TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ወላጆች የልጆቻችሁን ውሎና ሁኔታ እንድትከታተሉ አደራ እንላለን " - የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ

ህፃናትን የደፈረው ወንጀለኛ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። 

ወንጀለኛው የደፈራቸው ሁለት ሴት ህፃናት በማጣባቂያ ማስትሺና በጨርቅ በማፈን እንደሆነ ተሰምቷል።

ወንጀሉ መቼ እና እንዴት ተፈፀመ ? 

ወንጀሉ የተፈጸመው መጋቢት 2016 ዓ.ም ሲሆን ቦታው ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 04 ነው። 

የድርጊቱ ፈፃሚ ወንጀለኛ የ28 ዓመቱ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ሲሆን ፤ ነውረኛ ድርጊቱን የተፈፀመው  የ11 እና 12 ዕድሜ ባላቸው እንስት ህፃናት ላይ መሆኑ የጥፋተኛው የክስ የውሳኔ ማስረጃ ያስረዳል።

ወንጀለኛው እድሜያቸው ከላይ የተጠቀሰውን ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ፣ ክፉ ደጉን እንኳን የማይለዩ ሁለት ህፃናትን በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ መደለያዎች በመስጠት #እንዲቀርቡትና #እንዲለምዱት ካደረገ በኋላ ፤ ቀን መርጦ በጨርቅ እና በማጣበቂያ ማስትሺ ተጠቅሞ ድምፅ እንዳያሰሙ በማፈን አስገድዶ የመድፈር ተግባር ፈፅሞባቸዋል።

ይህ እጅግ ለመስማት የሚቀፍ አፀያፊ ደርጊት ለወራት ሲያጣራ የቆየው የፓሊስና የፍትህ አካል በመቀበል የግራና ቀኝ ምስክሮች ያዳመጠው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ግለሰቡ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ወንጀለኛ ሆኖ በመገኘቱ በ16 ዓመት ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። 

ጉዳይ በማስመልከት ለሚድያ መገለጫ የላከው የትግራይ ፍትህ ቢሮ ፤ ወላጆች በህፃናት ላይ ይህንን መሰል አፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙትን እንዲያጋልጡና የልጆቻቸው ውሎና ሁኔታ እንዲከታተሉ አደራ ብሏል።

በሀገራችን ሴቶች ላይ ለሚፈጸሙ ዘግናኝ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የሚሰጠው ፍርድ ምንም የማያስተምር ፤ ይልቅም ወንጀልን የሚያበረታታ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ ከፍተኛ ቅሬታ ነው።

በተለይ ህጻናትን የሚደፍሩ ወንጀለኞች ላይ የሚተላለፉ ፍርዶች ብዙ ጊዜ ዜጎችን የሚያስቆጡ እንደሆኑ በተደጋጋሚ የተስተዋለ ጉዳይ ነው።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia