TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው " ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ' ትዕዛዝ ' እንዲሰጡ ያስችላቸዋል " ብለዋል።

ይህም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት / በገፍ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ (ማስ ዲፖርቴሽን) እንደሆነ ጠቁመዋል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ይህ ሰነድ አልባዎችን በብዛት ከአሜሪካ የማስወጣቱ /ማስ ዲፖርቴሽን/ ተግባር የትራምፕ የመጀመሪያው ቀን ስራ ይሆናል ብለዋል።

ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በሚመለከት " ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ሲሉ ቃል ገብተው ነበር።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው።

#TikvahEthiopia
#USA #massdeportation

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA " እውነት ነው " - ትራምፕ ዶናልድ ትራምፕ ሰነድ አልባ ስደተኞችን በገፍ በጅምላ ከሀገር ለማባረር ጦሩን (መከላከያውን) ሊጠቀሙ ይችላሉ ተብሏል። ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፤ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው በገቡት ቃል መሰረት ሰነድ የሌላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደየመጡበት ሀገር ያባርራሉ። ለዚህም በመላ ሀገሪቱ አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ እንደሚችሉ…
" ቤተሰብ መበታተን አልፈልግም ፤ ቤተሰቦች የማይለያዩበት ብቸኛው መንገድ ሁሉንም አንድ ላይ ከአገር ማባረር ነው " - ትራምፕ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከNBC ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

በዚህም ቆይታቸው ከስድተኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ምን አሉ ?

ትራምፕ ወላጆቻቸው በውጭ አገራት ቢወለዱም በአሜሪካ የተወለዱ ልጆቻቸው ዜግነት የሚያገኙበትን መብት እሽራለሁ ብለዋል።

ወላጆቻቸው ሌላ ቦታ ቢወለዱም በአሜሪካ የሚወልዷቸው ልጆች የአሜሪካ ፓስፖርት የማግኘት መብት የሚሰጠውን በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት ለማስቆም ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ አሳውቀዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ተሰደው ወደ አሜሪካ የሄዱ ሰዎች የመኖሪያም ሆነ የዜግነት መብት ባያገኙም አሜሪካ ውስጥ የወለዷቸው ልጆች ዜግነትን ማግኘት ይችላሉ ታዲያ ትራምፕ ስራ ሲጀምሩ ይህንን ነው የሚሽሩት።

ሆኖም በልጅነታቸው ወደ አሜሪካ የመጡ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞች ለመርዳት ከዴሞክራቶች ጋር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

🇺🇸 በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት የአሜሪካ ህገ መንግሥት አንቀጽ 14ን መሰረት ያደረገ ነው። '' ማንኛውም አሜሪካ ውስጥ የተወለደ ወይም ተገቢውን ግዴታዎች የተወጣ ሰው የአሜሪካ ዜጋ የመሆን ሙሉ መብት አለው '' ይላል።

በሌላ በኩል ፤ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ያላቸውን ጨምሮ ህጋዊ ሰነዶች ያላሟሉ ስደተኞችን ከአገር ለማባረር የገቡትን ቃል ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

" ቤተሰብ መበተታተን አልፈልግም " ያሉት ትራምፕ " ስለዚህ ቤተሰቦች የማይለያዩበት ብቸኛው መንገድ ሁሉንም አንድ ላይ ከአገር ማባረር ነው " ብለዋል።

ትራምፕ በአንድ ወቅት ለመሰረዝ ሞክረው የነበረውን ወደ አሜሪካ ብቻቸውን ለሚመጡ ህጻናት ከለላ የሰጠውን የኦባማ 'ዲፈርድ አክሽን ፎር ቻይልድ ሁድ አራይቫልስ' በተሰኘው ፕሮግራም የታቀፉትን በተመለከተ ከምክር ቤቱ ጋር አብሬ እሰራለሁ ብለዋል።

" ከዴሞክራቶች ጋር በአንድ ዕቅድ ላይ እሰራለሁ " ያሉት ትራምፕ ከነዚህ ስደተኞች መካከል ጥቂቶች ጥሩ ስራ የያዙ በንግድ ላይ የተሰማሩም አሉ ሲሉ አክለዋል።

መረጃውን ኤንቢሲን ዋቢ በማድረግ ያጋራው ቢቢሲ ነው።

#USA #MASSDEPORTATION

@tikvahethiopia