TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Eritrea

አንድ ከኢትዮጵያ ወደ አስመራ የተመለሰ ሰውና አስራ አንድ (11) ከሱዳን ተመልሰው በኣዲባራ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ተረጋግጧል።

በአጠቃላይ በኤርትራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ አንድ (121) የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሰላሳ ዘጠኝ (39) ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Eritrea

በኤርትራ ተጨማሪ 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ሁሉም በቅርቡ ከሱዳን የተመለሱና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በአጠቃላይ ኤርትራ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 131 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Eritrea

ከ45 ደቂቃዎች በፊት ኤርትራ ላይ የሮኬት ጥቃት መሰንዘሩን የሚገልፁ ሪፖርቶች ወጥተዋል።

የአስመራ ነዋሪዎችም ምሽቱን የፍንዳታ ድምፅ እንደሰሙ አሳውቀዋል።

ከአስመራ ከተማ ውጭ በደቀምሓረ፣ አዲሃሎ አካባቢ ጥቃት ሳይሰነዘር እንዳልቀረ ተገልጿል።

እስካሁን በጥቃቱ ስለደረሰ ጉዳት የታወቀ ነገር የለም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Eritrea

ጎረቤታችን ኤርትራ ትላንት የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስተናግዳለች።

ሟቹ የ50 ዓመት እድሜ ያለው ወንድ #ደቀምሓረ ሆስፒተል ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና ሲደረግለት የነበረ ነው።

የዛሬ ሪፖርትን ጨምሮ በአጠቃላይ በኤርትራ ውስጥ 877 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ የ1 ሰው ህይወት አልፏል፤ 599 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በኤርትራ ጦር አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች። አሜሪካ የኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል ፈጽሟል ባለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት በጦሩ ዋና አዛዥ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች። ማዕቀቡ በኤርትራ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ የተጣለ ነው፡፡ ማዕቀቡን የተጣለው በአሜሪካ የፌዴራል ግምጃ ቤት (ትሬዠሪ) በኩል ሲሆን አዛዡ በአሜሪካ ያላቸው ሀብት እንዲታገድ እንደተወሰነ…
#Eritrea

ኤርትራ፤ አሜሪካ በሀገሪቱ የጦር መሪ ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ "መሠረተ ቢስ" ስትል ውድቅ አድርጋዋለች።

ኤርትራ "ህገ ወጥ" ያለችውን የአሜሪካን ማዕቀብ በተመለከተ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።

አሜሪካ በጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ "ተቀባይነት የሌላቸውን ክሶች ሰንዝሯል" ያለው መግለጫው የኤርትራ መንግስት የተቃጣበትን መሠረተ ቢስ ውንጀላና ክስ በደብዳቤም ሆነ በመንፈስ እንደማይቀበል አስታውቋል።

የአሜሪካ አስተዳደር እንዲህ ዐይነት መሠረተ ቢስ የውንጀላ ዘመቻዎችን በኤርትራ ላይ ሲያርግ የመጀመሪያው እንዳይደለም ሲል ጠቁሟል።

ባሳለፍነው መጋቢት መባቻ ላይ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳሌህ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን "እንዳለመታደል ሆኖ በሚዲያዎች በሚነዙ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ላይ ተመስርተው ማደማደሚያዎችን ይሰጣሉ" ሲሉ በጻፉት ደብዳቤ "ተከታታይ የአሜሪካ አስተዳደሮች ባለፉት 30 ዓመታት በኤርትራ ላይ ሲያራምዱት ወደነበረው ፖሊሲ የተመለሱ በሚያስመስለው ደብዳቤዎ አዝኛለሁ" ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸው እንደነበር አስታውሷል።

ሚኒስትሩ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች አልገባም ባሉበት በዚህ ደብዳቤ መፍትሔዎች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ስለመግለጻቸው ነው የተጠቀሰው።

ኤርትራ ምክንያታዊ ያልሆኑ ተደጋጋሚ ክሶችን በዝምታ ልታልፍ እንደማትችልም ይጠቁማል። "ሃሰተኛ" ያለው ውንጀላ ሊጣራ የሚችል ነገር ካለው በገለልተኛ አካል እንዲጣራም ለአሜሪካ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

የUN የጸጥታው ም/ቤት ተደጋጋሚ የዓለም አቀፍ ህግጋትና የሃገራትን የሉዓላዊነት ጥሰቶች በመግታትና መፈትሔ በመፈለግ ረገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስቧል።

(አል-ዓይን)

@tikvahethiopia
#US #Eritrea

አሜሪካ በኤርትራ ያሉ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሳሰበች።

አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና መንግስታቸው የህሊና እስረኞችን እንዲፈቱ አሳስባለች።

አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ " ፕሬዜዳንት ኢሳያስ እና መንግስታቸው በግእዝ የገና በዓል መንፈስ እና በክርስትናውም ሆነ በእስልምናው እምነት ውስጥ ይቅርታ ያለውን ትልቅ ሚና በመገንዘብ የኤርትራ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሜሪካ ታሳስባለች ። " ብሏል።

በአስመራ የሚገኘው አሜሪካ ኤምባሲ ስላሰራጨው መልዕክት በኤርትራ መንግስት ሆነ ባለስጣናት በኩል የተሰጠ ምላሽ/አስተያየት የለም።

@tikvahethiopia
#Eritrea

ባለፉት ሁለት ቀናት ከጎረቤት ኤርትራ ሠራዊት ጋር አዲስ ውጊያ መካሄዱን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ (ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2014 ዓ. ም.) የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ ነበር ብለዋል።

በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና 3 የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮችን እንደተገደሉ 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና 4 ወታደሮችን እንደተማረኩ ተገልጿል። አንድ ድሽቃ፣ አምስት የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እንደተማረከም ተገልጿል።

ቅዳሜና እሁድ ተከሰተ ካሉት ወታደራዊ ግጭት በተጨማሪ ከ4 ቀናት በፊት ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ. ም. የኤርትራ 57ኛ እና 21ኛ ክፍለ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ጥቃት ሰንዝሮ እንደነበርና አዲአዋላ በተባለው አካባቢ ይህንን ጥቃት መመከት እንደተቻለ አሳውቀዋል።

አቶ ጌታቸው ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኤርትራን መንግሥት ድርጊት በቃ እንዲለው ጥሪ አቅርበዋል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ተካሄደ ስለተባለው ውጊያ መረጃው እንደሌላቸው ገልጸው፣ ነገር ግን የኤርትራ ኃይሎች ጥቃት ሊፈጽሙ የሚችሉበት ሁኔታ የለም ብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ " ህወሓቶች ራሳቸው ትንኮሳ ፈጽመው " የሚያሰሙት ክስ ሊሆን ይችላል ሲሉ ገልፀዋል። በአሁኑ ጊዜ " በኤርትራ በኩል ጦርነት ይከፈታል የሚል እምነት የለንም " ያሉት ዶ/ር ለገሰ የተከሰተ ነገር ካለም አጣርተው መረጃ እንደሚሰጡ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በኤርትራ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሊያ #ኤርትራ የ5 ሺህ የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ከምን ደረሰ ? የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት ፤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ውስጥ (በሶማሊያ) ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ገልፀዋል። ኤርትራ የሶማሊያን ኃይል በማሰልጠን ረገድ ጥሩ ሀሳብ እንዳላትም ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል። …
#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በ3 ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ  ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።

የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ለ4 ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኤርትራ፣  አስመራ መግባታቸው ታውቋል።

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው የሶማሊያ አቻቸውን ተቀብለዋቸዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሀሙድ ወደ ፕሬዜዳንትነት የስልጣን መንበር ከመጡ በኃላ ወደ ኤርትራ በስራ ጉብኝት ሲያቀኑ ይህ ሁለተኛቸው ነው።

ከሶስት ወር በፊት ነበር ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ሄደው የነበር።

በወቅቱ በዛው በኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላትን (ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ ጋር) እንደጎበኙ ፣ ከጉብኝቱ በኃላ ወታደሮቹን ወደ ሀገራቸው ሶማሊያ ለመመለስ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየሰሩ መሆኑን ፤ በኤርትራ ከነበራቸው ቆይታ በኃላ ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅትም በኤርትራ ያሉትን 5,000 የሶማሊያ ጦር አባላትን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የአሜሪካን ድጋፍ እንደጠየቁ አይዘነጋም።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ውስጥ (በሶማሊያ) ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን መግለፃቸው እና ኤርትራ የሶማሊያ ወታደሮችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እያስታጠቀችም እንደሆነ መግለፃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሶማሊያ እና ኤርትራ ምን መከሩ ? የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ወደ ኤርትራ አቅንተው የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል። ፕሬዜዳንቱ ጉብኝታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በማብራሪያቸውም ፤ " ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ኤርትራ ለኛ እንደ ቤታችን ናት " ብለዋል። ወደ ኤርትራ የሄዱት ፦ - ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገች ባለችበት በሶማሊያ…
#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ ማሕሙድ ዳግም ወደ አስመራ ማቅናታቸው ተነግሯል።

ፕሬዝደንቱ ዛሬ አስመራ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል።

ሐሰን ሼይክ ማሕሙድ በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ #ግብዣ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ አስመራ እንደተጓዙ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ገልጸዋል።

የሶማሊያ ብሔራዊ የዜና ወኪል (SONNA) ሀሰን ሼይክ መሕሙድ ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በሁለቱ ሀገሮች ትብብር ላይ እንደሚወያዩ አስታውቋል።

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ባለፈው ጥር ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ “የአጋርነት እና የትብብር የመግባቢያ ሥምምነት” በተፈራረሙ በቀናት ልዩነት ወደ አስመራ አቅንተው ከፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው ነበር።

መረጃውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር / SONNAን ዋቢ በማድረግ ያጋራው ዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

Photo Credit - Yemane G. Meskel

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BiniyamGirmay🇪🇷

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ስፍራ የሚሰጠውን ቱር ደ ፍራንስ የተሰኘውን የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ‘ስቴጅ 3’ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ በመሆን ለኤርትራ እና ለአፍሪካ ታሪክ ሰርቷል።

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ቢኒያም በመሄድ " እንኳን ደስ አለህ ! አንተ በጣም ምርጡ ነበርክ ፤ በጣምም ጠንካራ ነህ፤ ለአፍሪካ እና ለዓለም ታሪክ ሰርተሃል ፤ እንኮራብሃለን " ሲሉ አወድሰውታል።

ቢኒያም ፤ " ሁሉንም ጥንካሬ እና ድጋፍ ስለሰጠኝ ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን " ሲል ተናግሯል።

ኤርትራዊው ቢኒያም በተለያዩ ጊዜያት ባስመዘገበው ስኬት " የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ " የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ኤርትራውያን በተለይ በብስክሌት ግልቢያ በዓለም መድረክ በእጅጉ ይታወቃሉ።

#Eritrea
#NBC_Sport
#BBC
@tikvahethiopia
#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ኤርትራ ናቸው።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ ፣ አስመራ መግባታቸው ተነግሯል።

አስመራ ሲደርሱ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ነው ኤርፖርት ተገኝተው የተቀበሏቸው።

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ፣በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ በቱርክ፣ አንካራ ከኢትዮጵያ ጋር ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚነት ጉዳይ ላይ ስምምነት ከፈረሙ በኃላ ነው ኤርትራ የሄዱት።

አንደንድ ዘገባዎች የኤርትራው እና የሱማሊያው መሪ የአንካራውን ስምምነት አጀንዳቸው ሊያደርጉት እንደሚችሉ አሳይተዋል።

የሶማሊያው መሪ ከዚህ ቀደም ወደ ኤርትራ በመመላለስ የሚታወቁ ሲሆን በተለይ ግን ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከፈረሙ በኃላ እንዲሁም ኢትዮጵያ ለህዝቦቼ የባህር በር ያስፈልጋቸዋል ይህ የህልውና ጉዳይ ጭምር ነው በማለት አቋማን ይፋ ካደረገችና ዓለም አቀፍ አጀንዳ ካደረገችው በኃላ ደጋግመው ኤርትራ ፣ አስመራ ኢሳያስ ጋር ተመላልሰዋል።

የኤርትራው መሪ በነዚህ ወቅቶች አንድም ጊዜ ሶማሊያ፣ ሙቃዲሾ ለጉብኝት ብለው ሄደው አያውቁም።

ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የግብፅ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ መሪዎች በአስመራ የሶስትዮሽ ጉባኤ አካሂደው የሶማሊያ ተቋማት እና ጦር ድንበሯን ለመጠበቅ እና የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚዘነጋ አይደለም።

#Somlaia #Eritrea

@tikvahethiopia