TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.2K photos
1.46K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Bank_of_Abyssinia

ለመጪዎቹ የአዲስ አመት፣ የመስቀልና የመውሊድ በዓላት ከውጭ አገራት በአቢሲንያ ባንክ በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ ሲቀበሉና ሲመነዝሩ የሞባይል አየር ሰዓት ያገኛሉ።
ከነሐሴ 26 ቀን 2015 እስከ መስከረም 19 ቀን 2016 የሚቆይ።

#holiday #newyear #Ethiopiannewyear #finance #transfer #Visa #Mastercard #BankofAbyssinia #BankingService #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ቅዳሜ የመጨረሻው ገንዘቡን የመመለሻ ቀን ነው " - ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ አሳስቧል። ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነውም ብሏል። በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ…
#Update

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባንኩ ገንዘብ ያለአግባብ የወሰዱ ግለሰቦች በዲጂታል የክፍያ አማራጭ መመመለስ ይችላሉ አለ።

ባንኩ ፤ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ እና ያዘዋወሩ ሰዎች እስክ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ ም ድረስ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት እንዲመልሱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

ዛሬ ምሽት ባወጣው መልዕክት ደግሞ ፤ " ያለ አግባብ ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች ከቅርንጫፎች በተጨማሪ የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም በቀጥታ ቀድሞ ገንዘቡ አለአግባብ ወጪ ወደተደረገበት በባንካችን የሚገኝ የባንክ ሂሳብ ማስተላለፍ (#transfer) እና ገቢ ማድረግ ይችላሉ " ብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘቡን እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 የማይመልሱ ግለሰቦችን ደረጃ በደረጃ በህግ አግባብ እንደሚጠይቅ ስማቸውንና ፎቶግራፋቸውንም በሚዲያ እንደሚያሰራጭ አስጠንቅቋል።

አርብ መጋቢት 6 ለሊት ከባንኩ ሲወጣ ያደረው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ ባይታወቅም ባንኩ በተደጋጋሚ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ ያወጡ ሰዎች ገንዘቡን እንዲመልሱ እያሳሰበ ይገኛል።

@tikvahethiopia