TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ባህር ዳር‼️

ከአንድ ወር ገደማ በፊት ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጸጥታ ሥጋት ሳቢያ ጥለው የወጡ ተማሪዎች #በአማራ_ክልል በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ልንመደብ ይገባል የሚል ጥያቄ ይዘው በባሕር ዳር ከተማ ሰልፍ አደረጉ። በዛሬው ሰልፍ ወደ 2500 ተማሪዎች መገኘታቸውን በቦታው የተገኘው የDW ዘጋቢ ተናግሯል። ተማሪዎቹ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተነስተው እስከ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተጉዘዋል። ሰልፈኞቹ በክልሉ መንግሥት ቢሮ ፊት ለፊት "መንግሥት የለም! መንግሥት ቢኖር ጥያቄያችንን ይመልስልን ነበር" የሚል መፈክር ማሰማታቸውን የDW ዘጋቢ ታዝቧል። የጸጥታ አስከባሪዎች ኹኔታውን በርቀት ሲከታተሉ ነበር። በአብዛኛው ጥቁር የለበሱት ተማሪዎች መንግሥት ጥያቄያችንን ይመልስልን፤ በአማራ ክልል እንመደብ" የሚል ጥያቄ በሰልፉ ላይ አሰምተዋል። የኢኖቬሽን እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ይመለሱ የሚል ምላሽ ባለፈው ሳምንት ሰጥቶ ነበር። ተማሪዎቹ ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑት "ሴቶች ይደፈራሉ፤ ወንዶች ይደበደባሉ" በሚል ምክንያት ነው። DW እንደዘገበው ተማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በሚገኝ ስታዲየም ተጠልለው ይገኛሉ።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WFP

በትላንትናው ዕለት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የዓለም ምግብ ፕሮግራም) ቃል አቀባይ ቶመሰን ፉሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• ከጦርነት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9.4 ሚሊዮን ደርሷል።

• የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች ወስጥ የሚገኙ 9.4 ሚሊዮን ሰዎች አስከፊ ሕይወት እየገፉ ነው።

• 7.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በጦርነቱ ምክንያት ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ አዳጋች የሆኑባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች ናቸው።

• የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት #በአማራ_ክልል ነው። በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ብቻ 3.7 ሚሊዮን ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

• ከትግራይ፣ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች የተሰበሰቡ መረጃዎች እንዳመለከቱት በሦስቱ ክልሎች ከሚገኙ ሕጻናት መካከል ከ16 እስከ 18 በመቶ የሚሆኑት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል። ነፍሰጡር ከሆኑ እና ከሚያጠቡት እናቶች መካከል 50 በመቶ ያህሉ በተመሳሳይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

• UN የምግብ አቅርቦት የጫኑ ተሸከርካሪዎች ከኮምቦልቻ ወደ ደቡባዊ ትግራይ እየላከ ነው። በቀጣይ ቀናት 2200 ሜትሪክ ቶን ሕይወት አደን ምግብ መቐለ ይደርሳል።

• WFP በትግራይ 2.5 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር መድረስ ሲኖርበት እስካሁን መድረስ የቻለው 180 ሺህ የሚሆኑትን ብቻ ነው።

ምንጭ፦ https://www.wfp.org/news/millions-more-need-food-assistance-direct-result-conflict-northern-ethiopia-says-wfp

@tikvahethiopia
#Amhara #Tigray #Afar

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ 🇪🇹 በግጭት በተጎዱ ክልሎች ላለው የጤና እና ሰብዓዊ ፍላጎቶች ምላሽ እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት አካላት ከ2 ቀን በፊት #በአማራ ክልል የወደሙ ሆስፒታሎችን በአካል የተመለከቱ ሲሆን የ2 ሚሊዮን ሰዎችን አስቸኳይ የጤና ፍላጎት ለማሟላት ወደ 100 ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ መድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዳስረከቡ ድርጅቱ ገልጿል።

ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶች ወደ #አፋር#ትግራይ እና ሌሎችም ክልሎች መላኩን ድርጅቱ አመልክቷል።

@tikvahethiopia