TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ዙሪያ የአሶሳ ፖሊስ ምን አለ ? የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው " ሰላም ሰፈር " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ረቡዕ ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ እንደሆነ አመልክቷል።…
#Update

የተማሪ ደራርቱ ገዳይ የ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ ላይ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል።

ረቡዕ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አቶ ዩሀንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የሆነችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የግድያ ወንጀል በመፈፀሙ ተከሳሽ በፈፀመው ሰው በመግደል ወንጀል ተከሷል።

መርማሪ ፖሊስና ዐቃቢ ህግ በጋራ ተጠርጣሪው ላይ ክስ መስርተው ምርመራ በማጣራት የወንጀል ድርጊቱን የሚያስረዱ የሰው ማስረጃና የህክምና ማስረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው ፍ/ቤት ልከዋል።

የክስ መዝገቡ የደረሰው የአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በቀን 15/9/2016 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት #በ18_ዓመት_ጽኑ_እስራት እንዲቀጣ ውስኗል።

መረጃው የአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።

#AssosaUniversity

@tikvahethiopia
🚨 #ትኩረት

ዝም አትበሉ !!

በሴቶች ፣ በተለይም ምንም በማያውቁ ፤ ክፉ ደጉን እንኳን በማይለዩ ትንንሽ ህጻናት ላይ የሚፈጸመው የግብረ ስጋ መድፍረት ተግባር እጅግ አሳሳቢ እጅግም እየከፋ እየሄደ ነው።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፥ መቼም ሴት ልጆቻችን ፣ እህቶቻችን ላይ ስለሚፈጸም የአስገድዶ መድፈር / የግብረ ስጋ ድፍረትናከዛ ጋር ተያይዞ ስለሚሰጡ ፍርዶች ብዙ ጊዜ መልዕክት መለዋወጣችን ይታወሳል።

ብዙዎችሁ በምትሰሙት ፍርድ እንደምታዝኑም ህጉ ሊስተካከል እንደሚገባ ስትገልጹ ኖራችኋል።

አንዳንድ ጊዜ " እንደው የሚሰጠው ፍርድ ለጆሮ የሚቀፍ ፣ ሰው ለማስተማርና ለመቅጣት ሳይሆን ወንጀለኞችንና ግፈኞችን ለማበረታታ " እንደሚመስል በመግለጽ መሰል መረጃዎች ለብዙሃን እንዳይሰራጩ የጠየቃችሁ ሁላ አላችሁ።

በተለይ በተለይ ሴት ህጻናትን የሚደፍሩ ሰዎች ምንም በማያጠያይቅ ሁኔታ ' የሞት ቅጣት ' እንዲጣልባቸውም የሚገልጽ ሀሳብ ስትፅፉ ነበር።

ከሰሞኑን ደግሞ የተሰሙት ከህጻናት የግብረ ስጋት ድፍረት / መድፈር ጋር የተያያዙ ፍርዶች በርካታ የቲክቫህ አባላትን አስቆጥቷል፤ አሳዝኗል።

ለመረጃ ይሆናችሁ ዘንድ ...

1. ተከሳሽ ሙሉነህ ኡጋሞ የ37
ዓመት ጎልማሳ ሲሆን የባለቤቱን እህት የሆነችውን የ12 ዓመት ህጻን ከ3 ዓመት በላይ በቆየ ጊዜ ውስጥ  " ለማንም ሰው ከተናገርሽ እገልሻለሁ ! " በማለት በማስፈራራት በተደጋጋሚ አስገድዶ የግብረ ስጋት ድፍረት እንደፈጸመ የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳ የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ ገልጿል።

ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ባለቤቱ በወሊድ ምክንያት ታማ ለ2 ወር ሪፌራል ሆስፒታል ከተኛችበት ከቀን 11/04/2013 ዓ.ም. ወንጀሉ እስከታወቀበት 27/05/2016 ዓ.ም. ድረስ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት
#በ14_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

2. የገዛ የአብራኩን ክፋይ የ9
ዓመት ልጁን የደፈረ ወላጅ አባት 17 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።

ተከሳሽ አዶኒያስ አቡታ 40 ዓመቱ ሲሆን የ9
ዓመት ህጻን ልጁን በቀን 07/07/2016 ዓ.ም.ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ከቤተሰቦቹ ጋር ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ውስጥ መድፈሩን የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

ተከሳሹ ድርጊቱን የተበዳይ እናት ቤተሰቧን ለማስተዳደር በከፈተችው የቁርሳ ቁርስ ቤት ውስጥ ለማደር በሄደችበት ዕለት የፈጸመ ሲሆን ተጎጂ ህጻን ተኝታ ካለችበት ቀስቅሶ አስገድዶ መድፈሩ ነው የተጠቀሰው።

የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት
#በ17_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

3. የ31 ዓመቱ ከሳሽ ልደቱ አስፋ የ7
ዓመት ህጻን ከቀን 01/01/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ አመት ያህል የተለያ ማባበያዎችን በመስጠት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ሲፈጽም መቆየቱን የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል።

የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ሲያከራክር የቆየው የሀዋሳ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስደገፍ በቀን 16/04/2017 ዓ.ም. በዋለው በህጻናት ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት
#በ18_ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

4. የ5
ዓመት ህፃን ልጅ የደፈሩ 2 ግለሰቦች የ19 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

በወናጎ ከተማ ቱቱፈላ ቀበሌ ኦዶላ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ የ5 ዓመቷ ህፃን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ዳቦ ለመግዛት በሄደችበት የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ተፈጸሞባታል።

ወንጀሉን የፈጸሙት አቶ ኤልያስ ኤቶ እና አቶ ታምሩ ንጋቱ የተባሉ የዳቦ መጋገሪያ ቤቱ ሰራተኞች ናቸው።

በግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞቹ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በወናጎ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለ ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው
#በ19_ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።

5. የ3
ዓመት ከ6 ወር ህጻን ላይ የመድፈር ሙከራ ያደረገው ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል።

ወጣት ኤርምያስ ፀጋዬ 3
ዓመት ከ 6 ወር በሆነችው ተበዳይ ህፃን ከምትጫወትበት ቦታ ወደ ኤት ኤል ትምህርት ቤት ይዞ በመሄድ የመድፈር ሙከራ ማድረጉን በምስክር ያረጋገጠው የወናጎ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግለሰቡን #በ10_ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ተጨማሪ ፦ የ28
ዓመት እድሜ ያለው ክብሮም ኣብርሃ የተባለ በትግራይ እንዳስላሰ ከተማ የሚኖር ወጣት የ11 እና 12 ዕድሜ ህፃናትን እንዲቀርቡትና እንዲላመዱት በማድረግ በጨርቅ እና በማጣበቂያ ማስቲሽ እንዳይጮሁ አፍኖ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል መፈጸሙ በመረጋገጡ #የ16_ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበታል።

ውድ የቲክቫህ አባላት ሆይ ፥ እነዚህ ያጋራናችሁ ከሰሞኑን የተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች ናቸው።

ድርጊቶቹ እጅግ አሰቃቂና ለጆሮም የሚከብዱ አስደንጋጭ ናቸው።

በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የጭካኔ ተግባራት በየጊዜው ይሰማሉ።

እኛ አሁን እየሰማን ያለነው ወደ ፍ/ቤትና ሚዲያ እየቀረቡ ያሉትን ነው በየመንደሩ በየአካባቢው ምን ያህል ልጆቻችን ጥቃት እየደረሰባቸው ይሆን ?

የፍርድ ውሳኔዎች አስተማሪ ናቸው ?

ልጆቻችንን ከዚህ የከፋ እና አስፈሪ ጊዜ ለመጠበቅ ምን መደረግ አለበት ?

መፍትሄው ምን ይሆን ?

በዚህ ጉዳይ ላይ የህግ ባለሙያ አስተያየት በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። እናተም የሚሰማችሁን በ @tikvahethiopiaBot ላይ ፃፉ።

@tikvahethiopia