" ወላጆች የልጆቻችሁን ውሎና ሁኔታ እንድትከታተሉ አደራ እንላለን " - የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ
ህፃናትን የደፈረው ወንጀለኛ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።
ወንጀለኛው የደፈራቸው ሁለት ሴት ህፃናት በማጣባቂያ ማስትሺና በጨርቅ በማፈን እንደሆነ ተሰምቷል።
ወንጀሉ መቼ እና እንዴት ተፈፀመ ?
ወንጀሉ የተፈጸመው መጋቢት 2016 ዓ.ም ሲሆን ቦታው ደግሞ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 04 ነው።
የድርጊቱ ፈፃሚ ወንጀለኛ የ28 ዓመቱ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ሲሆን ፤ ነውረኛ ድርጊቱን የተፈፀመው የ11 እና 12 ዕድሜ ባላቸው እንስት ህፃናት ላይ መሆኑ የጥፋተኛው የክስ የውሳኔ ማስረጃ ያስረዳል።
ወንጀለኛው እድሜያቸው ከላይ የተጠቀሰውን ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ፣ ክፉ ደጉን እንኳን የማይለዩ ሁለት ህፃናትን በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ መደለያዎች በመስጠት #እንዲቀርቡትና #እንዲለምዱት ካደረገ በኋላ ፤ ቀን መርጦ በጨርቅ እና በማጣበቂያ ማስትሺ ተጠቅሞ ድምፅ እንዳያሰሙ በማፈን አስገድዶ የመድፈር ተግባር ፈፅሞባቸዋል።
ይህ እጅግ ለመስማት የሚቀፍ አፀያፊ ደርጊት ለወራት ሲያጣራ የቆየው የፓሊስና የፍትህ አካል በመቀበል የግራና ቀኝ ምስክሮች ያዳመጠው የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ማእከላዊ ፍርድ ቤት ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት ግለሰቡ ክብሮም ኣብርሃ ኪዳነማርያም ወንጀለኛ ሆኖ በመገኘቱ በ16 ዓመት ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ጉዳይ በማስመልከት ለሚድያ መገለጫ የላከው የትግራይ ፍትህ ቢሮ ፤ ወላጆች በህፃናት ላይ ይህንን መሰል አፀያፊ ተግባር የሚፈፅሙትን እንዲያጋልጡና የልጆቻቸው ውሎና ሁኔታ እንዲከታተሉ አደራ ብሏል።
በሀገራችን ሴቶች ላይ ለሚፈጸሙ ዘግናኝ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የሚሰጠው ፍርድ ምንም የማያስተምር ፤ ይልቅም ወንጀልን የሚያበረታታ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚነሳ ከፍተኛ ቅሬታ ነው።
በተለይ ህጻናትን የሚደፍሩ ወንጀለኞች ላይ የሚተላለፉ ፍርዶች ብዙ ጊዜ ዜጎችን የሚያስቆጡ እንደሆኑ በተደጋጋሚ የተስተዋለ ጉዳይ ነው።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት አሳይቷል " - አታላይ አየለ (ፕ/ር) 🚨" የመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው " - አቶ አብዶ አሊ በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ…
#Earthquake
ዛሬ ምሽት 4:42 አካባቢ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደሰሙ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
አብዛኞቹ መልዕክታቸውን የላኩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ካለባቸው አካባቢዎች ነው።
አንድ የቤተሰባችን አባል ፥ " አራብሳ ኮንዶሚኒየም እንደሚኖሩና ከ10 እስከ 15 ሰከንድ ያህል ንዝረቱን እንደሰተማቸው " ገልጸዋል።
ሌላው የቤተሰባችን አባል ገላን ኮንዶሚኒየም አከባቢ 10:44 ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደሰማ አመልክቷል።
በተጨማሪም አንዲት የቤተሰባችን አባል " ከሰሞኑን የዛሬው ጠንክሮ ነው የተሰማኝ ያስፈራ ነበር " ስትል ገልጻለች።
ሌሎች በክልል ከተሞች በተለይ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ስሜት እንደተሰማቸውን ተናግረዋል።
እንደአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ፣ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት መረጃ ፤ በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳ እና አካባቢው ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ይገኛል።
ዛሬ ቀን 9 ሰዓት አካባቢ ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛው እና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።
የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት አሳይቷል።
በተጨማሪ የፍንዳታ ድምጽ እና ጭስም ታይቶ ነበር።

#Earthquake ዛሬ ምሽት 4:42 አካባቢ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደሰሙ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። አብዛኞቹ መልዕክታቸውን የላኩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ካለባቸው አካባቢዎች ነው። አንድ የቤተሰባችን አባል ፥ " አራብሳ ኮንዶሚኒየም እንደሚኖሩና ከ10 እስከ 15 ሰከንድ ያህል ንዝረቱን እንደሰተማቸው " ገልጸዋል።…
#Update
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ምሽት 4:41 ላይ ከመተሐራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል።
መሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን አመልክቷል።
ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ነው የተሰማው።

#BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ
እነዚህን መስፈርቶች ካሟሉ ከአፖሎ እሰከ መቶ ሺህ ብር ድረስ መበደር ይችላሉ።
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ ይጠቀሙ።
ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US
ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#ኮሬ 🛑 " ከትላንትና በስቲያም ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ቆስለዋል። የአርሶ አደሩ ስጋት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ነው " - ኮሬ ዞን 🔵 " እዛ አካባቢ ያለውን ህዝብ በማጽዳት መሬቱን መውሰድ ነው የተፈለገው " - የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ዳኖ ቀበሌ ከትላንት በስቲያ ሁለት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ጥቃት እንደቆሰሉ ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።…
“ ሰሞኑን በጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ንጹሐን ዜጎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - የዞኑ አካል
🔴 “ እስካሁን ድረስ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዳንዱ ግድያ ይገለጻል ፤ የአንዳንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ ” - በሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት የዞኑ ህዝብ ተወካይ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን የንጹሐን በታጣቂዎች ግድያ ባለመቆሙ ዞኑ እና በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዞኑ ተወካይና በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ዛሬም ፍትህ ጠይቀዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አንድ የዞኑ አካል፣ እሁድ ታኀሳስ 13 ቀን 2017 ዓ/ም 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ንጹሐን ዜጎች መገደላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
እኝሁ አካል በሰጡት ቃል፣ “ ምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮ ባርጉዳ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ዞኑ ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ገብተው ባደረሱት ጥቃት ሁለት አርሶ አደሮች ተገድለዋል ” ነው ያሉት።
ታጣቂዎቹ ከፈቱት ባሉት ተኩስ ዩኑሱ ኡሱማን ኃይሌ የተባለ ወጣት ወዲያው፣ ወጣት ቡቹቴ ማስረሻ ደግሞ ወደ ኬሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወታቸው ማለፉን ከቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።
በተለይ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ነቅተው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዞኑ በአጽንኦት አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ መንግስት በዞኑ የሚፈጸመውን ጥቃት እንዲያስቆም ከዚህ ቀደም ስለቀረቡት ጥያቄ ምን አዲስ ነገር አለ ? ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኮሬ ዞን ህዝብ ተወካይ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)ን ጠይቋል።
በፓርላማ የህዝብ ተወካዩ ምን ምላሽ ሰጡ ?
“ በፓርላማ ባለፈው እኔ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኬዙን አንስቼ ነበር። ሽማግሌዎችም በተደጋጋሚ እዛ ርዕሰ መስተዳድር ሄደው ነበር።
እስካሁን ድረስ ነዋሪዎቹ በየቀኑ ይገደላሉ። የአንዳንዱ ግድያ ይገለጻል፤ የአንዳንዱ አይገለጽም ሰው ተሰላችቶ። የተለዬ ምንም መፍትሄም የለም።
መንግስት ትኩረት ቢሰጥ ኖሮ ያ አካባቢ ይህን ያህል የሚያስቸግር አይደለም፣ ጠባብ ቦታ ነው ገላና ሸለቆና ነጭ ሳር ፓርክ የሚባለው እነዚህ ሽፍቶች የሚንቀሳቀሱበት።
በቀላሉ ኦፕሬሽን አድርጎ ችግሩን መፍታት ይችላል በሚል በተደጋጋሚ እናቀርባለን፤ ከዛም የመንግስት ሰራዊት ይሄዳል። ትንሽ ቆይቶ በሌሎች አካባቢዎች የጸጥታው ችግር ሲብስ የሚመለስበት ሁኔታ ነው ያለው።
የተለዬ የተሰጠ ትኩረትም የለም። የተለዬ መፍትሄም የለም ” ብለዋል።
በየጊዜው ጥቃት እንደሚፈጸም ቢገልጹም ጥቃቱ እስካሁን አለመቆሙን እየተገለጸ ነው፤ ችግሩ እንዲቆም ምን መደረግ አለበት ? እንደ ህዝብ ተወካይነትዎ ያለዎት መልዕክት ምንድን ነው? የሚል ጥያቄም አቅርበናል።
አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ምን መለሱ?
“ የምናስተላልፈው መልዕክት መንግስት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ነው። በተጨማሪም ህዝቡን ራሱን መጠበቅ መቻል አለበት።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተቻለው ጥረት እያደረገ ነው። በዬአካባቢዎቸለ የሚነሱ ግጭቶችን ኢንፍሎንስ ያደርጋል ኃይል በመላክና ትኩረት እንሰጥ በማድረግ።
የፓሊስ አባላት፣ ሚሊሻም በደንብ ተመልምሎ ለህዝቡ ጥበቃ እንዲያደርጉ መንግስት ከሌላው አካባቢ በተለዬ ሁኔታ ይህን ያመቻች የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነበር ለክልሉም፤ አሁንም ይህ ጥበቃ ቢደረግ ነው የተሻለ የሚሆነው።
በዘላቂነት ግን ከአገራዊ ሁኔታው ጋር በተያያዘ ጀነራል ኦፕሬሽን ሰርቶ ብቻ ነው ችግሩን ማቃለል የሚቻለውና ለዛ ትኩረት ይሰጥ።"
በኮሬ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ከጉጂ በሚነሱ ታጣቂዎች ዘርፈ ብዙ ጥቃት እንደሚያርሱባቸው በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጭምር መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁንም ጥቃቱ ባለመቆሙ የመንግስትን ትኩረት እየተማጸኑ ይገኛሉ።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ኢትዮጵያ
" በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር ነው " - ኢትዮጵያ
ትላንት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዶሎ በተባለ የጁባላንድ ከተማ " በፌዴራሉ የሶማሊያ ጦር ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ፤ በዚህ የሰው ሞት፣ ቁስለት ደርሷል " የሚል ክስ አሰምቷል።
ይህ መግለጫ እና በተፈጠረው ክስተት የኢትዮጵያ ኃይሎችን መክሰሱ ኢትዮጵያ አስቆጥቷል።
ክሱ ሀሰተኛ እንደሆነ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ " ሀሰተኛ ውንጀላው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታለመ ነው " ብሏል።
" ይህ የአፍሪካ ቀንድን ሰላም ለመበጥበጥ የሚፈልጉ እና በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር ነው " ሲል ገልጿል።
" በአንካራው ስምምነት ላይ እንደተገለጸው ሁለቱ ሀገራት ለሰላም የሚያደርጉት ቁርጠኝነት እንዳይደናቀፍ ክፍተት መፍጠር የለባቸውም " ሲል አመልክቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደሚቀጥልም አሳውዋል።
ኢትዮጵያ በአንካራ ስምምነት መሰረት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማደስ እና ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል።

#Ethiopia #Somalia #Egypt
የሶማሊያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ኤንድ ሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አብዱላሂ ሞሐመድ ዓሊ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።
አብዱላሂ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መክረዋል።
ውይይቱ የአንካራውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ሀገራት አቻ ተቋማት የሚጠበቁ የትብብርና የአጋርነት መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።
በውይይቱ የኢትዮጵያና ሶማሊያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት የሚፈጥሩ አካላትን ለመከላከል የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት የጋራ መግባባት እና ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።
በሌላ በኩል ፥ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ኢትዮጽያ ይገኛሉ።
በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋን ወደ ኢትዮጵያ በላከችበት በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ግብፅ ካይሮ ልካለች።
ሚኒስትሯ አሕመድ ፊቂ ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባድር አብደላቲ ጋር ከመከሩ በኃላ የጋራ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚሁ መግለጫ ፤ የግብፁ ሚኒስትር " የቀይ ባሕርን ዳርቻ መጠቀም የሚችሉት ከባሕሩ ጋር የሚዋሰኑ አገራት ብቻ መሆን ይገባል ፤ የቀይ ባሕር ዳርቻ አዋሳኝ ላልሆኑ ሀገሮች ክፍት ሊሆን አይችልም " በማለት መናገራቸውን " ኢጂፕት ዴይሊ " ዘግቧል።
ግብፅ ይህን አስተያየት የሰጠችው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ኢትዮጵያ የባህር በርን ልታገኝ የምትችልበትን ስምምነት ፈርመው ፊርማ ሳይደርቅ ነው። በቀጣይ ወር ደግሞ ለዚሁ ጉዳይ ንግግር እንደሚጀመር ይታወቃል።
ከዚህ ባለፈ የግብፁ ሚኒስትር ፤ " የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት መላው የሀገሪቱን ግዛቶች ሙሉ እንዲቆጣጠር " በሚችልበት አግባብ ላይ መምክራቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈ ግብፅ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ በሚያደረገው ተልዕኮ " ወታደሮቼን አወጣላሁ " ብላለች።
የሶማሊያው ሚኒስትር በሰጡት አስተያየት " ግንኙነታቸን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ተስማምተናል " ሲሉ መናገራቸውን ኢጂይፕት ዴይሊ አስነብቧል።

#Update በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ምሽት 4:41 ላይ ከመተሐራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል። መሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን አመልክቷል። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ነው የተሰማው። @tikvahethiopia
" ያለማቋረጥ እየመዘገብን ነው እስካሁን 4.9 ነው የተመዘገበው አሁንም ያለው ነገር ስናየው የሚቆም አይመስልም " - ፕ/ር አታላይ አየለ
በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኙ የሃገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ እየተሰማ ያለው ከዝቅተኛ መጠን እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በመሬት ውስጥ ያለው የማግማ እንቅስቃሴ ፈጣን (Active) በመሆኑ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል።
ይህ ፈጣን እንቅስቃሴ በመቀነሱ ምክንያት የመሬት መንቀጥቀጡ ረገብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ካለፉት 6 ቀናት ወዲህ ይህ እንቅስቃሴ በድጋሚ መታየት መጀመሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕ/ር አታላይ አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" መስከረም እና ጥቅምት ላይ ይታይ የነበረው እና ረግቦ የነበረው እንቅስቃሴ ከ6 ቀን በፊት ጀምሮ በድጋሚ መታየት ጀምሯል ያለማቋረጥ እየመዘገብን ነው እስካሁን 4.9 ነው የተመዘገበው አሁንም ያለው ነገር ስናየው የሚቆም አይመስልም " ብለዋል።
ትላንት ማታ 4:41 ላይ ከተመዘገበው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ሌላ ትንንሽ እንቅስቃሴዎች አሁንም በመኖራቸው ያለማቋረጥ የመመዝገብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
መንቀጥቀጡ እስካሁን ከመነሻው ቦታው አዋሽ ፈንታሌ ያደረገው ለውጥ እንደሌለ የተናገሩት ፕሮፌሰሩ ሌሎች አካባቢ እየተሰማ ያለው ድንጋይ ውሃ ውስጥ ስንወረውረው እንደሚፈጥረው አይነት ሞገድ መሆኑን ጠቁመዋል።
" አሁን ባለው ሁኔታ የከፋ ነገር ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት የለም " ያሉ ሲሆን በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ግን ሁለት አይነት መላምቶችን ሊታዩ እንደሚችሉ አስቀምጠዋል።
" አንደኛው ልክ እንደዚህ ቀደሙ ውስጥ ያለው ሃይል ሲጨርስ አስተንፍሶ ይቆማል ያ ካልሆነ ግን ሁለተኛው ምናልባት ገፍቶ የቅንጣሎች ፍሰት ሊያስከትል ይችል ይሆናል ምናልባትም ሃይል ያለው እና እንደጎርፍም ሊፈስ የሚችል ይሆናል " ነው ያሉት።
እንደዚህ አይነት ነገር የሚመጣ ከሆነ ቅድመ ሁኔታዎች የማስቀመጥ እና የማሸሽ ስራ የሚሰራ በመሆኑ በተዋረድ ያሉ የመንግስት አመራሮች ይህንን ሁኔታ ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አሳስበዋል።

🌟 ቴሌብር ሐዋላ ከዕለታዊ ምንዛሬ ላይ 8% ጨምሮ በምቾትና በቅልጥፍና ያስረክባል!!
ከውጭ አገራት የተላከልዎን ሐዋላ በቴሌብር ሲቀበሉ
🟡 በቴሌብር ሬሚትና በቪዛ የተላከልዎን ሐዋላ በአቢሲኒያ ባንክ ዕለታዊ ተመን
🟣 በዌስተር ዩኒየን (Western Union)፣ ኦንአፍሪክ (onafriq) እንዲሁም ቱንስ (Thunes) የተላከልዎን ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን
👉 ከተጨማሪ 8% የገንዘብ ስጦታ ጋር ይደርስዎታል።
🗓 እስከ ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia

" ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በመንግሰት በኩል ይከፈላል " - አቶ መሀመድ እድሪስ
ዛሬ የሰላም ሚኒስትር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ጋር ተገናኝተው በመንበረ ፓትርያርክ መወያየታቸው ተሰምቷል።
በቅርቡ የተሾሙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር የትውውቅ ፕሮግራም አድርገዋል።
በዚህም ወቅት በሀገሪቱ የተጀመሩ የሰላም ስራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ላይ የጋራ ምክክር ማድረጋቸውን ሰላም ሚኒስቴር አመላክቷል።
ሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በአገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩም ተገልጿል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተ-ክርስቲያኗ ከመንግስት ጋር በመደጋገፍና በመቀራረብ በሰላም ዙሪያ ከመቼውም በላይ በትጋትና በመቀራረብ እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።
አዲሱ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ለትውውቅና ለመወያየት ወደ መንበረ ፓትሪያርክ መምጣታቸውንና ላሳዩት የአመራር ትህትና አድናቆትና ምስጋና እንዳቀረቡላቸው ተገልጿል።
አቶ መሀመድ ፤ " አሁን ያለው ሰላም እንዲጎለብት ቤተ-ክርስቲያኗ በሰላምና በሀገረ መንግሰት ግንባታ ካላት የካበተና የዳበረ ልምድ በመነሳት በአሁኑ ሰዓት እየታዩ ያሉ የሰላም ፈተናዎች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ አገራዊ የሰላም ፀሎት እና ጥሪ እንዲደረግ " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
" ለሰላም የሚከፈል ማንኛውም ዋጋ በመንግሰት በኩል ይከፈላል የሰላም ሚኒስቴርም ከሁሉም የእምነት አባቶችና ተቋማት ጋር በትብብርና በመደጋገፍ ይሰራል " ሲሉ አረጋግጠዋል።
#MinistryofPeace

Photo
" የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ወጪ 100 በሆነበት ማግስት አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም " -የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
በትላንትናው ዕለት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ከተሻሻለው የምግብ ሜኑ ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲው የተፈጠረ ግርግር ለተማሪዎች መጎዳት እና ለንብረት ውድመት ምክንያት መሆኑ ተሰምቷል።
ለአለመግባባቱ መነሻ የሆነው በትምህርት ሚኒስቴር በተሻሻለው እና በሁሉም የዩኒቨርሲቲዎች ወጥነት ያለው የምግብ ሜኑ እንዲኖር የሚያዘውን መመሪያ ተከትሎ " ዩኒቨርሲቲው አግባብ ባልሆነ መንገድ ተግባራዊ እያደረገው ነው " በሚል ነው።
ዩኒቨርስቲው ከቅዳሜ 12/04/2017 ዓ/ም ጀምሮ አንድ ዳቦ ለቁርስ እየቀረበ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ከዚህ በፊት ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ዕለታዊ ለቁርስ ይቀርብልን የነበረው ዳቦ ምንም እንኳን መጠኑ በጣም አነስተኛ ቢሆንም ሁለት ነበር አሁን ግን የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ተመን ወጪ 100 በሆነበት ማግስት አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም " ሲሉ ወቅሰዋል።
በዚህ የምግብ አቅርቦት ደስተኛ ያልሆኑ የዋና ግቢ እና የዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች ድርጊቱን በመቃወማቸው ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በመቐለ ዩኒቨርስቲ የአሪድ የተማሪዎች ምግብ ቤት ሰራተኛን አነጋግሯል።
እኚሁ ሰራተኛ ፤ " ግርግሩ በቁርስ ሰዓት ነበር የጀመረው ተማሪዎቹ በቁርስ ሰዓት ሲቅርብላቸው የነበረው ሁለት ዳቦ ግራሙ ጨምሯል በማለት አንድ ዳቦ እንዲሰጣቸው ተደረገ ተማሪዎቹ ዳቦው አንድ መሆኑን እና የተጨመረ ግራም እንደሌለ ተናግረው የዩኒቨርስቲው አመራሮች እንዲያነጋግሩዋቸው ጠየቁ " በማለት የጉዳዩን መነሻ አብራርተዋል።
" ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት መልስ ባለመስጠታቸው የተቆጡ ተማሪዎች የምግብ ጠረጴዛዎችን ፣ የምግብ ቁሳቁሶችን ፣ መስታወቶችን እና ሌሎች ነገሮች ወደ መስበር ተሸጋግረዋል በምግብ ቤቱ ሰራተኞች ላይ ግን ያደረሱት ጉዳት የለም " ብለዋል።
በቁርስ ሰዓት በአሪድ ካምፓስ የጀመረው ግርግር ወደ ዓዲ ሓቂ ካምፓስ በመዝለቅ እስከ እራት ሰዓት ድረስ በዩኒቨርስቲ ንብረቶች ላይ ውድመት መድረሱን ተገልጿል።
የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ወደ ካምፓሶቹ የፀጥታ አካላት መላኩ ተነግሯል።
በዚህም ሳቢያ በፓሊስ እና በተማሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተማሪዎች የድብደባ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተነግሯል።
በሁለቱ ካምፓሶች ግን ለጊዜው ግምቱ ያልተጣራ ንብረት መውደሙን ለመረዳት ተችሏል።
በመቐለ ዩኒቨርስቲ አሪድ እና ዓዲ ሓቂ ካምፓሶች የተፈጠረው ግርግር በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ ቆሟል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲውን የኮሙኒኬሽን ኮርፓሬት ስለ ተፈጠረው ግርግር ማብራርያ እንዲስጥ ያቀረበው ጥያቄ " የጉዳዩ መነሻ እና መድረሻ የሚመለከት ይፋዊ መግለጫ በሚድያ እስከሚሰጥ ጠብቁ የሚል " ምላሽ ተሰጥቶታል።
በኃላም ተቋሙ ማብራሪያ አውጥቷል።
በዚህም ፦
- በሃገር ደረጃ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገራዊ የምግብ ሜኑ በትምህርት ሚኒስቴር ጸድቆ ለትግበራ መላኩን ገልጿል።
- ዩኒቨርሲቲው ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመነጋገር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ ሜኑን አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን አመልክቷል።
- በሜኑው ላይ የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ ብሄራዊ ሜኑ በይዘት እና በጀት ደረጃ እስካልተለየ ድረስ ጥያቄዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ቀርበው ማስተካከል እንደሚቻል አመልክቷል።
- በሃገር ደረጃ ተግባራዊ የሆነውን የምግብ ሜኑ ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲውን መሰረተልማት ማጥፋት እና የካፊተርያ እና የጥበቃ ሰራተኞች ላይ ጉዳት ማድረስ ተማሪዎችን እንዲሁም ማህበረሰቡን እና ሃገሪቱን የሚጎዳና ተግባር እንደሆነ ገልጿል።
- ተማሪዎች ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለጽ እንዳለባቸው አሳስቧል።
ጉዳዩን በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ህብረት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ ስለመሆናቸው የሚገልጽ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የአቋም መግለጫ ከሚመለከታቸው የማኔጅመንት አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ያለኣግባብ የታሰሩ ተማሪዎች እንዲፈቱ እና ያለ መረጃ በተማሪዎች ላይ እርምጃ እንዳይወሰድ መወያየታቸውን ይገልጻል።
በተጨማሪም አዲሱ ሜኑ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ በነባሩ ሜኑ እንዲቀጥል ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል።
ህብረቱ ለተማሪዎች ሰላማዊ ጥያቄ ከተማሪዎች ጎን እንደሚቆም ይሁን እንጂ በዋና ግቢ ካፍቴሪያ እና በኣዲ ሓቂ ተማሪዎች ላይ የደረሰው ጉዳት እና ስህተት ፈጽሞ መደገም የለበትም ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle