TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በመቐለ የተለያዩ ክፍሎች ጨምሮ በሌሎች የትግራይ ከተሞች ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እያጋጠመ ነው።

ይህን ተከትሎ ነዋሪዎች ለከፋ ችግር ተጋልጠለዋል።

የመቐለ የተወሰነ ክፍል የኤሌክትሪክ ሐይል ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ተቆጥረዋል።

ትላልቅ ኢንዳስትሪዎች ጨምሮ በኃይል እጦትና መቋረጥ እየተፈተኑ ነው።

በተለይ በተያዘው የክረምት ወቅት በስፋት እየታየ ያለው እና መቐለ ከተማ ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሚሸፍነው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ሐይል መቋረጥ በነዋሪዎች ዘንድ የከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ፈጥሮ ይገኛል።

በመቐለ በተለምዶ ሰብዓ ካሬ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኤሌክትሪክ ሐይል አገልግሎት ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ሆኗል።

ከመቐለ ውጪም ቢሆን በሀገረሰላም እና ወጀራት አካባቢዎች ከወር በላይ ለሚሆን ግዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተጓጉሎባቸው ቆይቷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ሪጅን የትራንስሚሽንና ሳብስቴሽን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ገብረእግዚአብሔር፥ " የኃይል መቋረጡ ዋነኛ ምክንያት በኃይል ማስተላለፊያ ላይ የደረሰ ጉዳት ነው " ብለዋል።

ችግሩ በግዚያዊነት እስከ መጪው ነሐሴ 5 ቀን 2016 ድረስ ለመፍታት ይሰራል። በዘላቂነት ደግሞ ተጨማሪ ጥረቶች ይደረጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ነው።

#DWAmharic

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ነዋሪዎች እጅግ እያማረረ ነው።

በርካቶች የኃይል የመቆራረጡ ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ፈተና ሆኖባቸዋል።

" የሚሰሩት የመንገድ ስራዎች እየተጠናቀቂ ሲመጡ የኃይል የመቋራረጥ ነገሩ ይቃለለል ብለን ብናስብም አሁንም ያው ነው " ብለዋል ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች።

በተለያዩ ቦታዎች ላይም የኃይል መቆራረጡ ንብረት እስከማቃጠል የደረሰ ጭምር ነው።

ከኤሌክትሪክ ኃይል ችግር ባለፈ ውሃም ፈተና እንደሆነ መቀጠሉን ጠቁመዋል።

በተለይ ብዙ ነዋሪዎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውሃ አለመኖር የሚፈጥረው ችግር ይታወቃል።

" በየጊዜው ያለው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ተደጋግሞ ቢነሳም ዛሬም ድረስ ይኸው ጥያቄ ቀጥሏል ፤ ዘላቂ መፍትሄ መቼ እንደሚመጣ ግራ ነው የገባን !! " ብለዋል።

#AddisAbaba #TikvahFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

ሰሞኑን " ዶላር በጣም ጨምሯል " በሚል የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ የንግዱ አካላት እጅግ እያማረሯቸዉ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ብለዋል።

" አሁን ላይ ነጋዴው እቃውን በሌሎች ነጋዴዎች ሱቅና በራሱ መጋዘን ሲያስቀምጥ አይናችን እያዬ እቃዉ የለም በሚል ዋጋ ሊጨምር ሲሞክር ማየት ያማል " ሲሉ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ " እስከ 1,080 ብር የነበረዉ ዘይት 1380 ብር ሲገባ ዶላር ነው " አሉን " እሺ የቲማቲምና ሽንኩርቱስ ዋጋ መናር ከየት መጣ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

1 ኪሎ ሽንኩርት ከ40 ብር ተነስቶ 90 ብር ቲማቲም 20 ብር የነበረው 40 እና 45 መግባቱን ጤፍም በኪሎ ከ10 ብር በላይ እንደጨመረ ጠቁመዋል።

ስሚንቶ ላለፉት ወራት ጥሩ ቢሆንም አሁን ላይ " የለም " እየተባለ እንደሆነ ገልጸዋል።

የነዳጅ ጉዳይ ግን በፊትም አንስቶ ፈተና ነበር አሁን ብሶበት ራስ ምታት ሆኖ ቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀዋሳ ላይ የገበያውን ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የተቋቋመ ግብረሀይል መኖሩን በመስማታችን  የነዋሪዎችን ቅሬታ ይዘን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን አነጋግረናል።

እሳቸውም ፥  " አሁን ላይ እቃ በሚደብቁ እና አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ግብረሀይሉ  ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው " ብለዋል

ግብረሀይሉ  በሰራዉ ስራ ሁለት ማደያዎች እና 62 የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች የምግብ ግብአትና የብረታብረት አቅራቢዎች በ8ቱ ክፍለ ከተሞች  መታሸጋቸዉንና እቃዎችም ተወርሰዉ ህገወጦቹ ግለሰቦች  በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል።

ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚገልጹት አዛዡ ማህበረሰቡም ህገወጦችን በመጠቆም የፖሊስን ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል። ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ…
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

" አሶሳ ላይ ያለው የመብራት ጉዳይ አሁንም መፍትሄ ሊያገኝ አልቻለም። በየጊዜው እየተቆራረጠ ነው።

ማህበረሰቡ እጅጉን ተቸግሮ ነው ያለው።

በተለይም ዉሃ ፣ ወፍጮ እንዲሁም ከመብራት ጋር የተያያዘ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች በጣም ችግር ላይ ናቸው። ምንም ስራ ሳይሰሩ የቤት ኪራይ እየከፈሉ ነው።

የመብራት አለምኖር በአጠቃላይ የከተማውን የንግድ እንቅስቃሴን አቀዛቅዞዋል። በጄነሬተር ሞባይል ቻርጅ ለማድረግ 40 ብር  ነው። ኑሮን የበለጠ ከባድ እያደረገብን ነው።

በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ቦታ ብልሽት አጋጥሞታል ይባላል። ጠንካራን እና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንፈልጋለን። "

#TikvahEthiopiaFamilyAssosa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎድምጽ • " ቤንዝል ሙሉ በሙሉ  ከጠፋ 4 ቀናት መሆኑን ተከትሎ ከስራ ውጭ ሆነናል " - በሀዋሳ ከተማና አካባቢዉ የሚገኙ አሽከርካሪዎች • " ከጅቡቲ የተነሱ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች እስኪደርሱ በትእግስት ጠብቁ " - የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከሰሞኑ በነዳጅ እጥረት ምክኒያት አልፎ አልፎ የነዳጅ ፕሮግራም ሲወጣ ቢቆይም ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ግን ሙሉ በሙሉ ድልድል ባለመውጣቱና…
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

ነዳጅ (ቤንዚን) በክልሎች ላይ ችግር ከሆነ እጅግ በርካታ ጊዜያት ያስቆጠረ ነው።

ከአዲስ አበባ ውጭ ነዳጅ እንደልብ ማግኘት አዳጋች ነው።

ለተለያዩ ጉዞ ወደ ክልሎች የሚወጡ መንገደኞች ይህንን ነገር ያውቁታል።

በአንድ በኩል ነዳጅ የለም እየተባለ በጥቁር ገበያ እስከ 150 ብር ከዛም ከፍ ብሎ ለጉድ ይቸበቸባል።

ይህንን ችግር ማስተካከል ፤ ጥቁር ገበያውን መቆጣጠር ለምን አልተቻለም ? የብዙሃን ጥያቄ ነው።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ነዳጅ ለማግኘት ሰዓታትን መሰለፍ ግድይላቸዋል ፤ ጾማቸው ላለማደር ልጆቻቸውን ላለማስራብ የዕለት ጉርሳቸውን ይዘው ለመግባት ከማደያ ውጭ ይገዛሉ።

በየጊዜው በየማደያው " የለም " ይባላል ውጭ ላይ ለጉድ ይሸጣል። ይህ ሰንሰለት ከላይ እስከ ታች መሆኑ እሙን ነው። ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋል።

ነዳጅ በአግባቡ ለተጠቃሚው እንዲደርስ ያሉት ችግሮች ተፈትሸው መታረም ግድ ይላለቸዋል።

በየጊዜው በነዳጅ ጉዳይ ዜጎች መማረር የለባቸው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

" የማህበሩ ይዞታ አለአግባብ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ ተሰጥቷል " - የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች

በአዲስ አበባ ከተማ የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ቤቶች ባለቤቶች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር የነዋሪዎች ይዞታ (600 ካ/ሜ በላይ) አለአግባብ ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ እንደተሰጠ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳወቀ።

ጉዳዩ ፍርድ ቤት ድረስ የደረሰና ፍርድ ቤትም ውሳኔ ያሳለፈበት ነው።

ጉዳዩ ምንድነው ?

ማህበሩ ይዞታው እንደሆነ የገለጸውና በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠበት እንዲሁም በሳይት ፕላን ሳይቀር በግልጽ የማህበሩ ይዞታ መሆኑ የታወቀ መሬት ተወስዶ ለግለሰብ ተሰጥቷል።

ማህበሩ በሳይት ፕላኑ መሰረት የነዋሪዎች ይዞታውን አጥሮ የበለጠ እንዲለማና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርግ ፍቃድ አግኝቶ አልምቶት ነበር።

ልማቱ የሕጻናት ስፖርት ማዘውተሪያ መጫወቻና የመኪና መተላለፊያ እና ፓርኪንግ ውሎ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪም ይህ ቦታ የተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች እንደ ደመራ ፣ ሀዘንና ሰርግ ማከናወኛ ቦታ የነበረ ነው።

ለዚህ የልማት ስራ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ከማህበሩ ወጪ ተደርጓል።

ከዚህ ባለፈ ለህበረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የጋራ መጠቀሚያ ፣ የሕጻናት ማቆያና የስፖርት ማዘውተሪያ የእርድ አገልግሎት መፈጸሚያ በከፍተኛ ወጪ አሰርቶ ለፍቃድ ሲጠባበቅ ነበር።

ነገር ግን ያለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ከክፍለ ከተማው (ልደታ) የመሬት ልማት አስተዳደር " ታዘዘ ነው " በሚል አንዳችም ደብዳቤ ሳይዙ በቃል ብቻ በፖሊስ ኃይል በመታገዝ ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የማህበሩን ይዞታ ጥሰው በመግባት ልኬት ወስደዋል።

ከዛ በኃላም ያለ ምንም የፅሁፍም ሆነ የቃል ማስጠንቀቂያ በግልጽ የማህበሩ ይዞታ እንደሆነ እየታወቀ ኮርዲኔት ተቀይሮ ለግለሰብ መሰጠቱን ማህበሩ እንደደረሰበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ማህበሩ ፥ በአንድ የጋራ መኖሪያ ክልል ውስጥ የሚገኙ የጋራ መጠቀሚያዎች በተለይም በ' ግሪን ኤርያ ' የተከለሉ ቦታዎችን ህብረተሰቡን ሳያማክሩ እና የከተማ ፕላንና ልማት መመሪያን ጥሶ አረንጋዴ ቦታዎችን ለግለሰብ እያነሱ መስጠት አግባብ አይደለም ሲል ወቅሷል።

ከዚህ ባለፈ ከአካባቢው የግንባታ ስታንዳርድ አንጻር ቦታውን ለግለሰብ ከመስጠት ይልቅ ለህብረተሰቡ ለልጆች መጫወቻ፣ ለእርድ ቦታ፣ ለኮሚኒቲ ፖሊሲንግ ፣ ለተለያዩ የማህበራዊ ክንዋኔዌች እንዲሁም ለመኪና ማቆምያ ቢውል የተሻለ እንደሆነ አስገንዝቧል።

ይህ የይዞታ ጉዳይ 2014 ዓ/ም ላይ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶም ነበር።

ከሰሽ ደግሞ ይዞታው የራሱ እንዳልሆነ የታወቀው አካል ሲሆን " ቦታውን ለመንጠቅ አጠሩብኝ ፤ ሁከትም ፈጥረዋል " የሚል ክስ ነው ያቀረበው።

ጉዳዩን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲከታተለው ከቆየ በኃላ ክርክር የተነሳበት ይዞታ የከሳሽ አለመሆኑን ወስኗል።

ነገር ግን ጉዳዩ የተረሳሳ አስመስሎ በቅርቡ ቦታው ታጥሯል። ማህበሩም ለሶስተኛ ወገን እንደተሰጠ እንደደረሰበት ጠቁሟል።

መፍትሄ ፍለጋ ብዙ ቢደክምም ሰሚ አላገኘም።

(የፍርድ ቤት ሂደቱን ከታች ይቀርባል)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

" በሰው ላይ ጨዋታ ነው እንዴ የያዙት ? " - ነዋሪዎች

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ' ጨፌ ሜዳ ' ነዋሪዎች በመብራት መቆራረጥ እንዲሁም ጠፍቶ እስከወዲያኛው መቅረት እጅግ በጣም ተማረዋል።

በተደጋጋሚ ቅሬታ ቢያቀርቡም መፍትሄ አላገኙም።

ነዋሪዎች ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ምን አሉ ?

➡️ ከአምትና ከሁለት ዓመት በፊት እንዲሁ ይጠፋል ይቃጠላል መጥተው ይቀይራሉ ፤ የሚቀይሩት ኃይሉ የተመጣጠነ አይደለም ወዲያ ይጠፋል።

➡️ ሰው ላይ ጨዋታ ነው እንዴ የያዙት ? ለምንድነው እንዲህ የሚደረገው ? ሰራን ብለው እንደሄዱ ወዲያው ይጠፋል። እነሱ ደመወዛቸውን እየበሉ ነው ፤ እንጀራ ጋግሮ መብያ ይጠፋል እንዴ ?

➡️ ከ30 እና 40 ዓመት በፊት ስንገለገልበት በነበረበት መጠን እንድንገለገል እየተደረገ ሰው ጭለማ ውስጥ ነው ያለው።

➡️ ፍሪጅ ተበላሽቷል አይሰራም ፤ ቴሌቪዥን ተበላሽቷል ለሰራተኛ ብር እየሰጠን ነው የምናሰራው። ለፍተን ደክመን አጠራቅመን በእርጅና ጾም እንፈታበታለን ያለው ነገር ሁላ እየተበላሸብን ነው። ባለፈው ብዙ ነገር ተበላሽቶ ጥለናል።

➡️ ፍሪጅ የሚፈልግ መድሃኒት አለ ያ ሁሉ ከንቱ ቀረ ሰው ይሙት እያሉ ነው ?

➡️ ህጻናት ፣ ልጆች ፣ አቅመ ደካማ አለ ስንት ጣጣ ነው ያለው። ቤት ውስጥ ብዙ ነገር ነው ያለው። ቢደወልላቸው አይመጡ ፤ መጣን መጣን እያሉ ያሾፋሉ። ሲመጡ ደግሞ ምኑን ነክተውት እንደሚሄዱ አይታወቅም ኬላ እንኳን ሳያልፉ ወዲያው ይጠፋል።

➡️ የተቦካ እህል እየተበላሸ ነው የት ይጋገር ?

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ኃላፊ ዳይሬክተር ይሄይስ ስዩም ለኤ ኤም ኤን በሰጡት ቃል ፤ ቅሬታው እውነትነት እንዳለው ገልጸዋል።

" ለፈጠርንባቸው ችግር ደንበኞቻችንን ይቅርታ ጠይቃለሁ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁለት ሳምንት ሳይሞላ ወይም ከዛም ባነሰ ጊዜ መፍትሄ እንሰጣቸዋለን " ብለዋል።

#ፈረንሳይለጋሲዮን #ጨፌሜዳ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

" የከንቲባዋ ቃል አሳዝኖናል " - የ97 ተመዝጋቢዎች

" የ1997 ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች 20 አመት ሙሉ የጠበቅነዉን ተስፋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ' 97 ሰጥተን ጨርሰናል ' ማለታቸዉ በጣም አሳዝኖናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቁጠባችንን በአግባቡ እየቆጠብን የነበርን በሺዎች የምንቆጠር ዜጎች አለን " ብለዋል።

" እኛም ዜጎች ነን በኪራይ ቤት እድሜችን አለቀ " ሲሉ አክለዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ " ለሕዝብ ዕንባ ጠበቂ ተቋም ደብዳቤ አስገብተናል አዲስ አበባ ቤቶች ኤጀንሲ ግን መልስ አልሰጣቸውም " ሲሉ አስታውሰዋል።

" ከዚህ ባለፈ የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮም መፍትሄ እንዲፈልግልን ብለን ነበር ጋር ግን ምላሽ ተነፍጎናል " ብለዋል።

" ወዴት እንደምንሄድ ጨንቆናል ፍትህ ተጓሎብናል ፤ አሁን ካለው የኑሮ ጫና አንጻር የቤት ኪራይ ትልቁ ፈተና ነው እባካችሁ መፍትሄ ፈልጉልን " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

🔴 “ ጩኸታችን ሰሚ በማጣቱ በውሃ እጦት እየተሰቃዬን ነው። አሁንም ችግሩ መፍትሄ አላገኘም ” - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ነዋሪዎች

🔵 “ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በኩል መንገዶች ዝግ ናቸው። በእጅባ ካልሆነ በስተቀር ማተሪያል መጥቶ እንደማይገባ ግልጽ ነው” - የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ገጥሞናል ያሉት የውሃ ችግር ባለመቀረፉ መቸገራቸውን በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል እሮሮ አሰሙ።

በወምበራ፣ ቡለን፣ አሶሳ፣ ዳንጉርና በሌሎች አካባቢዎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት ከተጋረጠባቸው ሰንበትበት እንዳለ አስረድተው፣ “ ጩኸታችን ሰሚ በማጣቱ በውሃ ችግር እየተሰቃዬን ነው። አሁንም ችግሩ መፍትሄ አላገኘም ” ነው ያሉት።

ከ6 ወራት እስከ ዓመታት የውሃ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች እንዳሉ ገልጸው፣ የሚመለከታቸው አካላት ግን መቼ ነው ጩኸታችንን ሰምተው መፍትሄ የሚሰጡን ? ሲሉ በአንክሮ ጠይቀዋል።

° ለምን ችግሩ እንደተፈጠረ ፣
° ችግሩ ካጋጠመ በኃላ ደግሞ ለምን በወቅቱ እንዳልተቀረፈ፣
° ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የቤንሻንጉል ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሐጂራ ኢብራሂም፣ ችግሩ እንዳለ አምነው ምላሽ ሰጥተዋል።

ኃላፊዋ ምን አሉ ?

“ አዎ ችግሮች አሉ። ስታንዳርዱ በሚፈቅደው መልኩ አይደለም ህብረተሰቡ ውሃ እያገኘ ያለው። ሄይንን ስንል ግን እንደ መንግስት ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ነው። 

ነገር ግን በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በኩል መንገዶች ዝግ ናቸው። በእጅባ ካልሆነ በስተቀር ማተሪያል መጥቶ እንደማይገባ ግልጽ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋር ድርጅቶች ድጋፍ ተገኝቶ የውሃ ቁፋሮ ለማድረግ የማሽን ጨረታ ይወጣል ተወዳድሮ ወደ ቤንሻንጉል የመጣ አካል የለም ።

እንደ ክልል እጅግ ትልቅ የውሃ ችግር ያለባቸው የለየናቸው ቦታዎች አሉ። ከሌሎች የበለጠ ብለን የምናስቀምጠው አንዱ ዳንጉር ነው። ዳንጉርና ጉባ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር አለባቸው። ይሄ የሆነው ደግሞ ሳይት ተመርጦ ነበር ከችግሩ በፊት፣ ውሃ ቁፋሮ ግን ውሃዎቹ አልተገኙም።

ስለዚህ የከርሰ ምድር ውሃ ነው እየጀመርን ያለው። ሁሉም ቦታ ላይ ጥናት አድርገን አስቀምጠን አጋር ድርጅቶች ሲመጡ ቀጥታ ችግሩ የት ጋ ነው ያለው? ለሚለው ጥናቱን ለማስረከብ ነው የክልሉ መንግስት የሰጠን አቅጣጫ።

ይሄ ይዘን ቀጣይ ብዙ ሥራዎችን ለመስራት አቅደናል።

ቡለን አካባቢ ችግሮች ነበሩ ውሃ ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ነው። የመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ብዙ ስራ እየሰራ ያለበት ያለ ወረዳ ነው። ግን አሁንም ቢሆን በቂ ነው ብለን አንጠብቅም። ተደራሽነቱ ላይ ክፍተቶች አሉ። 

የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው። የፌዳራሉ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግልን ማሽን ሁሉ ጠይቀን ማሽኑ አማራ ክልል ወደ ጎንደር አካባቢ ነው ያለው ለቁፋሮ ሂዶ፤ ከዛ አውጥቶ እንኳ ወደኛ ክልል ለማስገባት ትንሽ የተቸገሩበት ሁኔታዎች ስለነበረ  አሁን ከእነርሱ ጋርም እየተነጋገርን ነው ያለነው ”
ብለዋል።

ኃላፊዋ ፤ የማሽን ችግር እንደነበር እና ማሽን ሲገባ እንዳልነበር በፌደራል ደረጃ ጨረታ ወጥቶ ጨረታ ወጥቶ ተወዳዳሪ ይገኝ እንዳልነበር ፤ በአሁኑ ወቅት ግን አንጻራዊ ሰላም መንገዶች ላይ ስላለ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

(ጉዳዩን እስከመጨረሻው የምንከታተል ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

🔴 " ' ቦታው ሕገ ወጥ ነው ' በሚል ከቤት ካስወጡን በኋላ ሌላ ሰው እንዲገባ ተደርጎበታል " - ነዋሪዎች

🔵 " ሰዎቹ ሁሉም ተከራይ ናቸው። ... በሕጉ መሰረት የቀበሌ ቤትን መከራየት አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ ባለቤት የነበሩት ሲያርፉ የተከራዩት እንዲወጡ ተደርጓል " - ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አካባቢ ከ15 እስከ 40 ዓመት የኖሩበትን ቤት " ሕገ-ወጥ ነው " በሚል ከቤት እንዲወጡ ከተደረጉ በኃላ ሌላ ሰው እንደገባበት ቅሬታ አቅራቢ ነዋሪዎች ገለጹ።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ቃላቸውን የሰጡት ለአሐዱ ነው።

በቀድሞ ሥሙ ቀበሌ 19 በአሁኑ ወረዳ 6 አካባቢ የሚገኙት ነዋሪዎቹ ፤ በአንድ ቦታ ውስጥ 13 አባወራዎች የሚኖሩ ሲሆን አጠቃላይ ብዛታቸው 40 እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

እንዲኖሩ የፈቀዱላቸዉ ግለሰብ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ " የሰራችሁት ቤት ሕገ ወጥ ነው ትወጣላችሁ " በሚል በ2 ቀን ማስጠንቀቂያ ከቤት እንዲወጡ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

" የተሰራው ቤት ሕገ-ወጥ ከሆነ ለምን አይፈርስም ? ለምን ለሌላ ነዋሪ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ ? " በማለት በተደጋገሚ ወረዳና ክፍለ ከተማ በአካል ቅሬታችውን ቢያቀርቡም ምላሽ እንዳላገኙ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሸራ ወጥረው በረንዳ ላይ እንደሚገኙና ከወጡ ከ16 ቀን በላይ እንደሆናቸው አመልክተዋል።

ልጆቻቸው ትምህርት ለመማር እንደተቸገሩና ተጽዕኖ እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።

የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስጋናው ሒጂሉን ለተነሳው ቅሬታ ምን መለሱ ?

ኃላፊው ቦታው የቀበሌ ቤት መሆኑን ገልጸዋል።

" ሰዎቹ ሁሉም ተከራይ ናቸው " ብለዋል።

" በሕጉ መሰረት የቀበሌ ቤትን መከራየት አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ ባለቤት የነበሩት ሲያርፉ የተከራዩትን እንዲወጡ ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።

በመመሪያው መሰረት ቤቶች አስተዳደር ቤቱን ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠቱን ተናግረዋል።

" ማንኛውም ሰው ከመመሪያውና ከሕጉ ውጭ አይሰራም " ያሉት ኃላፊው " ስራው የተሰራው የቤቶች አስተዳደር ባወጣው መመሪያ መሰረት ነው " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሐዱ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

“ ባለስልጣናቱ  ህገ ወጥ ስራ ሲሰራ ለማስቆም ምንም አይነት ፍላጎት የላቸውም ” - ነዋሪዎች

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ልዩ ስሙ ‘ሰፈረ ገነት’ በተባለ ቦታ የሚገኙ ነዋሪዎች ካሳና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው የመስሪያ ቦታቸው ለባለሃብት ተላልፎ በመሰጠቱ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ቅሬታ አሰሙ።

ቦታቸው ጋራዥ፣ ላቢያጆ የመሳሰሉት ስራዎች የሚሰሩበትና በቤተሰብ ደረጃ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች የሚተዳደሩበት 12 ሺሕ ካሬ መሆኑን ገልጸው፣ ቦታው ከህግ ባፈነገጠ አሰራር ለአንድ ባለሃብት ስለተሰጠባቸው መብታቸው ተከብሮ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ መጀመሪያ ወረዳው ጠራንና ‘ቦታችሁ ለባለሃብት ተሰጥቷል። የተወሰነው በካቤኔ ነው’ አለን። ከዛ ክፍለ ከተማ ሄደን የካቢኔው ውሳኔ ነው ወይ? አሳዩን አልናቸው። 
‘ይህንን የመጠየቅ መብት የላችሁም። ጥቅማችሁን ነው ፕሮሰስ ማድረግ ያለባችሁ እንጂ ይሄ የኛ ጉዳይ ነው’ አለን። እሺ ብለን የሚያስፈልጉ ዶክሜንቶችን አቅርበን ፕሮሰስ ማድረግ ጀመሩ ክፍለ ከተማውና ወረዳው።

በመካከል የወረዳው ሥራ አስፈጻሚና የመሬት ልማት ማኔጅመንትን ሰብስበውን ‘የምትለቁ ከሆነ በፍጥነት ልቀቁ አለበለዚያ ልክ እንደ ህገ ወጥ ግንባታ በጫጭቄ እጥለዋለሁ’ አለ።

በዚህም ምትክ ቦታ ሳይሰጥ፣ የካሳ ክፍያ ሳይኖረው በሚል ሰው ተደናገጠ። ክፍለ ከተማ ሄደን ስናናግር ‘ማን ሰብስብ አለው?’ የሚል ጥያቄ አዘል ምላሽ ነው የሰጠን።

ከንቲባ ጽህፈት ቤትም ሄደን ቅሬታ አቀረብን ዓባይነህ ለሚባል ሰው፣ የካቢኔው ውሳኔ መሆኑን ማረጋገጥ እንፈልጋለን ስንለው ጌታቸው ለሚባል መራን። ጌታቸውን ስናናግራቸው ‘አረጋግጨ ይነገራችኋል እሱ የኛ ጉዳይ ነው’ አሉን።

በዚሁ ሁኔታ ቀጥለን በኋላ ስንጠይቅ ‘የካቢኔ ውሳኔ የተሰጠው ባለሃብቱ ወረዳ 10 ነው እንጂ ወረዳ አምስት ላይ አይደለም’ ተባልን።

በኋላም የወረዳ ዘጠኝ እንደሆነ ቀሪ ወረቀት ላይ አገኘን። ሄደን ቀጥታ ዓባይነህን ስናናግራቸው ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደውለው ሲያናግሩ ‘በካቢኔ ውሳኔ ነው  ፕሮሰስ የተደረገው ገንዘብ እየገባላቸው ነው’ አላቸው።

ከዛ ወረቀቱን ለዓባይነህ ስናቀርብ ለክፍለ ከተማው ‘አይ የካቢኔ ውሳኔ አይደለም፣ ከኛ መዝገብ ቤት ያለውንና ይሄንን አያይዤ እልክልሃለሁ ቼክ አድርገው’ አሉት። ከዚያ በኋላ ግን ማንም ምላሽ የሚሰጠን የለም። ባለሃብቱ የኛን ቦታ ሙሉ ለሙሉ አጥሮታል።

የኛ ቅሬታ ውሳኔው የካቢኔ ውሳኔ አይደለም ባለን ማስረጃ። ሲቀጥል የካቢኔው ውሳኔ ቢሆን እንኳ መጀመሪያ ካሳና ምትክ ቦታ ሊሰጠን ይገባል።

ባለስልጣናቱ ‘ይሄኮ ያስጠይቀናል። የእናንተ ጉዳይ እንዲፋጠን 22 ነው ግፊት ማድረግ ያለባችሁ’ የሚል አስተያዬት ነው የሚሰጧቸው እንጂ ህገ ወጥ ስራ ሲሰራ ለማስቆም ፍላጎት የላቸውም። ፍ/ቤት ሂደን እግድ ስናወጣ መደናገጥ ጀመሩ”
  ብለዋል።

NB. " 22 " ተብሎ የተገለጸው እዛ ያለውዥ የመሬት አስተዳደር ጉዳዩን እንደያዘ ለመግለጽ ሲሆን እነርሱ ባለወቁት መልኩ እዛ እንዲታይ መደረጉ አሻጥር እንደሆነ ገልጸዋል።

ለቅሬታው ምላሽ ለማግኘት ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሙከራ ያደረግን ሲሆን፣ ለጊዜው የስልክም ሆነ የፅሑፍ ምላሽ አልሰጡም።

ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ጉዳዩ እንደሚመለከታቸው በቅሬታ አቅራቢዎቹ የተነገረላቸው አቶ ግታቸው የተባሉ አካል፣ በስልክ ማብራሪያ እንደማይሰጡ ለቲክቫህ ገልጸዋል። በአካል ምላሽ ከሰጡ በቀጣይ ይቀርባል።

(ነዋሪዎች ህዝቡ ይወቅልን ብለው አጠቃላይ ቦታውን የተመለከተ ዶክመንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መሰረት ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM