#BDU
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ለጃፓናዊ ፕሮፌሰር አሱሺ ሱኔካዋ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀጣዩ ቅዳሜ በሚያካሂደው የ2013 ዓ/ም የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ ለአቶ ኦባንግ ሜቶ እና ለጃፓናዊ ፕሮፌሰር አሱሺ ሱኔካዋ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ታውቋል።
አቶ ኦባንግ ሜቶ 👉 በኢትዮጵያ ውስጥ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ፣ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፣ ለፍትሕና እኩልነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ እንደሚታወቁ ተገልጿል።
ፕሮፌሰር አሱሺ ሱኔካዋ 👉 በኢትዮጵያ እና በሌሎችም በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ህጸተ-ዝናብ አካባቢዎች በሰሯቸው የምርምር፣ የልማትና አቅም ግንባታ ሥራዎችና ባመጧቸው አወንታዊ ለውጦች ይታወቃሉ።
Credit : AMC
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ…
#BDU
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲጀመር ተማሪዎች ኃላፊነት ለመውሰድም ይዘጋጁ ብሏል።
በአማራ ክልል የሚገኙ 10 የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድ ፖስት፣ የፀጥታ አደረጃጀቶች፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ፀጥታ አካላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቶ የውይይቶቹ የመጨረሻው ክፍል ሐሙስ ከተደረገ በኃላ ነው ውሳኔው የተላለፈው።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ምን አሉ ?
- ከመስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተን የነበረ ቢሆንም፣ በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሳቢያ ተሰናክሏል።
- በእኛ በኩል የዝግጅት ክፍተት የለብንም።
- በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቁጥጥር ሥር የሆነ የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነም የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ውጪ በሆነው ጉዳይ ላይ ምንም ማድረግ አንችልም። ምንም ማድረግ ባልቻልንበት ሁኔታ የሰው ልጅ ጠርቼ አንድ መጥፎ ነገር ቢከሰት ምንድነው የምለው ? የሚለውን ተማሪዎችም፣ ወላጅንም ታሳቢ አድርገን ተማምነን ይቆይ የሚል አቋም ስለነበረን በዚህ ምክንያት ነው እስካሁን ቀስ እያልን የመጣነው።
- የመማር ማስተማሩ እንዲጀመር በነበረው ውይይት ሒደት አቅደን የነበረው ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ የትምህርት ግቢያቸው ማስገባት ነበር።
- እስካሁን ባለን ልምድ ግጭቶች እዚህም እዚያም ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። ቀጣይነታቸው ግን ብዙም አይደለም። አንድ ቀን ወይ ሁለት ቀን መስተጓጎል ሊፈጠር ይችላል ከዚያ ግን ያበቃል።
- ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ተጠርተው ሲመጡ ታሳቢ ማድረግ ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ፤ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ዕክሎችን ከግምት በማስገባት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው።
- ተማሪውም፣ ወላጅም፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብም እንደ አገር የሚመለከታቸውም አንድ ላይ ሆነን መደበኛ ትምህርት መጀመር አለብን ብለን ወስነናል።
- የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተቋማቸው ከልደት (ገና) በዓል በኋላ ባሉት ቀናት ለተማሪዎቹ ጥሪ ያደርጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ መሆኑን ያሳውቃል።

" ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ አቋሙን ያሳወቀን " - ተማሪዎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ያደረገውን ጥሪ ባላወቁት ምክንያት አራዝሞት እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህም “ ኑም ” ሆነ “ አትምጡ ” ባለማለቱና የትምህርት ጊዜው እያገፋ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸው ውሳኔውን እንዲያሳውቃቸው ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ይጠየቅልን…
#BDU
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ እስካሁን ጥሪ ባልተደረገላቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ ላይ ከተቋሙ ተጨማሪ ምላሽ አግኝቷል።
በዚህም ተቋሙ ፤ " ተማሪዎቹን ለመጥራት አስቻይ ሁኔታዎች እየተጠበቀ ነው። " ብሏል።
" አሁን ያለው ሁኔታ ተማሪዎቹን ለመጥራት እየተገመገመ ነው። ተማሪዎቹ በትዕግስት ይጠብቁ። " ሲል አሳውቋል።
ተጨማሪ ዝርዝር የምናጋራችሉ ይሆናል።
@tikvahuniversity @tikvahethiopia

ፍትህ ! ፍትህ ! ፍትህ ! " ሀኪም ህይወት እያተረፈ ፣ህይወቱን መነጠቅ የለበትም! " - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር አንዷለም ዳኜ ከስራ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተደብድቦ በመገደሉ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ፍትህን በመጠየቅ ላይ ናቸው። " ፍትህን እንሻለን ! " በሚል የፍትህ ጥያቄ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። …
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈትን ተከትሎ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ከዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራር አካላት ጋር የዶ/ር አንዱአለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን ገልጿል።
ውይይቱ በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸውና ሃኪሙ በህይዎት ዘመኑ ያከናወናቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ዶ/ር አንዱአለም ምንም እንኳን የተሰጠውን ጸጋ ሳይሰስት በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎችና በሙያው ላገለገላቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበረ እንቁ ባለሙያ ቢሆንም ገና በ37 ዓመቱ የተቀጠፈ በመሆኑ ለህጻናት ልጆቹና ቤተሰቡ ትቶ ያለፈው ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌለው መሆኑ ተገልጿል።
የቀረቡለትን በርካታ ዓለምአቀፍ የስራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገኑን ለማገልገል ቆርጦ የነበረ ባለሙያ ከመሆኑም በላይ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበረውን ልዩ አበርክቶና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣረ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሶ ያለፈ መሆኑ በውይይቱ ተነስቷል።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሞያዊ አቅም ተጠቅሞ ራሱን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥቶ ያለፈ ታላቅ ባለሙያ እንደነበረ የስራ ባልደረቦቹ ፣ተማሪዎቹ እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቹ የሚመሰክሩለት ድንቅ ሃኪም የነበረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አመልክቷል።
በመሆኑም ፦
➡ የዶ/ር አንዱአለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤
➡ ባለቤቱ ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ አቅም ያላት በመሆኑ በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የምትቀጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች፤
➡ ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሰራው እሱ በመሆኑና ክፍሉን እስከ ህልፈቱ ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረ በመሆኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስሙ ዶ/ር አንዱአለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም፤
➡ የዶ/ር አንዱአለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነቱን በቋሚነት ለመዘከርና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምለት፤
➡ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስሙ BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም፤
➡ ለ40ኛ ቀኑ መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶ/ር አንዱአለም የህይዎት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል።
ውሳኔው ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡