹ-የይዞታ አስ/የ/ጊ/ፕ/ፅ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
10. አቶ ተስፋዬ ጥላሁን-የመሬት ልማት ባንክና ማስተላለፍ ዋና ስራ አስኪያጅ
11. አቶ ነጋሽ ባጫ-የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ም/ስራ አስኪያጅ
12. አቶ ዘሪሁን ቢቂላ-የመሬት ይዞታዎች ማረጋገጥ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራአስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል።
©የከንቲባ ፅ/ቤት

#update ኢትዮ ቴሌኮም⬇
ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን መመዝገብ (equipment identification registration) ከነገ ጀምሮ ማቆሙን አስታውቋል።
@tikvahethiopia @tsegabwolde

#update ሱማሌ ክልል⬇️
አቶ #ሙስጠፋ_ሞሐመድ_ዑመር ጊዜያዊ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።
አቶ ሙሰጠፋ ሞሐመድ የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲመሩ የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንደመረጣቸው አዲስ አበባ የሚገኘው የቢቢሲ ሶማልኛ ሪፖርተር #አረጋግጧል።
አቶ ሙሰጠፋ ሞሐመድ የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነታቸው በተጨማሪ የሶህዴፓ ምክትል ሊቀመንበር ተደርገው ተሹመዋል።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጸ/ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ የሶህዴፓ ሊቀመንበር ተደርገው መሾማቸው ይታወሳል።
አቶ ሙስጠፋ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሐመድ ኡመር የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽማሉ በማለት በተደጋጋሚ በመተቸት ይታወቃሉ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አብዲ ሞሐመድ ኡመር ከስልጣናቸው ከተነሱ ሁለት ሳምንታት አልፈዋል።
አቶ አብዲ ሞሐመድ ክልል ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ከተሰማ ከሁለት ቀናት በኋላ አህመድ አብዲ ሼክ ሞሃመድ (ኤልካስ) ፕሬዚዳንት ተደርገው ተሹመው ነበር።
©BBC